በፒያሳ እና አካባቢው 11 ሺህ ሰዎች መነሳታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

በአዲስ አበባ በፒያሳ እና አካባቢው ከሳምንታት በፊት በተጀመረው ግንባታ ምክንያት ወደ 11 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መነሳታቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ ይህንን ያሉት በመንግስት መገናኛ ብዙኃን ትናንት ረቡዕ መጋቢት 18/2016 ዓ.ም ምሽት ላይ በተላለፈ ውይይት ላይ ነው።