አሜሪካ ልጅ ለሚወልዱ እናቶች ማበረታቻ መስጠት ልትጀምር ነው።

ኋይት ሃውስ ሰዎች ተጋብተው ልጅ እንዲወልዱ የሚገፋፋ ፖሊሲ በተግባር ላይ ለማዋል እያሰበ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አንዱ ልጅ ለሚወልዱ እናቶች የሚሰጠው ማበረታቻ ነው ተብሏል።

በቀረበው ሃሳብ መሰረት እናቶች ልጅ ከወለዱ በኋላ የ5000 ዶላር ቦነስ የሚሰጣቸው መሆኑ ሲዘገብ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው ለእኔ ጥሩ ሃሳብ ነው ብለው መልሰዋል።

የኋይት ሃውስ ፕሬስ ሴክሪታሪያት ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው ሃሳቡ የቀረበው የአሜሪካ ቤተሰቦችን ለመደገፍ መሆኑን አንስተው ፕሬዚዳንቱም ሁሉም የሚወለዱ ህፃናት አድገው የአሜሪካን ህልም እንዲያሳኩ ይፈልጋሉ ብለዋል።

የትራምፕ አስተዳደር ቤተሰባዊነትን የሚያበረታታ እና ብዙ ህፃናት በአሜሪካ መወለድ አለባቸው ብሎ የሚያምን ስለመሆኑ ሲገለፅ ቆይቷል።

ጉዳዩ በሃሳብ ደረጃ ላይ ያለ ሲሆን የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ውሳኔ ካገኘ እንደሚተገበር ይጠበቃል።

Source: ABC NEWS