ከ25 ዓመታት ገደማ በፊት የተቀረጸ “አቡነ ፋኑኤል” ሲቀጥፉና ሲያወናብዱ የሚያሳይ የድምፅ ቅጅ
የቀድሞው አባ መላኩ የአሁኑ “አቡነ ፋኑኤል” ጵጵስናቸውን በገንዘብ የሸመቱ፣ ጵጵስናን ያረከሱ፣ ያቀለሉና ለግል ኪሳቸው ማደለቢያ ያደረጉ መሆናቸው ይታወቃል። “አቡነ ፋኑኤል” ስጋ እንደሸተተው ጉንዳን ገንዘብ ያለበት ቦታ ቀድመው የሚገኙ፣ ቤተ ክርስቲያን ለማቋቋም ካሰቡ ሰዎች ፍቃድና ስያሜ ለመስጠት እንዲሁም “ለመባረክ” ጉቦ የሚቀበሉ ጭልፊት እንደሆኑ በሳቸው በኩል ያለፉ በሙሉ የሚያውቁት ነው። እኝህ ሰው ለህዝብ እልቂት፣ መፈናቀልና በአጠቃላይ በምዕመናንን ላይ ለሚወርድ መከራ ደንታ የሌላቸው ጨካኝ እንደሆኑ በርካታ ምዕመናን ይናገራሉ። “አቡነ ፋኑኤል” በሐዋርያት ስራ ምዕራፍ 20 ቁጥር 28-29 የተጻፈው ቃል በትክክልና በቀጥታ ከሚመለከታቸው ጳጳሳት ውስጥ አንዱ ናቸው። “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሱ እኔ አውቃለሁ።” እውነቱን ለመናገር በአቡነ ማቲያስ የሚመራው “ሲኖዶስ” አባላት ማለትም ጳጳሳቱ በስብሰባ በሚያሳልፉት የተለያየ ውሳኔዎች ለምሳሌ ያህል ከክርስትና ዕምነት ባፈነገጠ መልክ ኤጲስ ቆጶሳትን በዘር፣ በቋንቋና በማንነት መስፈርት ሲመት የሰጠ ሲኖዶስ የወደቀና የከሸፈ የዲያብሎስ መናኸሪያ እንጅ ሲኖዶስ ሊባል የሚገባው አይደለም።
ከታሪክ ማህደራችን ከዛሬ 25 ዓመታ በፊት ገደማ የተቀረጸ የአባ መላኩ (አቡነ ፋኑኤል) በሬዲዮ የሰጡትን ቃለ ምልልስ አቅርበንላችኋል። አባ መላኩ የፖለቲካ ጥገኝነት ማግኘታቸውንና ስደተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሆኖም አሜሪካ ከሚገኙ ምዕመናን የዘረፉት ገንዘብ ኪሳቸው ሲሞላና ጥጋብ ሲወጥራቸው ያወገዟቸውንና ግንኙነት የለኝም ያሏቸውን አቡነ ጳውሎስን በጉቦ ታርቀው ጳጳስ ለመባል በቁ። ምክንያቱም ጳጳስ መባልና ስልጣን መጨበጥ ገንዘብ ለማካበት ተጨማሪ ጉልበት እንደሚሰጣቸው ስላወቁ ነው። ጊዜ ለሁሉ ነውና እንደ “አቡነ ፋኑኤል” ዓይነት ነጣቂ ተኩላዎችን ከቤተ ክርስቲያን የሚወገዱበትና በምትካቸው እምነቱ፣ ንጽህናው፣ ስነ ምግባሩና ብቃቱ ያላቸውን አባቶች የሚሾሙልን ጊዜ እንዲያቀርብልን ጠንክረን ለቤተ ክርሲቲያናችን ትንሳኤ እንጸልይ።