­

እየታየ ያለው የዋጋ ንረት የበዓሉን ድባብ እያቀዘቀዘው ነው፤

[addtoany]

የበዓል ገበያው እንዴት ይዟችኃል ?

በየጊዜው እየታየ ያለው የዋጋ ንረት የበዓሉን ድባብ እንደሚያቀዘቅዘው እሙን ነው።

ምን ያህሎቻችን ባለው የዋጋ ንረት ሳቢያ ኑሮ ፈተና እንደሆነብን እናውቀዋል፤ ምንም ያህል የዋጋ ንረቱ በአስፈሪ ሁኔታ ቢያሻቅብም በዓል ነውና በአቅም ሸምቶ ለማሳለፍ የሚሮጠው ብዙ ነው።

የዘንድሮው ገበያ ግን ከአምናውም በእጅጉ የተለየ ነው።

በተለይም በሀገራችን አንዳድን አካባቢዎች የእንስሳት ግብይት ዋጋ የማይቀመሥ ሆኗል። በርካቶችም ባለው የዋጋ ውድነት ሳቢያ ገዝቶ ከቤተሰብ ጋር ተደስቶ በዐል ለማሳለፍ ፈተና ሆኖባቸዋል።

ለአብነት ዛሬ በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ ያለውን ውድነት እንመልከት ፤ በባለፈው ዓመት በበዓል ገበያ 20 ሺህ ብር ይሸጥ የነበረ በሬ በዘንድሮው ዓመት ከእጥፍ በላይ ጨምሮ በ45 ሺህ ብር ተሽጧል።

በባለፈው ዓመት የበዓል ገበያ አንደኛ ደረጃ በሬ 42 ሺህ 667 ብር የተሸጠ ሲሆን ዘንድሮው የበዓል ዋዜማ ገበያ በአማካኝ 59 ሺ 333 ብር ተሸጧል። የ16 ሺህ 666 ብር ጭማሪ አሳይቷል።

የበግ ሙክትን ባለፈው ዓመት የበዓል ገበያ 4 ሺህ 766 ብር የተሸጠ ሲሆን በዘንድሮው ዓመት የበዓል ዋዜማ ገበያ 8 ሺህ ብር ተሸጧል። ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በበግ የ3 ሺህ 234 ብር ጭማሪ አሳይቷል።

የደጀን ወረዳ ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት ፤ የዋጋ ጭማሪው መንስኤ የእንስሳት መኖ እጥረት እንደሆነ ማስረዳቱን ከደጀን ወረዳ ኮሚኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ውድ ቤተሰቦቻችን በአካባቢያችሁ ያለው የበዓል ገበያው እንዴት ይዟችኃል ? ዘይቱ ፣ እንቁላሉ ፣ ዶሮው ፣ በጉ ፣በሬው ስንት እየተባለ ነው …. ?