ከኑሮ ጋር አልመጣጠን ያለው የመንግስት ሰራተኛው ደሞዝ እና አዲሱ ረቂቅ አዋጅ

“አዲሱ የደመወዝ ገቢ ግብር ረቂቅ የኑሮ ጫናን ያገናዝብ” የሰራተኞች ኮንፌዴሬሽን

በትናንትናው እለት ለኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ በርካቶችን አከራክሯል፡፡

በምክር ቤቱ የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አዘጋጅነት የቀረበው ረቂቁ ግብር የሚቆረጥበት የደመወዝ መነሻ ከዚህ በፊት ከነበረው 600 ብር ወደ 2000 ብር ከፍ እንዲል ሃሳብ ያቀረበ ቢሆንም በበርካቶች እይታ ግን አመርቂ አለሆነም፡፡

በተለይም ከዚህ በፊት ግብር የሚቆረጥበት የደመወዝ ክፍያ መጠን መነሾ በትንሹ 8 ሺህ 300 ብር ገደማ መሆን አለበት በሚል ምክረሃሳብ አቅርቦ የነበረው የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፌዴሬሽን ትናንት የቀረበውን ረቂቅ ከመጽደቁ በፊት ዳግም እንዲታይ አሳስቧል፡፡

የደሞዝ ጭማሪው «ሳይመጣ የሄደ ተስፋ» ወይስ ደጓሚ ?

ስሜ ይቆይ ብለው አስተያየታቸውን ያጋሩን አንድ በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ የሚያስተምሩ መምህር የኑሮ ጫና ለሰራተኛው የሚከፈለውን ደመወዝ ጥሎት በመሄዱ በብዙ መልኩ እልባት ይሻል ይላሉ፡፡ ትናንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመከረበት አዲሱ የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ የኑሮና የታክስ ጫና ያለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረገ እና ከታክስ ስርአት ጋር ያሉ ችግሮችን ለመፍታት አበክሮ የሚያገናዝም መሆን አለበት የሚሉ ድምጾች ክፍ ብለው ተሰምተውበታል፡፡ ታዲያ በዚሁ ላይ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ ያቀረቡት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መምህሩ፤ አሁን ያለው የኑሮ ጫና እንኳን ከፍተኛ ቀረጥ (ታክስ) ኑሮበት በምንም የማይያዝ እየሆነ ነው ይላሉ፡፡ “ገቢያችን ከኑሮ ውድነቱ አኳያ በጣም ወደ ኋላ ቀርቷል” ያሉን አስተያየት ሰጪው “አሁን የሚከፈለውን የሰራተኛው ደመወዝ በእጥፍ እንኳ ብጨመር ኑሮን ለመቋቋም አቅም አይኖረውም” ነው ያሉት፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ እስከ 35 በመቶ የሚቆረጠው የታክስ ገቢ ጨናውን የሚያከብድ መሆኑን አስረደተዋል፡፡

አዲሱ ዓመት ለተቀጣሪው ሰራተኛ ተስፋ ወይስ ስጋት ?

ከኑሮ ውድነቱና የዋጋ ንረት አኳያ የገቢ ግብር መነሻው ከአምስት ሺ ብር ጀምሮ ቢሆን፣ የሚል ሃሳብም የቀረበበት ረቂቁ አሁንም ሰራተኛውን የሚያሳርፍ አልሆንም የሚሉት አስተያየት ሰጪው ከሚገኝ አነስተኛ ገቢ 35 በመቶ ድረስ ከማንሳት ይልቅ ሌላ በኑሮ ውድነቱ የተፈተነውን ሰራተኛ የሚያሳርፍ መፍትሄ ይዞ መምጣት ያስፈልጋልም ነው ያሉት። “35 በመቶ ከምትገኝ አነስተኛ ገቢ በግብር መልክ ማንሳት በጣም ይጎዳል፤ ነጋዴ ከትርፉ ነው ሰራተኛው ደግሞ ከዚያችው ማኖር ከማትችለው አነስተኛ ገቢ ነውና ብታሰብበት” ብለዋል፡፡

Äthiopien Tigray Mekele 2025 | Binnenvertriebene im Sebacare-Lager
ከኑሮ ውድነቱና የዋጋ ንረት አኳያ የገቢ ግብር መነሻው ከአምስት ሺ ብር ጀምሮ ቢሆን፣ የሚል ሃሳብም የቀረበበት ረቂቁ አሁንም ሰራተኛውን የሚያሳርፍ አልሆንምምስል፦ Alexander Mamo/AP/picture alliance

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፌዴሬሽን አዲሱን ረቂቅ አሁንም መፍትሄ ይዞ አልመጣም በሚል ከተቹት ተቋማት ነው፡፡ የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፤ “የደመወዝ ገቢ ግብር መነሻ ከዚህ በፊት 600 ብር ነበር፡፡ አሁን 2000 ብር ሆኖ ብርብም ከዚህ በፊት 600 መነሻ ሆኖ እንዲጸድቅ በተወሰነበት ጊዜ አንድ ዶላር 20 ብር በነበረበት የገንዘብ የመግዛት አቅሙ ትልቅ በነበረበት ነው” በማለት ለደመወዝ ገቢ ግብር በመነሻነት የተቆረጠው 2000 ብር በቂ እርከን አለመሆኑን ተችተዋል፡፡ አሁን ባለው የኑሮ ደረጃም 2000 ብር አንድን ሰው በልቶ ለማደር እንኳ የማይበቃ ነው በማለት በልቶ ከማያድር ሰው እንዴት ግብር ይሰበሰባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የሠራተኞች ማሕበራት በገቢ ግብር ማሻሻያ ዙሪያ ለመንግሥት ጠንካራ መከራከሪያ አቀረቡ

መስሪያ ቤታቸው ከዚህ በፊት 8 ሺህ 300 ብር ግድም መነሻ እንዲሆን ሃሳብ አቅርበው እንደነበርም አስታውሰው ያ ግን አለመሆኑን አሳሳቢ ብለውታል፡፡ ከዚህ በፊት የግብር ምጣኔው በአነስተኛ ደመወዝ ተከፋዮች ላይ 10 በመቶ እንደነበርም ያስታወሱት አቶ ካሳሁን፤ አሁን በቀረበው ረቂቅ ላይ ግን በመነሻነት የተያዘው የግብር ምጣኔ ከ15 በመቶ መጀመሩንም የሚተች ብለውታል፡፡ የሰራተኞች ኮንፌዴሬሽን ኃላፊው አቶ ካሳሁን ለዶይቼ ቬለ አክለው እንዳብራሩት መስሪያ ቤታቸው ያቀረበው ምክረሃሳብ ከድህነት ወለል በታች ያሉ ሰራተኞች ግብር መክፈል የለባቸውም የሚል ቢሆንም የተለያዩ አመክኖዎች ቀርበውበታል ነው ያሉት፡፡ “በተቻለ መጠን ለቋሚ ኮሚቴው ግብዓት እንዲሆኑት ምክረሃሳቦችን ሰጥተናልም” ያሉት አቶ ካሳሁን አዋጁ ለመጨረሻ ምህራፍ ቀርቦ ከመጽደቁ አስቀድሞ የሚታዩ ነገሮች ይኖራሉ የሚል ተስፋ አላቸው፡፡ በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል በተሰጠው ሀሳብ ግን የደመወዝ ገቢ ግብር መነሻ ከዚህ በታች የሚወርድ ከሆነ በተለይም ከተቀጣሪ ሰራተኞች ከፍተኛውን ገቢ የሚሰበስቡ ክልሎች አከባቢ የገቢ እጥረት እንዳይከሰት ስጋት ስለመኖሩ ተብራርተዋልም ብለዋል፡፡

በሰራተኞች ቀን የኢትዮጵያ ሀኪሞችና መምህራን ጥሪ

በዝቅተኛ ደመወዝ የሚተዳደሩ ሰራተኞች ፌስታል ይዘው በየሆቴሎች ተመላሽ ምግቦችን እስከመለመን ደርሰዋል ያሉት የሰራተኞች ኮንፌዴሬሽን ሃላፊው የኑሮ ጫናው ሻል ያለ ደመወዝ በሚያገኙትም ላይ ጫና ማሳደሩ እንዳልቀረ አብራርተዋል፡፡ “እኛ እያልን ያለነው ታች አነስተኛ ተከፋዮች ፌስታል ይዘው ልመና ወጥተዋል ነው” በማለት ከተለያዩ ወጪዎች አኳያ የተሻለ ክፍያ የሚከፈላቸውም የኑሮውን ጫና ለመቋቋም ተፈትነዋል ሲሉ ያለውን አሁናዊ እውነታ ለማስረዳት ጥረዋል፡፡  https://www.dw.com/am/