Blog Archives

በሀዋሳ ከተማ ሁከትን ተገን በማድረግ በህገወጥ መንገድ የተገነቡ 214 ቤቶች እንዲፈርሱ ተደረገ

በሀዋሳ ከተማ ሁከትን ተገን በማድረግ በህገወጥ መንገድ የተገነቡ 214 ቤቶች እንዲፈርሱ ተደረገ። $bp("Brid_46621_1", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-336015006942767.mp4", name: "በሀዋሳ ከተማ ሁከትን ተገን በማድረግ በህገወጥ መንገድ የተገነቡ 214 ቤቶች እንዲፈርሱ ተደረገ", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/IMG_20180823_220225.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪና የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን ለቀቁ ።

የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ አዱላ እና የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን የደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽም ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ። ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ አዱላ እና የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ በአካባቢው ለተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስና ተያይዞ ለተከሰቱት የህብረተሰብ ጉዳት ኃላፊነት በመውሰድን ከዛሬ ሰኔ 28 2010 ዓ.ም ጀምሮ በገዛ ፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው የለቀቁት። በቦታቸው የሚተኩትን አመራሮችን በሚመለከት በተለመደው የድርጅቱ አስራር መሰረት የሚፈጸም መሆኑን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽም ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል። በሀዋሳ ከተማና አካባቢዋ ተከስቶ በነበረው ችግር የ10 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 89 ሰዎች ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱ ይታወሳል። እንዲሁም ግጭቱን ተከትሎ 2 ሺህ 500 ሰዎች ደግሞ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በደቡብ ክልል ግጭት ወደተከሰተባቸው አካባቢዎች በማቅናት ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ግጭት የተፈጠረባቸው አካባቢዎች ያሉ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ሀላፊነት ወስደው በፈቃዳቸው ስልጣን እንዲለቁ ጥሪ ማቅረባቸውም ይታወሳል። ሰኔ፣ 28፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሀዋሳ ውሎ (በመሣይ መኮንን)

ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ሀዋሳን እየናጣት ያለው አለመረጋጋት ዛሬ በመጠኑ ጋብ ብሏል። ከትላንት ምሽት ጀምሮ ይህን ጽሁን እስካጠናቀርኩበት ደቂቃ ድረስ ሁኔታዎች በአንጻራዊ መልኩ የተሻሉ ናቸው። ከተማዋ ባለመደባት ድብታ ውስጥ መሆና የቀጠለ ቢሆንም የአንድ አፈር ልጆች የጀመሩትን የእርስ በእርስ ግጭት ጋብ አድርገውታል። በከተማዋ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አሁንም የለም። በእግር የሚጓዙ ሰዎች ከወዲህ ወዲያ ሲሉ ይታያሉ። አስፈሪው ስሜት ግን እንዳንዣበበ ነው። ጸጥታው ምቾት አይሰጥም። ሀዋሳ ጭር ስትል አያምርባትም። የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች ለግጭቱ ጋብ ማለት ያደረጉት አስተዋጽኦ የሚያስመሰግን ነው። ከትላንት ጀምሮ በከተማዋ የገባው ተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት በዋና ዋና የከተማዋ ክፍሎች ተሰማርቶ ይገኛል። ቢዘገይም ከመቅረት ይሻላል። ምንም እንኳን በሀዋሳ አሁን እፎይታ ቢኖርም ወደ ቀድሞ ”የፍቅር” ከተማነቷ ለመመለስ ጊዜ የሚወስድባት ይመስላል። ለሀዋሳውያን ክስተቱ ያልተጠበቀ ዱብ እዳ ስለሆነባቸው በቀላሉ ከጭንቀትና ስጋት መላቀቅ እንደማይችሉ ይጠበቃል። አሁን ሁለት ነገሮች በአፋጣኝ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል። አንደኛው በተለያዩ የሲዳማና የወላይታ አከባቢዎች የተፈጠሩ አለመረጋጋቶችን በአስቸኳይ እንዲቆሙ ማድረግ ነው። ይርጋለም፡ ጭኮ፡ አለታወንዶ፡ በንሳና ሌሎች የሲዳማ ወረዳና ከተሞች እየታየ ያለው አለመረጋጋት በቶሎ እንዲረግብ የሚመለከታቸው አካላት በተለይም የሀገር ሽማግሌዎች ሃላፊነታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል። በወላይታም በተመሳሳይ የሚታዩ ጥሩ ያልሆኑ አዝማማያዎች ሳይሰፉ በአጭሩ ሊገቱ ይገባል። ሁለተኛው በሀዋሳ ከተማ ግጭቱን በመሸሽ በቕዱስ ገብርዔል ቤተክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙ ነዋሪዎች የሚላስ የሚቀመስ አጥተው እየተሰቃዩ ነው። ህጻናት በብዛት የሚገኙ በመሆናቸው ችግሩ የከፋ እየሆነ ነው። አሁን እየታየ ያለውን መረጋጋት በመጠቀም የሀዋሳ ከተማ ህዝብ ለእኚህ ወገኖቹ ሊደርስላቸው
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News