ማለቂያ ቢስ የሚመስለውን የህወአት ግፍ ለፍፃሜ ያበቃው ሚስጥር ኦሮማራ ነው

ማለቂያ ቢስ የሚመስለውን የህወአት ግፍ ለፍፃሜ ያበቃው ሚስጥር ኦሮማራ ነው፡፡

ለማና ደመቀ መከሩ፡፡ አብይና ገዱ ዘከሩ፡፡ ህዝቦቻችንን እያናከሱ ለዘላለም እንዳይገዙን አሁን መንቃት አለብን አሉ፡፡ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ተማከሩ፡፡ ኦሮማራ እውን ሆነ፡፡

ኦሮማራ ባይኖር አንዳርጋቸው እስር ቤት ነበር፡፡

ኦሮማራ ባይኖር በቀለ ገርባ ቃሊቲ ነበር፡፡

ኦሮማራ ባይኖር የኦሮሞና የአማራ ልጆች በማዕከላዊ ዕቶን እየተቀቀሉ ነበር፡፡ የህወአት ሴረኞች ሸራተን በእምባና በደም በተጠመቀ ውስኪ እየተራጩ ነበር፡፡

ኦሮማራ ሲጠነክር ኦሮሞና አማራ ይጠነክራሉ፤ ኢትዮጵያ ትጠነክራለች፡፡ ኦሮማራ ሲደክም ኦሮሞና አማራ ይደክማሉ፤ ኢትዮጵያ ትደክማለች፡፡

ህወአት ኦሮሞና አማራን 27 ዓመት የተጫወችባቸው እርስበርሳቸው እንዲናከሱ አጀንዳ እየሰጠቻቸው ነው፡፡ ሁለቱ ሲናከሱ ነው ህወአት ፋታ የምታገኘው፡፡ ሁለቱ ሲዝሉ ነው ህወአት የምትጠነክረው፡፡

ኦሮማራ እንዲደክም ህወአት ዲጅታል ወያኔ የተባለ የፌስቡክ ሰራዊት አደራጅታ መጥታለች፡፡ ትናንት በምድር ጦርነት ስልጣን ጨብጠዋል፤ ዛሬ ደግሞ በሳይበር ጦርነት ስልጣን ለመጨበጥ እያሴሩ ነው፡፡

ኦሮማራ ሲደክም ወያኔ ትጠነክራለች፡፡ ይህን ሃቅ ለቅፅበት እንኳን ከዘነጋን ሞታችን ቅርብ ነው፡፡

ህወአት ኦሮማራን ለማዳከም የ27 ዓመት ልምዷን አሁንም እየተጠቀመችበት ነው፡፡ ኦሮማራ ይለምልም!


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV ON YOUTUBE