የምሥራቅ አፍርቃ ታሪክ መሠረቱ የዐባይ ሸለቆ ነው፡፡ የዐባይ ሸልቆ በኢትዮጵያ ወገብ የተጠመጠመ መቀነት ነው፡፡ በመቀነቱ ዙርያ ያለው አካል ለመላ ሰውነቷ ማእከል ነው፡፡ ወደ ነጥቡ ስንመጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ መላ አካሏ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንና ዐባይ እንዴት እንደተያያዙ ገልጸታል፡፡
ለመቀነቷ ቀረቢው ግን ዓባይ የሚያዋስናቸው ናቸው፡፡ የምሥራቅ አፍሪቃ ታሪክ መነሻውና መድረሻው ያባይ ሸለቆ ነው፡፡ ለአፍሪካ ምሳሌ የሆነው በዓባይ ሸለቆ አካባቢ የሚኖረው ሕዝብ ነው፡፡ መላው የኢትዮጵያ ልጆች ቢሆኑም፡፡ የበለጠ የሚቀርቡት ዓባይ የሚያዋስናቸው ሕዝቦች ናቸው፡፡ ቀሲስ አስተርአየ “እሬትና ማር”ብለው ያካፈሉን ጽሑፍ ላይ ያሰፈሩት የዐባይን ወቅታዊ መለዋዋጥ በክረምት ከላይ ዝናም ከታች ጎርፍ ሲበዛበት ይደፍርሳል ብለው በገለጹት ያካባቢውን ሕዝብ ስሜት ገልጸውታል፡፡
ዐባይ የሚያዋስናቸው ሕዝቦች ስነ ልቡናቸው የተቀረጸው በዓባይ ጠባይ ላይ ነው፡፡ ዓባይ ባራቱ ወቅቶች በመጸው በጸደይ በበጋና ክረምት ይቀያየራል፡፡ በክረምት ከላይ በሚወርደው ዝናብ ከታች ከታች በሚፈሰው የጎርፍ ማእበል ይቆጣል፡፡ በዓባይ ዙሪያ ያሉት ሰወች በኢትዮጵያ ላይ ክፉ ዘመን ሲመጣ፡፡ ይቆጣሉ፡፡ ይደፈርሳሉ ራሳቸው ለመሻገርና ሌላውን ለማሻገር ታጥቀው ይገቡበታል፡፡
“ዐባይ ሲደፈርስ ሲመስል እንቆቆ፣
ጋሬጣው ጎጃሜ ገባ ባጭር ታጥቆ”
ሲባል የኖረው ዛሬ አሁን በገሀድ እየታየ ነው፡፡ ፍኖይት የተባለቸው በህወቷ አረጋገጠችው፡፡፡ የፈሰሰውው ደሟ የሕብረተ ሰቡን መንፈስ የበለጠ አደፈረሰው፡፡ ያማራውን ሕይውርት የበለጠ እጅግ የመረ አደረገው፡፡ ሁሉም የኢትዮጵያን ልጆች እየዘለሉ ለመግባት እርስ በርስ እንዲጠራራ አደረገው፡፡
“ወዲያ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ተጣራ፣
ወዲ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው አቅራራ፣
ወዲያ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ወይ አለው፤
ወዲህ ማዶ ሆኖ ሌላው ሰው ወይ አለው፣
ጎበዝ ተጠንቀዉ ይህ ነገር የኛ ነው”
እያለ የደም እዳር ቆሞ የሚመለከተውን ሁሉ ቀሰቀስው ፡፡ “መፈናቀሉ መገደሉና መታረዱ በሚፈጸምበት ወቅት ስለ መደመርም ስለ ግድቡም ሲነገርና ሲተረክ የተሰማው ሁሉ “እሬትና ማር” የተቀላቀለበት ባዶ ዲስኩር ሆነ” ይሉና “በጠ/ ምንስቴሩ የቀርበው የመደመር ፍልስፍና ግን፦ የነበሩትን እሴቶች እንዲሸፈኑና እንዲዘነጉ ከተደረጉባቸው ብዙ አዘናጊወች አንዱ ስለመሰለኝ በግድቡ ደስ ቢለኝም እሬትና ማር ሆነብኝ” ብለው ጠ/ምኒስቴሩ በዲስኩራቸው ሊነኳቸው ያልደፈሯቸውን ኢትዮጵያ ስትደመርበት የኖረችባቸውን እሴቶች ለመግለጽ ባዘጋጇት ጦማር እንገናኝ” ብለው በሚያዘጋጇት ጦማር እንድንገናኝ ብለው ቀጥሮ አሲዘውናልና አንብናችሁ ክህሎታችሁን አዳብሩ። ጽሁፉን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ። ሕዳሴ ግድብ፣ ዓባይ፣ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን “እሬትና ማር”
ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
ጥቅምት ፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም. (October 16, 2025)