ጀግናው አርበኛ ዘመነ ካሴ ከእስር ተፈታ!

አርበኛ ዘመነ ካሴ በአሁኑ ሰአት ከማረሚያ ቤት ወጥቷል::
ከመስከረም ወር ጀምሮ በባህር ዳር ሰባታሚት ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የቆየው አርበኛ ዘመነ ካሴ ዛሬ ከማረሚያ ቤት ወጥቷል::

በተለያዩ ጊዜያት ፍርድ ቤት በመቅረብ ክርክር ሲያደርግ የቆየው አርበኛ ዘመነ ካሴ የአማራ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 25/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት አርበኛውን በነጻ ማሰናበቱ ይታወሳል::

ሁኖም የፍርድ ቤቱን ትዛዝ በመተላለፍ በመንግስት አመራሮች ከማረሚያ ቤት ድጋሚ ለሁለት ቀናት የቆየው አርበኛ ዘመነ ዛሬ የባህር ዳርና አካባቢው ወጣቶች በተገኙበት ከሰባታሚት ማረሚያ ቤት ወጥቷል::

የባህር ዳርና አካባቢው ወጣቶች ትላንትም አርበኛው ሲለቀቅ ለመቀበል ማረሚያ ቤት በር ላይ ሲጠባበቁ መዋላቸው የሚታወስ ሲሆን ዛሬ አርበኛው ሲወጣ በደስታና በጭፈራ ተቀብለው ይዘውት ወጥተዋል::

አርበኛ ዘመነ ለ9 ወራት ያክል በግፍ እስር ላይ ቆይቷል::