Blog Archives

የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የመቶ ቀናት ቆይታ

የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የመቶ ቀናት ቆይታ 1. ውስጣዊ መረጋጋትን ከመፍጠር አኳያ ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡበት ወቅት በሁሉም ረገድ እጅግ ፈታኝ የሆኑ ጉዳዮች ባረበቡበት ወቅት ነው። መንግስት ውስጣዊ መረጋጋት ማስፈን ተስኖት ሁለት ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የተገደደበት፣ እዚህም እዚያም ግጭቶችና ትርምሶች የሚፈሉበት፣ በማንኛውም ቅፅበት አዲስ አበባ በኹከት ልትናጥ እንደምትችል የምታስፈራበት፣ ተረጋግቶ መስራትና መኖር አዳጋች የሆነበት፣ ኢኮኖሚው ተንገጫግጮ የነበረውን ፍጥነት ለማስቀጠል የተቸገረበት፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረቱ ጫፍ የደረሰበት፣ ኢህአዴግ በየጊዜው መግለጫ ቢያወጣም ተሰሚነቱ/ተዓማኒነቱ እጅግ የቀነሰበት፣ … ነበር። ይህንን ነባራዊ እውነታ ከመቀየር አንጻር ባለፉት 100 ቀናት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው። 1.1. ተስፋን የሚያጭሩ ንግግሮች ገና ወደ ስልጣን ከመምጣታቸውም በፊት “ቃል ይገድላል፥ ቃል ያድናል” ይሉ የነበሩት ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐብይ፣ ባለፉት 100 ቀናትም ይህን እምነታቸውን በተግባር አሳይተዋል። በበዓለ ሲመታቸው ያደረጉት ንግግር ከላይ የነበረውን የጭንቀት መንፈስ ከመግፈፍ አንጻር ከፍተኛ ሚና ተወጥቷል። በዚህ ንግግራቸው ስለአንድነት፣ ስለኢትዮጵያዊነት፣ ስለዴሞክራሲና የሃሳብ ብዝሃነት ያነሷቸው ሃሳቦች እና ባልተለመደ ሁኔታ እናታቸውንና ባለቤታቸውን ለማመስገን የሄዱበት ርቀት ሰዎች ለውጡን ከምር (seriously) እንዲያዩት ያስቻለ የመጀመሪያው እርምጃ ነበር። እስካሁንም ድረስ እንደ ጥቅስ የሚነሱ ዓ/ነገሮች (ስንኖር ኢትዮጵያ ስንሞት ኢትዮጵያዊ)፣ ለቀጣይ ስራዎቻቸው መነሻ የሆኑ አቅጣጫ አመላካቾች (የኤርትራ ግንኙነት)፣ የዴሞክራሲ ምህዳሩን የምር የማስፋት እርምጃዎች፣ … የተንፀባረቁበት ንግግር ነበር። ከዚህም በኋላ በየክልሉ ባደረጓቸው ንግግሮች የየአካባቢውን ቋንቋ በመቀላቀል፣ የአካባቢውን ባህል በማንጸባረቅ፣ የምር የሚያማቸውን ጉዳይ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News