ጅቡቲ ድህነት አንሸከምም በሚል ኢትዮጵያዊያንን የማባረር እቅዷን ገፍታ ቀጥላበታለች

ጅቡቲ፣ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ሕጋዊ ሰነድ ሳይዙ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች እስከተያዘው ወር መጨረሻ በፍቃዳቸው እንዲወጡ ያዘዘችው፣ “በጸጥታ” እና “ጤና” ስጋት ሳቢያ እንደኾነ ተሠምቷል።

የፕሬዝዳንት ኦማር ጌሌ አማካሪ አሌክሲስ ሞሐመድ፣ ጅቡቲ የዓለምን ድኅነት ልትሸከም አትችልም በማለት፣ የውሳኔውን ምክንያት መናገራቸው የፈረንሳይ የዜና ወኪል ዘግቧል።

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ኢትዮጵያዊያን በፍቃዳቸው ከአገሪቱ ለመውጣት ሦስት ተጨማሪ ወራት እንዲሠጣላቸው ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት እንዳላገኘ ከቀናት በፊት መግለጡ አይዘነጋም።