መጀመሪያ የውስጥ ጉዳያችሁን ፍቱ … ኤርትራን መንካት ጣጣ ማምጣት ነው ! ( ኢሳያስ አፈወርቂ )

የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የኢትዮጵያ መሪዎች ከጠብ አጫሪ ንግግር ተቆጥበው በአገሪቱ የውስጥ ችግሮች ላይ እንዲያተኩሩ በሁለተኛው ክፍል ቃለ ምልልሳቸው መክረዋል። ፕሬዝዳንቱ፣ ኤርትራን መወንጀል ሌላ ጣጣ ማምጣት እንደሚሆንና የከፋ ውጤት ከመጣ ማቆም እንደማይቻል አጠንቅቀዋል። ኢሳያስ፣ በሱዳኑ ጦርነት ጀርባ ዋነኛዋ ተዋናይ ኢምሬቶች ናት በማለትም ከሰዋል።