“ በሙያው ጠቅላላ ሀኪም ነው ቤተሰብ ለመጠየቅ እየሄደ ነው በጥይት ተመትቶ የተገደለው ” – የሟች ጓደኛ
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መራቢቴ ወረዳ በእናት ሆስፒታል የጠቅላላ ህክምና ሀኪሙ “በተተኮሰበት ጥይት” መገደሉን የቅርብ ሰዎቹ ገለጹ።

ዶክተር ገብረሚካኤል ወልደ መላክ ተገደለ የተባለው ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ በመኪና እየተጓዘ መራቢቴ አካባቢ መሆኑን ገልጸዋል።
ቃላቸውን የሰጡን የሟች ጓደኛ፣ “ ቤተሰብ ለመጠየቅ እየሄደ ባለበት ነው በጥይት ተመትቶ የተገደለው። ትላንት ጠዋት 3 ሰዓት ነው የተገደለው ” ሲሉ ተናግረዋል።
ሌሎች የቅርብ ሰዎቹ በበኩላቸው፣ “ እናት ሆስፒታል ነበር ተቀጥሮ የሚሰራው። መንገድ ላይ መኪና ውስጥ ሆኖ ነው የተተኮሰበት ሰው ሲደርስ ሞቶ ነው ተገኘ ” ብለዋል።
የሙያ አጋሮቹ፣ “ ሕይወት የሚያድን ሀኪም ለዚያውም በጥይት እንዴት ሕይወቱ ባጭር እንዲቀጭ ይፈረድበታል ? እኛም ከፍተኛ ስጋት አለብን ” ሲሉ ሀዘነንና ስጋታቸውን ገልጸዋል።
የገዳዮቹ ማንነት እስካሁን እንዳልታወቀ፣ የቀብር ሥርዓቱ የሚፈጸመው ዛሬ እንደሆነ ተመልክቷል።
ዶክተር ገብረ ሚካኤል በ2015 ዓ/ም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀና ገና ወጣት ሀኪም ነው።