አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚያካሂደው የከተሞች የመንገድ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በሰብዓዊ መብት ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖ እስኪጠና፣ ነዋሪዎችን ማፈናቀሉን እንዲያቆም ጠይቋል።
አምነስቲ፣ መንግሥት “ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ” በከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶቹ ነዋሪዎችን እያፈናቀለ ይገኛል ሲል ከሷል። አምነስቲ፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት በኮሪደር ልማቱ ተጎጅ የኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በበቂ ሁኔታ እንዳላማከሩ፣ በቂ ማስጠንቀቂያ እንዳልሠጡና ካሳ እንዳልከፈሉ ጠቅሷል።
ዓለማቀፍ አጋሮች ዜጎችን በግዳጅ ከመኖሪያ አካባቢያቸው ማፈናቀላቸውን እንዲያቆሙ በፍጥነት ማግባባት እንዳለባቸው አምነስቲ አሳስቧል።