ትግራይ ( UPDATE )


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

ትግራይ ( UPDATE )
—————————————
Image may contain: 1 person, sitting and suitበመላው ትግራይ አዲስ የፖለቲካ አስተሳሰብና ባህል እንዲያብብ ሁሉም ትግራዋይ የራሱ ድርሻ ሊኖረው ይገባል -ዶ/ር አብርሃም በላይ
በመላው ትግራይ አዲስ የፖለቲካ አስተሳሰብና ባህል እንዲያብብ ሁሉም ትግራዋይ የራሱ ድርሻ ሊኖረው እንደሚገባ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር አብርሃም በላይ ገልጸዋል፡፡
የህዝቦች አንድነትና እኩልነት እንዲረጋገጥ፣ የትግራይ ህዝብ ፅኑ ፍላጎት አለው አለው ብለዋል ዶ/ር አብርሃም፡፡
ጥላቻና ፍረጃ የሀሳብ ድርቀት ያጋጠማቸው የፈሪዎች አካሄድ ነው ያሉት ዶ/ር አብርሃም፣ ይህ አካሄድ ከባለቤቱ ጋር አብሮ ሊያከትምለት እንደሚገባ በፌስቡክ ገፃቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል፡፡

ሕወሓትን ከትግራይ ሕዝብ መለየት – የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የትግራይ ሕዝብ ሕዝባችን ነው። በዚህ ሕዝባችን ላይ ምንም ዓይነት ክፉ ነገር እንዲደርስ አንፈልግም። ይሄንን የሚያደርጉትንም አንታገሥም። – የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ በኤርትራ ላይ የፈጸመውን ጥቃት እና ግጭቱን ዓለም አቀፋዊ ለማድረግ ያደረገውን ሙከራ አጥብቀን እናወግዛለን ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ፅፈዋል።

በምሥራቁ ግንባር ራያ ሙሉ በሙሉ ነጻ ወጥቷል። ጨርጨር፣ ጉጉፍቶ መሖኒን ሠራዊቱ ነጻ አውጥቷል። በየቦታው የነበሩ ወሳኝ የኮንክሪት ምሽጐችንም አፍርሷል። ሠራዊቱ በአሁኑ ጊዜ ወደ መቀሌ በመገሥገሥ ላይ ነው።
በምዕራብ ግንባር ደግሞ በአዲ ነብሪድና በአዲ ዳእሮ የሚገኙ ከባድ ምሽጎችን በማፍረስ ሽሬን ተቆጣጥሮ ወደ አኩስም በመገሥገሥ ላይ ይገኛል።
በውጊያው እጅግ ብዙ መሣሪያዎች ከመማረካቸውም በላይ ህወሓት ለክፉ ዓላማው ያሰለፋቸው የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
የመከላከያ ሠራዊቱ የህወሓት ጁንታን በሕግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል እየገሠገሠ ሲሆን የጁንታው ኃይል የመከላከያ ሠራዊቱን ክንድ መቋቋም አቅቶት ወደኋላ እየሸሸ ነው።

ጀርመን ለጦር ሀይሎች ሆስፒታል 1 ሚሊዮን ዩሮ የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

የትግራይ ሕዝብ ከማንም በላይ በሕወሓት ናርኪዝም ርዕዮተ-ዓለምና የህወሀት ማለቂያ የሌላቸው ጦርነቶች እጅግ የተጎዳ ሕዝብ ነው – ሙስጠፌ ኡመር

ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ለህወሀት ቡድን የዲፕሎማሲ ስራ ሲሰሩ እንደነበር ተገለፀ

የመቀሌው የመጨረሻ ኦፕሬሽን ለመጀመር የኢትዮጵያ ጦር ትእዛዝ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል

ጽንፈኛው የህወሓት ቡድን የትግራይ ወጣቶች የተሳሳተ አመለካከት እንዲኖራቸው ሲሰራ መቆየቱን በቁጥጥር ስር የዋሉ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት ተናገሩ

“በሰሜን እዝ ላይ የተፈፀመው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ተልኳችንን በእልህና በቁጭት ለመፈፀም ቁርጠኛ አድርጎናል” – የሠራዊቱ አባላት

Image
የአብረኸት እንባ
👉150 ጥይት ተሰጥቶኝ አንድም ጥይት ሳልተኩስ ነው እጄን የሰጠሁት፤
ምክንያቱም በዚህ ውጊያ አላምንበትም
********************
(ኢ ፕ ድ)
አብረኸት የጁንታው ታጣቂ የነበረችና እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት ከሰጡ ውስጥ አንዷ ነች። ገና የ21 አመት ወጣት ናት፡፡ ወጣቷ በ2011 ዓ.ም የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል በብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ስልጠና ወስዳለች፡፡ የኢትዮጵያ መካላከያ ሰራዊት አባል ሁና ነገሌ ቦረና ተመድባም ግዳጇን እየተወጣች ሳለ በጠና ታማ ከውትድርናው ዓለም ተሰናብታ ወደ ቤተሰቦቿ መመለሷን በስፍራው ተገኝቶ ላነጋገራት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ ገልጻለች።
የአብረኸት ህመም መጥናት ከምትወደው መከላከያ ቢለያትም ከጁንታው ዕይታ ግን መሰወር አልቻለችም። በጠላ ንግድ የሚተዳደሩትን እናቷን እያገዘች ኑሮን ብትቀጥልም፤ የጁንታው አባላት የአብረኸትን ወታደርነት ያውቁ ነበርና የጁንታውን ታጣቂ እንድትቀላቀል በእናቷ በኩል ግፊት ማድረግ ጀመሩ። ጁንታው የአብረኸትን እናት ሌት ተቀን በማስፈራራታቸው ልጃቸውን ሳይወዱ በግድ ለታጣቂው አስረከቡ፤ አብረኸትም ቤተሰቦቼን ለአደጋ ከማጋልጥ በሚል ታጣቂውን ተቀላቀለች።
“ሌላ ስራ በቀላሉ ማግኘት ስላልቻልኩና ጫናውና ማስፈራሪያው ሲበዛብኝ ታጣቂውን ተቀላቀልኩ። የቤተሰቡ አባላት ሰባት ነን ፤ አባቴ በህይወት የለም፡፡ እናቴ ብቻዋን ነው ጠላ ሽጣ ያሳደገችኝ፡፡ እሷን ለማገዝ ስልም ነው ወደዚህ የገባሁት” ስትልም ነው የታጣቂው አባል የሆነችበትን አጋጣሚ የምታስታውሰው።
አብረኸት የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ እየወሰዱት ባለው ህግ የማስከበር እርምጃ ላይ እጇን የሰጠችው አንድም ጥይት ሳትተኩስ መሆኑን ትናገራለች፤ “150 ጥይት ተስጥቶኝ አንድም ጥይት ሳልተኩስ ነው እጄን የሰጠሁኝ። ምክንያቱም በዚህ ውጊያ አላምንበትም። እየሞተ ያለውም የደሀው ልጅ ነው። እጄን ከሰጠሁ በሁዋላም ቢሆን ሶስት ቀን ሙሉ የሰራዊቱ አባላት ከሚበሉትና ከሚጠጡት እያካፈሉኝ ቆይቻለሁ።
በትግራይ ክልል በየአካባቢው ያለው ወጣት ተገዶ ወደ ግዳጅ እንዲገባ ተደርጓል የምትለው ወጣቷ፤ ስልጠና የሚሰጠውም የይድረስ ይድረስ መሆኑን አልሸሸገችም፤ “ለአጭር ጊዜ ክላሽ እንዴት እንደሚፈታና እንደሚገጠም፣ ኢላማ እንዴት እንደሚመታ አሳይተው ብቻ ነው ወደ ጦርነት የሚማግዷቸው፡፡ ይህ ደግሞ የህወሓት አመራሮች ለትግራይ እናቶችም ሆነ ወጣቶች ደንታ እንደሌላቸውና የራሳቸውን የስልጣን ጥም ለማርካት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ያሳያል” ነው ያለችው፤ አብረኸት፡፡
“የህወሓት አመራሮች፤ የትግራይን ህዝብ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች እንደሚጠላው፣ የትም ሄደው በሰላም መኖር እንደማይችሉ አድርገው ወጣቱንንም ሆነ ህጻናትን ጭምር ይሰብካሉ። ሁሉም የትግራይ ህዝብ የዚህ አይነት አስተሳብ ስላለውና ህወሓትን ስለሚፈራ የሚሉትን ለማድረግ ይገደዳል። ይህ ሰላም የማይወድ ድርጅት ውጤት ለማያመጣ ነገር ወጣቱን እያስፈጀ ነው” ብላላች፤ አብረኸት።
የህወሓት ጁንታ ወጣቱን መስዋዕት የሚያስከፍሉት የማይሆን ነገር እየሞሉት፣ እያስገደዱትና፣ በገንዘብም እያታለለሉት ጭምር መሆኑን አብረኸት ትናገራለች።
የትግራይ ህዝብ መከላከያን እንዲወጋ አይፈልግም፤ ምክንያቱም መካላከያ የትግራይ ህዝብን ደህንነት ከመጠበቅ ጎን ለጎን ለህብረተሰቡ ትምህርት ቤት እየሰራ፣ ጤና ጣቢያ እየገነባ የኖረ ወገን ነው፤ የምትለው አብረኸት፤ “ወርቅ ለአበደረ ጠጠር እንዲሉ እኛን አታለው እንደ ቤተሰብ የምናየውን መከላከያ ሰራዊትን እንድንወጋ አድርገውናል” ያለችው በከፍተኛ ጸጸት ውስጥ ሆና ነው።
“የህወሓት ቡድን እንደሚለው መከላከያ እኛን ቢጠላን ኖሮ እንዴት ትግራይን ይጠብቃታል” ስትልም ትጠይቃለች። “እኛ ምንግዜም ኢትዮጵያዊ ነን፤ አጸያፊ ስራ እስካልሰራን ድረስ ህዝቡ ዝም ብሎ አይጠላንም፡፡ በመሆኑም የትግራይ ወጣቶች ዓላማ የሌለው ጦርነት ውስጥ መግባት የለባቸውም። ለመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን በመስጠት በሰላም መኖር ይኖርባቸዋል” ስትል ሀሳቧን ቋጭታለች።

የትግራይ ሕዝብ የ80 እና 90 ዓመት ሽማግሌዎች ምክንያት ለሶስተኛ ጊዜ ልጆቹን ለጥፋት እንዲያቀርብ እየተገደደ ነው … ለአያቶች መኖር የልጅ ልጆች መስዋዕት መሆን የለባቸውም። …….. በመከላከያ ላይ የተፈጸመው የክህደት ጥቃት ከህወሓት በኋላ ያለች ኢትዮጵያን የምናይበት ነው – ሌ/ጄኔራል ዮሃንስ ገ/ሚካኤል

መንግስት ፅንፈኛውን የህወሓት ቡድን ለህግ ለማቅረብ እየወሰደ ያለውን እርምጃ ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ሊደግፍው ይገባል- ጠ/ሚ ጽ/ቤት

Image

የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ለተፈጠረው ቀውስ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲፈለግ ጥሪ አቀረቡ።
ርዕሰ መስተዳድር ትናንት ማታ በክልሉ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንዳመለከቱት ጦርነቱ መቀጠሉን ጠቅሰው ለችግሩ ፖለቲካዊ መፍትሔ ሊገኝለት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ደብረጽዮን (ዶ/ር) አክለውም እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ ዘመቻ በተደጋጋሚ በመቀለ፣ በአዲግራትና በአላማጣ የአየር ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ገልፀው የተከዜ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ረቡዕ ዕለት የአየር ድብደባ ተፈፅሞበታል፤ የትግራይ ከተሞችም ጨለማ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርገዋል ሲሉ ከስሰዋል።

ደብረጽዮን (ዶ/ር) ለተፈጠው ቀውስ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲፈለግ ድጋሚ ጥሪ አቀረቡ - BBC News አማርኛ

ምስል 8 ዶክተር ሙሉ ነጋ የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዲኤታ - YouTube

ዶክተር ሙሉ ነጋ

ዶክተር ሙሉ ነጋ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ 

ዶ/ር ሙሉ ነጋ በትግራይ ክልል የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሰየሙ ዶ/ር ሙሉ ነጋ በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሰየማቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።

የቀድሞ የትግራይ አስተዳዳሪዎች አንጋፋ ፖለቲከኞች አቶ ገብሩ አስራትና ወይዘሮ አረጋሽ ኣዳነ ወቅታዊውን ጉዳይ አስመልክቶ ለሳምንታዊው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ሐሳባቸውን ሰጥተዋል።  — https://mereja.com/amharic/v2/394123
የሕወሃት ወንጀለኞች በአዲስ አበባ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ፍርሃትን ለመንዛትና እና የሽብር ጥቃትን ለማድረስ አስፈፃሚ መረብ አቋቁመዋል፡፡ ግጭቶችን በማነሳሳት እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃቶችን በማካሄድ ተልዕኮ በሕወሃት ተላላኪነት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በፌደራል እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ቤቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከተለያዩ የኑሮ ዘርፎች የተውጣጡ የተለያዩ ብሔር ተወላጆች ናቸው ፡፡ በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ጠቅላላ ቁጥር ወደ 150 አካባቢ ነው፡፡ ከነዚህ ተጠርጣሪዎች መካከል ጥቂቶቹ የፀጥታ ስጋትን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዋስ ተለቀዋል ፡፡ እውነቱን ማወቅ ወሳኝ ነው። ቁጥሮች ይናገራሉ ፡፡ ብዙ ባለዝና ድርጅቶች እና ግለሰቦች በተሳሳተ መንገድ የእስረኞችን ቁጥር በተመለከተ ሙሉ በሙሉ ያልተረጋገጠ እና የተጋነነ መረጃ እያሰራጩ ይገኛሉ፡፡ የሕግ አስከባሪያችን አሠራር ደንብን የተከተለ እንጂ እንደሚወራው በማንነት ላይ ተመስርቶ ግለሰቦችን የሚያጠቃ አይደለም፡፡ ሁሉም ዓለም አቀፍ አጋሮች እና ተዋንያን በሕወሃት እየተፈፀመ ያለውን የውሸት መረጃ ዘመቻ ልብ እንዲሉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ Ethiopia State of Emergency Fact Check

—————————————————————————————————————-

“ከግጭቱ ዋዜማ የትግራይ ክልል መሪ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተደዋውለው ነበር” ያሉት ቃል አቀባዩ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን “ሁኔታውን በቀላሉ እንደሚይዙት እና በንግግር ሊፈቱት እንደሚችሉ ተነጋግረው ነበር” ብለዋል፡፡ …….. ሆኖም በዚያው ቀን ምሽት በክልሉ በሚገኘው የሃገሪቱ ጦር የተለያዩ ጣቢያዎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት መከፈቱን ነው የገለጹት፡፡ – አል-አይን

https://mereja.com/amharic/v2/392613

የአይን ምስክር …. ከአብርሀጅራ እስከ ማይካድራ !!

By Dr Abrham Amare

ወገኖቻችን እጅግ በአሰቃቂ ሁኔታ ተጨፍጭፈዋል ፤ ተረሽነዋል !! ማይካድራ እና አካባቢው ይኖሩ የነበሩ አማራዎች በሙሉ በሚባል ሁኔታ እዛው ነዋሪ በነበሩ ትግሬዎች ታድነዉ ተገድለዋል ። ሁሉም ጎረቤቱን ገድሏል ። ሚስት ባሏን ገድላለች ፤ በሚስቱ በገጀራ ተመቶ ሳይሞት የደረሰን ታካሚም አክመናል። በዚህ ደረጃ የአዉሬነት ተግባር በህዝባችን ተፈፅሟል!!
እኔ በህይወቴ በቀን ዉስጥ ከ200 በላይ ታካሚ ያዉም በድንገተኛ አደጋ ተጎድቶ በአንድ ቀን ዉስጥ ያዉም በአንድ ሆስፒታል ያየሁት ዛሬ ነዉ ። ለወደፊትም ማየቴን እርግጠኛ አይደለሁም ። ስራው እጅግ ቢያደክምም በቁጭት በእልህ የምንችለውን ሁሉ ስናደርግ ዉለናል!!
ለመከረኛዉ የአማራ ህዝብ ይህቺ ማድረግ የምንችላት ትንሽ ነገር ናት!!
~~~~
ህወሃትን እና ጀሌዎችን መረር ብሎ ከመደምሰስ ዉጭ ሌላ ምርጫ የለም ። ምንም ርህራሄ አያስፈልግም !!
በሌላውም የትግራይ አካባቢ የምትኖሩ አማሮች ተደራጅታችሁ ራሳችሁን ጠብቁ ፤ ራሳችሁን ከሞት ታደጉ!!
በሕወሓት የጥፋት ኃይል በሰሜን እዝ ጦር ላይ የተፈጸመ እጅግ አስፈሪና ጨካኝነት የተሞላው በጥላቻ የተሞላ ወንጀል
ሌ /ጄኔራል ባጫ ደበሌ በሕወሓት የጥፋት ቡድን በሰሜን እዝ ጦር ላይ ያደረሰውን ግፍ በተመለከተ በዋልታ ቴሌቭዥን ላይ በቀጥታ የሰጡት ምስክርነት ሳዳምጠው ከልብ ያሳዝናል።የሕወሓት ኃይሎች ወታደሮችን ገድለው ልብሳቸውን አውልቀው ሬሳቸውን አንድ ላይ ከምረው ሌሊቱን ሙሉ ሲጨፍሩ አደሩ በዚህ ላይ አሁንም ድረስ አስክሬናቸው አልተቀበረም። አሞራና ጅብ እየበላው ነው። የኦነግን ባንድራ የያዙ የኦነግ ወታደሮች በሽራሮ፣ በራማ፣ በፆረና እና በዛላንበሳ በኩል የሰሜን እዝን ተዋግተዋል። የተፈጸመውን እና እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በተመለከተ በዝርዝር አብራርተዋል። ያዳምጡት።

ሕይወት በጦርነት ቀጣና ውስጥ በምትገኘው መቀለ ከባድ ሆኗል። በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይል መካከል ግጭት ከተከሰተ ዛሬ 7ኛ ቀኑን አስቆጥሯል። ዘገቢያችን በመቀለ እና አከባቢዋ ከፍተኛ የሆነ የውሃ እጥረት መኖሩን እንዲሁም የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ነግሮናል። ባንኮችም እንዲዘጉ መደረጉ ነዋሪዎች ሕይወት እንዲከብዳቸው ሌላው ምክንያት ሆኗል ይላል።

ሙሉ ዘገባውን ይመልከቱ –  https://bbc.in/3khQwNC
መቀለ ከተማ

የተጀመረውን ተኩስ አቁመን ወደ ድርድርና ውይይት እንምጣ – ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል

ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ለሮይተርስ የዜና ማእከል እንደተናገሩት ከፌደራል መንግስቱ ጋር የተጀመረውን ተኩስ አቁመን ወደ ድርድርና ውይይት እንምጣ ብለዋል።………

———————————————————————————

ህወሓት ከተወገደ የትግራይ ህዝብ ሰላሙንና ነጻነቱን ያገኛል ሲሉ የትግራይ ተወላጅ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ገለጹ።
በከሃዲው የህወሓት ቡድን ላይ እየተወሰደ የሚገኘውን እርምጃ እንደሚደግፉም ገልጸዋል።የብልጽግና ፓርቲ የትግራይ ተወላጅ አባላት፣ ደጋፊዎችና ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡የውይይቱ ተሳታፊዎች ህወሓት የሀገር አለኝታና መከታ በሆነው የመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት አውግዘዋል።
“ድርጊቱ ህወሓት ከትግራይ ህዝብ ባህልና እሴት አፈንግጦ ብቻውን በአምባገነናዊነት የሚኖር ቡድን ለመሆኑ ማሳያ ነው” ብለዋል፡፡በውይይቱ ወቅት ሃሳባቸውን የሰጡት የትግራይ ተወላጆቹ እንዳሉት፤ የትግራይ ህዝብን የማይወክለው ህወሓት ከተወገደ የትግራይ ህዝብ ሠላሙንና ነጻነቱን ያረጋግጣል፡፡
የህወሓት ቡድን መሪዎች ተይዘው ለሕግ ቀርበው የህግ የበላይነት ምን እንደሆነ ማወቅ እንደሚገባቸውም ገልጸዋል።ህወሓት በመከላከያ ሰራዊት ላይ ለወሰደው እርምጃና ዕድሜውን ሙሉ ሲሰራ ለነበረው ጥፋት ተግባር የእጁን ማግኘት እንዳለበትም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በዚህ ቡድን ላይ እርምጃ በሚወሰድበት ወቅትም ህዝቡን ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።ህወሓት የክፋት መገለጫ መሆኑን ገልጸው፤ እየተወሰደበት ያለውን እርምጃ እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ እየተወሰደ ያለው እርምጃ በወንጀለኛው በህወሓት ቡድን ላይ ነው፡፡
=
የህወሃት ክህደት አላግባብ ለመበልጸግ ከማሰብና ስልጣንን የሙጥኝ ከማለት የመነጨ እንደሆነ ተናግረዋል።ቡድኑ ወደ ሰላማዊ መስመር እንዲገባ በተደጋጋሚ ጥረት ቢደረግም ሰላማዊ አማራጭን መጠቀም አለመፈለጉን በተግባር እንዳሳየ ገልጸዋል።በቡድኑ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃም የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና ሕገ ወጥ ቡድኑን ለሕግ ማቅረብ ዓላማ ያደረገ እንደሆነም አብራርተዋል ሲል ኢዜአዘግቧል።

የብልጽግና ፓርቲ የትግራይ ተወላጅ አባላት፣ ደጋፊዎችና ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡

 

——————————————///—————————————–///——————-
“ህወሃት ስለ አማራ ህዝብ የነገረንና በተግባር ያየነው ፍጹም ተቃራኒ ነው” በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው የትግራይ ልዩ ሃይል አባላት
(አብመድ) ስለ አማራ ክልል ከተነገራቸው በተቃራኒ ሁኖ እንዳገኙት በጦርነቱ ጉዳት ደርሶባቸው በአብረሃጂራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድጋፍ እየተደረገላቸው የሚገኙ የትግራይ ልዩ ሃይል አባላት ተናግረዋል።
ጉዳት ደርሶባቸው በአብርሃጂራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድጋፍ እየተደረገላቸው የሚገኙ የትግራይ ልዩ ሃይል አባላት የትግራይ ህዝብ ምንም በማያውቀው እየተጎዳ መሆኑን ገልጸዋል።
የትግራይ ህዝብ ለጊዜያዊ እና ለጥቂት የትህነግ ህገወጥ ቡድኖች የፖለቲካ ትርፍ መጠቀሚያ እንዳይሆን ራሱን ወደ ጦርነት ማስገባት እንደሌለበትም አስገንዝበዋል።
የልዩ ሃይል አባላቱ ከነዋሪው እና ከሆስፒታሉ ሰራተኞች ተገቢ እንክብካቤና የህክምና አገልግሎት እያገኙ መሆኑንም ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የህክምና ግብዓቶችን በማሟላት ተገቢ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን የአብርሃጂራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ደረጀ አምባው አስታውቀዋል።
——————
መንግስት የጀመረው ሕግ የማስከበር እርምጃ ከማንም በላይ ሰፊውን ትግራዋይ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው – ጠ/ሚ አብይ አህመድ
የመከላከያ ሠራዊቱ ዳንሻን ፡ ባከርን እና ከሽራሮ አስከ ሽሬ ያሉ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ወደ ፊት እየገሠገሠ ይገኛል

በኃይል ተገደው ወደ ጦርነት የገቡ የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት ወደ አማራ ክልል በሰላማዊ መንገድ እየገቡ ነው፡፡

የውጭ ምንዛሬን ወደ ተለያዩ ሀገራት የሚያሸሹ የሕወሓት አባላት እየተያዙ ነው

በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይሄንን ጁንታ ሳያውቁት ከማገዝና ሀገራቸውን ከመጉዳት እንዲቆጠቡ፣ ወንጀለኞችንም እንዲያጋልጡ፣ ገንዘባቸውን በባንክ በመላክ ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ መንግሥት ጥሪ ያደርጋል።

የቀድሞ የፌደራል ዳኛ የማእከላዊ ገራፊና የፍትሕ ቀበኛ በአዳማ እና ዱከም አከባቢ የህወሓት የሽብር ሴራ ጠንሳሽ አቶ ዘርዓይ ወልደሰንበት በቁጥጥር ስር ውሏል በህወሓት/ኢህአዴግ ዘመን በፍትህ ላይ ሲያላግጥ፣ ሌሊት ሌሊት ማዕከላዊ እስር ቤት በመሄድ ተከሳሾችን ሲገርፍ አድሮ ሲነጋ ችሎት ላይ ደኛ መስሎ ሲሰየም የነበረው፣ ለውጡን ተከትሎ ወደ መቀሌ ሸሽቶ በመሄድ የትግራይ ክልል መስተዳደር አማካሪ የነበረው፣ ከተወሰኑ ወራት ቆይታ በኋላ የሥራ መልቀቂያ በማስገባት በአዳማ እና ዱከም አከባቢ የህወሓት የሽብር ሴራ ጠንሳሽ የነበረው፣ የቀድሞ የፌደራል ዳኛ፣ የፍትህ መጋኛው አቶ ዘርዓይ ወልደሰንበት በዛሬው ዕለት ጠዋት በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን ለማወቅ ተችሏል።
ግጭቱ ከትግራይ ህዝብ ጋር ሳይሆን በህወሓት እና በኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ነው – የፈንቅል እንቅስቃሴ የትግራይ ወጣቶች አስተባባሪ
በሴራ ፖለቲካ አራማጁ ህወሓት ምክንያት የተቀሰቀሰው ግጭት ከትግራይ ህዝብ ጋር የሚካሄድ ሳይሆን በህወሓት እና በኢትዮጵያ ህዝብ መካከል የሚደረግ መሆኑን የፈንቅል እንቅስቃሴ የጋራ አመራር እና የትግራይ ወጣቶች አስተባባሪ ገለጸ።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ጣልቃ እንዲገባ እና ጊዜያዊ መንግስት (አስተዳደር) እንዲቋቋም ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ድምጽ ፀደቀ፡፡ ምክር ቤቱ በዛሬው እለት አስቸኳይ ስብሰባውን አካሄዷል፡፡ በስብሰባውም በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)
በትግራይ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ አገልገሎት በከፊል የጀመረ መሆኑ ተመለከተ። የቴሌኮምኒኬሽን አገልግሎት ግን አሁንም እንደተቋረጠ መሆኑን ከስፍራዉ መረጃ የላከልን የዶቼ ቬለ ወኪል ሚሊዮን ኃይለሥላሴ ጠቁሞናል።
ትላንት አርብ የአውሮፕላን ጥቃት ደረሰባት የተባለችው የመቀሌ ዙርያ ዛሬ ዉሎዋ ሰላማዊ ነዉ ሲል ነዉ የዶቼ ቬለ ወኪል ከስፍራዉ የገለፀልን። በመቀሌ ከተማ መደበኛ ግብይትና የሰዎች እንቅስቃሴ ቀጥሎ ዉሎአል፤ የመንግስትና የግል ባንኮች ግን ዛሬም ዝግ ሆነዉ ነዉ የዋሉት።
በከተማዋ የ12ኛ እና 8 ክፍል ተማሪዎች በየትምህርት ቤቶቻቸዉ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ዉለዋል። በቅርቡ ተመራቂ ተማሪዎቹን የተቀበለው መቀሌ ዩኒቨርስቲም ለተማሪዎቹ አገልግሎት እየሰጠ መሆንን መስማቱን ወኪላችን ነግሮናል።

አየር ኃይሉ በወሰደው እርምጃ 300 ኪሎ ሜትሮች ድረስ መወንጨፍ የሚችሉ ሮኬቶችን ሙሉ በሙሉ አውድሟል:: የህወሓት ኃይል ላይ የተደረገው የመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን በስኬት ተጠናቋል – ጠ/ሚ አብይ

ኢትዮጵያ ለወንጀለኛ አካላት ቦታ የላትም ! ኩሩው ኢትዮጵያዊ የሆነው የትግራይ ህዝብና ሌሎች ዜጎች ለዘለዓለም ፍትህ ሊነጠቁ አይችሉም ! ጠ/ሚ አቢይ አህመድ

ግጭቱን ተከትሎ በመቀሌ ከተማና በክልሉ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክና የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀምሯል።
የኤሌክትሪክ አገልግሎት ትናንት ጥቅምት 26/2013 ዓ.ም የተመለሰ ሲሆን የትራንስፖርት አገልግሎት ደግሞ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም መጀመሩን የመቀሌ የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል።
ምንም እንኳን ትራንስፖርት ቢጀመርም ከመቀሌ ከተማ ወደተለያዩ ክፍሎች የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች በሙሉ ከከተማው ፖሊስ ልዩ ፍቃድ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።
ግጭቱን ተከትሎ የተቋረጠው የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት እንደተቋረጠ ነው።
ከቀናት በፊት ተኩስ የተሰማባት መቀሌ ከተማ በአንፃራዊ ሁኔታ የተረጋጋ ሁኔታ ላይ ብትገኝም ማህበረሰቡ ግን ጦርነቱ በፈጠረው ውጅንብር ስጋት ላይ መሆኑንም የቢቢሲ ዘጋቢ ይናገራል።
በትናንትናው እለት በመቀሌ ከተማ የጦር አውሮፕላን ሲያንዣብብ የነበረ መሆኑን የታዘበው የቢቢሲ ዘጋቢ በድምፁም በርካቶች መደናገጥና ፍራቻ ውስጥ እንደገቡ አክሎ ገልጿል።
‘በትግራይ ክልል የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ’
አዋጁን የሚያስፈፅሙ ግብረ ኃይል እንዲንቀሳቀሱ እውቅና ከሚሰጣቸው ሰዎች እና ተሽከርካሪዎች ውጭ ማንኛውም ሰው ወይም ተሽከርካሪ መመሪያው ተፈፃሚ በሚሆንበት ቦታ ሁሉ ከምሽት 2 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት መንቀሳቀስ አፈቀድለትም።
ከግብረ ኃይሉ ፍቃድ ውጭ ማንኛውም ሰልፍ ፣ በአደባባይ ወይም በቤት ውስጥ ስብሰባ ማድረግ እንዲሁም 4 እና ከዛ በላይ ሆኖ በቡድን መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ተብሏል።
ከመከላከያ ፣ ከፌዴራል ፖሊስ ፣ ሌሎች ፍቃድ ከተሰጣቸው የፀጥታ አካላት ውጪ ማኛውም የጦር መሳሪያ ሆነ ጉዳት የሚያደርሱ የተለያዩ እቃዎችን ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።
የፌዴራል ፖሊስ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያት በወቅታዊ የሀገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
Image may contain: one or more people and people standingየፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል እንዳሻው ጣሰው እንዳሉት በትግራይ ክልል ጽንፈኛው የህወሓት ታጣቂ ቡድን የተከፈተውን ጦርነት ለመመከት የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ ሌሎች የጸጥታ ኃይሎች እና ሚልሻዎች በቅንጅት በወሰዱት እርምጃ አብዛኛው በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
የተቀረውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ መንግስት እና ህዝቡ ፊቱን ወደ ሰላምና ልማት እንዲያዞሩ ለማስቻል እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በቀሪው ጊዜያትም ሁሉም የጸጥታ እና ደህንነት መዋቅሩ በአንድነት ተደራጅተው በመስራት በዚህ እኩይ ተግባር ላይ የተሰማራውን ኃይል ከስረመሰረቱ መንቀል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የመንግስትና የህዝብ ተቋማትን መጠበቅ የህዝቡ የዕለት ዕለት ኑሮ እንዳይስተጓጎል ማድረግ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈፃሚ እንዲሆን ይሰራልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም ህብረተሰቡ በየአካባቢው በመደራጀት ፀጉረ ልውጦችን ለጸጥታ ኃይሉ በመጠቆም ትብብር እንዲያደርግና መንግስት ለሚያደርገው ጥሪ ዝግጁ እንዲሆን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው፣ ህብረተሰቡ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እና ኃላፊነት ከማይሰማቸው የመገናኛ ብዙኃን እየተላለፉ ያሉ የሀሰት መረጃዎችን ከማሰራጨትና ከመቀበል መቆጠብ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በዚህም ህብረተሰቡ ከትክክለኛ እና ከሚመለከታቸው አካላት መረጃውን በማጣራት እና በመቀበል ከሰራዊቱና ከመንግስት ጎን ሊቆም ይገባል ብለዋል፡፡ በቀጣይም ወቅታዊ መረጃዎች ለህብረተሰቡ የሚሰጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሰሜን ኢትዮጵያ አየር ክልል ተዘግቷል ::

ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በሰሜን የኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ የሚያቋርጡ የአለም አቀፍ እና የሃገር ውስጥ የበረራ መስመሮች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት የተዘጉ መሆናቸው ተገልጿል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ያለው የአየር ክልል ለማንኛውም በረራ የተዘጋ ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ይህንን ተላልፎ በረራ የሚፈጽም ማንኛውም አውሮፕላን እንዳይኖር ን አሳስቧል።

ከዛሬ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ጥዋት 2 ሰዓት ጀምሮ የመቐለ፣ ሽሬ ፣ አክሱም እና ሁመራ ኤርፖርቶች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት ዝግ መሆናቸውን ተገለፀ።

ይህን የገለፀው የኢትዮጵያ ሲቨል አቪዬሽን ባለስልጣን ነው።

በተመሳሳይ ሁሉም የሚመለከታቸው አካሎች (ኤርሜንስ) በተገቢው የመገናኛ ዘዴ በ (ኖታም) አንዲያውቁት መደረጉን አስታውቋል።

1. የትግራይ ተወላጆች የሆኑ የብሄራዊ ጸጥታና ደኅንነት ተቋማት ሠራተኞች በግዳጅ ዕረፍት እንዲወስዱ እንደተደረጉ ዋዜማ ሰምታለች፡፡ በተያያዘ፣ በአውሮፕላን ወደ ውጪ ሀገራት ጉዞ የነበራቸው የትግራይ ተወላጅ መንገደኞች መታወቂያቸው እየታየ እና ብሄራቸውን እየተጠየቁ ከጉዟቸው እንዲቀሩ እና ወደቤታቸው እንዲመለሱ መደረጋቸውን ዋዜማ ድርጊቱ ተፈጽሞብናል ካሉ ምንጮች ሰምታለች፡፡ ዋዜማ በጉዳዩ ላይ የመንግሥትን አስተያየት ለማግኘት እየሞከረች ነው፡፡
2. ተዋጊ ጄቶች ዛሬ መቀሌ አካባቢ የቦንብ ድብደባ ፈጽመዋል ሲል የትግራይ ክልል መንግሥት በክልሉ ቴሌቪዥን በኩል ባሰራጨው ዜና መንግሥትን ከሷል፡፡ ድብደባው በትክክል የት እንደተፈጸመ እና ምን ጉዳት እንዳደረሰ ግን ዜናው የጠቀሰው ነገር የለም፡፡ እንግሊዝኛው ቢቢሲ በበኩሉ፣ አንድ ተዋጊ ጄት ዛሬ ረፋዱ ላይ በመቀሌ ከተማ ላይ ሲያንዣብብ እንደታየ ዘግቧል፡፡
3. የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረ ጺዮን ገ/ሚካዔል ዛሬ በክልሉ ቴሌቪዥን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በክልሉ የሠፈረው የሰሜን ወታደራዊ ዕዝ እጅ የነበሩ ከባድ ጦር መሳሪያዎች በሙሉ በክልሉ ጸጥታ ሃይል እጅ እንደገቡ ተናግረዋል- ደብረ ጺዮን፡፡ በቅርብ እና ሩቅ ያሉ የትግራይ ሕዝብ ጠላቶችን ለመምታት የሚያስችል አቅምም አለን ብለዋል፡፡ በምዕራብ ትግራይ ውጊያ እየተካሄደ እንደሆነ የገለጹት፣ ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ፌደራል መንግሥቱ በዚሁ መስመር በኩል ወደ ኤርትራ ጦር እያሰገባ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
4. የኢትዮጵያ መንግሥት በሱማሊያ ከአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ ውጭ በተናጥል የሠፈሩ ወታደሮቹን ማስወጣት እንደጀመረ ዋዜማ ከአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል ምንጮቿ ሰምታለች፡፡ ወታደሮቹ የተጠሩት የሀገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ክልል ጸጥታ ሃይል ጋር የገባበትን ግጭት እንዲያግዙ ነው፡፡ ከባድ ጦር መሳሪያ የታጠቁ ወታደሮች የኢትዮጵያ አዋሳኝ ወደሆነችው የሱማሊያዋ ጌዶ ግዛት ተመልሰዋል፡፡ በተያያዘ፣ የሱማሌ ክልል ልዩ ሃይል ወደ ኢትዮጵያ-ሱማሊያ ድንበር ተጠግቶ ድንበር እየጠበቀ እንደሆነ ታውቋል፡፡
5. ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የከዱ 16 የትግራይ ብሄር ተወላጅ መኮንኖች ማክሰኞ’ለት ወደ ጅቡቲ በመግባት የፖለቲካ ጥገኝነት እንደጠየቁ አንድ የጅቡቲ ዜና ምንጭ በድረ ገጹ ዘግቧል፡፡ ጥገኝነት የገቡት አንድ ኮሎኔል፣ አንድ ኮማንደር እና 12 መቶ አለቃዎች ናቸው፡፡ ጅቡቲ ትናንት ምሽት መኮንኖቹን በወታደራዊ አውሮፕላን ጭና ለኢትዮጵያ መንግሥት ለማስረከብ ዝግጅት ላይ እንደነበረች ዘገባው ገልጧል፡፡ መኮንኖቹ ለኢትዮጵያ ተላልፈው ይሰጡ አይሰጡ ግን ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ መንግሥት ስለዚህ ዘገባ እስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም፡፡
6. ጡረተኛው ጀኔራል አለምሸት ደግፌ ወደ ሀገሪቱ ጦር ሠራዊት እንዲመለሱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጥሪ እንዳደረጉላቸው ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጽሕፈት ቤት ፌስቡክ ገጽ ተመልክተናል፡፡ ዐቢይ ትናንት ሦስት ጡረተኛ ጀኔራል መኮንኖች ወደ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
7. መከላከያ ሠራዊት ከሕወሃት ታጣቂ ሃይል የተሰነዘረበትን ጥቃት በመመከት፣ ታጣቂ ሃይሉን ከሕዝብ ነጥሎ የመምታት ርምጃ እየወሰደ እንደሆነ የጦር ሃይሎች ም/ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም እና የዘመቻ መምሪያ ሃላፊ ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ዛሬ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ ሀገሪቱ ሳትፈልግ ጦርነት ውስጥ መግባቷን የገለጹት ም/ኤታማዦር ሹሙ፣ የክልሉ ታጣቂ ሃይል የሰነዘረውን ጥቃት መከላከያ ሠራዊት እዚያው ይቋጨዋል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ በክልሉ የሠፈረው መከላከያ ሠራዊት ባልጠበቀው ሁኔታ በወገን ሃይል እንደተጠቃም በመግለጫቸው አውስተዋል፡፡
8. በመከላከያ ሠራዊት እና በትግራይ ክልል ታጣቂዎች ሃይሎች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት ለማስቆም አፍሪካ ኅብረት ከመጋረጃ ጀርባ የጀመረውን የዲፕሎማሲ ጥረት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እንዳልተቀበሉ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ በተያያዘ፣ ከዛሬ ጧት ጀምሮ በትግራይ-አማራ ድንበር የመድፍ እና ጥይት ተኩስ ይሰማ እንደነበር እና በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ በአብደራፊ ከተማ 24 ያህል ቁስለኛ ወታደሮች ሕክምና ሲሰጣቸው ምንጮች መመልከታቸውን ሮይተርስ ጨምሮ ጠቅሷል፡፡ ቁስለኞቹ ከየትኛው ወገን እንደሆኑ ግን ምንጮች ማረጋገጥ አልቻሉም ብሏል፡፡
9. የሚንስትሮች ምክር ቤት ትናንት በትግራይ ክልል ላይ ለ6 ወራት ያወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ አጽ,,እንዳጸደቀ በፌስቡክ ገጹ ገልጧል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ግብረ ሃይል የበላይ ሃላፊ ጠቅላይ ኤታማዞር ሹሙ ጀኔራል አደም ሞሐመድ ሆነዋል፡፡ ግብረ ሃይሉ በክልሉ ፖሊስን ጨምሮ ሌሎች ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት፣ ሰዓት እላፊ ለማወጅ፣ ጦር መሳሪያ ይዞ የመንቀሳቀስ እና ትራንስፖርት እንቅስቃሴዎችን ለማገድ ሥልጣን እንደተሰጠው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡ [ዋዜማ ራዲዮ]
ራያን ከህወሓት አፈና እና ጭቆና ነፃ የማውጣቱ ትግል ተጀምሯል። ጀግናው የራያ ህዝብ ለ3 አስርት አመታት የተጫነበትን የጭቆና እና አፈና ቀንበር ሰባብሮ ለመጣል ባለ በሌለ አቅሙ መረባረብ ይኖርበታል። እንሆ የራያ ራዩማ ትግል የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደረሰ።
የኢትዮጵያ የጦር ጄቶች ዛሬ አመሻሽ ላይ የትግራይ ርዕሠ ከተማ መቀሌ አካባቢን በቦምብ መደብደባቸዉን የትግራይ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ።
የክልሉ የመንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ በክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ባሰራጨዉ መግለጫ ጄቶቹ መቀሌ አካባቢ ቦምብ ጣሉ ከማለት ባለፍ ትክክለኛዉን ሥፍራ አልጠቀሰም።
የአዲስ አበባና የመቀሌ ወኪሎቻችን እንደጠቀሱት መግለጫዉ፣ በጥቃቱ የደረሰ ጉዳት ሥለመኖር አለመኖሩ ያለዉ ነገር የለም።
ይሁንና ጥቃቱን «የትግራይ ሕዝብን ለማንበርከክ» ያለመ ብሎታል።
በትግራይ ክልል የነበረውን ጦር መሳርያ በመጠቐም ትግራይን ለመጨፍጨፍ የነበረውን ህልም ሙሉ በሙሉ ከሽፏል
ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል
=====
የአሸባሪው ትህነግ ማዘዥያ ጣቢያ የነበረው የማይደሌ ጣቢያ በዚህ መልኩ ተደምስሷል!

የአሸባሪው ትህነግ ማዘዥያ ጣቢያ የነበረው የማይደሌ ጣቢያ በዚህ መልኩ ተደምስሷል!

የአሸባሪው ትህነግ ማዘዥያ ጣቢያ የነበረው የማይደሌ ጣቢያ በዚህ መልኩ ተደምስሷል!

የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል በሚገኙ የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ኃይል ሰፈሮች ላይ ጥቃቶችን ማድረጉ በጥልቀት አሳስቦናል።  https://mereja.com/amharic/v2/387638
ከሃዲው የሕወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረገው ትንኮሳ በመከላከያ እና በሕዝብ ትብብር ከሽፏል – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

በሁመራ፣ በዳንሻ እና በቅራቅር አካባቢ በነበሩ ውጊያዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ያደረጉት ተጋድሎ በታሪክ የሚዘከር ነው ሲሉ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ተናገሩ።

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ፥ በመከላከያ ሰራዊት ተግባር ‘ህውሓት’ ያሻውን ሳያደርግ የሞከራቸው ሙከራዎች ከሽፈው ውለዋል ሲሉ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማምሻውን የሰጡት መግለጫ።
ጀግናዉ ሰራዊት በወሰደዉ የማጥቃት እርምጃ በህወሓት ነብሰ በላ ቡድን ሃይል ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ የቡድንና የነብስ ወከፍ መሳሪያዎችንም ማርኳል ፡፡

መቀለ ከተማ ዛሬ

መቀሌ የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ከትላንት ጀምሮ በከተማዋ የነበረው ሁኔታ እንዲህ ዘግቦታል። የሚከተሉትን ፎሮ ግራፎችም ልኮልናል።

ትላንት [ማክሰኞ] እኩለ ለሊት ገደማ መቀሌ ከተማ ተኩስ ይሰማ ነበር።

የከተማው ሰው እየሆነ ባለው ነገር ተደናግጦ ነበር። ይሄኔ ሁኔታውን ለማረጋገጥ ወደ ፀጥታ ኃይል ሰዎች ስደውል ‘አሁን ልናናግርህ አንችልም፤ ቢዚ ነን’ አሉኝ። ከደቂቃ በኋላ የስልክ መስመር ተቋረጠ። ስልኬ ‘ኖ ሰርቪስ’ የሚል ምልክት ያሳየኝ ጀመር።

መቀለ ከተማ ዛሬ

በመቀጠል የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ። ጥዋት ስንነሳ ከተማዋ የኤሌክትሪክ አገልግሎቷ እንደተቋረጠ ተረዳሁ። መብራት የጠፋው መቀሌ ብቻ ሳይሆን ትግራይ ክልል ሙሉ እንደሆነ ማረጋገጥ ችያለሁ።

ወደ ከተማ ወጣ ስል የሰዎች ፊት ላይ ግራ መጋባት ተመለከትኩ። አብዛኛው ሰው በእግሩ ነበር ሲንቀሳቀስ የነበረው።

ከተማዋ ላይ ያሉ የባንክ ቅርንጫፎች ተዘግተው ነበር። ሁለት የባንክ አስተዳዳሪዎች እንደነገሩኝ አገልግሎት ያቋረጡ የበይነ መረብ [ኢንተርኔት] አገልግሎት ስለሌለ ነው።

ረፋድ ላይ የኢትዮቴሌኮም ሠራተኞች መስሪያ ቤታቸው ደጃፍ ላይ ሰብሰብ ብለው ቆመው ነበር።

መቀለ ከተማ ዛሬከረፋፈደ በኋላ ከፀጥታ ኃይል ሰዎች እንደተረዳሁት ተኩሱ የተሰማው የትግራይ ክልል ወታደሮች ከሰሜን ዕዝ ጋር በነበራቸው የተኩስ ልውውጥ መሆኑን ተረድቻለሁ።

ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮና ወደ ሌሎች የጉዞ ወኪሎች አምርቼ ለጊዜው በረራ ሙሉ በሙሉ መቋረጡን መረዳት ችያለሁ። በትግራይ የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል

መቀሌ ከተማ ያሉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ሆቴሎች አካባቢ ከበድ ያለ የፀጥታ ኃይል ይታያል።

የክልሉ መንግሥት ክልሉ ውስጥ ምንም ዓይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳይኖር አግዷል።

የትራንስፖርት አገልግሎትም ሙሉ በሙሉ ቆሟል። የክልሉ የአየር ክልልም ከበረራ ውጭ እንዲሆን ታዟል።

መቀሌ ከተማ አሁን ላይ ሰላማዊ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። BBC Amharic

የፀገዴ ወረዳ ሙሉ በሙሉ ከህወሓት ማፊያ ቡድን ነፃ ወጥቷል
ቀራቅር ላይ ድል አድርጎ ወደ ከተማ ንጉስ የገባው የመከላከያ ሰራዊት፣ የአከባቢው ገበሬዎች እና የአማራ ልዩ ኃይል የ”ፀገዴ” ወረዳ ተቋማትንና ከተማዋን ተቆጣጥሯል። ሆስፒታሉና ሌሎች ተቋማቶች በቁጥጥር ስር ሆነዋል። ከአይን እማኝ ባገኘሁት መረጃ መሰረት በትህነግ በኩል ለቁጥር የሚያታክቱ ልዩ ኃይሎቿን አጥታለች

PHOTO : ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ

በመቐለ ከተማ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ነው ያለው።

ባንኮች፣ መስሪያ ቤቶች እና ቴሌ ግን ዝግ ሆነው ነው የዋሉት።

የነዋሪዎች መደበኛ ህይወት እንደወትሮው ሁሉ ሰላም ነው።

PHOTO : ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ

ዛሬ ጥቅምት 25/2013 ዓ.ም በዚህ ሰዓት ትህነግ በራያ አላማጣ ከተማ ጅሃን አካባቢ የሚገኘውን የመብራት ኃይል ንኡስ ማከፋፈያን (sub station) ሲጠብቁ በነበሩ 15 በሚሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ድንገተኛ ተኩስ ከፍቶባቸዋል::
የኢትዮጵያ ህዝብ ሃብትና ንብረት የሆነውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ስቴሽንን በሚጠብቁ ጥቂት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ በእጅግ በርካታ ልዩ ሃይልን አሰማርቶ ጥቃት ከፍቶባቸዋል።
በሰሜን ዕዝ የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት ደርሶበት የነበረውን ጥቃት በማካካስ አሁን ላይ የህግ የበላይነትን የማስከበር ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉን አዲስ የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያት አስታውቋል፡፡

በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት ላይ በትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ደርሶበት የነበረው ጥቃትን ተከትሎ ሠራዊቱ ህግ ወደ ማስከበር ስራ መግባቱን ሴክሬታሪያቱ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዳሉት የትግራይ ልዩ ኃይል ከአማራ ክልል ጋር ግጭት እንዲፈጥር የሚታዩ ትንኮሳዎች እየታዩ ነው፡፡
ሠራዊቱ አሁንም ቢሆን የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየሰራ መሆኑን የገለፁት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ የትግራይ የመከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ህዝብ ጋር ዋጋ በከፈለ የጥቃት ዒላማ መሆኑ የሚያሳዝን ተግባር ነው ብለዋል፡፡ የትግራይ ክልልም ሆነ ኢትዮጵያ ህዝብ ይህን ተገንዝቦ ከሠራዊቱ ጎን እንዲሰለፍ አሳስበዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያት ኃላፊ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው የተፈጠረው ግጭት በአጠቃላይ በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ክልል መንግስት መካከል ሳይሆን ከተወሰኑ ጥቅመኛ ስብስቦች ጋር የተፈጠረ ግጭት መሆኑን የክልሉ ህዝብ ሊረዳ ይግባል ብለዋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊቱ ደርሶበት የነበረውን ጥቃት በማካካስ አሁን ላይ የህግ የበላይነትን የማስከበር ተግባር እና ቦታዎችን የመቆጣጠር ሥራዎችን በመሥራት ላይ መሆኑንም አምባሳደር ሬድዋን ገልፀዋል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያቱም ተጨማሪ መረጃዎችን በቀጣይ ለህዝቡ እንደሚያደርስ አስታውቋል፡፡ ምንጭ፦EBC

ከዚህ በፊት ከመከላከያ ሠራዊት ተቀንሰው የነበሩ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መኮንኖች ወደ መከላከያ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ትእዛዝ ተሰጥቷቸዋል:-

1. ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ

2. ሌ/ጄኔራል ዬሐንስ ገ/መስቀል

3. ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ

– በትግራይ ብቻ ሳይሆን የአፋር ሰሜናዊ ዞንም ከኔትወርክ አገልግሎት ውጭ ሆኖዋል።
ሱዳን በትግራይ ክልል ጋር የሚያገናኛትን ድንበር ዘግታለች።
የመቐለ የመጀመሪያ ዙር ኦፕሬሽን በድል ተጠናቋል!

በመቀሌና አካባቢው ተኩሱም ቆሟል። የህወሃት ሀይል እየሞተ እና ቀሪው ደግሞ እየሸሸ ነው ድል ለሰፊው ህዝባችን።
መከላከያው የትህነግን አለቆች ከያሉበት እያደነ ሲሆን በ ክልሉ ልዩ ሀይል ተይዘው የነበሩ ቦታዎችንም አስለቅቋል መሳሪያቸውንም አስማርኳል።
ጠገዴ አዳይጦ በተባለ ቦታ ሰፍሮ የነበረው የወንበዴው ቡድን፣ በዳንሻ በኩል ጥቃት ቢፈጽምም በመልሶ ማጥቃት ድባቅ ተመቷል። ኃይሉ የተዳከመበትና የተበታተነበት ትሕነግ ባእከር ላይ እየተሰራ ካለው እንዲስተሪ ፓርክ ያሰፈረውን ኃይል ወደ ዳንሻ አካባቢ ቢያንቀሳቅስም መለሶ ተደምስሷል።
አዳይጦ፣ ሶሮቃና ቅራቅር ላይ ድል የነሳችሁ የአማራ ልዩ ኃይል ጓዶች! የመከላከያ ሠራዊታችንን ከከበባ በማውጣት፣ ከባድ መሳሪያዎችንም ወደ ዋናው ቤዝ ማስፈር የተቻለው በልዩ ኃይላችንና በሕዝባዊ ሚሊሻው ተጋድሎ። ይህ እጅግ የሚያኮራ ተግባር ነው። መከላከያ ሠራዊትን ከከበባ መታደግ የቻለ፣ ከባባድ የጦር መሳሪያዎችን ከከበባ ማውጣት የቻለ ኃይል ልዩና ሕዝባዊ ሚሊሻ ስላለን ክብር ይሰማናል።
አሸባሪው ትህነግ በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ የነበሩ 2 የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ለመጥለፍ ሙከራ አድርጎ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። አውሮፕላኖቹን ለመጥለፍ ትሕነግ የከፈተው ተኩስ በመከላከያ ሠራዊት መቀልበሱ ታውቋል። አውሮፕላኖቹ አሁን እንደገና አርፈዋል።
በዳንሻ በኩል ወደአማራ ክልል ለማጥቃት ከመጣው የአሸባሪው የትህነግ ሰራዊት በርካታ መሳርያ ተማርኳል። ወልቃይት ጠገዴ አካባቢ በተለያየ ዕዝ ያለ በርካታ የአሸባሪው ሰራዊት በመኖሩ የፌደራሉ ፀጥታ ኃይል ጠንካር ያለ እርምጃ ሊወስድ ይገባል። በተለይ በቀራቅር በኩል በተደጋጋሚ የማጥቃት ሙከራ ማድረጉ ተገልፆአል።
ራያቆቦ ከማንኛውም ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ ነፃ ስትሆን የክልሉ ልዩ ሀይል ጮቢ በር ላይ በተጠንቀቅ መቆሙንና በትግራይና በአማራ ክልል አዋሳኝ ቦታ ዋጃ ኬላ ላይ ሰፍሮ የነበረው የትግራይ ክልል ልዩ ሀይል አካባቢውን ለቆ መውጣቱን በስፍራው የሚገኙ የአይን እማኞች ገልፀዋል::
የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት ሰራዊቱን ወደ ደንበር አስጠግቶ ሁኔታዎችን በንቃት እየተከታተለ ነው።
ትህነግ/ህወሓት ዳንሻ ከተማ ውስጥ ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መሳሪያ እያከፋፈለ ነው። ይህ በመላው ወልቃይት ጠገዴ እየሰሩበት ያለው ጉዳይ ሲሆን የዳንሻው ግን አሁን በዚሁ ቅፅበት እያደሏቸው ነው ተብሏል።
ብዛት ያላቸው የቆሰሉ የትግራይ ልዩኃይሎች ወደ ከተማ ንጉስ ሆስፒታልና ወደ መዓረግ ሆስፒታል እየገቡ ነው። በቀጥታ ወደ ትግራይም እየተጫኑ ያሉ አሉ። ምናልባት የሞቱ ሊሆኑ ይችላሉ ቀጥታ ወደ ትግራይ የሚወስዷቸው።
በምስኪኑ የጠገዴ ህዝብ ላይ ህወሀት ከባድ መሳሪያ እየተኮሰች ትገኛለች ።አሁን ላይ ቅራቅር ከባድ ውጊያ ከባድ ውጥረት ላይ ትገኛለ ። እናቶችና ህፃናት አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ጫቃ እየተሰደዱ ነው ።የፌድራል ፣የክልልና የዞን የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ለዚህ ሰላማዊ ህዝብ ፈጥነው ሊደርሱለት ይገባል።
ትላንት ማታ የተቋረጠው ኔትወርክ ተለቋል። ማታ የተጀመረው ተኩስም እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ቀጥሏል። ተኩሱ እረፍት የለውም። አሁን በዳንሻ ካዛ ወንዝ አከባቢ ከባድ ተኩስ እየተደረገ ነው።
መከላከያ ሰራዊት በትግራይ አንዳንድ ተቋማትን ተቆጣጥሯል እየተባለ ነው። ከቀራቅር ያፈገፈገው የትህነግ ኃይል አቅጣጫውን ቀይሮ አሁን ሁለተኛ ዙር ተኩሱን ጀምሮታል። የቀራቅር ከተማ ህዝብ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ከተማውንም ከበባ ውስጥ ሊከቱት ስለሚችሉ ጥንቃቄ ይደረግ።
ጦርነቱ ወደ አማራ “ክልል” ቀራቅር ከተማ ገብቷል። ትህነግ በጠገዴ ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል። በጠገዴ ቅራቅር በኩል ያለው ተኩስ እንደቀጠለ ነው።ትህነግ/ህወሓት በወልቃይት ጠገዴ ላለፉት ሁለት ዓመት የአማራ አዋሳኝ በሆኑ አከባቢዎች ሲቆፍራቸው በነበሩት ምሽጎች ውስጥ ልዩኃይሎችን አስገብቷል። ሁሉም ወደ ወልቃይት ጠገዴ መግቢያ በሮች በታጣቂዎቹ ለመዝጋት ሞክሯል።
ይህ ጦርነት ለሚቀጥሉት መቶ ዓመታት የምንኖርበትን አገራዊ ይዘት የሚቀይር መሆኑን እያሰብን ማድረግ ያለብንን ሁሉ እያደረግን ነው። ከሃዲያኑ አይቀጡ ቅጣት እየተቀጡ ነው!
~
ይህ ጦርነት ለምስራቅ አፍሪቃ ቀጣና አደገኛ በሆነው አሸባሪው የትሕነግ ቡድን እና ሀገረ-መንግሥቱን ለመታደግ በተሰለፈው ሠራዊት መካከል የሚካሄድ እንጅ፣ የሕዝብ ለሕዝብ ጦርነት አይደለም! በፍጹም ሊሆንም አይችልም። ወንድም ከሆነው የትግራይ ሕዝብ ጋር ከትሕነግ መደምሰስ በኋላ ሠላማዊ አብሮነታችን ይቀጥላል።
~
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የሰጡት መግለጫ ዋናዋና ነጥቦች
Image may contain: 1 person• ውድ የሀገሬ ህዝብ ሆይ ዛሬ ከሃዲ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን ወግተዋል።
• ኢትዮጵያ በጎረሰ እጇ ባጠባ እጇ ተነክሳለች ።
• ላለፉት 20 ዓመታት የቀበሮ ምሽግ ውስጥ በመሆን ሀገሬን ወገኔን ህዝቤን ብሎ በብዙ ሺዎች መስዋዕትነት ከፍሎ ቆስሎ ደምቶ ሀገሩንና ህዝቡን የታደገው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ዛሬ ምሽት ከመቀሌ ጀምሮ በበርካታ ስፍራዎች በካሃዲው ኃይሎች እና ባደራጁት ኃይል ጥቃት ተፈፅሞበታል።
• ይህ ጥቃት በሀገራችን እስካሁን ከደረሱት ጥቃቶች እጅግ አሰፋሪ የሚያደርገው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰላም ለማስከበር በተለያዩ ሀገራት በተሰማራበት ሀገር በውጭ ኃይል እንኳ አጋጥሞት በማያውቀው ሁኔታ በገዛ ወገኑ ከጀርባው ጥቃት ተፈፀሞበታል።
• በዳንሻ በኩል በአማራ ክልል ላይ የፈፀሙት ጥቃት በአማራ ክልል በነበረው ኃይል ተመክቷል
• የትግራይ ሕዝብ ወገናችን ነው ለጥቂት እኩዮች ሲባል ምንም እንኳ የእኩዮች መሸሸጊያ ዋሻ ቢሆንም ሕዝባችን ላይ ጥቃት አንሰነዝርም ብሎ በትዕግስት በቆየው ሰራዊት ላይ ጥቃት ተፈፅሞበታል
• በመላ ሀገራችን ቀድመው ባሰለጠኑት ባሰማሩት ባዘጋጁት ኃይል በተለያየ ቦታ በተለያየ ከተማ በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃት ሊፈፅሙ ስለሚችል መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከሚሊሻው ከፖሊስ ሰራዊት እንዲሁም በአካባቢያቸው ከሚገኝ የመከለከያ ሰራዊት ጋር በመተባበር ቀያችሁን ሰፈራችሁን እንድትጠብቁ አሳስባለሁ
• የመከላከያ ሰራዊት ከጠቅላይ ሰፈር በሚሰጥ ትዕዛዝ መለዮውን ሀገሩንና ህዝቡን እንዲከላከል ለሚከፍለው መስዋዕትነት ዛሬም እንደተለመደው በታሪኩ ውስጥ የሚታሰብ መሆኑን እገልፃለሁ።
• ይህ እኩይ ኃይል መጥፊያው በመድረሱ በሰላም በንግግር በውይይት ሊፈቱ የሚችሉ ነገሮችን ባለፉት ጥቂት ቀናት ካለምንም ሀፍረት በሚዲያ በመውጣት ከየትኛውም የውጭ ኃይል ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን እወጋለሁ ብሎ ሲያውጅ የነበረው ኃይል ይህን ለማመን የሚያስቸግር ንግግር በተግባር ማዋሉን በዚህ ምሽት አረጋግጧል።
• የትግራይ ህዝብ ወገኔ ዘመዴ ሕዝቤ ብሎ ላለፉት 20 ዓመታት በቀበሮ ምሽግ ውስጥ በመሆኑ በብዙሺዎች የሚቆጠር መስዋዕትነት የከፈለውን አንተን ለመጠበቅ አስፈላጊውን ሁሉ ያደረገው የመከላከያ ሰራዊት የደረሰበት ጥቃት ጥቃትህ መሆኑን በመገንዘብ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ሀገርህን ከነዚህ ከሃዲ ኃይሎች እንድትከላከልና በንቃት እንድትጠብቅ አሳስባለሁ።
• ይህ ጉዳይ ለኢትዮጵያ አሳዘኝ አሳፈሪም ተግባር ቢሆንም ዛሬም እንደተለመደው በተደመረ በተባበረ ክንድ ይህንን ከሃዲ ጡት ነካሽ ኃይል ለማሳፈርና ለመደምሰስ እስፈላጊውን ሁሉ የምናደርግ መሆኑን እገልፃለሁ።
ይህ አሳፋሪ ተግባር በማይደገምበት ሁኔታ የሚቀለበስበትን ተግባር መላው የኢትዮጵያ ህዝብና የሀገር መከላከያ ሰራዊት በመተባበር የሚፈፅሙት ይሆናል።
• ለመላው የሀገራችን ህዝቦች አስፈላጊውን መረጃ በየጊዜው በሚመለከታቸው የመንግስት አከላት የሚሰጥ መሆኑን እገልፃለሁ።
(ምንጭ፦ኢቢሲ)