ኤርትራ በያዘቻቸው ሦስት የአዘርባጃን መርከቦች ላይ ምርመራ እያደረገች መኾኗ ታወቀ

[addtoany]

ኤርትራ ባለፈው ጥቅምት ወር በያዘቻቸው ሦስት የአዘርባጃን መርከቦች ላይ ምርመራ እያደረገች መኾኗን የአዘርባጃን ጋዜጦች ዘግበዋል። በመርከቦቹ 18 የአዘርባጃን ዜጎችን ጨምሮ 24 መርከበኞች እንደሚገኙ ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

ሦስቱ መርከቦች በኤርትራ የባሕር ኃይል ቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ ከስዊዝ ካናል ወደ አቡዳቢ በመጓዝ ላይ ሳሉ በአስቸጋሪ የአየር ኹኔታ ሳቢያ ወደ ኤርትራ ባሕር ክልል በመግባታቸውና ከኤርትራ ባሕር ኃይል ጋር የተሟላ ግንኙነት ሳያደርጉ በመቅረታቸው እንደነበር ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

የአዘርባጃን ባለሥልጣናት መርከቦቹን ለማስለቀቅ አዲስ አበባ በሚገኘው የኤርትራ ኢምባሲና በሌሎች የግንኙነት መስመሮች በኩል ጥረት ማድረጋቸውን ቀደም ሲል ገልጸው ነበር።