ጀኔራል ታደሰ እርስበራሱ የሚጋጭ አዲስ ቀውሰ አዋላጅ ነው

“ለቅቄ ወጥቻለሁ”
<<እኔን የወከለ አስተዳዳሪ የለም ፤ ህጋዊ የዞኑ አስተዳዳሪ እኔ ነኝ ፤ አላስፈላጊ ግጭትና ደም መፋሰስ ለማስቀረት በማሰብ ፅህፈት ቤቴን ለቅቄ ወጥቻለሁ። በዞኑ የሚደረግ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ቀይ መስመር ነው ፤ ወታደር ስለአሰማራህ አስተዳድረሀል ማለት አይደለም ከትናንት ሀምሌ 14 ከምሽቱ 3፡30 ጀምሮ የአድማ ብተና ፖሊስና ታጣቂ ሰራዊት ወደ ዞኑ ተሰማርቷል።ለረጅም ጊዚያት እቅድና ዝግጅት ሲደረግበት የቆየ የዞኑ አስተዳደር የማፍረስ ተግባር እየተፈፀመ ነው። ጀኔራል ታደሰ እርስበራሱ የሚጋጭ አዲስ ቀውሰ አዋላጅ ነው። ህውሃት ኃላቀርና ቆሞ ቀር ቡድን ነው።>>
አቶ ሃፍቱ ኪሮስ
የትግራይ ደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ