በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ ልዩ ስም “ፍልቅልቅ” በተባለ ሥፍራ ለጂፕሰም የፋብሪካ ምርት ጥሬ ዕቃ በማውጣት ላይ የነበሩ የማሽን ሠራተኞች ጨምሮ አስር ያህል ሰዎች ትናንት በታጣቂዎች እንደታገቱ ዋዜማ ሰምታለች። አጋቾቹ ከአማራ ክልል ተሻግረው የገቡ መሆናቸውን ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል። ታፍነው ከተወሰዱት ሰዎች በተጨማሪ፣ ከታጣቂዎቹ ጥቃት ለማምለጥ ሲሞክሩ የነበሩ ሌሎች ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች በተከፈተባቸው ተኩስ አካላዊ ጉዳት እንደደረሰባቸው ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል። አጋቾቹ ሰዎቹን ወደየት እንደወሰዷቸው ምንም ፍንጭ እንዳልተገኘም ተናግረዋል።