የአለም ጤና ድርጅች የቺኩንጉንያ ቫይረስ በፍጥነት እየተዛመተ ነው ሲል አስጠነቀቀ።
በአለም ላይ ከ20 አመት በፊት ተከስቶ የነበረውና በወባ ትንኝ ዝርያ የሚከሰተው የቺኩንጉንያ ቫይረስ በህንድ ውቅያኖስ አካባቢ በሚገኙ ሃገራት ዳግም ተቀስቅሶ እየተስፋፋ ነው ተብሏል።
በ119 ሃገራት የሚኖሩ 5.6 ቢሊየን ሰዎች የቫይረሱ ስጋት ውስጥ መሆናቸውም ተገልጿል።
በላ ሪዩኒየን ደሴት ከሚገኘው ህዝብ አንድ ሶስተኛው በቫይረሱ ተይዟል ያለው የአለም ጤና ድርጅት ቫይረሱ በአሁኑ ጊዜ ወደ ማዳጋስካር ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ ተስፋፍቷል ብሏል።
በሽታው ወደ አውሮፓ ተስፋፍቶ 800 ሰዎች በፈረንሳይ በቫይረሱ ተይዘዋል ሲባል በጣሊያንም የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል።
ቫይረሱ ምንም አይነት ህክምና የሌለው ሲሆን የሚተላለፈው በወባ ትንኝ ዝርያ እንደሆነ ሲገለፅ እንደ ድካም፣ ትኩሳት እና የራስ ምታት ያሉ ምልክቶችም አሉት ተብሏል።
የአለም ጤና ድርጅት ሰዎች ራሳቸውን በልብስ በመሸፈን እና እንደ አጎበር ባሉ ነገሮች በመጠቀም እንዲጠብቁም መክሯል።
በ2005 በተከተሰው ወረርሽን ወቅት በሚሊየኖች በበሽታው ሲያዙ በመቶዎቾ የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወትም አልፏል።
ቫይረሱ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ በ2008 ዓ.ም ተከስቶ የነበረ ሲሆን ከተከሰተባቸው አከባቢዎች አንዱ ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር በምትዋሰንበት ዶሎ አዶ አካባቢ ሲሆን በድሬዳዋም በተመሳሳይ ተከስቶ ነበር።
በቫይረሱ ዙሪያ በቅርብ በተደረገ ጥናት (https://www.frontiersin.org/journals/public-health/articles/10.3389/fpubh.2025.1538911/full) ኢትዮጵያ ለቫይረሱ ተጋላጭነት አድሏ 24 በመቶ መሆኑን ይጠቁማል። በዚህም ቫይረሱ የህብረተሰብ ጤና ስጋት መሆኑን ያነሳል።
Source: USA TODAY