Blog Archives

ላመነችበት የዋተተች ሕይወት – ታዲዮስ ታንቱ

ዋለልኝ አየለ፣ አዲስ ዘመን ጋዜጠኝነትን እንደነፍሳቸው ይወዱታል። ከ30ዓመታት በላይ ኖረውበታል። በመምህርነት አገልግለዋል። በፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ረጅም ጊዜ አሳልፈዋል፡፡ በታጠቅ፣ ኢትዮጲስ፣ ፍትሕ… ጋዜጦች ላይ ይጽፉ ነበር፡፡ በሚጽፏቸውና በሚያደርጉት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በርካታ ውጣ ውረድ አጋጥሟቸዋል፡፡ በእስር ቤት ስቃይና እንግልት ደርሶባቸዋል፡፡ የዛሬ የ ‹‹ሕይወት እንዲህ ናት›› እንግዳችን ጋዜጠኛ ታዲዮስ ታንቱ ይባላሉ። በ1944ዓ.ም በቀድሞው ሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት በወላይታ አውራጃ በዳሞት ወይደ ወረዳ ግራራ ሚካኤል በሚባል አካባቢ ነው ተወልደው ያደጉት። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተማሩት ሻሸመኔ አጼ ናኦድ ትምህርት ቤት ሲሆን፤ ከዚያም ወደ ናዝሬት በመሄድ በአጼ ገላውዲዎስ መርሐ ሙያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምረዋል፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በውጭ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ተመርቀዋል፡፡ ከዚያም በእንግሊዝኛ ቋንቋ፣ አማርኛ ቋንቋና በታሪክ መምህርነት አገልግለዋል፡፡ ከእርሳቸው ጋር የነበረንን ቆይታ እነሆ! አዲስ ዘመን፡- ከመምህርነት ሙያ ወጥተው በምን ሙያ ላይ ተሰማሩ? ታዲዮስ፡- ከመምህርነት በኋላ በጦር ኃይሎች ዋና ፖለቲካ አስተዳደር በጋዜጠኝነት ተቀጥሬ በታጠቅ ጋዜጣ ላይ መሥራት ጀመርኩ፡፡ የታጠቅ ጋዜጣ ርዕሰ አንቀጽ ጸሐፊም እኔ ነበርኩ፡፡ ከዚያ በኋላም በልዩ ልዩ ጋዜጦች ላይ ሰርቻለሁ፡፡ እምቢ በይ ሀገሬ፣ አስኳል፣ ሜዲካል፣ ጦቢያ፣ ፍትሕ፣ አዲስ ታይምስ፣ ልዕልና፣ ፋክት፣ ኢትዮ ምህዳር፣ ነገረ ኢትዮጵያ እና የቀለም ቀንድ ላይ ሰርቻለሁ፡፡ አዲስ ዘመን፡- እነዚህ ሁሉ ጋዜጦች ላይ ሲሰሩ በአምደኝነት ብቻ ነው ወይስ ባለቤት የሆኑባቸው አሉ? ታዲዮስ፡- አንድም ጋዜጣ ላይ ባለቤት ሆኜ አላውቅም፡፡ አቅሜም ለዚህ የሚፈቅድ አልነበረም፡፡ ግን በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ በቋሚ ዓምደኝነት የሰራሁ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጄኔራል አሳምነው ፅጌ የተመራ ክልላዊ የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ መደረጉን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ (DW)

በብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ የተመራ ክልላዊ የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ መደረጉን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አስታወቀ። የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራው መክሸፉን የክልሉ ገዢ ፓርቲ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በአማራ ቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጠው መግለጫ ማሳወቁን ጀርመን ራዲዮ (DW) ዘገበ። በተጨማሪም፣ በባህር ዳር የሚገኘው ጀርመን ራዲዮ ጋዜጠኛ የሚከተለውን ዘግቧል። የፌደራል የጸጥታ አስከባሪ ኃይሎች የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ በተደረገባት የባሕር ዳር ከተማ ተሰማሩ። የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት መኮድ ተብሎ ከሚጠራው የጦር ሰፈር ወደ ከተማዋ የዘለቁ ወታደሮች የጸጥታ ቁጥጥር እያደረጉ ናቸው። ከመንፈቅለ መንግሥት ሙከራው ጋር በተያያዘ የክልሉ መንግሥት መቀመጫ በሆነችው ባሕር ዳር ከምሽቱ 12 ከ30 ጀምሮ ቢያንስ ለግማሽ ሰዓት የዘለቀ የተኩስ ድምጽ ሲሰማ እንደነበር የአይን እማኞች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። የከተማዋ ነሪዎች እንደሚሉት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የክልሉ ምክር ቤት እና የርዕሰ-መስተዳድሩ ፅህፈት ቤት በሚገኙባቸው አካባቢዎች የተኩስ ድምፅ ተሰምቷል። አንድ የከተማዋ ነዋሪ “ተኩስ የጀመረው ፖሊስ ኮሚሽን አካባቢ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ከፖሊስ ኮሚሽን ፅህፈት ቤት አቅራቢያ የነበሩት እኚሁ የዐይን እማኝ “የቀላል እና የከባድ መሳሪያ ተኩስ” መስማታቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በክልሉ ልዩ ኃይል አዲስ እና ነባር አባላት መካከል ቀደም ሲል ግርግር እንደነበር መስማታቸውንም ገልጸዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መስሎ መኖር ከእራስ እውነታ ጋር ሲጣረስ – ፀጋ ወርቅ

ከፀጋ ወርቅ ይህንን ጽሁፍ ስናነብ ውሕድ ማንነታቸውን በአግባቡ ተቀብለውት ለዘመናት በአብሮነት ሃገራቸውን የመሩ ፣ ለሃገራቸው ህልውናና ፍቅር እራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ እና እኛን የወለዱ የምንኮራባቸው ጀግኖች ቀደምቶቻችንን ሁል ግዜ ክብራቸው ክብራችን ጉድለታቸው ጉድለታችን ብለን ተቀብለን መሆኑ እንዳይዘነጋ። መስሎ መኖር ከእራስ እውነታ ጋር ሲጣረስ ሊያመጣ የሚችለው ውጤት ምን እንደሚሆን ገምተውት ያውቃሉ? ሰዎች በውሕድነታችው ምክንያት ሊወያዩባቸው የሚችሉት ጉዳዮች በርካታ ቢሆኑም ዛሬ ጥቂቶቹን በግርድፍ ልናይ መርጠናል። ባለፈው ውይይታችን ላይ ውሕድ ኢትዮጵያዊ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ ማንነት የለውም ከተባለ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ላይ መወያየት ሲቻል በተናጠል ውሕዶችን ብቻ የሚመለከት ውይይት ለምን አስፈለገ የሚል ሃሳብ ተነስቶ ነበር። የውይይቱ መድረክ አስፈላጊነት ውሕድነት የራሱ የሆነ ስብእና ስላለው በጋራ የሚጋራው የማንነት ጥያቄዎች እና በተለይም በዘር እና ቋንቋ ተኮር ብድኖች ስብስቦች እና አስተዳደሮች የተደፈጠጠና ፍጹም ቦታ ያልተሰጠው በመሆኑ ምክንያት የሚፈጠሩ መብት ነክና ስነልቦናዊ ችግሮችን በጋራ ለመወያየት እና መፍትሔም ለመፈለግ ስለሚረዳ ነው ። የሰዎች የማንነት ጥያቄ ከግል ህይወት ጀምሮ እስከ ሃገር ግንባታ ድረስ ትልቅ ሚና ስላለው ውሕድነት ሊፈተሽ ሊመረመር እና በሰፊው ሊሰራበት ይገባል ወደሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰናል። በተለይም ቋንቋና ዘር ተኮር ክልል እና አስተዳደር ባለበት ሃገር ላይ ውሕዶች ምን ቦታ እንዳላቸው መነጋገር የምርጫ ጉዳይም ሳይሆን የህልውናም ጉዳይ ጭምር ነው። የተወሰነውን ሕብረተሰብ ማንነት የሚያከብር ሥርዓት ለመመሥረት በሚል ሰበብ የተቀረውን ሕብረተሰብ ማንነት መደፍጠጥ ፍትሐዊ ሊሆን አይችልም። እነዚህ ውይይቶች ግን አንድ ወጥ ማንነት ያላቸውን ወይም አለን ብለው
Posted in Amharic News

ኦዴፓን ከሞት ያነሳሁት እና ስሙን ያደስኩለት እኔ ነኝ። ከእኔ ጋር (ኦዴፓ) እንዲህ ዓይነት ሳፋጣ ቢያቆሙ ይሻላቸዋል። – ጃዋር መሃመድ

ከደረጀ ሃብተወልድ ለምን እውነቱን አወጣብኝ ብሎ ኢሳትን የከሠሰው ኦዴፓ እንደሚከተለው በOMN ኃላፊ በተራው ተከሷል፣ ማስጠንቀቂያም ተሰጥቶታል:- “ትናንት ምሽት የጃዋርን OMN ቲቪ ስመለከት አቶ ጃዋር ቃለ ምልልስ እየሰጠ ነበር:: ውይይቱ የተካሄደው በኦሮምኛ ቋንቋ ሲሆን ዋንኛው ማጠንጠኛው “ኦዴፓ” እና ወቅታዊ “መግለጫው” ነበር:: ቃለመጠይቅ አቅራቢው አቶ ተስፋዬ:- “ኦዴፓ በፓርቲዬ እና ኦሮሞ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶብናል” ያለው አንተን አፍህን ለማዘጋት ነው እያሉ ነው:: አንተ ምን ትላለህ?” ሲል ጃዋርን ጠይቆታል:: ጃዋር እንዲህ ሲል መልሷል:- – ኦዴፓን ከሞት ያነሳሁት እና ስሙን ያደስኩለት እኔ ነኝ:: ከእኔ ጋር (ኦዴፓ) እንዲህ ዓይነት ሳፋጣ ቢያቆሙ ይሻላቸዋል:: – ኦዴፓን እያዳከሙ ያሉት በውስጡ የተሰገሰጉ የድሮው ኦህዴድ ሌቦች ናቸው!! – ገላን ላይ 500 ሄክታር መሬት የሸጡ ሌቦች እሁንም ኦዴፓ ውስጥ በሥልጣን ላይ አሉ:: – ሰበታ ላይ በሌለ ድርጅት ስም 40 ሄክታር መሬት የሸጡ ሌቦች አሁንም በኦዴፓ ሥልጣን ላይ ናቸው:: – ወለጋ ላይ ኦነግ ባንኮችን ሲዘርፍ አብረው ያዘረፉ እና የተካፈሉ ኦዴፓ ውስጥ ያሉ ባለሥልጣናት አሉ:: – ወለጋ ላይ የኦነግ ወታደሮች ትጥቅ ፈትተው ካምፕ እንዳይገቡ የሚያደርጉት የኦዴፓ ሰዎች ናቸው:: ምክንያቱም ባንክ ዘርፈው መካፈላቸውን ምስጢር እንዳያወጡባቸው ነው:: – ታከለ ላይ የሚነዛው ጥላቻ ምንጩ ከኦዴፓ ከእራሱ ውስጥ ካሉ ሌቦች ነው:: – የለማ እና የዐብይ ሥርዓት እየፈራረሰ ነው:: – የኦሮሚያ መንግሥት በሙሰኞች እና በሌቦች ሽባ (paralyzed) ሆኗል:: ይህን ያለው የኢሳት ዳይሬክተር ቢኾን ኖሮ …. ብላችሁ አስቡት። ለትርጉሙ
Posted in Ethiopian News

ለአታላይ ስለማያመቹት የኢትዮጵያ ወሰን ፈጣሪ ወንዞችና ስለክልል የለሹ አማርኛ ተናጋሪ ጥቂት ነጥቦች – ኤፍሬም የማነብርሐን

ከኤፍሬም የማነብርሐን (J.S.D.) ባለፉት 27 ዓመታት፣ ማለትም ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረበት 1983 ዓመት ምህረት ጀምሮ፣ ወያኔ ኢትዮጵያን በትግራይ የበላይነት ቢያንስ ለመቶ ዓመታት ለመምራት የሚያስችለውን የወሰን አከላለልና የሕዝቦቿን የዜግነት መብት ለራሱ በሚያመቸው አኳኅን ብዛት ያለው ሕዝብ ያለተወከለበትን ሕገመንግስት ነድፎ፣ በሕዝቦቿ ላይ ከፍተኛ ሰቆቃ በመፈጸም ይህንን የክፋትና የጥፋት ዓላማ ለመተግበር ላይ ታች ሲል ከረመ። ለዚህም ዓላማ መሳካት የመጀመሪያ ዋና ኢላማ ያደረገው አገሪቱ በመጀመሪያ የተቋቋመችባቸው በዋና መሰረት በመልከዓ ምድራዊ የወንዞችን አወራርድ፣ የሕዝብን ባሕልና፣ የሕዝብን ስነልቦናዊ መስፈርቶችን ባላገናዘብ መልኩ፤ የራሱን ተስፋፊነትና፣ አማራና አማርኛ ተናጋሪውን ሕብረተሰብ በሚጎዳ አኳኃን አስልቶ፣ በማንኛውም መስፈርት ተአማኒነት በሌለው በፖለቲካ ውሳኔ ላይ የተመሠረተ የአገር ውስጥ ወሰን አከላልን በጉልበት ላለፉት 27 ዓመታት ሲተገብርና ሲያስተገብር መክረሙ ገሃድ ሐቅ ነው። በተለይ ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያን ከኛ ሌላ ማነም ሊገዛት አይገባም፣ ከአጼ ዮሐንስ አጼ ሚኒሊክ ስለነጠቁን ነው እንጂ የሚለውን በሐሰት ላይ የተመሠረተ ትርክት ለረጅም ዓመታት ሲያብላላ የሰነበተው የትግራይ ጽንፈኛ ኤሊት፣ ዕድልና በለስ ቀንቶት በሸዋ የሚኒሊክን ግቢ ሲቆጣጠር፣ የሌት ተቅን ስሌቱ ይሕንን የረጅም ዓመታት የትግራይ ኤሊትን ምኞት እንዴት እንደሚተግብረው ነበር። የወያኔ መሠረታዊ ችግሩ፣ “ከኔ በላይ ብልጥ ላሳር” እንዳለው የሰፈር አውደልዳይ ሞኝ ሁሉ ነገር በገሃድ የሚታይበት መሆኑን አለመገንዘቡ ወይም “የት ይደርሳል ተወው” የሚል አባዜ ውስጥ ሁሌም የተነከረ መሆኑ ነው። በአማራው ላይ ከበባ እያደረግበት መሰንበቱ ደጋግሞ የተነገር ቢሆንም፣ የዚህ ሴራ ጥልቀት ግን በቅርቡ የቤኒሻንጉሉ የቀድሞ ባለሥልጣን “ወልቃይትም እኮ የቤኒ ሻንጉል ክልል
Posted in Ethiopian News

ማለቂያ ቢስ የሚመስለውን የህወአት ግፍ ለፍፃሜ ያበቃው ሚስጥር ኦሮማራ ነው

ማለቂያ ቢስ የሚመስለውን የህወአት ግፍ ለፍፃሜ ያበቃው ሚስጥር ኦሮማራ ነው፡፡ ለማና ደመቀ መከሩ፡፡ አብይና ገዱ ዘከሩ፡፡ ህዝቦቻችንን እያናከሱ ለዘላለም እንዳይገዙን አሁን መንቃት አለብን አሉ፡፡ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ተማከሩ፡፡ ኦሮማራ እውን ሆነ፡፡ ኦሮማራ ባይኖር አንዳርጋቸው እስር ቤት ነበር፡፡ ኦሮማራ ባይኖር በቀለ ገርባ ቃሊቲ ነበር፡፡ ኦሮማራ ባይኖር የኦሮሞና የአማራ ልጆች በማዕከላዊ ዕቶን እየተቀቀሉ ነበር፡፡ የህወአት ሴረኞች ሸራተን በእምባና በደም በተጠመቀ ውስኪ እየተራጩ ነበር፡፡ ኦሮማራ ሲጠነክር ኦሮሞና አማራ ይጠነክራሉ፤ ኢትዮጵያ ትጠነክራለች፡፡ ኦሮማራ ሲደክም ኦሮሞና አማራ ይደክማሉ፤ ኢትዮጵያ ትደክማለች፡፡ ህወአት ኦሮሞና አማራን 27 ዓመት የተጫወችባቸው እርስበርሳቸው እንዲናከሱ አጀንዳ እየሰጠቻቸው ነው፡፡ ሁለቱ ሲናከሱ ነው ህወአት ፋታ የምታገኘው፡፡ ሁለቱ ሲዝሉ ነው ህወአት የምትጠነክረው፡፡ ኦሮማራ እንዲደክም ህወአት ዲጅታል ወያኔ የተባለ የፌስቡክ ሰራዊት አደራጅታ መጥታለች፡፡ ትናንት በምድር ጦርነት ስልጣን ጨብጠዋል፤ ዛሬ ደግሞ በሳይበር ጦርነት ስልጣን ለመጨበጥ እያሴሩ ነው፡፡ ኦሮማራ ሲደክም ወያኔ ትጠነክራለች፡፡ ይህን ሃቅ ለቅፅበት እንኳን ከዘነጋን ሞታችን ቅርብ ነው፡፡ ህወአት ኦሮማራን ለማዳከም የ27 ዓመት ልምዷን አሁንም እየተጠቀመችበት ነው፡፡ ኦሮማራ ይለምልም!
Posted in Amharic News, Ethiopian News

እኛ አብይን የደገፍነው እንደልባችን መናገር፣ መቃወም፣ መተቸት ስላስቻለን ነው – ሩታ አለሙ

ሩታ አለሙ በለገጣፎ ጉዳይ ዶ/ር አብይ ተቃውሞ ገጠመው ብለው የሚፈነጩ የህወሃት አክቲቪስቶችን እዛም እዚህም እያየን ነው! እኛኮ አብይን የደገፍነው… በሀብት ላይ ሀብት ስለደረበልን አይደለም… ከህወሃት ዘመን በተለየ በቀን ሶስቴ ጠግበን መብላት ጀምረን አይደለም… መንገድና ህንፃ በመገንባትማ መለስ ተወቅሶበት አያውቅም። እኛ አብይን የደገፍነው እንደልባችን መናገር፣ መቃወም፣ መተቸት ስላስቻለን ነው! ለውጥማ ድብን አድርጎ አለ!! በፊትም ወጣት በጅምላ ይታፈስ ነበር። አሁንም ሲታፈስ አይተናል… ቢያንስ ግን ለምን ታፈሱ ብለን ኡኡ ብሎ የመጮህ መብት አለን ዛሬ። የህዝብን ጩኸት ፈርቶ እርምጃውን የሚያርም፣ የታሰሩት የሚፈታ መሪ አግኝተናል። በፊትም የዜጎችን ቤት አፍርሶ ጎዳና የሚጥል መንግስት ነበረን። አሁንም ነገሩ ሲደገም እያየን ነው። ነገር ግን ዛሬ ለምን ቤት ፈረሰ ብለን በመፃፋችን እስርና እንግልት ይደርስብናል ብለን አንፈራም። ተዘቅዝቀን አንገረፍም። ብልታችን ላይ ኮዳ አይንጠለጠልም! በፊትም መንግስትን ተቃውሞ ህዝብ ሰልፍ ይወጣ ነበር። ዘንድሮም እንደዛው። ዘንድሮ ግን ባዶ እጁን ሰልፍ የወጣ ህዝብ ላይ ጥይት አይተኮስም። በፖለቲካ አቋሙ ምክኒያት ህዝብ በሽብርተኝነት አይፈረጅም። ብሄር ከብሄር እያጣላ ዘመኑን የሚያረዝም ተንከሲስ መንግስት የለንም። ቢያንስ ቦታው ላይ ያሉ ሰዎች ሀገራቸውን ይወዳሉ። ሀላፊነት ይሰማቸዋል። በፊትም ምርጫ ነበረን፤ ዘንድሮም ይኖረናል! መቶ ፐርሰንት የሚመረጥ መንግስት እንደማይኖረን ግን እርግጠኞች ነን። አንጭበረበርም። አንታለልም። አብይን የደገፍነው እንደልቡ እንድንቃወመው ስለፈቀደልን ነው። ሲያጠፋ እንወቅሳለን። ሲያለማ እናመሰግናለን። ጥፋቱ ከልማቱ ከበለጠብን በምርጫ በክብር እናወርደዋለን። ይሄንን ማድረጉ በራሱ በታሪክ መዝገብ ላይ ስሙን አድምቀን እንድንከትበው ያደርገናል! ቅር ስንሰኝ መንግስትን መቃወም ወላዋይነት
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ከተማ የሚገነባው የግድ ሰፈርን በማፍረስና ሕዝብን ለጎዳና በመዳረግ አይደለም – መላኩ አላምረው

ከመላኩ አላምረው – የግል አስተያየት እንደዚህ አይደለም! ሕግ ይከበር፤ ነገር ግን ሕግ የሚከበረው ሰዎችን በተለይም አቅመ ደካሞችን በማዋረድ አይደለም፡፡ የሕግ የበላይነት ይረጋገጥ፤ ነገር ግን የሕግ የበላይነት የሚረጋገጠው የሰውን ልጅ ተፈጥሯዊ መብት በመረጋገጥ አይደለም፡፡ ከተሞች ተውበው ይገንቡ፤ ነገር ግን ከተማ የሚገነባው የግድ ሰፈርን በማፍረስና ሕዝብን ለጎዳና በመዳረግ አይደለም፡፡ በሥርዓት እንመራ፤ ነገር ግን ዘመናዊ ሥርዓትን የምናሰፍነው እዚህ ያደረሰንን ማኅበረሰባዊ ትውፊት በመናቅና በመጣል አይደለም፡፡ ሀገር የምናሳድገው ሕዝብን በማማረርና በማስለቀስ አይደለም፡፡ የተበላሸ ሥርዓት የተጣሰም ሕግ ቢኖር እንኳን መሰተካከል የሚችለው በአግባብና በሥርዓት ቀስ በቀስ እንጅ ንቀትና ትዕቢትን ባስቀደመ ማናለብኝት አይደለም፡፡ ልዩነቶች በበዙባት ሀገር ውስጥ መግባባት የሚፈጠረው ልዩ ጥንቃቄ በተሞላበትና ቅንነት በታከለበት ሰዋዊና የሰከነ አካሄድ እንጅ በስሜት በሚመራና ለሰዎች በማይራራ የጭካኔ እርምጃ አይደለም፡፡ ሀገርን መምራትም ሆነ መገንባት የምንችለው ሁሉንም በእኩል ዓይን በመመልከት እና ፍትሕና ርትዕን በማስፈን እንጅ በራስ ወዳድነት፣ ለይቶ በማቀፍና ለይቶ በማግለል፣ በአድሏዊነት አይደለም፡፡ በታሪክ አጋጣሚ አንድንመራት ዕድል እጃችን ላይ የጣላትን ሀገር ወደተሻለ ከፍታ የምናሸጋግራት ሕዝቦቿን በእኩልነት እጆቻችን በፍቅር አቅፈን፣ የተጣሉትን አስታቀን፣ የተራራቁትን አቀራርበን፣ ስጋትን እያስወገደን ተስፋን በማለምለም እንጅ የተለመደን ጥላቻና በቀል እየሰበክን፣ በመካከላቸው ልዩነትን እያሰፋን፣ አንዱን አቅፈን ሌላውን እየገፋን፣ ለአንዱ አለኝታ ለለላው በሽታ እየሆንን…. ከችግር ወደ ችግር፣ ከአንዱ አዙሪት ወደ ሌላኛው አዙሪት በማሽከርከር አይደለም፡፡ እንደዚህም አይደለም! የሕዝብ ጠበቆች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎች፣ የሥርዓት መሪዎች ነን የምንል ሁሉ ሕዝቡን ልንጠቅም የምንችለው የሕዝቡን ፍላጎት በትክክል ስንረዳና በዚሁ መሠረት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የለገጣፎ – ለገዳዲ ሕገወጥ ቤቶች መፍረስ የሚታወቁ ሐቆች – መንግስቱ አሰፋ

የለገጣፎ – ለገዳዲ ሕገወጥ ቤቶች መፍረስ ብዙ እያነጋገር ይገኛል። ጉዳዩን በሕግ እና ፍትሕ ዓይን ከማይታችን በፊት ስለቤቶች እስኪ የሚታወቁ ሐቆችን እናስቀምጥ። ~ቤቶቹ ገበሬዎች ተታለው በካድሬ በትንሽ ብር ከተገዙ በኋላ በደላሎች እና ኦሕዴድ (ኦዲፒ) ካድሬዎች ለነዚህ ቤት የሚፈስርባቸው ባላቤቶች በተቸበቸቡ መሬት ላይ የተገነቡ ናቸው። ከ1990ዎቹ ጀምሮ ማለት ነው። አንዳንዶቹ ከተማ አስተዳድሩ ከመቋቋሙ (1998ዓ.ም.) በፊት ነበሩ። ሕጋዊ የመሬት ባለቤትነት ካርታ ባይኖራቸውም የመብራት እና የዉሃ ውጪ አንዳንዶቹም ግብር ሁላ እየከፈሉ ነበር። መንግሥትም ለነዚህ ቦታዎች ካሳ መክፈሉን ይናገራል። ~ከጥቂት ወራት በፊት የኦሮሚያ ክልል መሬት አስተዳደር ቢሮ በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ባደረገው ጥናት ከ 12000 በላይ ሕገ ወጥ ቤቶች መኖራቸውን እና ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አሳውቆ ነበር። የዚያ አካል የሆነው ነገር ነው እንግዲህ አሁን ቤቶቹን እንዲፈርሱ የማድረግ ሥራ እየሠራ ያለው። ~ቤቶቹን ማፍረስ ምናልባት ሕጋዊ መሠረት ሊኖረው ይችላል። ሕገወጥ ከሆነ ሕገወጥ ነው። ግን ፍትሓዊ ነው ወይ? ከጥቅሙ ጉዳቱ አያመዝንም ወይ? ሕግ በማስከበር የሚከሰተው ማኅበራዊ ቀውስ ከ collateral damage ገዝፎ የችግር መንስዔ አይሆንም ወይ? ፖለቲካውን አያጦዘውም ወይ? ሕፃናት እና ሴቶች፣ አቅመደካሞች፣ እርጉዝ እና አራስ እናቶች ፣ አዛውንት ውና መበላቶች ጎዳና ተዳዳሪ እንዲሆኑ ማድረግ አይሆንም ወይ ብለን ስንጠይቅ የሕግ የበላይነት ማስከበር ሳይሆን በራሱ ዞሮ ትልቅ ችግር ይሆናል። ይህንን ችግር የፈጸሙ ካድሬዎች ዛሬ ወይ የትም አይገኙም ወይ እቅፋችሁ ውስጥ “የለውጥ አመራር” ሆኖ ሸገር ከትመዋል። እነሱ ላይ የኽ የሕግ ዱላ እንደማያርፍ
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በእንተ ለገ ጣፎ ወለኩላ ኢትዮጵያ – አምሃ ልዑልሰገድ

ከአምሃ ልዑልሰገድ መማር ማወቅ መጠየቅ መረዳትና መመርመር ለባለጌ እንዳልተሰጡ በግልጥ ያሳየን የትናንቱ ገቢረ ጣፎ ነው። በቀዬአችን ተክለው ያሳደጉትን ዛፍ ለሥራ ፈልገው ሊቆርጡ የወጡ ገበሬዎች ብዙ የወፍ ጎጆ ከተመለከቱበት ሳይቆርጡ ያልፉታል። የዛፉ መቆረጥ ግድ ቢሆን እንኳ ለሥራ በማይውል ጠማማ ወይም ለመቆረጥ ወዳልተመረጠ ዛፍ የወፎቹን ጎጆ አዘዋውረው ይቆርጡታል። ልማት በሰው ለሰው የሚከወን ካልሆነ ምን ፋይዳ አለው? እንኳን ለሰው ለፍጥረት ሁሉ ተስማሚ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ የተሰራው የእስከዛሬው ልማት ለምን አላስተማረንም? አዲስ አበባ እኮ ከማዘጋጃው ፈጥኖ ጥንቧን የሚያነሳላት የዱር አውሬ ነበር እንደ ዛሬው የብሎኬት ደን ሳይከባት በፊት። ስለዚህ ልማታችን ለፍጥረት ሁሉ ተስማሚ ካልሆነ ልማት ሳይሆን ጥፋት ነው። እሱ ነው ሕገ ወጥነት። ይሔንን አሰራራችንን ነው በሐሳብ ዶዘር ማፍረስ ያለብን። እንጂማ ሰውን እያፈረስን ለማነው የምንገነባው? ሕገ ወጥ ማለት ምን ማለት ነው? ማነው ማንን ሕግ አክባሪ እና ሕግ አስከባሪ የሚለው? ስለ ሕግና ሕጋዊነት ምንም የማያውቁ ከአስተዳደጋቸው ጀምረው ጋጠወጦችና ነጣቂዎች ሆነው በንፍገትና በስግብግብነት ያደጉ ጥቂቶች በሕዝብ ውክልና ለኃላፊነት ሳይሆን በብልግና ልኬት የተሾሙ ጠማሞች ብዙሃኑን ሲያስለቅሱ ሲገድሉ ዝም የሚል ሰው አይኑር። በሃይማኖትም፣ በመንግስትም ይሁን ሰው በመሆን ሥልጣን የምንገኝ ከግፉአን ጋር ብንገፋ የሚሻለውን እናገኛለን። “ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” እንዲሉ ለግፈኞች ያላቸው አጭር ጊዜ ስለሆነ በዚህ ግፋቸው እንዲቀጥሉ እድል አንስጥ። ከትናንት መማር ያልሆነለት የሐገሬ ሰው ዛሬም ትናንትን እየደገመ ነገ ላለመኖር በመሥራት ተጠምዷል። ሕሊና አለን የምትሉ ባለሥልጣናት የየትኛውም እምነት መሪዎች እባካችሁ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የህወሃት ከፍተኛ አመራር ዛዲግ አብርሃ ለህወሓት ያስገቡት የስንብት ደብዳቤ

ለ – ህወሐት ልዩ ዞን ጽ/ቤት አዲስ አበባ ላለፉት አመታት በህውሃት ድርጅት ስር ተደራጅቼ እንቅስቃሴ ሳደርግ እንደቆየሁ ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳን ከዚህ ቀደም በፖለቲካው መስክ የመሳተፍ ፍላጎቱ ያልነበረኝ ቢሆንም በታሪክ አጋጣሚ የአገራችንን ፖለቲካ የመቀላቀል እድሉን አግኝቻለሁ፡፡ በተፈጠረው አጋጣሚም ስለሃገሬ የፖለቲካ ምንነት እና በፖለቲካ ገበያው ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦችንና ተቋማትን በቅርበት የማውቅና የመሳተፍ እድሉ ገጥሞኛል፡፡ በዛው ልክ ደግሞ በህወሀት ውስጥ አደርግ በነበረው ትሳትፎ በር የመዝጋት የመጠራጠርና እንደ ባዳ የመታየት ስሜት ከላይ እስከ ታች ድረስ አጋጥሞኛል፡፡ ገና ከጅምሩ ትግሉ ድርብ ድርብርብ ነበር ፡፡ በአንድ በኩል የመጣሁበት አካባቢ በክልሉ ፓለቲካ ውስጥ በዳርነት የሚመደብ ነውና አጠቃላይ ጉዞው እጅግ አቸጋሪ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ድርጅቱ ወጣቶችን የመጠራጠርና ያለማመን ከፍተኛ ችግር የተንሰራፋበት ነውና እኔም እንደማንኛውም ወጣት ጉዞየ በሳንካ የተሞላ እንዲሆን አድርጎብኛል፡፡ ነገር ግን ሁሉንም በአንድ ሙቀጫ መውቀጥ ጥሩ አይደለምና በህይወቴ ነገሮችን በተለየ መልኩ እንዳይ ያደረጉኝ እንዲሁም ትምህርት የሰጡኝ ጥቂት ሰዎች ነበሩና በነሱ ድጋፍና ምክር በችግርም ውስጥ ቢሆን እስካሁን ድረስ ለመዝለቅ ችያለሁ፡፡ በእርግጥም! በየሃገሬ ፖለቲካ ረጅም ርቀት ተጉዤ አስተቃጽኦ ላደርግበት የምችልና የሚገባ መሆኑን የማታ ማታ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ ይሁንና ገና ከማለዳው ጀምሮ በህውሃት ውስጥ የነበረኝ የፖለቲካ ተሳትፎ አልጋ በአልጋ አልነበረም፡፡ በአጭሩ በሴራና በአሜኬላ የተሞላ ነበር ብሎ መናገር ማጋነን አይሆንም፡፡ ሆኖም ችግር ሲመጣ መሸሽና ማፈግፈግ ሳይሆን ፊት ለፊት ተጋፍጦና ተፋልሞ ማሸነፍ እንደሚገባ ላስተማረኝ ለውድ አያቴ ለሃዋደ ሻረው አቢቱ አበራ እና
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢሳና አፋር ደም አፋሳሹ ግጭት መቼ ነው የሚያበቃው? እንዴስ ያበቃል? – አካደር ኢብራሂም

ከአካደር ኢብራሂም በኢትዮጵያ ውስጥ ዝነኛ የሆነ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ፣ ማለቂያ የለለውና መፍትሄ ያልተግኝለት ጦርነት። በተለምዶ በግጦሽና በሳር የሚፈጠር የአርብቶ አደሮች ግጭት በመባል ይታወቃል። ጉዳዩ ግን ሰፋ ያለ ሌላ ትኩረት የሚስብ ፖለቲካዊ አጀንዳ ያነገበ ስለመሆኑ ብዙ የተባለ ቢሆንም የተገኘ መፍትሄ ግን የለም። ችግሩ የሚመለከተው አካል መፍትሄ አለመስጠቱ ብቻ አይደለም። ዋናው ችግሩ መንግስታት የሁለቱ ወገኖች ግጭትን ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀማቸው ነው። በዚህ ጉዳይ የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ ምሁራን ብዙ ጥናቶች አድርገዋል። በጣም ብዙ ጊዜ ደግሞ በሃይማኖት አባቶችና በባህላዊ ሽምግልና ዕርቅ ተሞክሯል። ችግሩ ግን ሊቆም አልቻለም። ለምን ይሆን? የታሪክ ደርሳናት እንደሚናገሩትና ኢሳዎችም ጭምር የማይክዱት አንድ ሀቅ አለ። የኢሳ ሶማሌ ጎሳ ከዘላዓ ወዲህ የሚታወቁበት መሬት እንዳልነበራቸውና በተለያዩ ጊዜያቶች በተደረጉ ጦርነቶች ግዛታቸውን እያስፋፉ እንደመጡ ይነገራል። ብዙ ሰዎች በተለይ አሁን አሁን ከማንነትና ከመሬት ይገባኛል ጋር የሚያያዙ ግጭቶች ከፌደራሊዝም ጋር ያያዙታል። የኢሳና አፋር ግጭት ግን በጣም የቆየና ቁርጠኛ የሆነ ገለልተኛ ውሳኔ የሚፈልግ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። ከንጉሠ ነገስት ሃይለስላሤ አገዛዝ ዘመን ጀምሮ በኢሳና በአፋር መሃል የተደረጉ ስምምነቶችን ጥሶ የሚገኘው የኢሳ-ሶማሌ ጎሳ እንደሆነ ማስረጃዎች ያሳዩሉ። የኢሳ (ሶማሌ) ድንበር ከአፍደም ወደ አሁኑ የሶማሌ ክልል 147 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እንደነበረ በ1962 ዓ.ም በኤረር ላይ በአፋርና ኢሳ መካከል በተደረገ ስምምነት ተገልጿል። ነገር ግን በአሁኑ ግዜ ኢሳዎች አፋርን እያጠቁ ያሉት ከኤረር 300 ኪ.ሜ. ወደ ውስጥ ገብቶ የአዋሽ ወንዝ ዳርቻ አዳይቱ፣ ኡንዳፎኦ እና ገዳማይቱ በተባሉ
Posted in Amharic News

የአረና ፓርቲ ተወካይ ዓምዶም ገብረስላሤ ከአዲስ ድምጽ ራዲዮ ጋር በመረጃ ቲቪ

Posted in Amharic News

ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ድንገተኛ ሞት በስተጀርባ የጠላት እጅ ይኖር ይሆን? አብረን የምናይ ይሆናል!

ጋዜጠኝ ደምስ በለጠ ከመሞቱ ዋዜማ የነበረውን ውሎ አባይ ዘውዱ እንደሚከተለው ዘግቧል የታህሳስ 12 ቀን ውሏቸውን በተመለከተ ዛሬ ያገኘሁት መረጃ ይህን ይመስላል – (ለምርመራው ከጠቀመ) 1. ረፋድ 4 ስዓት ላይ ፒያሳ ቀጠሮ አለኝ ብለው መነን ት/ቤት አካባቢ ካለው ከእናታቸው ቤት ወጡ፣ 2. 4 ስዓት ላይ ከቤት እንደወጡ ከሁለት ጓደኞቻቸው ጋር እዛው መነን አካባቢ ከሰብለ አረጋ ከተባለች ቤተሰባቸው ቤት ቡና ጠጥተው፣ለ30 ደቂቃ ያህል ከቆዩ በኃላ ስልክ ሲደወልላቸው ፒያሳ የማገኘው ሰው ስላለ በኃላ እመጣለሁ ብለው ከሰዎች ተለይተው ሄዱ።(ዘመዳቸው ሰብለ አረጋ ከተናገረችው) (የተደወለላቸውን ስልክ ሳይ ልክ 4 ስዓት ከ28 ደቂቃ ላይ የደወለላቸው ደግሞ አንድ ጓደኛቸው ነው(ስማቸው ይቆየን)።በአካል ያግኛቸው በስልክ ብቻ ገና አልተጣራም። 3. ከቀኑ 6 ስዓት አካባቢ ስደውልላቸው ሩሲያ ኤግዚቪሽን አካባቢ እንደነበሩ ነግረውኛል።ማገኛቸው ሰዎች አሉ ብለውኛል። (ከእህታቸው ልጅ ከህይወት ተፈሪ ንግግር የተገኘ) 4. ከቀኑ 9 ስዓት ተኩል ወደ እናታቸው ቤት ተመለሱ፣ጥሩ የጤንነት ስሜት ላይ አልነበሩም፣የቀረበላቸውን ምግብ ቀማምሰው ነው የተውት፣የድካም ስሜት አለባቸው፣የሆኑትን ነገር ብትጠይቃቸውም ስሜታቸውን አላጋሯቸውም። (እህታቸው ወ/ሮ አዜብ በለጠ ከተናገረችው ) 5. በመሀል አቶ ወርቁ (ጓደኛቸው) እና ወ/ሮ እታፈራሁ ካሳ ወደ እናታቸው ቤት በመምጣት ጋዜጠኛ ደምስንና ቤተሰቡን ሲያጫውቱ ቆዩ፣ከተወሰነ ቆይታ በኃላ እህታቸው ወ/ሮ አዜብ በለጠ እና ልጃቸው ህይወት ተፈሪ ለስራ ጉዳይ ከቤት ወጡ። 6. ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ እና ከእናታቸው ጋር እነ ወ/ሮ እታፈራሁና አቶ ወርቁ ሲጫወቱ እስከ 12 ስዓት አካባቢ አብረው ቆይተዋል፣ነገር ግን በመሀል
Posted in Amharic News

የቀድሞው ደህንነት ምክትል ሃላፊ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ያሬድ ዘሪሁን በዱከም ከተማ የተደበቁበት ሆቴል ውስጥ እንዳሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሴቶች መብት ተሟጋች እና ጠበቃ መዓዛ አሸናፊ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ናቸው ተሿሚዋን ተሰናባቹን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዳኜ መላኩ ተክተው እንዲሰሩ በእጩነት ያቀረቧቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወ/ሮ መዓዛ ባላቸው የዳበረ ልምድ ምክንያት የአገሪቱን የፍትህ ስርዓቱ ወፊት ያራምዱታል በሚል በእጩነት እንዳቀረቧቸው ለምክር ቤቱ ተናግረዋል፡፡ በዚህም መሰረት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ ይሁንታውን ሰጥቷቸዋል፡፡ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በህግ የዳበረ ልምድ ያላቸው ፣ በተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ከፍተኛ ተቋማት ውስጥ በማገልገል አንቱታን አትረፈዋል፡፡ ከህገ መንግስት አርቃቂ ከሚሽን አባልነት በግላቸው ለሴቶች ከለላ የሚሆን ድርጅት እስከማቋቋምም ደረሰዋል፡፡ በመሆኑም በዛሬው ዕለት የተሰጣቸው የጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዝዳንትነት ሹመት በፍርድ ቤቱ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ያደርጋቸዋል፡፡ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊም ቃለ መሃላ ፈፅመው በህዝብና በመንግስት የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡ ምንጭ፦ ኢቲቪ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በለዛ ሽልማት የዚህ አመት የኢትዮጵያ ምርጥ ዘፈን ተሸላሚ – ይመልከቱ

Posted in Music

የለዛ ሽልማትን የዚህ አመት ምርጥ አልበም ያሸነፈውና ከቴዲ አፍሮ ሽልማቱን የተቀበለው አርቲስት ማነው? ይመልከቱ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሽማግሌ ቢጠፋ ዛፍ ገላጋይ ነበር! ወንድሞቼ ነብስሳችሁን ይማርልን! (ሄኖክ አያና)

ያኔ ድሮ አማራ ወጉ ሃያል ነበር! ሊኗኗር ብቻም አደል ሊገዳደል ህግ ነበረው። አማራ ሲገድልም በክብር ነበር፥ መጣሁ ሳይል የወንድ በር ሳይሰጥ ለመግደል አደለም ለማሸነፍም ቃታ አይሰብም! አማራ እምነትና ደግነት ነበረው! ሊገድለው እድል የመሸበትን ባላንጣውን በዛፍ ቢጠለል ያልፍ ነበር። አማራ ወንድ ነበር፣ መጣሁ ሳይል፣ ታጠቅ ሳይል እጁ አይስትም። ያልታጠቀን አይነካም፥ ብዙ ሆኖ አንድ አይገድልም። ትልቅ ሆኖ ትንሽን፣ ጎበዝ ሆኖ ደካማን ፍጹም አይነካም። አማራ ወጉ ግሩም፣ ልማዱና እሴቱ ድንቅ ነበር። የአማራ ስሪት የሰው ነበር! ምን ዋጋ አለው ይሄ የኛ የዝቅታ ዘመን ነው። አማራ ቢደኸይም ሃብታም ነበር። በድህነቱ ውስጥ ዘመናትን የተሻገረው በሰውነት ሃብቱ ነው። አሁን ሰውነትም የለ፥ ሃብትም የለ!! መደህየት እሱ ነው። በስማ በለው የበሬ ወለደ ጫጫታ ሙህራን በጠራራ ጠሃይ በማይማን የተወገሩበት ይሄው እኛ ቁልቁል የወረድንበት የኛው ዘመን ነው። ወንድሞቸ ነብስሳችሁን ይማርልን!
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በምዕራብ ጎጃም ዞን አዲስ አለም ከተማ ዶ/ር ወሰን ታፈረ እና የስራ ባልደረቦቹ ላይ ግድያ በመፈጸም የተጠረጠሩ ታሰሩ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዱራሜከተማ ደቡብ ኢትዮጵያ ስራ እንዲሰጣቸው በሰላማዊ ሰልፍ የጠየቁ የዩኒቨርስቲ ምሩቃን በፖሊሶች ተደበደቡ

(ኢሳት – ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓ/ም) – በከምባታ ጠምባሮ ዞን ካለፉት 4 ዓመታት ወዲህ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ተመርቀው ስራ ያጡ ወጣቶች ወደ ዞን መስተዳደር ምክር ቤት ማምራታቸውን ተከትሎ በፖሊሶች ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። ተማሪዎቹ ቀደም ብለው ጥያቄያቸውን ለመስተዳድሩ አቅርበው ለዛሬ አርብ ተቀጥረው የነበረ ቢሆንም፣ በቀጠሮአቸው መሰረት ወደ መስተዳድሩ ሲሄዱ ያጋጣማቸው የፖሊስ ዱላ ነው። በጉዳዩ ዙሪያ የከተማውን የአስተዳደር አካላት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። ተጨማሪ ዘገባ ከፌስቡክ ፔጅ ተከታታያችን፦ በከምባታ ጠምባሮ ዞን በተለያዩ ትምህርት መስኮች ካለፉት አራት አመታት ወዲህ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተመርቀው ስራ ያጡ ወጣቶች ዛሬ ወደ ዞን መስተዳድር ምክር ቤት አምርተው ነበር። ይሁን እንጂ ቁጥራቸው ወደ300 የሚደርሱት ወጣቶች በምላሹ መደብደባቸውንና መበተናቸውን የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በከተማው የነበረውን መሯሯጥ እንደተሰማ ሁኔታውን እንደተከታተልኩት ዱላ የያዙ ፖሊሶች ወጣቶቹን እያሯሯጡ ሲደበድቡ ብዙዎች ታዝበዋል። ሮጠው ማምለጥ ያልቻሉ ሴቶችና የፖሊሶችን እርምጃ ለመቋቋም የሞከሩ ወጣቶች ክፉኛ ተደብድበዋል። በሶስት የወታደር ላንድክሩይዘር መኪና የተጫኑት ፖሊሶች በመቶዎች የሚቆጠሩትን ወጣቶች ከመደብደብ በተጨማሪ ቁጥራቸው ባይታወቅም የተወሰኑት ታስረው ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ ያደረባቸው ብዙዎች ናቸው። ጥያቄያቸው ምን እንደነበረ ለማወቅ ቀርቤ ያነጋገርኳቸው ተደብዳቢዎች ውስጥ በዱላ የደረሰበትን ድብደባ እያሳየ አንድ ወጣት እንደገለፀልኝ÷ “የዞን መስተዳድር ምክር ቤቱ በክልሉ የሚታወቀው ምንም ስራ አጥ እንደሌለበት በመሆኑ ድምፃችን ታፍኖ ትኩረት ተነፍገናል ስለዚህ ዋናው አስተዳዳሪ በሰጡን ቀጠሮ መሰረት ያነጋግሩን በማለታችን ተደብድበናል። ይህ ቀጠሮ በአስተዳዳሪው ብቻ ሲቀየር ለሦስተኛ ጊዜ ነው÷ ብዙ ወጣቶችም ተጎድተዋል÷ ምናልባትም የታፈሱ ልጆችም
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የራያ ጥያቄና የሰሞኑ የአላማጣ ግጭት መንሳኤ ሲመረመር

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ንግግር በፓርላማ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የቡራዩ ነዋሪዎች ወደቤታቸው ተመልሰዋል

Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኬንያ ተሰዶ የነበረው ጋዜጠኛ ቴዲ ካሳ – መረጃ ቲቪ 7 ደቂቃ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከሀረር ከተማ የውሃ ጥማት በስተጀርባ ያለው የሃረሪ ሊግ እና የኦህዴድ ፍጥጫ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 13/2011) የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በይፋ ተጀመረ። https://www.ethiopiatrustfund.org/ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በይፋ ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ በፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም የሚመራ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት አማካሪ ቦርድ መሰየሙም ይታወሳል። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሃገር ቤት የሚኖሩ ችግረኛ ዜጎችን ለመደገፍ በቀን አንድ ዶላር እንዲያዋጡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የተቋቋመው አማካሪ ቦርድ ትላንት በይፋ ...

The post የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ተጀመረ appeared first on ESAT Amharic.

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የትግራይ ክልል የኮምዩኒኬሽን ሃላፊ የራያ-አዘቦን ውዝግብ አስመልክቶ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጎሳ ግጭት ምክንያት የሃረር ከተማ ህዝብ በውሃ ጥም እየተሰቃየ ይገኛል

Posted in Amharic News, Ethiopian News

አባ መላ በመረጃ ቲቪ – ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ/ም እአአ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለቄሮ መሬት አልሰጠንም። ውሸት ነው። አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው… – ከንቲባ ታከለ ኡማ ለኢቲቪ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ብፁዕ አቡነ መርቆርዮስ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ከመረጃ ቲቪ ጋር ያደረጉት ቆይታ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጎንደር ከተማ ከንቲባ ከአዲስ ድምጽ ጋር ያደረጉት ቆይታ – አዲስ ድምጽ በመረጃ ቲቪ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጋዜጠኛ እስክድር ነጋ ለጠ/ሚ አብይ የሰጠው ምክር

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የታጠቁ ወታደሮች ወደቤተመንግስት የመጡበት ሁኔታ ለውጡን ለመቀልበስ ነበር ሲሉ ጠ/ሚ አብይ ለፓርላማ አብራሩ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

«ራሳችንን ለመከላከል በወሰድናቸው እርምጃዎች የሰው ህይወት አልፏል፣ በዛ በጣም እናዝናለን» – የኢህአፓ ሊቀመንበር

Posted in Amharic News, Ethiopian News

«ሁሉም የአዲስ አበባ ታክሲ ሹፌር በአሁን ሰዓት መሮታል። ሰርተን መብላት አቃተን» – የታክሲ ማህበር ተወካይ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአዲስ አበባ አስተዳደር አፍኖ የወሰዳቸውን በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ሊፈታ ይገባል – ዋሜራ በመረጃ ቲቪ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሙስና እና ዘረኝነት የተተበተበው መከላከያ ሰራዊት የህዝብ አገልጋይ እንዲሆን ስራ መሰራት አለበት – አባ መላ በመረጃ ቲቪ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠ/ር አብይ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ሰቃ ፏፏቴን ከጎበኙ በኋላ የጅማ ህዝብ በዚህ መልክ ተቀብሏቸዋል

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኦሞ ኩራዝ የስኳር ፋብሪካ ቁጥር 3 በጠ/ሚ አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተመረቆ ተከፍቷል – ቪዲዮ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

7 ደቂቃ ከጋዜጠኛ እስክድር ነጋ ጋር – መረጃ ቲቪ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ወታደሮች ቤተመንግስት እንዲከቡ ሲያነሳሱ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው – ጄኔራል ፀዓረ መኮንን

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ቄሮ ብለው ራሳቸውን የሚጠሩ ቡድኖች በተለያዩ አካባቢዎች ህዝብ እያሸበሩ ይገኛሉ – ዋሜራ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ግንቦት ሰባት በናዝሬት – video

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የፖለቲካ መገለጫ የሆነ ባንዲራ፣ አርማ መፈቀድ የለበትም – ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ፓይለት ዮሃንስ ተስፋዬ ወደስራው መመለስ እንደሚችል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ

በማንነቴ ስራ ቦታ ላይ በደል ተፈጸመብኝ ያለው ፓይለት ዮሃንስ ተስፋዬ ወደስራው መመለስ እንደሚችል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ። ዘገባውን ይከታተሉ ↓
Posted in Amharic News, Ethiopian News

«ደረሰኝ ስጡን ስንላቸው ደረሰኙ ዱላ ነው» – የአዲስ አበባ ወጣት ነጋዴ

«ደረሰኝ ስጡን ስንላቸው ደረሰኙ ዱላ ነው» – የአዲስ አበባ ወጣት ነጋዴ በከተማው እብሪተኛ አስተዳደርና ፖሊስ ወጣቱ እየተፈጸመበት ያለውን በደል ይናገራል
Posted in Amharic News, Ethiopian News

7 ደቂቃ ከአክቲቪስት ኦባንግ ሜቶ ጋር

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የመከላከያ ሃይል ላይ ሳቦታጅ እየተደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊፈትሹ ይገባል – አባ መላ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን በወታደሮች ታግተው ነበር ወይ? የመረጃው ምንጭ «እውነታው ይህ ነው» ይላል (ሃብታሙ አያሌው)

ከሃብታሙ አያሌው መንግስት ስለሁኔታው ከዚህ በላይ እንዲል አልጠብቅም። መቼም ታገትን እንዲሉ አይጠበቅም። ያለቀጠሮ መሳሪያ ይዞ መጥቶ አስገድዶ ያናገረን ሰራዊት አብርዶ መመለሱ ጥሩ ቢሆንም በጎ ሁኔታ እና ልምድ ግን አይደለም። የሆነው ሁኖ ወደ መረጃ ምንጬ ተመልሼ የሆነውን በዝርዝር እንዲያስረዳኝ በመጠየቅ በርግጥ በርግጥ እገታ አልነበረምን ? ስል ለጠየኩት ጥያቄ እውነታው ይህ ነበር ብሎኛል! ጠዋት 4:45 ~~~~~~ ከወትሮው ባልተለመደ መልኩ የመከላከያ ሰራዊት የተውጣጡ ቀይ ቦኔት የለበሱ አባላት አራት ኪሎ በአራቱም አቅጣጫ ላይ መታየት ጀመሩ። ወዲያው ባፋጣኝ ወደ ጊቢ ገብርኤል የሚወስደው መንገድ ለተሽከርካሪ ዝግ ተደረገ። ቀትር 6:30 ~~~~~~ በተለያየ አቅጣጫ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የሚመጡት ልዩ ሃይሎች ቁጥራቸው እየበዛ መጣ። ከቀኑ 7:45 ~~~~~~ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሚሊኒየም አዳራሽ የኮንስትራክሽን ኤግዚቢሽን በይፋ ከፍተው ከቦሌ ወደ አራት ኪሎ ፅ/ቤታቸው አቀኑ። ከቀኑ 7:55 ~~~~~~ ከተለያየ አቅጣጫ የሚጎርፉት የሰራዊቱ አባላት ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ፤ አራት ኪሎ አካፋይ መንገድ ላይ ወደ ቤተመንግስት የሚወስዱ መኪናዎች አቅጣጫ እየቀየሩ አከባቢው ተጨናንቆ ነበር። ከቀኑ 8:00 ~~~~~~ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀን የያዘው መኪና {ጥይት የማይበሳው} ወደ አራት ኪሎ አካፋይ መስቀለኛ መንገዱ ጋር ደረሰ። የአቶ ደመቀ ልዩ ጠባቂዎች በፍጥነት ከመኪናው ወርደው አጅበው ለማሳለፍ ፤ አልተሳካም ወታደራዊ ሃይሉ አቶ ደመቀን አግቶ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዋና ጠባቂ {Cheif Secirty} ጋር ቃላት ተመላለሱ። ይህ ሁኔታ ድንጋጤ ፈጠረ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን መንገድ ላይ ያገኙት በእቅድና በዝግጅት ወይስ ባጋጣሚ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አስደናቂ የፈረስ ትዕይንት በባህር ዳር – video

Posted in Amharic News, Ethiopian News

አጭር ቀሚስ የምትለብስ ሴት ስናይ ዘራፍ እያልን፣ ግን ተደብቀን ወሲባዊ ፊልሞችን በኢንተርኔት እናያለን – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለውጡ እንዲሳካ የጠ/ሚ አብይ መንግስት አስቸኳይ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ጉዳዮች – አባ መላ በመረጃ ቲቪ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

አባ መላ አባ መላ በመረጃ ቲቪ ያለፈው ሳምንት የተካሄደውን የኢህአዴግ ጉባኤ ይገመግማል – ይመልከቱ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢህአዴግን 11ኛ ጉባኤ እኛ እንደ 1ኛው ጉባኤ አድርገን ነው የምንወስደው – ደምሴ ቱሉማ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

መንግስት በግብታዊነት የሚጨምረው ቀረጥ ነዳጅ አመላላሾችን እያከሰረ መሆኑ ተገለጸ – ዋልታ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶ/ር ተዋበች ቢሻው ስለኢትዮጵያ መንግስት የዳያስፖራ ፖሊሲ የሰጡት ማብራሪያ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢህአዴግ 11ኛ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ሪፖርትና የአቋም መግለጫ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም በቅርቡ ወደሀገር ቤት ስለጠሩት 90 አምባሳደሮች እና ሌሎችም ጉዳዮች ለመረጃ ቲቪ ማብራሪያ ሰጥተዋል

የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም በቅርቡ ወደሀገር ቤት ስለጠሩት 90 አምባሳደሮች እና ሌሎችም ጉዳዮች ለመረጃ ቲቪ ማብራሪያ ሰጥተዋል
Posted in Amharic News, Ethiopian News

11ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ የታዘብናቸው ነገሮች – አባ መላ በመረጃ ቲቪ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

አዴፓ (የቀድሞው ብአዴን) 9 የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ እና የድርጅቱን 13 ስራ አስፈጻሚ አባላትን መርጧል

ባሕር ዳር፡መስከረም 22/2011 ዓ.ም አዴፓ 9 የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ አባላትን አሳወቀ፡፡ 1.አቶ ደመቀ መኮንን 2.አቶ ገዱ አንዳርጋቸው 3.ዶክተር አምባቸው መኮንን 4.አቶ ብናልፍ አንዷለም 5.አቶ ተፈራ ደርበው 6.ዶክተር ይናገር ደሴ 7.አቶ መላኩ አለበል 8.ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ 9.አቶ ምግባሩ ከበደ አዴፓ የድርጅቱን 13 ስራ አስፈጻሚ አባላት፡፡ 1.አቶ ደመቀ መኮንን 2.አቶ ገዱ አንዳርጋቸው 3.ዶክተር አምባቸው መኮንን 4.አቶ ብናልፍ አንዷለም 5.አቶ ተፈራ ደርበው 6.ዶክተር ይናገር ደሴ 7.አቶ መላኩ አለበል 8.ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ 9.አቶ ምግባሩ ከበደ 10.አቶ ላቀ አያሌው 11.አቶ ዮሀንስ ቧያለው 12.አቶ ጸጋ አራጌ 13.አቶ ንጉሱ ጥላሁን አዲሱ የድርጅቱ አርማ የምርጫውን ሂደት የሚያሳይ ቪዲዮ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለግንቦት 7፣ ኦነግ፣ OMN እና ኢሳት አመራሮችና አፈቀላጤዎች አጭር መልእክት አለኝ (አባዊርቱ)

ሀሳባችሁ በጭራሽ ሊገባኝ አልቻለም:: በደፈናው ግን የበላችሁበትን ወጪት ሰባሪዎች ናችሁ:: እኒህ ቅን መሪ እውራን በበዙበት ሀገር በፈጣሪ ሀይል ብቅ ብለው ለአገር በጋራ እንተልም ባሉና ዘንባባ አንጥፈው በተቀበሉ ያውም ሹማምንት ኤርፖርትና በየኬላው እየላኩ አክብረው ትልቅ ትንሽ ሳይሉ አስቤዛና ማረፊያ ቤት ሳይቀር በተቀበሉ እጉያቸው ስር ሆናችሁ እንደምስጥ ትሰረስሩዋቸው ጀመር? ለናንተ ስልጣን ብላችሁ መንበሩ ሳይረጋ እንዲህ ባደባባይ ታሳፍሩን? […]
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኦሮሞ ድርጅቶች መግለጫ እና የእኔ ዕይታ! (ግርማ ሠይፉ ማሩ)

የኦሮሞ ድርጅቶች ነን ያሉ አምስት ድርጅቶች በኦሮሞ እሴቶችና ጥቅም ላይ በመመርኮዝ የኦሮሞን አንድነት በሚያንጸባርቅ እና እንደ በሚያደርጋቸው ፤ እንዲሁም በወቅታዊ አንገብጋቢ የፖለቲካ ጉዳዮች ናቸው ብለው ባመኗቸው ጉዳዩች ዙሪያ የጋራ ያሉትን አቋም ወስደዋል፡፡ ይህ አቋማቸው ግን በሁሉም ዘንድ በሁሉም ጉዳይ ሰምምነት ይፈጥራል ባይባልም- ጫጫታ ፈጣሪ እንደሆነ ግን የሚካድ አይደለም፡፡ በእኔ ዕይታ ይህ መግለጫ በኦሮሚያ ክልል ለሚንቀሳቀሱ […]
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አቶ በቀለ ገርባ፣ ምነው እንዲህ አይነት የወረደ አስተሳሰብ ውስጥ ወደክ? (አቡ ሳለም)

ከአቡ ሳለም የት ይደርሳል የተባለን ዛፍ ቀበሌ ቆርጠው እንዲል ይህ ትውልድ አንተም በቀበሌኛ መጥረብያ ከብዙዎች ልብ ተቆረጥህ። ለመሆኑ በኦርምኛ ብቻ የተጻፉትን ጹሑፎች ካላነበብክ በቀር ፊንፊኔ የሚለው የቀደመ የአዲስ አበባ መጠርያ የመጣው በእቴጌ ጣይቱ ምክንያት እንደሆነ እና ይኸውም ከፍል ውሃ አካባቢ ጋር የተያያዘ መሆኑን ይሄ ጠፍቶህ ነው? እቴጌይቱ ከእንጦጦ ወርዳ ይህን አካባቢ ባየች እና የፍል ውሃ ወደ ላይ ፊን ፊን ሲል ባየች ግዜ “ፊን ፊን ” ስትል አካባቢውን ጠራችው እናም እየቆየ ሲሄድ በአካባቢው ነዋሪዎች(ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ይሁኑ አይሁኑ ማረጋገጫ መስጠት አይቻልም) ምክንያቱም ኦሮምኛ እሰማለሁ እናገራለሁ ግን ይሄ ቃል ኦሮምኛ ስለመሆኑ አላውቅም እንደውም ፊን ፊን ወደ አማርኛው ያደላ ወይም በሁለቱ መሃል ነው። በሌላ በኩል እቴጌይቱ ከኦሮሞና ከአማራ ዘር የሚመዘዙ እንደሆነ የሚናገሩ የታሪክ ፀሃፊዎች አሉ። እናም ኦሮሞ እንደቆረቆራት ከተማ ለመወሰድ አያስኬድም ከእቴጌይቱ በፊት የተቆረቆረች ከተማ ነች የሚሉ ከሆነ ከዝያ በፊት የነበረውን ስሟን እና መከራከሪያ ነጥቡን እንወቀው። አለም በመኃሏ ያለውን አርቴፍሻል ወሰን እየናደች ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ እና ፓለቲካዊ ትስስር እየተፈጠረ ባለበት በ21ኛው ክ/ዘመን ዝም ብሎ የኛ የኛ እያሉ ሌሎች ባለቤት እንዳልሆኑ በድፍረት መናገር አሳፋሪም የእውቀት እጥረትም ነው። ካለበለዝያም የዘረኝነት በሽታ። ኦሮሚያ ወይም ኦሮሞ ከአዲስ አበባ ማግኘት ያለበትስ ጥቅም ምንድነው? ለምን? ጣልያን አዲስ አበባን ይዞ በነበረበት ግዜ የጣልያንን ሹማምንት በጨበጣና በቦንብ በልዩ ልዩ መንገድ እየተፋለሙ ያርበደበዱ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ኦሮሞዎች ብቻ ነበሩ እንዴ? ሌላው ይቅርና አዲስ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በቡራዩ እና አካባቢው የደረሰው የህይወት መጥፋት በሌሎችም ቦታዎች እንዳይደገም መንግስት የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ሊያደርግ ይገባዋል

የፌዴራል ፖሊስና ሁሉም የጸጥታ ሃይሎች ግጭቶች በሚፈጠሩበት ወቅት በሰው ህይወት መጥፋት የተቆጣውን ህዝብ ድምጽ ከማፈን እና ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ጥይት ከመተኮስ ይልቅ ወዲያው የወንጀል ድርጊቶች እንደተፈጠሩና ከመፈጠራቸውም በፊት ፈጣን እርምጃዎችን መውሰድና በየተወሰኑ ሰዓታት ጋዜጣዊ መግለጫዎች በመስጠት ህዝብ የማረጋጋት ስራ እንዲሰሩ መመሪያ እና ስልጠና መስጠት ያስፈልጋል። የፌዴራል ፕሊስ የአመራር ጉድለት ለቡራዩ እልቂት ትልቅ አስተዋጻኦ ማድረጉ ግልጽ እየሆነ መጥቷል። ከዚህም አልፎ ፌደራል ፖሊስ 5 ዜጎችን በጥይት ገድሏል። ለዚህ የሰው ህይወት መጥፋት ተጠያቂ የሆኑ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል። ስህተቶቹ እንዳይደገሙ ከኮሚሽነሩ ጀምሮ የአመራርና የመመሪያ ለውጥ ያስፈልጋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በህብረተሰቡ ማካከል ግጭት ሊፈጥሩ ከሚችሉ ድርጊቶችና ቅስቀሳዎች እንዲቆጠቡ ሊመከሩና ሊገሰጹ ይገባል። የተጀመረውን ለውጥ ህብረተሰቡ እንዴት እንደሚያግዝና ወደሰላም፣ አንድነትና እና ልማት መንገድ ማምራት እንደሚቻል የሚጠቁሙና የሚያስተምሩ ተከታታይ የውይይት ፕሮግራሞችን ከሚዲያ ጋር በመተባበር ማካሄድ። ግጭቶች ሲከሰቱ ኢንተርኔት መዝጋት እና የህዝብ ድምጽ ማፈን ችግሮችን ማባባስ እንጂ መፍትሄ እንዳልሆነ አሁንም መንግስት የተማረ አይመስልም። ለሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት የፖለቲካ ፓርቲዎች የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባዎች እንዳያካሂዱ ትብብራቸውን መጠየቅ። በቅርቡ ሲፈጸሙ ከቆዩት ግጭቶች ጀርባ ከፍተኛ መጠን ያለው ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ፍሰት እንዳለ ይታወቃል። የዚህን ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ምንጭ መመርመርና ተጠርጣሪዎቹን ለፍርድ ማቅረብ። በአሁኑ ወቅት ከ60 ፐርሰንት በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ብር የት እንዳለ ብሄራዊ ባንክ እና መንግስት እንዳማያውቅ ተነግሯል። ይህ ከመንግስትና ከባንክ እውቅና ውጭ ያለ ብር ከፊሉ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የዳያስፖራ ኤጀንሲ ስለማቋቋም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም የሰጡት ማብራሪያ

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

አባ መላ በመረጃ ቲቪ – ልዩ ውይይት ከአክቲቪስት መስፍን ፈይሳ ጋር

Posted in Amharic News, Ethiopian News

በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራ የኤርትራ መንግስት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ወደ አማራ ክልል ሊመጣ መሆኑ ተገለጸ

በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራ ልኡክ ወደ አማራ ክልል ሊመጣ መታቀዱን FBC ዘገበ። የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን የሚመሩት ልኡክ በአስመራ ይገኛል። በቆይታቸውም አቶ ንጉሱ ጥላሁን ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ልዩ አማካሪ ከአቶ የማነ ገብረአብ ጋር የኤርትራውያንንና የኢትዮጵያዊውያንን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ላይ መወያየታቸውን አስታውቀዋል። በዚህም መሠረት በቅርቡ በአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚመራ የልዑካን ቡድን ወደ አስመራ እንዲጓዝ መስማማታቸውንም አቶ ንጉሱ ገልፀዋል። እንዲሁም የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመሩት የልዑካን ቡድን ወደ አማራ ክልል እንዲሚመጣ ከስምምነት መድረሳቸውም አቶ ንጉሱ ያስታወቁት። […] ተጨማሪ ዝርዝር
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጥብቅ ሚስጥር የያዘው የታህሳሱ የደብረጽዮን ኢሜይል

በታህሳሱ (December 2017) የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ላይ የተከናወነ ነበር። የአገሪቷ ወሳኝ ምዕራፍ መወሰኛ ስብሰባ፡፡ የለማና የገዱ ቡድን እየተጠናከረ ሲመጣ ትህነግ ስብሰባው ውስጥ ቁጭ ብሎ የሙስና ወንጀል በኦህዴድና በብአዴን ስራ አስፈጻሚዎች ላይ በሰፊው ይፈልግ ነበር። ደብረጽዮን ቀናውና በአዲስ አበባ ከንቲባ ደሪባ ኩማ መስተዳደር በግፍ የተባረረው የቀድሞ አማካሪና የአሁኑ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ (Harvard University) ተመራማሪ Dec 17, 2017 ቀን ኢሜይል ጻፈ። በሙስና ሰበብ ለማምበርከክ የተፈለገው ደግሞ የአዲስ አበባውን ከንቲባ ደሪባ ኩማ ዋነኛነት ነበር። ኢሜይሉ እንደሚያሳየው የአዲስ አበባ ትራንስፖር ቢሮ ሃላፊው የዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ስም የተጠቀሰ ሲሆን ከዚህ ግለሰብ ጋር በተያያዘ ከንቲባው በሚከተሉት ሙስናዎች በከፍተኛ ሁኔታ በሰራተኞቹ ይታማ ነበር። በ850 አውቶቢስ ግዢና ከአለም ባንክ የተገኘው የ300 ሚሊየን ዶላር ብድር አፈጻጸም ከንቲባው በሚመራው በትራንስፖርት ቢሮ ስር የትራንስፖርት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በማቋቋምና ከንቲባው ራሱን የጽ/ቤቱ የቦርድ ዳሬክተር በማድረግ ጠያቂና ተጠያቂ እንዳይኖር በማድረግ በየአመቱ ከ600 ሚሊየን ብር በጀት በላይ ኦዲት ሳይደረግ ለዝርፊያ አመቻችቶ ስላዘጋጀ። ስለሆነም ፈስ ያለበት መዝለል አይችልም እንደሚባለው በስብሰባው ወቅት ከንቲባ ደሪባ ለትህነግ (ህወሃት) ወግኖ በለውጥ ሃይሉ (የለማና ግድዱ ቡድን) ላይ ከፍተኛ ሂስ ሲያወርድ ነበር። ደረጀ ገርፋ በትክክል እንዳስቀመጠው ለግብ የሚሆኑ ኳሶች ለነደብረጽዮን ያቀብል ነበር። የለውጡ ቡድንም ቂም ይዞበት ስለነበር ስልጣን ከያዘ በኋላ ደሪባ ኩማን ከስልጣን ለማራቅ አምባሳደር አድርጎ በመሾም ከፖለቲካው በጡረታ አስወጥቶ ታከለ ኩማን በከንቲባነት ሹሟል። በሙስና የሚጠረጠረው ዶ/ር ሰለሞን የታከለ ምክትል ሆኖ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በሻሸመኔ አሰቃቂውን ግድያ የፈጸሙት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል

(ኢሳት) – በሻሸመኔ ከተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ጋር በተያያዘ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቃል አቀባይ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ እንደተናገሩት በተፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት እጃቸው ያለበትን አካላት በመያዝ ለፍርድ ለማቅረብ ሂደቱ ተጀምሯል። የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የልዑካን ቡድንን ለመቀበል በአስርሺዎች የሚቆጠሩ የሻሸመኔና አካባቢዋ ነዋሪዎች አደባባይ መውጣታቸውን ተከትሎ በተፈጠረ ግርግር የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉም ታውቋል። ፖሊስ ከተማዋን ለማረጋጋት እየሰራሁ ነው ብሏል። በሻሸመኔ በአሰቃቂ ሁኔታ የተፈጸመውን ግድያ በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያንን አስቆጥቷል። የሻሸመኔው አሰቃቂ ግድያ ብዙዎችን አስደንግጧል። አንድን ግለሰብ በድብደባ ህይወቱ ካለፈ በኋላ ቁልቁል ተሰቅሎ የሚታይበት ፎቶግራፍ በማህበራዊ መገናኛ መድረኮች በስፋት ተሰራጭቷል። ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን በማውገዝ የተቃውሞ መልዕክቶችን በየመድረኩ አሰምተዋል። VOA ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የልዑካን ቡድን አባላት አቀባበል የወጣው የሻሸመኔ ከተማና አከባቢዋ ነዋሪ በተሰሳሳተ መረጃ በተፈጠረ ግርግር አራት ሰዎች ተረጋግጠው መሞታቸንም ለማወቅ ተችሏል። ቦምብ ይዟል ብሚል ያልተጣራ መረጃ ተደብድቦ የተገደለው ወጣት ከተሰቀለም በኋላ በመኪና ለመጎተት የተደረገው እንቅስቃሴ ብዙዎችን አስቆጥቷል። ጉዳዩ ከውግዘት ባለፈ ድርጊቱን በፈጸሙ ሰዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ተጠይቋል። በዛሬው ዕለት ለኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔት ወርክ መግለጫ የሰጡት የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ አሰቃቂውን ግድያ የፈጸሙት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል። በሻሸመኔ ከተማ ቦምብ ተገኝቷል በሚል የተፈጠረው ግርግር የሰው ህይወት ማጥፋቱንም በመግለጽ መረጃ ትክክል አልነበረም ብለዋል። ፖሊስ እስከአሁን ባደረገው ማጣራት ቦምብም ይሁን ከቦምብ ጋር የሚመሳሰል ምንም ዓይነት ነገር እንዳልተገኘ ዶ/ር
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ስራ አስኪያጅ ጆዋር መሃመድ እና የስራ ባልደረቦቹ በአማራ ክልል ቲቪ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዮስ አቀባበል በቦሌ ኤርፖርት – LIVE

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሜነሶታ ነዋሪዎች ከጠ/ሚ አብይ ጋር ያደረጉት ጥያቄና መልስ – video

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ግንቦት ሰባት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ለመግባት ወሰነ – ጋዜጣዊ መግለጫ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በሚኒያፖሊስ – ቀጥታ ስርጭት

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በሎስ አንጀለስ – ቪዲዮ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ የዋሽንግተን ዲሲ ጉብኝት – ቀጥታ ስርጭት

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጠ/ሚ አብይን የአሜሪካ ጉዞ ለማደናቀፍ አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃንና ግብረአበሮቹ የሸረቡት ሴራ (መሳይ መኮንን)

የዶ/ር አብይ አህመድን የአሜሪካን ታሪካዊ ቆይታ ለማሰናከል አንድ ሃይል ጉልበት ያገኘ ይመስላል። በዋሽንግተን ዲሲና በሎስአንጀለስ ዝግጅቱን በበላይነት የሚመሩት አፍቃሪ ህወሀቱ ካሳ ተ/ብርሃንና ብርሃኔ ኪዳነማርያም ናቸው። ይህን ታሪካዊ ጉብኝት በእነዚህ የህወሀት ወኪሎች እንዲመራ መደረጉ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል። ታማኝ በየነን ከመርሃ ግብሩ የሰረዘው ኤምባሲው ነው። ካሳ ተክለብርሃን የኮንቬንሽን ማዕከሉን መድረክ እመራለሁ ብሎ የታማኝን ቦታ አስለቅቋል። ስለኤችአር 128 ማብራሪያ ለመስጠትና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ ለማቅረብ ፕሮግራም የተያዘላቸው ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪም በመጨረሻው ሰዓት ምንም ዓይነት ንግግር እንደማያደርጉ በኤምባሲ በኩል በተላለፈ ትዕዛዝ መሰረዙ ተሰምቷል። የዲያስፖራው ድምፅ እንዲታፈን በካሳና ግብረአበሮቹ እየተደረገ ያለው ስውር ዘመቻ እየተሳካላቸው ነው። ካሳ ተክለብርሃን በአፉ ጤፍ ሲቆላ፣ ሲያታልል ቆይቶ ባለቀ ሰዓት ያደፈጠበትን መረብ ዘርግቷል። እየተጣጠፈ በብልጣብልጥ ተራ የማታለል እንቅስቃሴው ውስጥ ቆይቶ መሰሪ ባህሪውን ከሸለፈቱ በመፈልቀቅ በእኩይ ተግባሩ የዶ/ር አብይን ታሪካዊ ጉዞ እየበጠበጠው ነው። እንደሰማነውም የ1500 ሰዎች የውይይት መድረክም በህወሀት ተጠልፏል። ካሳ መድረኩን በህወሀት ደጋፊዎች እንዲሞላ በጀርባ የግብዣ ጥሪዎችን በትኗል። የጠቅላይ ሚኒስትሩን ታሪካዊ ቆይታ ለማደብዘዝ የታቀደው የእነካሳ ሴራ ካልተሰበረ ችግር ሊገጥመው እንደሚችል ይገመታል። ይህ አጋጣሚ እንዳይሰናከል የመስተንግዶው ኮሚቴ በቀረው ጊዜ ሁሉም የሚችለውን ማድረግ ይጠበቅበታል። የካሳ ሴራ መክሸፍ አለበት። ዶ/ር አብይ ይህን ሰው ዋሽንግተን ዲሲ ማስቀመጥ አልነበረባቸውም። ለቀጣይ አብዝተው ቢያስቡበት ጥሩ ነው። በዋሽንግተን ዲሲ የበረከት ስምዖን ጀሌ አምባሳደር ካሳ ተከለብርሃን
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ውይይት እያደረጉ ናቸው … ቀጥታ ስርጭት

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠ/ሚ አብይ በሚገኙበት መድረክ ላይ አርቲስት ታማኝ በየነ የዳያስፖራውን መልዕክት እንዳያስተላልፍ የዲሲው ኢትዮጵያ ኢምባሲ ለምን አገደ?

በበረከት ስምኦን ጀሌዎች ካሳ ተክለብርሃንና ረታ አለሙ የሚመራው የዋሽንግተን ዲሲ ኢትዮጵያ ኢምባሲ የጠ/ሚ አብይ አህመድ የአሜሪካ ጉብኝት እንዳይሳካ ብዙ አሻጥሮችን ሲሰራ ቆይቷል። አርቲስት ታማኝ በየነና ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን የታዘቡትን እንዲህ ሲሉ አብራርተዋል፦
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዮስ የፊታችን ሳምንት አዲስ አበባ ሲገቡ እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ ለመቀበል ዝግጅት ተጀምሯል

ላለፉት 27 ዓመታት በስደት የቆዩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁህ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ የፊታችን ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ይጠበቃል። ፓትሪያርኩ የአሜሪካ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ከሚመለሱት ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ጋር አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት ዝግጅቱን በሰፊው ጀምሯል። ለኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አንድነት ሲጸልዩ የቆዩ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ፓትሪያርኩን እና ጠቅላይ ሚኒስትሩን በነቂስ ወጥተው ለመቀበል በጉጉት እየጠበቁ ናቸው። ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን። ተከታተሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የእርቅ ስምምነት ስነስርዓት – ቀጥታ ስርጭት ከዋሽንግተን ዲሲ – LIVE

Posted in Amharic News, Ethiopian News

“ይሄ አገዛዝ የኦሮሞ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው” – ጠ/ሚ አቢይ አህመድ

$bp("Brid_36098_1", {"id":"12272","video":"273181","width":"550","height":"309"});
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከጠ/ሚ አብይ ጋር በአሜሪካ የሚደረጉ ውይይቶች ይዘታቸው ሁለገብ ሊሆን ይገባል

የሚቀጥለው ሳምንት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በአሜሪካ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ለመወያየት ዋሽንግተን ዲሲ ይገባሉ። በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሎስ አንጀለስና በሚኒያፖሊስ ከተማዎች የተለያዩ ስብሰባዎች ተዘጋጅተዋል። አንዳንዶቹ ስብሰባዎች ብዙ ሺህ ህዝብ የሚሳተፍባቸው ሲሆኑ፣ የተቀሩት ደግሞ የተለያዩ ድርጅቶችንና ማህበሮችን የሚወክሉ ጥቂት የተጋበዙ ግለሰቦች የሚካፈሉበት የውይይት ፕሮግራሞች ናቸው። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በእነዚህ ሶስት ከተሞች የሚደረጉት ስብሰባዎች ላይ የሚገኘው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመሩትን የለውጥ እንቅስቃሴ ለመደገፍና በርቱ ለማለት ነው። የውይይት መድረኮቹ ግን ትንሽ ለየት ያለ ይዘት ይኖራቸዋል። ማለትም የተለያዩ የህብረተሰቡን ክፍል የሚወክሉ፣ በተለይም ባለፉት 27 ዓመታት በተቃውሞ ጎራ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የቆዩ አክቲቪስቶች ተገኝተው ጥያቄዎች የሚጠይቁበትና አስተያየቶች የሚያቀርቡበት ፕሮግራሞች ይኖራሉ። ከፕሮግራሞቹ ውስጥ አንዳንዶቹ ግን ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ወደአሜሪካ ከሚመጡበት ዓላማ ጋር የሚጋጩ ናቸው። በተለይ ቪዥን ኢትዮጵያ የሚባለው ቡድን ባልታወቀ ሁኔታ የጠለፈውና ወደ 100 የሚጠጉ ግለሰቦች የሚሳተፉበት በዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው የውይይት መድረክ የተለያዩ ድርጅቶችን አመለካከቶች የሚያንጸባርቅ ሳይሆን የአንድን ድርጅት፣ ማለትም የግንቦት ሰባትን አጀንዳ ለማራመድ የተሰናዳ ሆኖ ተገኝቷል። ግንቦት ሰባት በዳያስፖራ ካሉ ኢትዮጵያውያን መካከል 1 ፐርሰንቱን እንኳን አይወክልም። ከዛም በተጨማሪ ከውጭ መንግስት (ኤርትራ) ጋር ባለው ጥብቅ ትስስር ምክንያት ኢትዮጵያውያን በጥርጣሬ የሚያዩት ድርጅት ነው። ለዚህ ድርጅት ከሚገባው በላይ እውቅና ሰጥቶ ሌሎችን ማግለል ተገቢ አይደለምና ሊስተካከል ይገባል። የውይይት መድረኮቹ ሁሉገብ ይዘት ይኖራቸው።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ህወሓት አማራንና ኦሮሞን ለማጣላት የተቀነባበረ የሶሻል ሚዲያ ዘመቻ በአዲስ መልክ ጀምሯል

የህወሓት ካድሬዎች ለጸረ-ለውጥ የሶሻል ሚዲያ ዘመቻቸው ከሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች አንዱ የኦሮሞና የአማራ በሚመስሉ ስሞች ብዙ ሺህ የፌስቡክና የትዊተር አካውንቶች ከፍተው በመርዝ የተለወሱ አስተያየቶችን በመጻፍ ጠብ መጫር ነው። የኦሮሞንና አማራ ህዝብን ለማጣላት ህወሓት የማያደርገው ነገር አይኖርም። አጼ ምኒሊክ የኦሮሞ ሴቶችን ጡት ቆርጠዋል የሚል የውሸት አፈታሪክ በመንዛት አርሲ ውስጥ በሃያ ሚሊዮን ብር የተቆረጠ ጡት ሃ ውልት ያቆመ መሰሪ ድርጅት መሆኑን አንርሳ። ሰሞኑን ኦህዴድ የኢትዮጵያን መንግስት ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሯል የሚል አሳሳች ወሬ በስፋት በሶሻል ሚዲያ እየተነዛ ነው። የዚህ ወሬ ምንጭ እነማን እንደሆኑ ለማወቅ ከባድ አይደለም። እንደገዢ ፓርቲ ቁልፍ ቦታዎችን ኦህዴድ ሊቆጣጠር ይገባል። በተለይ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ሌሎቹ ድርጅቶች እራሳቸውን ከወያኔ ሰላዮችና ካድሬዎች ሳያጠሩ ለእነሱ ቁልፍ የመንግስት ቦታዎች መስጠት ለለውጡ እንቅስቃሴ አደገኛ ነው። የመረጃና ደህንነት ሚኒስቴር፣ ለምሳሌ፣ በኦህዴድ ስር መሆን ሲገባው አቋሙ ገና በእርግጠኝነት ያልታወቀው የብአዴን አባል ጄኔራል አደም መሃመድ እጅ ነው ያለው። ኦህዴድ ሀገሪቱን በአግባቡ እስካስተዳደረና ወደ ዴሞክራሲ ጎዳና እስከመራ ድረስ ለጊዜው መንግስትን ሙሉ በሙሉ ቢቆጣጠር ምን ክፋት አለው? ቁልፍ ከሆኑ የሀገር ጸጥታ ሃላፊነት ቦታዎች ውጭ የተለያዩ ድርጅቶች አባላት ከፍተኛ ስልጣን ላይ ተመድበዋል። ለምሳሌ የፓርላማ አፈጉባኤ፣ የፌዴራል ፖሊስ አዛዥ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮ-ቴሌኮም፣ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የንግድ ሚኒስቴር፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ የፋይናንስ ሚኒስቴር፣ የመረጃና ደህንነት፣ የኢንሳ፣ እና ሌሎችም በርካታ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን መስርያ ቤቶች ሃላፊዎች የኦህዴድ አባላት አይደሉም። ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህን
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“ተሿሚው ሁሉ ኦሮሞ ነው” ስለምትለው ወሬ እውነታውን እንነጋገር – ከሩ ከሬ

ከከሩ ከሬ “ተሿሚው ሁሉ ኦሮሞ ነው” የምትለው ወሬ እግር አውጥታ እውነት መስላ ወደ እኛው ሳትመለስ አንድ ሁለት ነገር ማለት ያለብን ይመስላኛል። እውነታውን እንነጋገር። ኦሮሞ በኢትዮጵያ ፓላቲካ፣ኢኮኖሚ፣ መህበራዊ ተቋማት፣ የኃይማኖት ተቋማት (በክርስትናውም ሆነ በእስልምናውም)፣ በከተማ አሰፋፈሩ እና በኢትዮጵያ የመንግስት ተቋማት ውስጥ (አዲስ አበባ ከተማ መስተዳደርን ጨምሮ) የለም። አገር አልባ ህዝብ ተደርጓል። ኦሮሞ በኢትዮጵያ መንግስት ተቋማት አለ ተብሎ የሚደለለው እንደባንዲራ ከሩቅ የሚታዩ ውስን ቦታዎችን ለኦሮሞ ግለሰቦች በመስጠት ነው። ለምሳሌ፣ 1ኛ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ፣ ህወሃት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ያቺ የይስሙላ ቦታ የኦሮሞ ነች። ነገር ግን ከምክትሎቹ አንስቶ ቁልፍ የመምሪያ ኃላፊዎችና የክፍለ ከተሞች ከንቲባዎች በሙሉ ኦሮሞ አይደሉም። የማዘጋጃ ሠራተኞቹ ውስጥ በደም ኦሮሞ ነገር ግን ኦሮሚኛ የማይናገሩ ወደ 10% አሉ። 90% ቱ ሌላ ናቸው። የኦሮሞ ህዝብን የሚደልሉት ግን ከንቲባው ኦሮሞ ነው ተብሎ ነው። አዲስ አበባ ባለፉት 15 ዓመታት ብቻ ወደ 700,000 ኦሮሞ ገበሬ መሬቱን ቀምታ አፈናቅላለች። ባለፉት 27 ዓመታት አዲስ አበባ ከአንድ ሚልዮን በላይ ኦሮሞ አፈናቅላለች። 2ኛ፣ ውጭ ጉዳይ፣ ከሁለት ዓመት ጀምሮ ሚንስትሩ ኦሮሞ ነው። የውጭ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊዎች ውስጥ ከልተሳሳትኩ አንድ ኦሮሞ የለም። ምክትል ሚንስትሮቹም ውስጥ እንደዛው። ከአስር አመት በፊት እኔ መ/ቤቱን በፓላቲካ ምክንያት ስለቅ ከ600 በላይ ዲፕሎማቶች ውስጥ ኦሮሞ ቁጥር 13 ብቻ ነው።አሁንም እውነታው ይኸው ነው። የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ውስጥ ኦሮሞ አለ ለማለት አይቻልም። ኦሮሞ ውጭ ጉዳይን ተቆጣጥሮታል ተብሎ ግን ይወራል። 3ኛ፣ መከላከያ ሚንስትር፣
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የእርቅ ልኡካን ቡድን ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ደርሰዋል – ቪዲዮ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የ”ኦሮማይ” መጽሃፍ ደራሲ በዓሉ ግርማ እንዲገደል የሚያዝ በጄኔራል ገብረየስ ወልደሀና ተጽፎ ለኮ/ል ተስፋዬ ወልደስላሴ የተላከ ደብዳቤ

በበአሉ ግርማ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በብ/ጄ ገ/ዮሃንስ ወ/ሀና ተጽፎ ለ ተስፋዬ ወ/ስላሴ የተመራ ደብዳቤ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አምባሳደር ደስታ ወልደዮሃንስ ዴልካሶ የተመሰረተባቸውን ክስ አስተባበሉ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠ/ሚ አብይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ – ቀጥታ ስርጭት

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ኢሌይ የኢህአዴግ ባለስልጣናትን ጉድ ሁሉ አወጣለሁ፣ ብቻዬን አልወርድም ሲሉ አስጠንቅቀዋል – BBC Amharic

Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአስመራ ጉብኝታቸው ወቅት ጠ/ሚ አብይን እና ባለስልጣኖቻቸውን ከመቀመጫቸው ያስነሳቸው ሙዚቃ – ቪዲዮ

በኤርትራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድና ባለስልጣኖቻቸው የተደረገላቸው የእራት ግብዣ ላይ በዚህ መልክ ተስተናግደዋል፤ mereja.com ዩቲዩብ ቻነልን ሰብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ላይ ይጫኑ → https://goo.gl/YZcLT1
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

በአስመራ ቤተመንግስት ለጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አቀባበል ልዩ ፕሮግራም (የእራት ግብዣ) – ቀጥታ ስርጭት

Posted in Amharic News

በትግራይ ከተሞች ለጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ የድጋፍ ሰልፍ በውጡ ነዋሪዎችና በፀጥታ ሀይሎች መካከል ግጭት ተፈጥሯል

በትግራይ የተለያዩ ከተሞች ለጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ የድጋፍ ሰልፍ ለማደረግ የወጣው ህዝብ ላይ የክልሉ ፖሊሶች ድብደባና ወከባ አካሄዱ። በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ዋጃ ከተማ ልሙጡን ሰንደቃላማ እና የጠቅላይ ሚንስትሩን ፎቶ በመያዝ የድጋፍ ሰልፍ በውጡ ነዋሪዎችና በፀጥታ ሀይሎች መካከል ግጭት ተፈጥሯል። pic.twitter.com/7vKAyArMch — Ethiopia Live Updates (@Ethiopialiveupd) July 7, 2018 በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን አላማጣ ከተማ ለድጋፍ ሰልፍ የወጡ ነዋሪዎችና የክልሉ ፖሊስ ተጋጭተዋል። ፖሊስ በርከት ያሉ ወጣቶችን ማሰሩም ተነግሯል። pic.twitter.com/ysaEukXR4O — Ethiopia Live Updates (@Ethiopialiveupd) July 8, 2018 በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን አላማጣ ከተማ ለድጋፍ ሰልፍ የወጡ ነዋሪዎችና የክልሉ ፖሊስ ተጋጭተዋል። ፖሊስ በርከት ያሉ ወጣቶችን ማሰሩም ተነግሯል። pic.twitter.com/8J41M8XjPZ — Ethiopia Live Updates (@Ethiopialiveupd) July 8, 2018
Posted in Amharic News

በአዊ ዞን የቻግኒ ከተማ ህዝብ በዚህ መልክ የለውጥ እንቅስቃሴውን ደግፏል

Posted in Amharic News, Ethiopian News

በስዊዘርላንድ በተደረገ የሩጫ ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ሰሎሞን ባረጋን ቁምጣውን ጎትቶ እንዲሸነፍ አድርጓል

በስዊዘርላንድ በተደረገው የ5000 ሜትር ዲያመንድ ሊግ ውድድር ሊጠናቀቅ ጥቂት ሜትሮች ሲቀሩ አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ሰሎሞን ባረጋን ቁምጣውን ጎትቶ አስቀርቶታል። VIDEO $bp("Brid_30993_2", {"id":"12272","video":"269842","width":"550","height":"309"});
Posted in Sports

በከፋ ዞን ቦንጋ ከተማ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ዛሬ እንዲህ አጊጣ ውላለች

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የቴዲ አፍሮ ዘፈን ‘ቴዎድሮስ’ የባህር ዳር ህዝብ ለጠ/ሚ አብይ ባካሄደው የምስጋና ሰልፍ ላይ – ቪዲዮ

Subscribe to mereja.com YouTube channel: https://goo.gl/YZcLT1 የቴዲ አፍሮ ዘፈን ‘ቴዎድሮስ’ በባህር ዳር ስታዲዮም
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Music

የባህር ዳር የለውጥ ድጋፍ ሰልፍ ቀጥታ ስርጭት – ቪዲዮ

Posted in Amharic News
Follow us on Facebook
Follow us on Facebook