ቋሚ ሲኖዶስ በአቡነ ገብርኤል የኑፋ*ቄ ትምህርት ጉዳይ ላይ ተወያየ

(ሚያዚያ ፲፭ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም/ April 23/2025):- ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቅድስት ድንግል ማርያምን በማስመልከት ባስተላለፉት ትምህርት ዙሪያ ተወያየ።

ቋሚ ሲኖዶስ ዛሬ ማለዳ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ባለፈው አርብ በስቅለት ዕለት በፎኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በቅድስት ድንግል ማእያም ዙሪያ ያስተላለፉትን ትምህርት በተመለከተ ውይይት አድርጓል።

ብፁዕነታቸው የተላለፈውን ትምህርት ዝርዝር ሁኔታን በመመርመርም ውሳኔ ለማስተላለፍ ይቻል ዘንድ ሁሉም የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምልዓት በተገኙበት ለሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ ማለትም ሚያዝያ ፳፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም (April 30/2025) ቀጠሮ ተይዟል።