የጌታቸው ረዳ ቡድን የትግራይን ሕዝብ አንድነት ለመከፋፈል እየሠራ ይገኛል ( ደብረጺዮን )

በደብረጺዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የሕወሓት ክንፍ፣ የጌታቸው ረዳ ቡድን አሁንም የትግራይን ሕዝብ አንድነት ለመከፋፈል እየሠራ ይገኛል በማለት አዲስ ባወጣው መግለጫ ከሷል። የደብረጺዮን ቡድን፣ የጌታቸው ቡድን በመገናኛ ብዙኀን አማካኝነት በሕወሓት ላይ የስም ማጥፋት ድርጊቶችን የሚያሠራጨው በጫና ወደ ሥልጣን ለመመለስ በማሰብ ነው በማለት ወቅሷል። የጌታቸው ቡድን፣ “የዘር ማጥፋት ወንጀል” ፈጻሚዎችን ነጻ ለማስደረግና ባንጻሩ ሕወሓትን ተጠያቂ ለማድረግ ያለመታከት እየሠራ ይገኛል በማለት የደብረጺዮን የሕወሓት ክንፍ ክሱን አሰምቷል።