በኦሮሚያ ክልል የመንግሥት መዋቅር አመራሮች የመሠረታዊ ውትድርናና ፖለቲካ ሥልጠና ሊወስዱ ነው

በኦሮሚያ ክልል የወረዳና የቀበሌ የመንግሥት መዋቅር አመራሮች ከመጭው ሐሙስ ጀምሮ ለ40 ቀናት የመሠረታዊ ውትድርናና ፖለቲካ ሥልጠና ሊወስዱ እንደኾነ ዋዜማ ሠምታለች። ሥልጠናውን የሚወስዱት አመራሮች የወረዳና ቀበሌ ዋና አሥተዳዳሪዎችና የሠላምና ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች መኾናቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ለ40 ቀናት ይቆያል የተባለው ሥልጠና የሚሠጠው፣ በአዋሽ ቢሾላ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ካምፕ ውስጥ መኾኑንም ምንጮች አስረድተዋል። የሥልጠናው ዓላማ በሁለቱ የመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ የሚሠሩ አመራሮችን የመሠረታዊ ውትድርና ክህሎትና ፖለቲካዊ አቅም ማሳደግ እንደኾነ ዋዜማ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገረቻቸው ምንጮች ገልጸዋል።