የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ ማርክ ሩቢዮ በአፍሪካ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ተዘገበ።
ኃላፊው በመጀመሪያ ጉብኝታቸው ኬንያን እና ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ተነግሯል።
ማርክ ሩቢዮ መጀመሪያ ወደ ናይሮቢ ካመሩ በኋላ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ ተነግሯል።
በጉብኝታቸው ወቅትም ማርክ ሩቢዮ ከሁለቱ ሃገራት መሪዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ተዘግቧል።
የውጪ ጉዳይ ኃላፊው ከወራት በፊት ከኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እና ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በስልክ መወያየታቸው ይታወሳል።
Source: Africa Intelligence