ናይጄሪያ በኢትዮጵያ መንግስት አዝኛለሁ አለች

ናይጀሪያ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የፍርደኛ እስረኞች ልውውጥ የመግባቢያ ስምምነትን ባስቸኳይ እንዲፈርም መጠየቁን የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የናይጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደኤታ ቢያንካ ኦጁኩ፣ በአቡጃ ከኢትዮጵያ አምባሳደር ለገሠ ገረመው ጋር ሰሞኑን በተወያዩበት ወቅት፣ ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ያላቸውን ጨምሮ በአዲስ አበባ ወህኒ ቤቶች የሚገኙ ናይጀሪያዊያን የተያዙበት ሁኔታ መንግሥታቸውን እንዳሳዘነ መናገራቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱን ለመፈረም ለመፈረም ዳተኝነት ማሳየቱንም ኦጁኩ ተችተዋል ተብሏል።

በቅርቡ አንድ ናይጀሪያዊ እስረኛ በአዲስ አበባ ወህኒ ቤት ውስጥ ሕይወቱ ማለፉንም ሚንስትር ደኤታዋ ለአምባሳደሩን ማንሳታቸውን የዜና ምንጮቹ ዘግበዋል።