አሜሪካ ከተመድ የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ተቋም (UNESCO) ልትወጣ ነው።

አሜሪካ ከተመድ የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ተቋም (UNESCO) ልትወጣ ነው።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዳግም ወደ ነጩ ቤተመንግስት ከተመለሱ በኋላ አሜሪካ ከአለም አቀፍ ተቋማት እንድትወጣ እየሰሩ ሲሆን አሁን ከዩኔስኮ እንድትወጣ መወሰናቸውን የነጩ ቤተመንግሥት ምክትል ቃለ አቀባይ አና ኬሊ ተናግረዋል።

አና ኬሊ የዩኔስኮ የባህል እና ማህበራዊ ፖሊሲ አሜሪካውያን ድምፃቸውን ከሰጡበት ፖሊሲ ጋር ስለሚቃረን ፕሬዚደንቱ አሜሪካ እንድትወጣ መወሰናቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪ የውጪ ጉዳይ ቢሮ ቃለ አቀባይ ታሚ ብሩስ የአሜሪካ በዩኔስኮ መቀጠል ከብሔራዊ ጥቅሟ በተቃራኒ መሆኑን ገልፀዋል።

ታሚ ብሩስ ተቋሙ ውስጥ ፀረ ሴማዊነት አለ ያሉ ሲሆን ተቋሙ ፍልስጤምን እንደ አባል ሃገር መቀበሉ ከአሜሪካ ጥቅም በተቃራኒ ነው ብለዋል።

የዩኔስኮ ዳይሬክተር ኦድሪ አዙላይ ተቋማቸውን ይህንን ውሳኔ ሲጠብቅ እንደነበር ገልፀው ሲዘጋጁበት እንደነበርም ገልፀዋል።

አሜሪካ ከተመድ የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ተቋምም በፈረንጆቹ ታህሳስ 31፥2026 ትወጣለች ተብሏል።

አሜሪካ በ1945 ዩኔስኮን ከመሰረቱ ሃገራት አንዷ ስትሆን በ1984 ከፋይናንስ አያያዝ እና ከአሜሪካ በተቃራኒ ቆሟል በሚል ከወጣች በኋላ ተቋሙን በ2003 ዳግም ተቀላቅላለች።

በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ፕሬዚዳንት ሆነው በተመረጡ ጊዜ አሜሪካን ከተቋሙ አስወጥተው የነበረ ቢሆንም ጆ ባይደን ዳግም መልሰዋት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ሁነት መሆኑ ይታወሳል።

Source: CNN