ለ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አስቸኳይ ምክር
************************************
ለ ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር
ትንሽ ጠቃሚ ምክር
ከፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ
ውድ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ
ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን በአለዎት ፍቅር የተነሳ ስልጣን ከያዙ ሶስት ወር እንኳን ሳይሞላ እርስዎና ባልደረቦችዎ የፈፅማችሁአቸውን ታላላቅ ተግባሮች አሁን እኔ እዚህ አልዘረዝራችውም። እርስዎ፣ እቶ ለማ መገርሳ እና አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የለኮሳችሁት ኢትዮጵያዊነት እሁን ወደ ፍቅርነት አየተለወጠ እየነደደ ነው። በፍቅር ላይ ደሞ እርስዎ መደመርን፣ እንዲሁም ይቅርታ እና ምህረት ማድረግን ጨመሩባቸው። በጣም ደስ ይላል። ዳሩ ግን የእርስዎ ፍቅር፣ መደመር፣ ይቅርታና ምህረት የማይስማሟቸው የጭለማ ሰራዊቶች መኖራቸውን በቀደም እለት ለእርስዎ አነጠጥረው በህዝብ መሀል ያለርህራሄ ባፈነዱት ቦንብ እና በአፈሰሱት ንፁህ ደም ይፋ አድርገዋል።
ከቡር ጠቅላይ ሚንስትር ሆይ፡ የምንኖረው አብሪት፣ ትእቢት፣ጭካኔ፣ ሴራ እና ግድያ በሞሉበት ዐለም ውስጥ ነው። ይህ የጭለማ ዐለም የፍቅርን፣ የይቅርታን እና የምህረትን ብርሃን ጠልቶ ሊያጠፋው እንደሚጥር አሙን ነው። ሆኖም ቦምቡ የተወረወረው ከላይ ለእርስዎ ቢሆንም ከውስጥ መላውን የኢትዮጵያን ህዝብ ለማጥቃት እና አሁን የተቀዳጁትን ፍቅር፣ አንድነት እና የኢትዮጵያዊነት ስሜት ለመንጠቅ የታቀደ እኩይ ሴራ ነው።
እርስዎ የአበሰሩቸው ይቅርታና ምህረት በመሰረቱ መልካም ቢሆኑም ይቅርታ እና ምህረት የሚደረጉት ስለበደሉ ተፀፅተው ይቅርታን እና ምህረትን ለሚጠይቁ ሰዎች ብቻ ነው። አጥፍቻለሁ ይቅር በሉኝ፣ ማሩኝ የሚሉ ሳይኖሩ ይቅርታ እድርጌላችኋለሁ፣ ምሬአችኋለሁ ማለት ትርጉም የለውም። በዳዮቹ ስንትና ስንት ግፍ ፈፅመው ሳይፀፀቱ በቀላሉ ምሬአችኋለሁ ሲባሉ ስላልተቀጡ ታብየው አዲስ ጥፋት ሊያደርሱ ይችላሉ። ለማድረስም ሲጥሩ