በቅማንት ስም የሚንቀሳቀስ ጽንፈኛ አርሶ አደሮችን ገሏል ሲል የጭልጋ አስተዳደር ከሰሰ

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን የጭልጋ ወረዳ አስተዳደር፣ “በቅማንት ስም የሚንቀሳቀስ ጽንፈኛ” ሲል የጠራው ታጣቂ ቡድን ሰኔ 7 ቀን በጎዶ ሞላሊት ቀበሌ በትንሹ 8 ንጹሃን አርሶ አደሮች ገድለዋል በማለት ከሷል።

የወረዳው አስተዳደር፣ ቡድኑ አርሶ አደሮችን ማገቱንና በሃብትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱንና ሌሎች 5 ሰዎች እንደቆሰሉና 6ቱ ታፍነው እንደተወሰዱ ገልጧል።

ጥቃቱን ተከትሎ፣ መከላከያ ሠራዊት ወደ ቀበሌው ገብቷል ተብሏል። ቡድኑ በአማራና ቅማንት መካከል ድጋሚ “የብሔር ግጭት” እንዲቀሰቀስ ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱንም የወረዳው አስተዳደር ገልጧል።