ሰሙነ ሕማማት !
ከሆሳዕና በዓል (እሁድ) ስድስት ሰዓት እስከ አርብ (ስቅለት) ማታ ድረስ ያሉት ቀናት ሰሙነ ሕማማት ናቸው።
ሳምንቱ ” ዘመነ ፍዳ ” የሚታሰብበት ጊዜ ነው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰሙነ ሕማማት ወቅት ” የፈጣሪን ህመም ” ታሳቢ ያደረግ ልዩ ህግና ስርዓት አለ።
ቤተክርስቲያን ወትሮ የምታከናውናቸው ስርዓቶች በሕማማት ቀናት አይከናወኑም።
ህዝበ ክርስቲያኑ በሰሙነ ሕማማት የፈጣሪውን መከራ በማሰብ በተለየ ስርዓት ነው ቀናቱን የሚያሳልፈው።
በሰሞነ ሕማማት የትኞቹ የቤተ ክርስቲያን ስርዓቶች አይተገበሩም ?
በሰሙነ ሕማማት በቤተ ክርስቲያን ” ግብረ ህማማት ” የሚባል መጽሀፍ ይነበባል ፤ ለሳምንቱ የተዘጋጀ ልዩ ጸሎት ይደረጋል።
የሌሎች ስርዓቶች ክዋኔ ይገታል።
በሰሙነ ሕማማት ፦
- ቅዳሴ አይቀደስም (ከጸሎተ ሀሙስ ውጭ)
- ማህሌት አይቆምም
- ጸሎተ ፍትሀት አይደረግም
- መስቀል አይሳለምም
- ክርስትና አይነሳም
- ኑዛዜ አይሰጥም አይቀበልም
እነዚህ ስርዓቶች በሆሳዕና ዕለት አስቀድመው የሚከናዎኑ ናቸው።
ምዕመናን ሰሙነ ሕማማትን በምን ስርዓት ይከውናሉ ?
በቤተ-ክርስቲያኗ ” የመከራ ዘመን ” የሚባለውን 5500 ዓመትን በመወከል አምስት ቀናት ተኩል የሆነው ሰሙነ ሕማማት በምመናን ዘንድ በተለያዩ ድርጊቶች ይታሰባል።
የሚተገበሩት ድርጊቶች ሀዘንን ለመግለጽ እንዲሁም ከአስተምሮ ጋር መልዕክ ያላቸው ናቸው።
ምእመናን በሰሙነ ሕማማት ፦
- ከመጨባበጥና መሳሳም በመራው
- በባዶ እግር በመቆም
- በስግደት
- በጸሎት
- ራስን ዝቅ ማድረግ ያስባሉ።
አባቶች በሕማማት ሳምንት ምዕመኑ ፦
° ወደ ራሱ ጠልቆ በመግባት መጸለይ እንዳለበት
° ሰው ስለ ኃጢያቱ ማሰብ እንዳለበት
° ስለ ሀገሩ ማዘን እንዳለበት
° ለሰላም መጸለይ እንዳለበት
° የሰው ልጅ ሰላም እንዲያገኝ ሰላም ያጣው ህዝብ ሰላም እንዲያገኝ መጸለይ እንዳለበት
° ፈጣሪ የተቀበለውን መከራ በማሰብ ለሀገር ሰላም እንዲሰጥ ህይወታችንን ያስተካክል ዘንድ መለመን እንዳለበት
- ከኃጢያታችን ይቅር እንዲለን መጸለይ እንዳለበት ያስገነዝባሉ።
(መላከ ገነት ክብሩ ገ/ጻድቅ – ከዚህ ቀደም ለአል አይን ከሰጡት ቃል)