Blog Archives

የዘር ፖለቲካ፣ የዘር አወቃቀር፣ የዘር ሕገመንግስት አስከፊ ውጤቶች ፣ በዝርዝር #ግርማካሳ

ጠቅላይ ሚኒስተር ዶር አብይ አህመድ በፓርላማ አንድ ንግግር ተናገሩ። ደስ ያለኝ ንግግር። “ትግሬ፣ አማራ፣ ኦሮሞ …መባባል ያታረፈልን ድህነትና እከክ ብቻ ነው” ነበር ያሉት። ትልቅ አባባል።  ምንም ጥርጥር የለውም ያተረፈልን ድህነት ብቻ ነው። እኔ ግን ከዚያ አልፌ እሄዳለሁ። ድህነትና እከክ ብቻ ሳይሆን ደም መፋሰስ፣ መገዳደል፣ መተራረድንም ነው ያተረፈልን። የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ለዜግነት ለስብእና እውቅና የሚሰጥ አይደለም። ኢትዮጵያ የዜጎቿ ሳይሆነ የጎሳዎቿ ( ህገ መንግስቱ ብሄር ብሄረሰብ ህዝብ የሚለው) ናት። ስለዚህ አንድ ዜጋ በአንድ ጎሳ ጆንያ ውስጥ ካልታጠረ እውቅና አያገኘም። ያ ብቻ አይደለም የአገሪቷ ግዛቶች የተሸነሸኑት በዘር ነው። የአማራ መሬ፣ የትግሬ መሬት፣ የኦሮሞ መሬት እየተባለ። ምን ማለት ነው ዶር አብይ አህመድ እከክና ድህነት ነው ያተረፈልን፣ እኔ ደግሞ ደም መፋሰስን ነው ያተረፈልን ያልኩት ነገር ፣ በዋናነት ምንጩ ሕወሃትና ኦነግ የዘረጉት ከፋፋይ በኢትዮጵያዉያን መካከል አጥሮች የገነባ የዘር ሕገ መንግስቱ፣ የዘር አወቃቀር፣ በአጠቃላይ የዘር ፖለቲካው ነው።   ምን ያህል ከዘር ጋር በተገናኝ ደም እንደፈሰሰ ለማሳየት የሚከተሉትን 41 የዘር ግጭቶች ወይም የዘር ማጥራትና ማጥፋት ወንጀሎችን በሶስት ከፍዬ እዘረዝራቸዋለሁ። አንባቢያን ምን ያህል በዚህ በሕህወሃት ሕግ መንግስትና አወቃቀር ምክንያት እንደ አገር እየደማን መምጣታችንን እንዲያውቁ። እነዚህ የተዘረዘሩት ጥቂቶቹ ናቸው። ቁጥሩ ከዚያ በላይ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል። እነዚህ እኔ የማውቃቸው ናቸው። ከደርግ ፍጻሜ እስከ አቶ ለማ መገርሳ መምጣት ላለፉት 28 አመታት በአገራችን እጅግ በጣም መርካታ አስከፊ የዘር ተኮር ግጭቶችና እልቂቶች ተከስተዋል። ኢሕአዴግ አዲስ
Posted in Ethiopian News

የቀረች እንጥብጣቢ ርህራሄ ለትግራይ ወጣት ካላችሁ እጅ ስጡ #ግርማካሳ

ህወሃቶች ክ27 አመታት በላይ ብዙ ግፍና ሰቆቃዎች የፈጸሙ ናቸው። ሆኖም የኢትዮጵያ ህዝብ በይቅርታ መንፈስ አልፏቸው ነበር። ለውጥ መጣ የተባለው ከራሱ ከኢሕአዴግ ስለነበረ። በዚህ አጋጣሚ እነ አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ አባይ ጸሃዬ …በሰላም ለወጣቶች ሃላፊነቱን አስረክበው ገለል ቢሉ ጥሩ ነበር። ሕገ ወጥ ምርጫ ሲያደርጉ ይቅር ተባሉ። ምርጫው እንዳልተደረገ ይቆጠራል ተብሎ። ከስልጣን ዉረዱ አልተባሉም። ምን ችግር ነበረው እንደገና ለመጪው ምርጫ እንሳተፋለን ቢሉና ነገሮችን ለማብረድ ቢሞክሩ ኖሮ ??? ያንን እንዲያደርጉ ብዙ ጻፍን፣ ተመጻንን፣ ግፊት አደረግን። በጣም የሚገርማችሁ እንደሚሸነፉ ነግረናቸዋል። ሚሊሺያዎች ተገደው ስለሆነ አይዋጉላችሁም። “ከላይ በኤርትራ ከታች በጎንደር፣ በወሎና በአፋር ተከባችሁ፣ ዉሃ ነዳጅ፣ ምግብ በአጠቃላይ ስንቅ (provisions) ችግር ያጋጥማቹሃል። በመሳሪያና በሰው ኃይል ብቻ ጦርነትን ማሸነፍ አትችሉም። መሸነፋችሁ አይቀርም” ብለናቸው ነበር። ግን ሰዎቹ ግትር ሆኑ። ማስተዋል ተሳናቸው፡፡ በልዩ ኃይላቸውና በመሳሪያቸው ተመኩ። ከደርግ መማር ተሳናቸው። የፌዴራል መንግስቱን ጎትተው ጦርነት ውስጥ አስገቡት። አሁን ከሕወሃት ጋር የሚደረገው ውጊያ 2 ሳምንት ሆኖታል። ብዙ ወገኖች ሞተዋል፡፡ብዙዎች ተፈናቅለዋል።ብዙ ውድመቶች ተከስተዋል። በጣም ያሳዝናል። ይሄ ሁሉ መሆን አልነበረበትም።በጣም ልብን ያደማል። ህወሃት በሰሜን፣ ኦነግ በምእራብና በደቡብ አገራችንን አመሷት። በዚህ ሁለት ሳምንት በተደረገው ዉጊያ ወልቃይት ጠገዴ ካፍታ ሁመራና ራያ ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል ክሕወሃት ነጻ ወጥተዋል። አልፎ አልፎ አንዳንድ ቦታዎች ገና ያልጠሩ ቢሆንም። በአሁኑ ወቅት መከላከያ ወደ መቀሌ እየገሰገሰ ነው። መቀሌ በአምስት አቅጣጭ መግባት ይቻላል፡ ከአዲግራት በዉቅሮ አድርጎ ከሰሜነ ወደ ደቡብ በመጓዝ ( በአሁኑ ወቅት
Posted in Ethiopian News

በወልቃይት ጠገዴ፣ ራያና ትግራይ ያለው ሁኔታ #ግርማካሳ

  እስከአሁን በተደረገው  አካባቢዉን ከሕወሃት ነጻ የማውጣት ዘመቻ ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው የትግራይ ክልል ተብሎ ይቆጠር የነበረው ግዛት ነጻ ሆናል፡፡  በዚህ ከቀጠለ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የትግራይ ሕዝብ ሙሉ ለሙሉ ከሕወሃት ግፈኛ አገዛዝ ይለቀቃል ተብሎ ነው የሚጠብቀው፡፡ ሕወሃት ስንል አካላዊዉን ሕወሃት ነው፤ እንጂ ሕወሃት እንደ መንፈስ አሁን በተለይም በኦሮሞ ብልጽግና  አመራሮች ውስጥ መስረጹን መዘንጋት የለብንም፡፡ በስሜን እነ ዶር ደብረ ጽዩን ሽንፈት ቢከናነቡም፣ እነርሱ ያመጡትን የዘር ፖለቲካ፣ የዘር ሕገ መንግስት፣ የዘር አወቃቀር እንኳን ሊቀየር ያንን ለመቀየር የታሰበ ነገር ስለመኖሩ ትንሽ እንኳን ፍንጭ ከኦሮሞ ብልጽግና አካባቢ አይታይም፡፡ የሚመስለው ከድህረ ሕወሃት በኋላ፣ የህወሃት ፖለቲካና ሌጋሲ እንደሚቀጥል ነው፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ ያገኘሁትን አንዳንድ አስደሳች፣ አሳዛኝም መረጃዎች ላቀብላችሁ ወደድኩ፡ ጦርነት አስከፊ ነገር ነው፡፡ “ወደ ጦርነት መኬድ የለበትም” ብለን ባለን አቅም ከፍተኛ ግፊት  ስናደርግ ነበር፡  ነገሮች ግፍተነው ከሄዱም፣ ጦርነትን ያላከታተ፣ ሕወሃት ላይ ብቻ ያነጣጠረ፣ ቀጪ እርምጃዎች እንዲወሰዱ፣ ሕወሃትን እንደ አሸባሪ ደርጅት እንዲፈረጅ  ነበር ስንጠይቅ የነበረው፡፡ ሆኖም ግን የፌዴራል መንግስቱ ሊሰማ አልቻለም፡፡ በተለይም ሕወሃት የፌዴራል ሕግን  ጥሶ ምርጫ እስከማድረግ ሲደርስ፣  የፌዴራል መንግስቱ ቁርጠኛ አመራር መስጠትና ሕግን ማስከበር ሲገባው፣  ዳተኝነትን  ነበር ያንጸባረቀው፡፡ እርምጃዎች ባለመውሰድ ፣ በሌላ አባባል ሕወሃት የበለጠ ጥፋት እንድታደረግ ነው የተበረታታችው፡፡ አሁን ይኸው ሕወሃት የሰሜን እዝ አባላት ላይ ጥቃት በመፈጸሟ፣  ምንም ምርጫ ስለሌለው፣ ፍላጎት ባይኖረውም ፣  የዶር አብይ መስተዳደር ወታደራዊ እርምጃዎች ለመውሰድ ተገዷል፡፡ ከሕወሃት ጋር
Posted in Ethiopian News

የዶ/ር አብይ መንግስት ግፍ እየፈጸመብኝ ቢሆንም ፣ እኔ ከአገርና ህዝብ አልበልጥም ትላለች እህታችን #ግርማካሳ

አዲስ አበባ ውስጥ አንድ ዜጋ መኪና ተገጭቶ ይሞታል፡፡ የሚኒሊክ ሆስፒታል አስክሬኑን ኦቶፕሲ አድርጎ ዜጋው የሞተበትን ምክንያትና ቀን ይመዘግባል፡፡ በነገታው አንድ ሌላ ኢትዮጵያዊ ከውጭ አገር በቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ወደ አዲስ አበባ ይገባል፡፡ ይህ ሰው አዲስ አበባ የገባበት ቀን ፓስፖርቱ ላይ ይታተማል፡፡ ኢሚግሪሼን ሲስተም ውስጥ ይመዘገባል፡፡ ከውጭ አገር የመጣው ኢትዮጵያዊ በሕወሃቶች ጥርስ ውስጥ የገባ ኢትዮጵያዊ ነበር፡፡ በዚህ ሰው ላይ የበቀል ስሜት ነበረባቸው፡፡ ይህ ሰው ተወዳጁ፣ “ፍቅር ያሸንፋል” ባዩ፣ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን፣ ቴዲ አፍሮ ነው፡፡ ያስተሰርያል በሚለው ዘፈኑ፣ “አዲስ ንጉስ እንጂ መች ለውጥ መጣ” በማለቱ ነበር ወያኔች ቂም በውጣቸው ቋጥረው የነበረው፡፡ ቴዲ አፍሮ በውጭ አገር በነበረበት ወቅት ፣ መኪና ገጭተህ ሰው ገደልክ በሚል በዉሸት ክስ፣ በዉሸት ምስክርነት ከሰሱት፡፡ “ውጭ አገር ነበርኩ” ብሎ ተናገረ፡፡ ፓስፖርቱ ላይ የታተመውን ቀን አሳየ፡፡ ከሚኒሊክ ሆስፒታል የኦቶፖሲ ውጤት ሲመጣ ቴዲ ትክክል መሆኑም ተረጋገጠ፡፡ የሚያስቀው፣ አቃቤ ሕግ የሚኒሊክ ሆስፒታል ሰነዱን እንዲቀይርና ተገጭቶ የሞተው ሰው የሞተበት ቀን እንዲለወጥ አደረገ፡፡ በዚህ መልኩም ከሁለት አመት ተኩል በላይ ቴዲ አፍሮ፣ ባላጠፋው ጥፋት፣ በውሸት ክስ ተከሶ፣ የዉሸት ምስክርነት ቀርቦበት በወህኒ ማቀቀ፡፡ አሁን ለውጥ መጣ ተባለ፡፡ መደመር፣ ፍቅር አሉን፡፡ በቴዲ አፍሮ ላይ አስቂኝ የዉሸት ድራማ ሲያቀናብሩ ከነበሩት መካከል፣ በቀዳሚነት የነበረው፣ ያኔ በአቃቤ ሕግ ጽ/ቤት የዉሸት ክስ ሰነዱን የጻፈዉና ያዘጋጀው፣ አቶ ፍቃዱ ጸጋ ቦካ ይባላል፡፡ አቶ ፍቃዱ አሁን በዶር አብይ በሚመራው የ”ለውጥ” በሚባለው መስተዳደር ትልቅ ሹመት አግኝቶ
Posted in Ethiopian News

አሁን ባለው ሁኔታ ትራምፕ የማሸነፍ እድሉ የመነመነ ነው #ግርማካሳ

የአሜሪካን ፖለቲካና ምርጫን በተመለከተ ብዙ ግንዛቤ ለሌላቸው ወገኖች የሚከተለውን አጭር ትንተና እንደሚከተው አቀርባለሁ፡፡ አሜሪካ 50 ስቴቶች አሉ፡፡ የአገሪቷ ፕሬዘዳንት የሚመረጠው በየ አራት አመቱ ነው፡፡ እጩ ተወዳዳሪዎች ምን ያህል ህዝብ ድምጽ አገኙ (popular vote) የሚለው ሳይሆን ምን ያህል ስቴቶችን አሸናፊ ሆነ፣ ምን ያህል ኤሌክቶራል ኮሌድ የሚሉት አገኘ የሚለው ነው የሚታየው፡፡ ሁሉም ስቴቶች አንድ አይነት አይደሉም፡፡ ስቴቶች እንደ ሕዝብ ብዛታቸው የተወሰነ ድምጽ ይሰጣቸዋል፡፡ Electoral college or electoral vote ይሉታል፡፡ ለምሳሌ ካሊፎርኒያ 56 ኤሌክቶራል ድምጽ አላት፣ ቴክሳስ ደግሞ 38፡፡ ዋሺንገትን ዲሲ 3 ሲኖራት፣ የጆ ባይደን አገር ዴላዌርም 3 አላት፡፡ እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም ከጆርጅ ቡሽ በላይ ብዙ ሕዝብ የመረጠው አል ጎርን ነበር፡፡ ከአራት አመት በፊት ደግሞ ብዙ ሕዝብ የመረጠው ዶናልድ ትራምፕን ሳይሆን ሂልሪ ክሊንተንን ነበር፡፡ ግን ፕሬዘዳንት የሆኑት ቡሽና ትራምፕ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በካሊፎርኒያ 10 ሚሊዮን፣ በቴክሳስ 8 ሚሊዮን፣ በፍሎሪዳ ደግሞ 6 ሚሊዮን መራጭች መረጡ እንበል፡፡ አንድ ተወዳዳሪ ከ10 ሚሊዮን የካሊፎርኒያ ነዋሪ 9ኙን ፣ ከቴክሳስ 3ቱን ፣ ከፍሎሪዳ ደግሞ 2ቱን ቢያሸነፍ በአጠቃላይ 14 ሚሊዮን የሕዝብ ድምጽ አገኘ ማለት ነው፡፡ ያኛው ተወዳዳሪ ደግሞ ከካሊፎርኒያ 1 ሚሊዮን፣ ከቴክሳስ 5 ፣ ከፍሎሪዳ ደግሞ 4 ሚሊዮን ቢያሸነፍ 10 ሚሊዮን የሕዝብ ድምጽ ያገኛል፡፡፡ ኤሌክቶራል ድምጽን ካየን ግን 10 ሚሊዮን ድምጽ ያገኘው 67 ድምጽ ሲኖረው፣ 13 ሚሊዮን የሕዝብ ድምጽ ያገኘው ግን 56 ነው የሚኖረው፡፡ አሜሪካኖች እንግዲህ ይህ አይነት አሰራር
Posted in Ethiopian News

በባልደራሶች ላይ ስለቀረበው የዉሸት የመጋረጃ ጀርባ ምስክርነት  

የመጋረጃ የዉሸት ምስክርነት በባልደራሶች ላይ ተሰማ በገለታው ዘለቀ የባልደራስ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ በእስክንድርና በስንታየሁ ላይ የቀረቡት ምስክሮች ለመሆኑ ምን ብለው መሰከሩ? __________________________________ በዛሬው እለት ሰምንት ሰአት አካባቢ እስክንድርንና ስንታየሁን ለመጎብኘት ወደ ሜከሲኮ አቀናሁ። እነ እስክንድር የታሰሩበት ቦታ ስደርስ አሰፈቅጄ ወደ ውስጥ አመራሁና እነዚያን ሁለት አንበሶች አየሁ….እሰክንድርንና ስንታየሁን…. ከመጋረጃ በስተጀርባ ሰለተባለው ምስክርነትና ስለዝግ ችሎቱ አጫወቱኝ። እነ እስክንድር ሲያጫውቱኝ የቀረቡትን ምስክሮች በሙሉ አናውቃቸውም አሉ። በመጋረጃ ውስጥ ተደብቆ የሚመሰክረው ሰዉ በድምፅ ማጉያ ነበር ሲናገር የነበረው። ነገር ግን የዚህን ሰው ድምጹን አናውቀውም ድምጹ እንግዳ ድምጽ ነው ብለዋል እነ እስክንድር ። ለመሆኑ ምን ሲሉ መሰከሩ የሚለው ነገር ነበር የእኔ ግርምት የተሞላበት ጥያቄ። እስክንድርና ስንታየሁ ሲያጫውቱኝ ሁሉም ምስክሮች ተመሳሳይ ነገር ነበር የሚናገሩት ። ሁሉም ምስክሮች የሚሉት እነ እስክንድር ቄሮ አብያተክርስቲያናትን ሊያጠቃ ነውና ቤተክርስቲያንን ጠብቁ ተከላከሉ ብለዋል የሚል ነው። ሁሉም ምስክሮች የደገሙት ነገር ይህንን ነው። በቤተ ክርስቲያን ላይ ቄሮ ጥቃት ሊፈጽም ነውና ቤተክርስቲያናችሁን ተከላከሉ ብሎ እስክንድር 500,000 ብር በጀት ይዞ እንደነበር እስክንድር ራሱ ነግሮናል የሚል አሳዛኝ ውሸትም ተጨምሮበት ነበር አሉ። ስንታየሁና እስክንድር የምስክሮቹን ድራማ ካጫወቱኝ በሁዋላ ነገ ደግሞ ሌሎች ምሰከሮች እንደሚመሰከሩባቸዉና የሚሆነውን እንደማያውቁ ገልጸውልኛል። ነገ ደግሞ ሌሎች ምስክሮች ይመሰከሩባቸዋል። እነ አስክንድር የፍርድ ቤት ድራማውን ዝም ብለው ከማዳመጥ ውጭ የሚናገሩት የለም። ጠበቃም የለም መናገርም የለም። ስለምስክሮቹ አውርተን ስንጨርስ ስለጤናቸው ጠየኳቸው። ስንታየሁ አሞታል። የኩላሊት ህመም ነው። የጣቢያው ዶክተር
Posted in Ethiopian News

ለነሻሸመኔና ተጎጂዎች ‘ማርሻል ፕላን” ያስፈልጋል #ግርማካሳ

ዶር አብይ አህመድ አገራችንን ለማስተዋወቅ፣ የተለያዩ የቱሪዝም ቦታዎችን ለማስፋፋት፣ ሸገርን ከተማችንን ለማስዋብ፣ አገራችን ያለው deforestation ለመቀነስ ችግኞች እንዲተክሉ ለማድረግ የሚያደረጉት እንቅስቃሴዎች የሚመሰገኑ ናቸው፡፡ መልካም ተግባራት ናቸው፡፡ በስራዎቹ የማይደሰት፣ የሚቃወም ጤናማ አይምሮ ያለው ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ ሆኖም ግን ለሁሉም ነገር ጊዜና ቦታ አለው፡፡ ብዙ ነገሮችን ማድረግ ጥሩ ቢሆንም ከብዙዎች በጣም ቅድሚያ ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ትኩረት መደረግ አለበት፡፡ ያ ብቻ አይደለም እነዚህን ስራዎች፣ ምን አልባትም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሌሎች አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ እንዳያተኩሩ አድርጓቸው ከሆነም፣ በሌሎች እንዲሰሩ ማድረግም ይቻላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአገራችን አንደኛ ትልቁ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ በኦሮሞ ክልል በተፈጠረው የዘር ማጥፋት ወንጀል የተጎዱ ወገኖችን መካስ፣ ማቋቋምና በአይምሮና በስነልቦንና እንዲፈወሱ ማድረግ ነው፡፡ ከዚህ የሚበልጥ አንገብጋቢ አጀንዳ አሁን አለ ብዬ አላስብም፡፡ ይሄን ጉዳይ በተመለከተ ምን ይደረግ ? በመጀመሪያ የሆነውን መካድና መቀባባት አያስፈለግም፡፡ በምስራቅ ኦሮሞ ክልል የነበረው የዝውር ማጥፋት ወንጀል ነው፡፡ ወንጀሉን በስሙ መጥራት መቻል አለብን፡፡ ከዘር ማትፋት ወንጀል በተጨማሪ በኃይማኖትም ጥቃት ተፈጽሟል፡፡ በርካታ ኦሮቶዶስክ ክርስቲያኖች ክርስቲያን ስለሆኑ ብቻ ተገድለዋል፡፡ በመቀጠል አራት ቁልፍ ስራዎች መደረግ አለባቸው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ሁለቱ የአጭር ጊዜ ፣ ሁለቱ ደግሞ የረጅም ጊዜ ዘለቂታዊ መፍትሄ የሚያመጡ እርምጃዎች ናቸው፡፡ እርምጃ አንድ ፡ ለነ ሻሸምኔ ማርሻል ፕላን ያስፈልጋል =========================== ከሁለተኛ የአለም ጦርነት በኋላ ወድማ በነበረችው ጀርመን የሆነውን እንደ ምሳሌ መወስድ እንችላለን፡፡ ጀርመን እንደወደመች አልቀጠለችም፡፡ ጀርመንን ያወደሟት አሚሪካኖች ፣ ሰላም ከወረደና የሂትለር
Posted in Ethiopian News

ከነበረከት ስሞንና አሁን ካሉ የብአዴን አመራሮች ማን ይሻላል ? ግርማ ካሳ

ከነበረከት ስሞንና አሁን ካሉ የብአዴን አመራሮች ማን ይሻላል ? ግርማ ካሳ – በቢኔሻንጉል በጉባ ወረዳ ዘር ተለይቶ ሕጻናት ሳይቀሩ በግፍና በጭካኔ ተገድለዋል፡፡ አርሶ አደሮች፣ የእርሻ ሥራቸው በማከናወን ላይ የነበሩ፣ አማራዎች፡፡ እስከነ ልጆቻቸው፡፡ – በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገር ፣ “ጥቃቱን የፈጸመው ኃይል በአካባቢው የብሔር ግጭት የመቀስቀስ ዓላማ በመያዝ ተደጋጋሚ የጥፋት ሙከራ ሲያደርግ የቆየ ነው። ታጣቂ ኃይሉ በህውሓት የስልጠናና የገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት ነው፡፡ ህውሓት ሀገርን ለማተራመስ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ አካል ነው” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ – ብአዴኖች/አዴፓዎች ምን አለ ሕወሃት ላይ ማሳበብ ቢያቆሙ ?????? አሁን አሁንማ ኮሮናን ያመጣው ሕወሃት ነው ሊሉን እንደሚችሉ መጠበቅ አለብን፡፡ – ችግሩ ያለው የቤኔሻንጉል ክልል የብልጽግና ፓርቲ አመራርና የክልል መንግስቱ ላይ ነው፡፡ ክልሉ ወደ 45% አካባቢ የሚሆኑት አማራና ኦሮሞ ናቸው፡፡ ከበርታዎች ቀጥሎ ትልቁ ማህበረሰብ አማራው ነው፡፡ ሆኖም አማራዎችና ኦሮሞዎች በክልሉ ሕገ መንግስቱ መሰረት፣ በክልሉ መጤና ሰፋሪ ተደርገው ነው የሚቆጠሩት፡፡”ሌሎች ብሄር ብሄረሰብ ሕዝቦች(አማራውና ኦሮሞዉችን ማለታቸው በዋናነት) በክልሉ እንደሚኖሩ ቢታወቅም፣ የክልሉ ባለቤቶች የሸናሽ፣ ማኦ፣ ኮሞ፣ በርታና ጉምዝ ብሄረሰቦች ናቸው” ነው የሚለው የቤነሻንጉል ክልል ሕገ መንግስት፡፡ ያ ማለት በዚያ የሚኖሩ አማራዎችና ኦሮሞዎች የክልሉ ባለቤቶች አይደሉም፡፡ በክልሉ አመራር ውስጥም አይካተቱም፡፡ በክልሉ ውክልና የላቸውም፡፡ – ስለዚህ በክልሉ ያሉ ጽንፈኞች ፣ “የኛ ክልል ነው፣ ሌሎች ወራሪዎች ናቸው” የሚል ስሜት ነው ውስጣቸው ያለው፡፡ “አማራዎችና ኦሮሞዎች የኛ አገር
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ብልጽግና ፓርቲ ለመቀየር የሚያመነታበት በኦሮሞ ክልል ያለው አስከፊ ገጽታ #ግርማካሳ

ኢትዮጵያ ውስጥ እስከ አሁን በኢሕአዴግ መንግስት ሁለት የህዝብ ቆጠራዎች ተደርገዋል፡፡ የመጀመሪያው የተደረገው በ1986 ዓ/ም ሲሆን ሁለተኛው የተደረገው በ1999 ዓ/ም ነው፡፡ እነዚህ የሕዝብ ቆጠራዎች የራሳቸው ችግሮች እንደነበራቸው ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ሆኖም እስከነ ችግሮቻቸው፣ ያሉት ኦፊሴላዊ ሪፖርቶች እነርሱ ብቻ በመሆናቸው፣ እርሱን ተጠቅመን ነው መነጋገር የምንችለው፡፡ በ1999ኙ ሪፖርት፣ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በመለየት በከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎችን ቁጥር አልተዘረዘረም፡፡ ስለሆነም በከተሞች ያለው ስብጥር ለማየት የ1986ቱ ሪፖርት ተብቻ ለማለየት እንገደዳለን፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የተለወጡ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ በተለይም በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ከተሞች የአማርኛ ተናጋሪው ማህበረሰብ ቁጥር በብዙ እጥፍ የጨመረ ስለመሆኑ አዲስ አበባና አዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖር ሰው ያጣዋል ብዬ አላስብም፡፡ በዚህ ሪፖርት 17 ከተሞች ተመርጠዋል፡፡ ከነዚህ መካከል ፡ በአምቦ፣ በመቱና በጊምቢ ኦሮምኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የሆኑ ነዋሪዎች ከግማሽ በላይ ናቸው፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን በአምቦ ከ42% በላይ፣ በጊምቢ ደግሞ ከ39%፡ ኦሮምኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው አይደለም፡፡ በ 5 ከተሞች፣ ጂማ፣ ወሊሶ፣ ፍቼ፣ አሰበ ተፈሪና ሰበታ ኦሮምኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የሆኑ ከአንድ ሶስተኛ በታች ሲሆኑ በ 9 ከተሞች ከአንድ አራተኛ በታች ናቸው፡፡ሰሞኑን የጽንፈኞች ስለባ በሆነችው በአርሲ ኔጌሊ 3% ብቻ ናቸው፡፡ በሻሸመኔ ደግሞ 13%፡ ከአምቦ፣ መቱና ጊምቢ በስተቀር በሁሉም የተጠቀሱ ከተሞች አማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የሆኑ ከግማሽ በላይ ናቸው፡፡ በአስር ከተሞች ፣ ናዝሬት፣ ጂማ፣ ሻሸመኔ፣ ደብረዘይት፣ አሰላ፣ ወሊሶ፣ ሞጆ፣ ፍቼ፣ መተሃራና ወለንጭቲ አማርኛ ተናጋሪዎች ከ2/3ኛ በላይ ናቸው፡፡ እነዚህ፣ አማርኛ ተናጋሪዎች በብዛት፣
Posted in Ethiopian News

መክሸፍ እንደ ኦሮሚያ፤ የከሸፈ ክልል እና የምስኪኖች ሰቆቃ – ጠበቃውና የአርሲ ኔጌሌው ልጅ ተክሌ

መክሸፍ እንደኦሮሚያ፤ የከሸፈ ክልል እና የምስኪኖች ሰቆቃ ተtክለሚካኤል አበበ፤ ቶሮንቶ፤ ካናዳ፤ ሀምሌ፤ 2012/2020 እንደመግቢያ፤ “ነፍጠኛው ተነሳ፤ ሞቶ፤ ርቆ ከተቀበረበት፤” ይህ ጽሁፍ፤ ቀደም ሲል የነገሌ አርሲው ተወላጅ፤ ወንደወሰን ተሾመ ከጻፈው ጽሁፍ የቀጠለና በዘዚያ ጽሁፍ የተነሳሳ ነው፡፡ የሀጫሉን ሞት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የደረሰውን ጥፋት ሳስብ፤ በእውኑ የኦሮሚያ መንግስት፤ ክልል መምራት ይችላል ወይንስ ከሸፈ የሚል ጥያቄና ክርክር አጭሮብኛል፡፡ የኦሮሞ ልሂቃን፤ ክልል አሉ፤ ክልል አገኙ፡፡ ቋንቋ አሉ፤ እሱንም አገኙ፡፡ በአገራችን፤ አባቶቻችንና እናቶቻችን በገነቡት አገር ላይ ባይተዋርና ባእዶች ተደረግን፡፡ በቱርጁማን መኖርን፤ በአስተርጓሚ መነገድን፤ መዳኘትን ለመድን፡፡ እንደሚባለው፤ አያት ቅድመአያቶቻችን፤ ሰፋሪዎች፤ ቅኝ ገዢዎች፤ ጡት ቆራጮች ቢሆኑ እንኳን፤ በእውኑ እኛ የአያቶቻችን የልጅ ልጆች የምንሳደድበት አመክንዮም ሞራልም እንደሌለ ጠፍቶን አይደለም፡፡ ግን ይሁን አልን፡፡ ተሸንፈን፤ ይሄን ብለንም ግን፤ ነፍጠኛውን ላይመለስ አርቀን ቀብረነዋል ካሉን፤ ከ30 አመታት በኋላም ያፈራነው፤ ክልላቸውን በሀላፊነትና በብቃት የሚመሩ መሪዎችን ሳይሆን፤ ዜጎችን የሚገድሉ፤ የሚያስገድሉ፤ ንብረት የሚያቃጥሉ፤ የሚያስቃጥሉ፤ ሽብርተኞችን ነው፡፡ ጀግኖችን አይደለም፡፡ በኦሮሚያ ውስጥ ለደረሰው ጥፋት፤ የፌደራሉም የክልሉም መንግስት ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ካለፈው ስንቀጥል፤ ኦሮሞ ደግ፤ ቅን፤ በጦርነት እንኳን የማረካቸውን እንደልጅ የሚያሳድግ እንደ ሚስት የሚጠብቅ፤ አደንና ግድያ ለይቶ የሚያውቅ ህዝብ ነው፡፡ ኦሮሞ፤ ጫካ እንጂ ከተማ አደን አይወጣም፡፡ ኦሮሞ ሰው ዘቅዝቆ የሚሰቅልም አይደለም፡፡ እነዚህ ነገሌና ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞ ውስጥ፤ ሰው በገጀራ የቆራረጡ፤ ሰው ዝቅዝቀው የሰቀሉና ከግዳያቸው አጠገብ ፎቶ የሚነሱ ሰዎች፤ ይሄን ሰው ማረድና መቆራረጥ ከየት አመጡት? የኢትዮጵያ ባህል ነው እንዴ?
Posted in Ethiopian News

የኢሊባቡር ኦሮሞዎች #ግርማካሳ

የኢሊባቡር ኦሮሞዎች #ግርማካሳ በተለይም በሃረርጌ፣ ባሌና አርሲ ጽንፈኛ ኦሮሞዎች ያደረጉት ሰቆቃ የብዙዎችን ልብ እያደማ ነው። እጅግ በጣም። እነዚህ ጽንፈኞች አብዛኛዉን የኦሮሞ ማህበረሰብ የማይወክሉ ናቸው። በአንድ አካባቢ ያሉ እነዚህ ጽንፈኞች በሰሩት ስራ፣ ኦሮሞዎችን በተመለከተ የብዙ ኢትዮዮጵያውያን አይምሮ ሊቆሽሽ እንደሚችል ይገባኛል። ሆኖም ግን አንደኛ የኦሮሞ ማህበረሰብ፣ በሰፊ ግዛት የሚኖር መሆኑን መርሳት የለብንም። ሁለተኛ ከ21 የኦሮሞ ክልል ዞኖች አሰቃቂ እልቂትና ጄኖሳይድ የነበረው በ6ቱ ዞኖች ነው።በኦሮሞ ክልል ካሉ ወደ 300 ወረዳዎች 50 አካባቢ በሚሆኑት። ስለዚህ ችግር ፈጣሪዎቹ ጥቂቶች ናቸው። ችግር ያለባቸው አካባቢዎች ጥቂት አካባቢዎች ናቸው። ጥቂቶች ባደረጉት ደግሞ ሁሉንም አንድ አድርገን ማየት የለብንም። እንደሚታወቀው የሸዋ ኦሮሞዎችም ሳይቀሩ፣ “አማራ” ተብለው ብዙ እልቂት ተፈጽሞባቸዋል። አርሲ፣ ባሌ፣ ሃረርጌ ላሉ፣  ክርስቲያን የሆነ ብዙ ጊዜ  “አማራ” ነው የሚባለው። ስለዚህ ክርስቲያን የሸዋ ኦሮሞዎች  “አማራ” ተብለው የዘር ተኮር እልቂት ሰለባ መሆናቸውን መርሳት የለብንም። ድሮ ጨቦና ጉራጌ፣ ሃይቆችና ቡታጅራ በሚባሉ ቦታዎች ከጉራጌ ጋር፣ በሰላሌ፣ ጅባትና ሜጫ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከአማራ ጋር የሸዋ ኦሮሞ ተዋልዷል።  ለዚህ ነው ከሸዋ ዉጭ ያሉ የኦሮሞ ብሄረተኞች የሸዋ ኦሮሞን አይምኑም። የሸዋ ኦሮሞዎች “ዲቃላ” ናቸው ነው የሚሉት። ያ ብቻ አይደለም የሸዋ ኦሮሞ በኢትዮጵያዊነት ቀልድ ስለሌለው በጽንፈኞች ብዙ አይወደድም።  የሸዋ ኦሮሞ የሸዋ ኦሮሞ ነው። ከሽዋ አልፈህስ ? የሚል ጥያቄ ቢነሳ የምሄደው ወደ ምእራብ፣  ሌላኛው ሸዋ ወደምላት  ኢሊባቡር ነው። ስለ ኢሊባቡር አንድ ሁለት ነገር ልበላችሁ። ኢሊባቡር በፊት ራሷን የቻለች ክፍለ ሃገር
Posted in Ethiopian News

ሻሸመኔ ስትወድም መንግስት የት ነበር ? #ግርማካሳ

ሻሸመኔ ስትወድም መንግስት የት ነበር ? #ግርማካሳ ሻሸመኔ ከተማ እንደ አሌፖ ሲሪያ መውደሟን እይተናል፡፡ ሻሸመኔ የሻሼ ቤት ማለት ነው፡፡ በንግድ በተለያዩ ምክንያት ወ/ሮ ሻሼ የሚባሉ ጠላ ቤት የነበራቸው እናት ነበሩ፡፡ እርሳቸው ጋር፣ ከመንገዳቸው ሰዎች አረፍ ይሉ ስለነበረ፣ ጠላ ለመጠጣት፣ ቦታው የሻሼ ቤት ወይንም ሻሸመኔ ተባለ፡፡ አንድ የሻሸመኔ ሰው እንዳጫወተኝ፡፡ ሻሸመኔ የምእራብ አርሲ ዞን ዋና ከተማ ብቻ ሳይሆን ትልቅ የንግድ ማዕከል ነበረች፡፡ በሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሰረት፣ በሕዝብ ብዛት ፣ በኦሮሞ ክልል ካሉ ከተሞች ከናዝሬትና ከጂማ ቀጥሎ በሶስተኛነት የምትቀመጥ ናት፡፡ ከነ ነቀምቴ፣ አሰላና መቱ ሁሉ የትናየት የምትበልጥ፡፡ በሻሸመኔ ዉድመት ሲፈጸም በከተማዋ ከ500 በላይ የኦሮሞ ክልል ፖሊሶች፣ የአንድ የመከላከያ ደቡብ ዕዝ ብርጌድ ወታደራዊ ካምፕ ነበር፡፡ በአንድ ብርጌድ ከ1500 እስከ 3000 ወታደሮች ይኖራሉ፡፡ በአጠቃላይ  ከ2000 እስከ 3500 የታጠቁ የፖሊስና የመከላከያ አባላት ነበሩ፡፡ ከከተማዋ 27 ኪሎሚትር ርቆ በሚገኘው ወንዶ ጢቆ በሚባል ቦታ የአየር ወለድ ትልቅ ካምፕ አለ፡፡ በካምፑ አዛዥ የነበሩት ኮሎኔል ተክለብርሃን ገብረመድህን ሲሆኑ የርሳቸው አለቃ ደግሞ ሜጀር ጀነራል ሹማ አብደታ ናቸው፡፡ ከሻሸመኔ 7 ኪሎሚትር ብቻ ርቃ በምትገኘው በደቡብ ክልል ባለችው ቶጋ ደግሞ በጀነራል ሰለሞን የሚመራ ሌላ የመከላከያ ጦር አለ፡፡ በአጠቃላይ በሻሸመኔ፣ በቶጋና በወንዶ ጢቆ ከ5000 እስከ 9500 ታጣቂዎች ነበሩ፡፡ ሻሸመኔ ከዚህ በፊት ሁለት አሳዛኝና አንገት አስደፊ ክስተቶችን አስተናግዳለች፡፡ የመጀመሪያው ጃዋር መሐመድ በሻሸመኔ ህዝባዊ ስብሰባ ሊያደርግ አስቦ በነበረበት ወቅት፣ ከሻሸመኔ ዙሪያ ደጋፊዎቹ መጥተው፣ በከተማዋ ፍራፍሬ
Posted in Ethiopian News

የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ለናዝሬት/አዳማ #ግርማካሳ

በናዝሬት/አዳማ ባለፈው የሕዝብ ቆጠራ፣ 74% የሚሆኑት ነዋሪዎች ኦሮምኛ ተናጋሪ አይደሉም። ሆኖም በከተማዋ አስተዳደር ፣ በቀበሌዎች የሚቀጠሩት ኦሮምኛ ተናጋሪ ኦሮሞዎች ብቻ ናቸው። የከተማዎ ፓሊስ ሆነው የሚሰሩት አብዛኞቹ የአዳማ/ናዝሬት ተወላጆች አይደሉም፡፡ ከሌላ ቦታ የመጡ ናቸው፡፡ ኦሮሞዎችም ኦሮምኛ የማይናገሩ ከሆነ በከተማዋ ቦታ የላቸውም፡፡ አቶ አብርሃም አዶሌ፣ አቶ በከር ሻሌ፣ አቶ ሲሳይ ነጋሽ፣ አቶ ጉቱ፣ አቶ ጀማል አባስ፣ አቶ ሀብታሙ ሃይለሚካኤል፣ ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣ አቶ አሰገድ ጌታቸው …ሁሉም የአዳማ ከተማ ከንቲባ ሆነው የሰሩት ኦሮምኛ ተናጋሪ ኦሮሞዎች ናቸው። አንዳቸውም በአዳማ ከተማ ሕዝብ አልተመረጡም። በቀጥታ በኦሮሞ ክልል ርእስ መስተዳደሮች ነው የተሾሙት። የአሁኑ የአዳማ ከንቲባ አቶ አስገድ ጌታቸውና ከአቶ አሰግድ በፊት የነበሩት ወ/ሮ አዳነች አበቤን የሾሙት አቶ ለማ መገርሳ ነበሩ። ከነዚህ ከንቲባዎች ደግሞ ጥቅት የማይባሉ ቢያንስ ወደ ስድስት ከንቲባዎች በሙስና በዘረፋ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል። አቶ ጉቱ፣ አቶ ሲሳይ ነጋሽን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። የናዝሬት/አዳማ አብዛኛው ኦሮምኛ የማይናገር ነዋሪ ከከተማዋ መስተዳደር መንግስታዊ አገልግሎት የማግኘት ችግር አለበት። ጉዳዮችን ለማስፈጸም ሰነዶችን ፣ ፎርሞችን ለአስተርጓሚ ከፍሎ አስተርጉሞ ነው የሚያቀርበው፡፡ ደብዳቤዎችን ወደ ላቲን/ቁቤ ለማስቀየር ለተርጓሚዎች በገጽ መቶ፣ ሁለት መቶ ብር ነው የሚክፈለው። በአጭሩ አነጋገር የናዝሬት/አዳማ ከተማ ሕዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት የለውም።አንድ በናዝሬት የተወለደ፣ እናቱ አባቱ በናዝሬት የተወለዱ ኦሮምኛ የማይናገር የናዝሬት ነዋሪ ካለው መብት ይልቅ፣ ከአርሲና ወለጋ ከመጡ ስድስት ወራት የሆናቸው ኦሮምኛ ተናጋሪዎች የበለጠ መብት አላቸው። ይሄም በአዳማ ያለው አሰራር አፓርታይዳዊ አሰራር መሆኑን
Posted in Ethiopian News

ጌዴኦ ተፈናቀለ፣ አሁን ደግሞ እየተቆመረበት ነው፣ ማን ለጌዴኦ ይጩህ ? #ግርማካሳ

(ከዚህ በታች ያሉት አሓዞች የተገኙት ከህዝብ ቆጠራ ሪፖርትና ከተባበሩት መንግስታት ነው፡) ከ13 አመት በፊት በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ 729955 ጌዴኦዎች እንዳሉ ተገልጿል፡፡ ከነዚህ ውስጥ 731871 ወይም 74.8 % በደቡብ ክልል፣ 729955 ወይም 73% በጌዴኦ ዞን ውስጥ ይኖራሉ፡፡ 19% የሚሆኑት ደግሞ፣ በኦሮሞ ክልል የጊዴኦ ዞንን በሚያዋስኑ፣ በገለና፣ በአባያ፣ በቡሌ ሆራ፣ በቀርቻ፣ በሃምቤላ ዋሜናና በኡራጋ ወረዳዎች ተካተዋል፡፡ በኦሮሞ ክልል የሚኖሩ ጌዴኦዎች በተለይም ኦህዴድ አራት ኪሎን ከተቆናጠጠ በኋላ፣ በኦሮሞ ጽንፈኞች ትልቅ ችግርና ሰቆቃ እንደደረሰባቸው በስፋት አለም የሚያወቀው ጉዳይ ነው፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞችን ጉዳይ ባወጣው መረጃ፣ በሁለት የስደተኞች ካምፕ ከ600 በላይ አብዛኞቹ ጌዴኦዎች መፈናቀላቸውን ይገልጻል፡፡ ከቀርጫ ወረዳ 202819፣ ከከቡሌ ሆራ፣ ገለናና አባያ ወረዳዎች 252427 ፣ ከሃምቤላ ዋሜናና ኡራጋ ወርዳዎች 1505275፣ በአጠቃላይ 620747 ዜጎች፡፡ ከጌዴኦ ዞን በስተ ምእራብና ደቡብ ያሉት የቡሌ ሆራ፣ ገላናና አባያ ወረዳዎችን ብንወስድ፣ ባለፈው የሕዝብ ቆጠራ መሰረት 438394 ዜጎችን ይኖሩባቸው ነበር፡፡ ቁጥራቸው በ36% አድጓል ብለን ብንወስድ አሁን የሕዝብ ብዛታቸው 596216 ይደርሳል ብለን ልንገምት እንችላለን፡፡ እንግዲህ ከነዚህ ወረዳዎች 252427 ወይንም 42% ተፈናቅለው ነበር፡፡ ከጌዴኦ ዞን በስተ ምስራቅ ያለው የቀርቻ ወረዳን ብንወስድ በሕዝብ ቆጠራው 227198 ነዋሪ የነበረው ሲሆን በ36% አድርጓል ብንል አሁን የሕዝቡ ቁጥር 308989 ይደርሳል፡፡ ከዚህ ወረዳ 202819 ወይንም 66% ተፈናቅለው ነበር፡፡ ከቀርቻ ወረዳ ወደ ሰሜን ስንሄድ፣ አሁን ከጊዴኦ ዞን በስተ ምስራቅ ያሉትን የሃምቤላ ዋሜናና ኡራጋ ወርዳዎችን ብንወስድ በሕዝብ ቆጠራው 281036 ነዋሪዎች የነበራቸው ሲሆን
Posted in Ethiopian News

“ፈንቅል” በሚል ስም ለፍትህ የሚኦደረግ ጸረ-ሕወሃት ን ትግራይ እያጥለቀልቀ ነው #ግርማካሳ

Updates from Tigray “ፈንቅል” በሚል ስም ለፍትህ የሚኦደረግ ጸረ-ሕወሃት ን ትግራይ እያጥለቀልቀ ነው #ግርማካሳ ሕወሃትና የክልሉ መንግስት በአንድ በኩል የፌዴራል መንግስትን ከሚቆጣጠረውና በዶር አብይ አህመድ ከሚመራው የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ውዝግብ ውስጥ መግባቲ ይታወቃል። በድርጅቱ ውስጥ ከፍተኛ ልዩነቶችን መከፋፈለኦች እንዳሉ እየተነገረ ነው። ሆኖፕም ኅወሃት በውስጡ ካሉ መከፋፈሎችና ከፌዲርል መንግስቱ ጋር ካለው ችግር በባሰ ሁኔታ ግን ለሕልውና ትልቅ አደጋ እየፈጠረበት ያለው በትግራይ የተነሳው መጠነ ሰፊ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ናቸው። በተለይም በወጣቱ ድጋፍ እንደሌለው የሚነገርለት ኅወሃት በየወረዳውና በየቀበሌው ባሰማራቸው ታጣቂዎቹና ካድሬዎቹ፣ የክልል መንግስት እንድመሆኑም ባለው የመንግስት መዋቀር ላይ በተቀመጡ ሃላፊዎቹ አማካኝነት ህዝቡብ በማስፈራራት፣ በማፈን ፣ በጉልበትና በጫና የኅዝብን መስረታዊ የፍትህ፣ የሰላምና የልማት ጥያቄዎችን ለመጨፍለቅ ደፋ ቀና እያለ ነው። በዚህ ሳምንት ውስጥ ብቻ በትግራይ ያሉ ብርካታ አውራጃዎችና ከተማዎች ተቃውሞን ሲያስተናግዱ ነበር። ሌላው ቢቀር ኅወሃት ተወለድችበት በሚባለ በሬ/ደደቢት እኗን ሳይቀር ጸረ-ሕወሃት ተቃውሞ ሲሰማ ነበር። ተቃውሞኢ ሲደረግባቸው ከነበሩት ጥቂቶቹን እንደሚከተው ቀርበዋል፡ እንደርታ/መቀሌ የትግራይን ሕዝብ የማይወክሉ ለጥቅማቸው የቆሙ የሕወሃት ሰዎች የሚያደርሱን ግፍነ በደል በመቃወም በተነሳው ተቃውሞ የክልል መንግስትይ ታጣቄዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ተኩስ ከፍተዋል። ሁለተ የመቀሌ ወጣቶች ሲሞቱ ብዙዎች ቆስለዋል። እንደርታ/ወጀረት “በተፈቀደ የወረዳነት ጥያቄ ህዝብ መሃል ገብታቹ ልዩነት ለመፍጠርና ወደ ኋላ ለመመለስ እያካሄዳቹ ያላቹ ተንኮል ኣቁሙ” በማለት ዛሬ ቅዳሜ ተቃውመው ኣሰምተዋል። ህወሓት የተመለሰ ጥያቄ ወደ ስራ እንዳይገባ በህዝቡ መሃል ገብታ እያጣላች መሆንዋ በመንቃቱ ተግባርዋ ኣምርሮ እየተቃወመ ይገኛል። በተመሳሳይ
Posted in Ethiopian News

ገበሬና ሐኪምን ሕግ ተርጉሙ ማለት አማርኛ የማይችልን በአማርኛ አስተርጉም ማለት ነው #ግርማካሳ

በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት፣ አንቀጽ 80፣ በሕገ መንግስቱ ዙሪያ ትርጓሜ የሚሰጠው፣ ፍርድ ቤት ሳይሆን የፊዴሬሽን ምክር ቤት የሚባለው ነው፡፡ “የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል ጉዳዮች ላይ የበላይና የመጨረሻ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል ” ነው የሚለው አንቀጹ።፡ብዙዎቻችን የፌዴሬሽን ምክር ቤትን በተመለከተ ብዙ የመረጃ ክፍተቶች አሉብን፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወሰን፣ አከላለልንና የማንነት ጉዳዮችን የሚመለከት ኮሚሽን አቋቁሞ በነበረበት ወቅት፣ የዚህን ኮሚሽን መቋቋምን አንዳንድ ወገኖች “ሕገ መንግስቱን የጣሰ ነው፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ሃላፊነት የሚጋፋ ነው” የሚል ክስ አቅርበው ነበር፡፡ ያን ተከትሎ፣ ከአንድ አመት በፊት ስለፌዴሬሽን ምክር ቤት አንዲት ጦማር አስነብቤ ነበር፡፡ “በፌዴሬሽን ምክር ቤት ዙሪያ ያሉ ሕገ መንግስታዊ ግድፈቶች!!!” በሚል ረእስ ስር፡፡ ስሞኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ መጪውን ምርጫ በማራዘም የሚፈጠረውን የመንግስት ስልጣን ክፍተት በተመለከተ እንደገና የመነጋገሪያ አጀንዳ እየሆነ ነው፡፡ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 58 መሰረት መደረግ ያለበት ምርጫ ማድረግ እንደማይቻል ምርጫ ቦርድ አስታወቀ ፡፡ ከዚህም የተነሳ አሁን ያለው የመንግስት እድሜ በመስከረም ወር ላይ ሲያበቃ ምን ይሁን ለሚለው ፣ ገዢው የብልጽግና ፓርቲ አራት አማራጮችን አቀረበ፡፡ አንደኛው አማራጭ፣ የሕገ መንግስቱን አንቀጽ 60 በመጥቀስ ፓርላማዉን መስከረም ላይ በትኖ ለስድስት ወር ምርጫውን ማራዘም ነው፡፡ ሁለተኛ አማራጭ አንቀጽ 93ን በመጥቀስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ሲሆን ሶስተኛ አማራጭ የሕገ መንግስት ማሻሻያዎችን ማድረግ ነው፡፡ አራተኛው ለሕገ መንግስት ጉዳዮች ተርጓሚ ለሆነው የፊዴሬሽን ምክር ቤት ጉዳዩን ማስተላለፍ ነው። ገዢው የብልጽግና ፓርቲ ከተወሰኑ ተቃዋሚዎች ጋር፣
Posted in Ethiopian News

በሽግግሩ ዙሪያ ላለው ውዝግብ አስታራቂ የመፍትሄ ሐሳብ#ግርማካሳ

  በፕሮፌሰር በየነ የሚመራው ፣ ኢሶዴፓ፣ ኢዜማ፣ አብን ፣ በአቶ ዳዎድ የሚመራው ኦነግን፣ የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባርን ፣ የሞጫ ና የአገው ሸንጎን ያቀፈው ትብብር፣ ዶር አብይ አህመድ ምርጫው እስኪደረግ ድረስ ቢቆዩ ችግር እንደሌለባቸው ገለጸዋል፡፡ ሲደመሩ ሰባት ደርጅቶች፡፡ እነዚህ ድርጅቶች የዶር አብይ መስተዳደር እንዲቀጥል ቢጠይቁም አንዳንዶቹ መጭው ምርጫ ሰላማዊ ፍታሃዊን ነጻ እንዲሆኑ የሚረዱ ክሚሽኖች እንዲቋቋሙ፣ ሌሎች ደግሞ ችግሩ ሕግ መንግስቱ ራሱ ስለሆነ ሕግ መንግስቱን የማሻሻል ሂደቶች እንዲጀመሩ ጠይቀዋል። በአንጻሩ ኢዴፓና ሕብር  የሽግግር መንግስት፣ አረና/ኦፌኮ/ሲሃንና መኢአድ የብሄራዊ አንድነት መንግስት፣ ባልደራስ ደግሞ የባለሞያዎች መንግስት ይቋቋም የሚል አቋም ይዘዋል፡፡በአጠቃልይ ስድስት ድርጅቶች፡፡ ኢዴፓዎች ምንም እንኳን የሽግግር መንግስት ይቋቋም የሚል አቋም ቢይዙም፣ በሽግግሩ መንግስት ግን ዶር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው እንዲቀጥሉ ነው ፍላጎት ያላቸው፡፡ “እኛ ሀሳባችን ይሄ ነው፤ ያ ማለት ግን የሌሎችን አንቀበልም ማለት አይደለም፣ እንነጋገር” ሲሉ ፣ በገዢው ፓርቲና በተቃዋሚዎች መካከል ንግግር እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ከዚህ የምንማረው የኢዴፓም አቋም በተወሰነ መልኩ ከነአብንና ኢዜማ ጋር የሚመሳሰል መሆኑ ነው፡፡ ባልደራስ ያቀረበው ሐሳብ፣ በመርህ ደረጃ የሚስብ ቢመስልም፣ተግባራዊ ሊሆን የመቻሉ ጉዳይ ላይ ግን አጠያያቂ ነው፡፡በርግጥ ኢትዮጵያ፣  ለአገር አይደለም ለአህጉር ብሎም ለአለም የሚበቁ ምህራን ያሏት አገር ናት፡፡ የምሁር ድሃ አይደለችም፡፡ አገር በበማለሞያዎች ብትመራ ደግሞ የበለጠ ታድጋለች፡፡ ሆኖም ግን ይሄን የባለሞያዎች መንግስት በአጭር ጊዜ በማሰባሰቡ አንጻር ያለውን ዉስብስበነት በማየት የባልደራስ ሐሳብ ተግብራዊ የመሆን እድሉ በጣም ትንሽ ነው፡፡በመሆኑም ባልደራስ የአቋም ማሸጋሸግ
Posted in Ethiopian News

ኢትዮጵያ፣ ሉላዊ ካፒታሊዝም የሚያተራምሳት ሀገር? የነ ኢንጂነር  ዳንኤል ጉዳይ (ያሬድ ጥበቡ)

ኢትዮጵያ፣ ሉላዊ ካፒታሊዝም የሚያተራምሳት ሀገር? የነ ኢንጂነር  ዳንኤል ጉዳይ (ያሬድ ጥበቡ) የዲቨንተስ የኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ አምራች ኩባንያን አሳዛኝ ፍፃሜና የባለቤቱን የኢንጂነር ዳንኤል ግዛውን የእስርቤት ሰቆቃ የሚያሳየውን የዘገባ ፊልም ካየሁ በኋላ ለኢትዮጵያ አለቀስኩ። ለምን እንዲህ ይሆናል ብዬም ጠየቅኩ። ወደ እእምሮዬም የመጣው የሶስት ሰዎች ምስል ነው። የዶክተር ፍቅሩ ማሩ፣ የኤርምያስ አመልጋና የኢንጂነር ዳንኤል ግዛው ምስሎች። ሶስቱንም የሚያመሳስሏቸው ነገሮች ብዙ ናቸው። ከፍተኛ ትምህርት፣ ከፍተኛ የሥራ ልምድ፣ ከፍተኛ የሃገር ፍቅርና ሁሉም በምዕራባውያን ሀገሮች አንቱ የተባሉ ሰዎች የነበሩ መሆናቸው። ሌላው ሶስቱም የሚጋሩት ደግሞ የኢትዮጵያ የሙስና ህግ ተጠቂዎች ተደርገው በግፍ በእስር መንገላታታቸው ነው። ዶክተር ፍቅሩ ማሩ የልብ ቀዶጥገና ባለሙያ ሲሆኑ፣ አቶ ኤርምያስ የኢንቨስትመንትና ባንኪንግ ፈርቀዳጅ ነው፣ ኢንጂነር ዳንኤል ደግሞ ከ40 በላይ የፈጠራ ሥራዎችን (patents) ያስመዘገበ የኤሌክትሪካል ኢንጂነርና ባለሀብት ነበር። ሶስቱም በኢህአዴግ ባለሥልጣናት ላይ እንዲመሰክሩ ስለተፈለገ ዘብጥያ የወረዱ ናቸው። ሁለቱ ክሳቸው ተቋርጦ ሲፈቱ ኢንጂነር ዳንኤል አሁንም በባህርዳር እስርቤት በመሰቃየት ላይ ይገኛል። ሰለዳንኤል ብዙ በተናገርኩ ደስ ይለኝ ነበር። ሆኖም ከታች የተያያዘው የቪዲዮ ፋይል በብቃት ያስረዳል፣ ተመልከቱት። ዳንኤልን ሳውቀው ድፍን 25 ዓመታት አለፉ። የታላቅ ወንድሜ ሠርግ ላይ በሚዜነት ታጭተን ነበር ቶሮንቶ ላይ የተዋወቅነው። ወንድሜ እጅግ ከሚኮራባቸውና መልካም ምግባራቸውን አንስቶ ከማይጠግባቸው ጓደኞቹ መሀል፣ ቀዳሚ ሥፍራን የያዘው ዳንኤል ነበር። ፖላንድ የድህረ ምረቃ ትምህርት ላይ በ1970ዎቹ የተገናኙ ለ40 ዓመታት የዘለቀ ጥብቅ ወዳጅነት አላቸው። ታላቅወንድሜ ስለ ዳንኤል አንስቶ ስለማይጠግብ እኔም የማውቀው ብዙ ነው። ዳንኤል
Posted in Ethiopian News

ለአብኖችና ለባልደራሶች ከነኢዴፓ ጋር ተቀናጁ፣ ቶሎ ፍጠኑ #ግርማካሳ

የካቲት 30 ጥምረት/ቅንጅት/ግንባር የሚፈጥሩ ድርጅቶች አስፈላጊዉን ሰነዶች ለምርጫ ቦርድ የሚያቀርቡበት የመጨረሻ ቀን ነው። እንደሚታወቀው ባልደራስ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ነው የሚወዳደረው። አብን ደግሞ በሁሉም ቦታ መወዳደር ቢችልም (አገር አቀፍ ሆኖ ስለተመዘገበ) ከአማራ ክልል ውጭ የማሸነፍ እድሉ በጣም የመነመነ ነው። በመሆኑም ለአብንም፣ ለባልደራስም ከሌሎች በኢትዮጵያ አንድነት ከሚያምኑ ጋር መቀናጀታቸው በጣም ይረዳቸዋል። በኔ እይታ ባልደራስ፣ አብን፣ መኢአድ፣ ኢዴፓ፣ ሕብር ቢቀናጁ በጣም ጠንካራ ስብስብ መፍጠር ይችላሉ። ወንድም እስክንደር ነጋ ከነ አቶ ልደቱ ጋር በዘጠና ሰባት በነበረው ሁኔታ ችግር ሊኖረው ይችላል። ከዚህ በፊት ብዙ ስህተቶች ተሰርተው ይሆናል። ብዙ ተጋጭተን ይሆናል። ማንም የማይሳሳት የለምና ከስህተቶች ተምረን ባለፈው ሳንታሰር ወደፊት መሄድ መቻል አለብን። የአገር ጉዳይ ከግል ጉዳይ በላይ ነው። ከግል ስሜት ባለፈ ለአገርና ለሕዝብ የሚጠቅመው ምንድን ነው ብሎ ማሰብ አስፈላጊ ነው። በመሆኑም ባልደራስ የወደፊቱን እንዳያይ ፣ ባለፈው መያዝ የለበትም። አብኖች ጋር ስንመጣ ብዙ ጊዜ እንደጻፍኩት አብን የአማራ ድርጅት ቢሆንም ፕሮግራሞቹ በኢትዮጵያዊነት ላይ የተመሰረተ ነው። ሁለት ቀላል ምሳሌዎችን ላስቀምጥ። አብን አሁን ያለው የጎሳ ፌዴራሊም ቢቀየርና በዘር መደራጀት በአገር ደረጃ ቢታገድ ደስተኛ ነው። አብን አዲስ አበባ የአማራ ናት አይልም። አዲስ አበባ የአዲስ አበቤዎች ናት ነው የሚለው። አብን ለአማራ የበላይነት አይደለም የሚታገለው። አማራው ሳይገፋ፣ እንደ ጠላት ሳይታይ ፣ ከሌላው ጋር በእኩልነት የመኖር መብቱ እንዲጠበቅ ነው የሚሰራው። ባልደራሶችና አብኖች ጥቂት ቀናት ስለሆነ የቀራቸው በቶሎ መፍጠን መቻል አለባቸው። ለሕዝቡ በፕርግራም ከሚመሳሰሏቸው
Posted in Ethiopian News

የምርጫዉን ውዝግብ በተመለከተ የመፍትሄ ሐሳብ #ግርማካሳ

በአገራችን ፖለቲካ አንዱ ትልቁ ውዝግብ መጪውን ምርጫ በተመለከተ ነው፡፡ “ምርጫ መካሄድ አለበት፣ መካሄድ የለበትም” በሚሉት ዙሪያ ብዙ መቋጫ ያልተገኘላቸው የተወሳሰቡ ችግሮች አሉ፡፡ ቀላል የማይባሉ ድርጅቶች “ምርጫው መደረግ አለበት” ባይ ናቸው፡፡ ምርጫውን አለማድረግ የበለጠ ችግር እንደሚያመጣና ሕገ መንግስቱን እንደ መጣስ አድርገው ያዩታል፡፡ በሌላ በኩል አሁን ሜዳ ላይ ያለው አለመረጋጋት በማየት፣ ሰላማዊ ምርጫ ማድረግ አይቻልም በሚል ምርጫው እንዲራዘም የሚጠይቁ ብዙ ናቸው፡፡ ምርጫውን ያለማድረግ ችግሮች —————————– በሕገ መንግስቱ፣ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 3 ላይ “የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚመረጠው ለአምስት ዓመታት ነው፡፡ የሥራ ዘመኑ ከማብቃቱ ከአንድ ወር በፊት አዲስ ምርጫ ተካሂዶ ይጠናቀቃል” ይላል፡፡ የፓርላማው የስራ ዘመን የሚጀምረው መስከረም መጨረሻ ነው፡፡ ስለዚህ ከመስከረም መጨረሻ በፊት ፣ ማለትም ከጳጉሜን 5 በፊት ምርጫ መጠናቀቅ ይኖርበታል ማለት ነው። ምርጫውንም በተለምዶ ከሚደረገበት ከግንቦት ወር ወደ ነሐሴ መጨረሻ መግፋቱ ችግር ላይኖረው ይችላል። ከጳጉሜን በፊት ምርጫውን ማድረግ ካልተቻለ ግን፣ ሊሆን የሚችለው ሁለት ነገር ነው፡፡ አንደኛው አሁን ያለው አገዛዝ በሕዝብ ሳይመረጥ፣ የሕዝብን አዎንታ ሳያገኝ እንድገዛ መፍቀድ ነው፡ ይሄ በአጭር አማርኛ አምባገነንነት ብቻ ሳይሆን የሕዝብን ስልጣን ወደ ጎን ማድረግና ሕዝብ መናቅ ነው፡፡ ሁለተኛው የሽግግር መንግስት ማቋቋም ነው፡፡ የሽግግር መንግስት ማቋቋሙ ደግሞ በራሱ የተወሳሰበ ችግር ይፈጥራል፡፡ “ማን ነው የሽግግሩ መንግስት አካል የሚሆነው ? በምን መስፈርት ነው የሽግግር መንግስት አካላት የሚመረጡት? የሽግግር መንግስት ጉብዬዉን የሚያዘጋጀው አካል ማን ነው ? …..” ወዘተረፈ ለሚሉ ጥያቄዎች መልስ
Posted in Ethiopian News

የስራ ቋንቋ በጥናት ይመረጥ – ክፍል 1 የደቡብ አፍሪካ ተመክሮ #ግርማካሳ

በቅርቡ ይፋ የሆነው የብልጽግና ፓርቲ፣ ለጊዜው አምስት የአገራችን ቋንቋዎች፣ አማርኛ፣ ትግሪኛ፣ ሶማሌኛ፣ አፋርኛና ኦሮምኛ፣ የድርጅቱ የስራ ቋንቋ እንደሚሆን ገልጿል፡፡ የድርጅቱ መሪ ጠ/ሚ አብይ አህመድም ከአማርኛ በተጨማሪ ሌሎች ቋንቋዎችም የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋ እንዲሆኑ ድርጅታቸው እንደሚሰራ ማሳወቃቸው ይታወቃል፡፡ ከአማርኛ በተጨማሪ ሌሎች ቋንቋዎችን የስራ ቋንቋ ይሁኑ ሲባል የሚነሱ ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች አሉ፡፡ አንደኛው የፌዴራል የስራ ቋንቋ እንዲሆኑ ቋንቋዎች ሲመረጡ መመዘኛው ምንድን ነው የሚለው ነው ? ኢትዮጵያ ወስጥ ከሰማኒያ በላይ ቋንቋዎች አሉ፡፡ ሁሉም የስራ ቋንቋ እንዲሆኑ ካልተደረገ፣ የተወሰኑት ተመርጠው የተወሰኑት የሚቀሩ ከሆነ፣ በግልጽ ምክንያቶቹና መመዘኛዎቹ መቀመጥ አለባቸው፡፡ ያ ብቻ አይደለም መመዘኛው ፍትሃዊ ስለመሆኑ መረጋገጥ አለበት፡፡የተወሰኑ ቡድኖች፣ አመጽ ስለቀሰቀሱ፣ ወይንም ስላስፈራሩ፣ እነርሱ የሚናገሩት ቋንቋ ቅድሚያ የሚሰጠው ከሆነ፣ መስፈርቱ አመጽና ኃይል ነው ማለት ይሆናል። ያ ደግሞ ለዘለቄታው ችግር የሚፈጥር ነው። ምን ጊዜም በኃይልና በጉልበት በማስፈራራት የሚሆን ነገር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚያይል ስለሚሆን። ቋንቋውን መጠቀም ከመግባቢያነቱ አልፎ ሌላ ትርጓሜ እንዲሰጠውም ስለሚያደርግ። ሁለተኛው ጥያቄ የአፈጻጸም ጥያቄ ነው፡፡ አንድ ቋንቋ የፌዴራል የስራ ቋንቋ ሆነ ሲባል ምን ማለት ነው ? የቋንቋው ተናጋሪዎች በብዛት በሚኖሩበት አካባቢዎች በቋንቋ የፌዴራል መንግስት አገልግሎት ያገኛሉ ማለት ነው ? ያ ካልሆነ ደግሞ “ የፌዴራል ሰራተኞች የፌዴራል ቋንቋዎችን ማወቅ ፣ ወይም በያንዳንዱ የፌዴራል መስሪያ ቤት ፣ በሁሉም የፌዴራል ቋንቋዎች ፣ ተገልጋይ ባይኖርም፣ ቋንቁዎቹን የሚናገሩ በእኩልነት መቀጠር አለባቸው” ማለት ነው ? እነዚህም ጥያቄዎች ግልጽ ምላሽና ጥናት የሚጠይቁ
Posted in Ethiopian News

አቶ ለማ አልተከበሩም የሚሏቸው የኦሮሞ ጥያቄዎች ምንድን ናቸው ? #ግርማካሳ

በቅርቡ አቶ ለማ መገርሳ የብልጽኛ ፓርቲን እንደማይቀበሉ የገለጽበት ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው፡፡ አቶ ለማ የተናገሩትን አቶ በቀለ ገርባ ወይንም ጃዋር መሀመድ ቢናገሩት ፣ ሁሎ ሲናገሩት የምንሰማው ስለሆነ ንቀነው ነበር የምናልፈው፡፡ ሆኖም ግ ን በሕዝብ በጣም ተወዳጅ ከሆኑት ከአቶ ለማ ኝ ይሄን ስንሰማ ብዙዎቻችን ማዘናችን አልቀረም፡፡ አቶ ለማ “ የኦሮሞ ህዝብ ቆጥሮ የሰጠን አደራ አለ፡፡ የኦሮሞን ጥያቄ መጀመሪያ ማስፈጸም አለብን፡፡ የኦሮሞ ጥያቄ ደግሞ ሊያስፈጽም የሚችለው ኦዴፓ ነው” የሚል መልስ በመስጠት ነበር ከነ ዶ/ር አብይ ጋር ያላቸውን ልዩነት በይፋ የገለጹት፡፡ አቶ ለማ ያልተመለሰ የኦሮሞ ጥያቄ የሚሉት ምንድን ነው ? ያንን በቃለ ምልልሳቸው ግልጽ አላደረጉም፡፡ የኦሮሞ ማህበረሰብ መሰረታዊ ጥያቄዎች የሰላም፣ የፍትህ፣ የእክሉነትና የልማት ጥያቄዎች ናቸው የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡ እነዚህም ጥያቄዎች ደግሞ የኦሮሞ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዉያን ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ይመስለኛል አቶ ለማ መገርሳና በርካታ የኦሮሞ ብሄረተኞች “የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ አልተከበረም” ሲሉ አንዱ የሚያነሱት የኦሮሞ ባህል፣ ቋንቋ አልተስፋፋም የሚል ነው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ “ኦሮምኛ የፌዴራል ቋንቋ ለምን አልሆነም” ይላሉ፡፡  እስቲ ይሄን ቅሬታቸው ምን ያህል ሚዛናዊ እንደሆነ እንፈትሸው፡ በአዲስ አበባ ፣ ስታዲየም ፊት ለፊት፣ ብዙ ፎቆችን የያዘ የኦሮሞ ባህል መዓከል አለ፡፡ በዚህ ባህል ማእክል የኦሮሞን ባህልና ስርዓት የሚገልጹ የተለያዩ ኤግዚቢሽኖች ፣ ስብሰባዎች፣ ሴሚናሮች …ይደረጋሉ፡፡ ለሁለት ቀናት የከተማዋን ዋና ዋና መንገዶች በመዝጋት፣ ሌላው ማህበረሰብ ቤቱ እንዲቀመጥ ተደርጎ፣ ኢሬቻን በአዲስ
Posted in Ethiopian News

የኦሮሞ ብሄረተኞች ጥያቄ የእኩልነት ሳይሆን የበላይነት ነው #ግርማካሳ

(በወለጋ በሚደረጉ ጥሮነቶች የተፈናቀሉ እናት) የኦሮሞነት ፖለቲካን ተቃውመን ስለኦሮሞ ማህበረሰብ ስንጽፍ ነፍጠኛ  ጸረ_ኦሮሞ ይሉናል፡፡ ኦሮሞነትን እነርሱ ጋር ብቻ እንዳለ በማሰብ እነርሱ የኦሮሞ ተሟጋች ሌላው የኦሮሞ ጠላት አድርገው ያስባሉ፡፡ እውነታው ግን ኦሮሞ የሌለበት ኢትዮጵያዊ በጣም ጥቂት ነው፡፡ እኔ አዲስ አበባ ተወልጂ ያደኩ ነኝ፡፡ ሁለት አያቶቼ ኦሮሞ ናቸው፡፡ ከቦረናና ከአዳ፡፡ የኦሮሞ ማህበረሰብ የሚደርስበት መከራ እንደ ኢትዮጵያዊ ያመኛል፡፡ አሁን ኦሮሞን እንወክላለን የሚሉ ጥቂት ጽንፈኞች ከማንም በላይ እየጎዱ ያሉት ኦሮሞዉን ነው ብዮ ነው አጥብቄ የምቃወማቸው፡፡ በማህበራዊ ሜዲያ ጉልህ ተሳትፎ ከሚያደርጉ የኦሮሞ ብሄረተኛና አፍቃሪ ኦህዴድ ጦማሪ መካከል አንዱ ዶ/ር ደረጄ ገረፋ ቱሉ ነው። ዶ/ር ደረጄ፣ የኦሮሞ ጥያቄን አልመለሰም በሚል ዶ/ር አብይ አህመድ ላይ ቅሬታዉን ያሰማል፡፡ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ሲመጡ መሬት የረገጡ እና ለረጅም ዓመት ህዝቡ ሲታገልላቸው ያሉ የኦሮሞ ጥያቄዎች ነበሩ።ከነዚህ መካከል የሸገር እና የአፋን ኦሮሞ ጉዳይ ዋና ዋናዎቹ ናቸው። በተለይ የሸገር ጉዳይ ለህወሃት ከስልጣን ማማ መፈጥፈጥ ዋናው እና የቅርብ ገፊ ምክንያት ነው” ሲል ነበር ቅሬታዉን ያቀረበው፡፡ዶ/ር ደረጄ ብቸውን አይደለም፡፡ አብዛኞቹ የኦሮሞ ብሄረተኛ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች “የኦሮሞ ጥያቄዎች” አልተመለሱም በሚል ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንደ “ከሃዲ” በመቁጠር ማርጎምጎም ከጀመሩ በጣም ሰነባብተዋል፡፡ ከዶ/ር ደረጄ አስተያየት እንዳየነው፣ እነዚህ የኦሮሞ ብሄረተኞች የ”ኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ አልተከበረም” ሲሉ አንዱ የሚያነሱት የኦሮሞ ባህል፣ ቋንቋ አልተስፋፋም የሚል ነው፡፡ እስቲ ይሄን ቅሬታቸው ምን ያህል ሚዛናዊ እንደሆነ እንፈትሸው፡ በአዲስ አበባ ፣ ስታዲየም ፊት ለፊት፣ ብዙ ፎቆችን የያዘ
Posted in Ethiopian News

አዲስ የሚመሰረተው የሲዳማ ክልል ልክ እንደ ኦሮሞ ክልል አፓርታይዳዊ ክልል ሊሆን እንደሚችል ለአፍታም መዘንጋት አያስፈለግም። – ግርማ ካሳ

በምርጫ ቦርድና በደሃዴን የተረሳው የጌዲኦ ዞን ሕዝብ – ግርማ ካሳ የሲዳማ ክልል እንሁን ሕዝብ ውሳኔ አዋሳ ከተማን ጭመሮ በሲዳማ ዞን ይደረጋል። ሕዝብ በጠዋቱ ድምጹን ለመስጠት እየተሰለፈ ነው። ከአዋሳ ከተማ ውጭ የሚኖሩ የዞኑ ነዋሪዎች ብዙዎቹ (ከ90% በላይ) የሲዳማ ክልል ይኑር ብለው ይመርጣሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው። የአዋሳ ከተማ ሕዝብ አብዛኛው ፣ የሲዳማ ክልል ተፈጠረ ማለት፣ አፓርታይድ ተዘረጋ፣ ሲዳማዎች አንደኛና የበላይ ሌሎች ሁለተኛ ዜጎችና የበታች የሆኑበት ክልል ይሆናል የሚል ስጋት ስላላቸው (በኦሮሞ ክልል እንዳለው) የሲዳም ዞንን ክልልነት ተቃውመው ድምጽ ሊሰጡት ይችላሉ ተብሎ ይገመታል። ከአምስት አመታት በፊት ሞቶ በመቶ በተባለው ምርጫ በሕዝብ ተመርጫለሁ የሚለው፣ ራሱን የደቡብ ክልል ምክር ቤት ቤት ብሎ የሚጠራው አካልን በወ/ሮ ሙፈሪያት የሚመራው ደሃዴን፣ ሕገ ወጥ በሆነ መልኩ፣ የአዋሳን ሕዝብ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ገፈው፣ የአዋሳ ሕዝብ የፈለገውን ውሳኔ ይስጥ ፣ በሲዳማ ዞን ውስጥ ነው የሚቀጥለው የሚል ውሳኔ አሳልፈዋል። ይህ ማለት የአዋሳ ሕዝብ በሲዳም ክልል ስር መቀጠል ባይፈልግም በግዴታ በሲዳማ ክልል ስር እንዲሆን ይደረጋል ማለት ነው። ይህ ውሳኔ ሕገ ወጥና ጸረ-ዴሞክራሲያዊ እንደመሆኑ፣ የአዋሳ ነዋሪዎች ተደራጅተው ወደ ፍርድ ቤት በመሄድና የተለያዩ ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች በማድረግ ፣ ነገ ሁለተኛ ዜጎችና የበታች ከመሆን ራሳቸውን ማዳንና መታገል ያለባቸው መሰለኝ። አዲስ የሚመሰረተው ክልል ልክ እንደ ኦሮሞ ክልል አፓርታይዳዊ ክልል ሊሆን እንደሚችል ለአፍታም መዘንጋት አያስፈለግም። ሲዳሚኛ የማይናገር በክልሉ መስሪያ ቤት የመስራትና የመመረጥ መብት አይኖረውም። በአዋስ ከታማ አብዛኛው
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጽንፈኞችን ለሕግ ማስገዛት ካልቻሉ ዶ/ር አብይ ቢለቁ ይሻላል #ግርማካሳ

ሰሞኑን በአገራችን የመጀመሪያው ያልሆነ ዘግናኝና አንገት የሚያስደፋ የሽብር ተግባራት በዜጎች ላይ ተፈጽሟል፡፡ ጠ/ሚ አብይ አህመድ 83 ኢትዮጵያዉያን ሕይወታቸው እንደተቀጠፈ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም የተገደሉ ዜጎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ራሱን ቄሮ ብሎ የሚጠራው ቡድን ፣ የጃዋር መሀመድን “ተከብቢያለሁ” ጩኸት ተከትሎ በዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት ግድያ፣ ድብደባ፣ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችንና የእምንት ተቋማትን የማውደም፣ የማቃጠል ተግባር የፈጸመ ሲሆን፣ ፣ ዜጎች ራሳቸውን ለመመከት በወሰዱት እርምጃና በአንዳንድ አካባቢዎች ከጸጥታ አካላት ጋር በተደረገ ግጭት የተወሰኑት ቄሮዎች ተገድለዋል፡፡ በዶዶላ ፣ በሕመም ሲሰቃዩ የነበሩ፣ የ80 አመት አዛዉንት ነበሩ፡፡ አቶ ኃይሉ አማረ፡፡ አንገታቸው ታርዶ፣ ራሳቸው በድንጋይና በስለት ተፈጥፍጦ፣ አይናቸውን ወጥቶ፣ ምላሳቸው ተቆርጦ፣ አገጫቸው ተከፍሎ፣ቀኝ እጃቸውን ተቆርጦ፣ ሆዳቸውን በስለት ተቀድዶ…በዘግናኝ ሁኔታ ነበር የተገደሉት፡፡ በኦሮሞ ቄሮዎች፡፡ ዘምሼ ሲሳይ ትባል ነበር፡፡ እህታችን፡፡የሁለት ሕጻን እናት፡፡ ጡቷን ቆርጠውና አርደው ነበር የገደሏት፡፡ ከድረዳዋ ቀርብ ብላ ባለች የምስራቅ ሃረርጌ ዞን አካባቢ፣ ከነበረው ግርግር በመሸሽ ተደብቀው የነበሩ አንዲት እናትና ሴት ልጃቸው በቤታቸው እንዳሉ፣ በር ተዘግቶባቸው ፣ ቤታቸው ላይ እሳት በቄሮዎች ተለኩሶ ነው የተገደሉት፡፡ አሁንም በምስራቅ ሀረርጌ በሮዳ በሚባል ቦታ አቶ ደረጀ ኃይሉና አቶ ደመና የተባሉ በንግድ የሚተዳደሩ ሁለት ወንድማማቾች፣ የአቶ ደመና ባለቤት ወ/ሮ ወላንሳ ፍቅሬ በቄሮዎች ታርደዋል፡፡ በተለይም አቶ ደረጄ ለማምለጥ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቢገቡም፣ ፖሊስ ጣቢያዉን ሰብረው በመግባት፣ የኦሮሞ ክልል የአካባቢው ፖሊስ እየተመለከተ፣ በዱላ ቀጥቅጠው፣ ብልታቸውን ቆርጠው አፉቸው ውስጥ በመክተት ነበር አሰቃይተው የገደሏቸው፡፡ በፊታቸው ይሄ ሁሉ
Posted in Ethiopian News

ትእግስታችን ተሟጧል – አቶ ደመቀ፣ አቶ ለማና ወ/ሮ ሙፈሪያት (ዳ/ን ኢንጂነር አባይነህ ካሴ)

የኦህዴድ ም/ሊቀመነርና የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ፣ የደሃዴን ሊቀመነበርና የሰላም ሚኒስቴር ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚልና የአዴፓ ሊቀመንበርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቲር አቶ ደመቀ መኮንን ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ጋር ዉይይት አድርገዋል። አመራሮች ሕግና ስርዓትበማስጠበቅ አንጻር ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ ፣ ” አቅም አለን፣ እየተነሣ ያለውን አቧራ በአንድ ጀምበር ጸጥ ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህ ግን መግደልን ይጨምራል፡፡ የመግደልን መንገድ ደግሞ የመጣንበት ስለሆነ አልፈለግነውም ነበር” ያሉት አመራሮቹ “ከእንግዲህ ግን ትዕግስታችን ተሟጥጧል” ሲሉ ሕግን የማስከበር ስራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። አመራሮቹ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ያለውን ሁኔታ ተረድተው በአገሪቷ ሕግን ለማስክበር በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ድግፍ እንዲያደረጉላቸውም ተማጽነዋል። ዳ/ን ኢንጂነር አባይነህ ካሴ  የኢሕአዴግ አመራሮች ከአባቶች ጋር ስላደረጉት ዉይይት የሚከተለውን አስፍሯል የመንግሥት ልዑካን ቤተ ክርስቲያን ትራዳቸው ዘንድ ተማጸኑ ትላንት ዐርብ ጥቅምት ፲፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት ለማነጋገር ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመጡት የመንግሥት ባለሥልጣናት ቤተ ክርስቲያን ትራዳቸው ዘንድ ተማጽኖ አቅርበዋል፡፡ ወደ ጉባኤው የመጡት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን፣ የመከላከያ ሚንስትር ለማ መገርሳ፣ የሰላም ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚል እና የፌድራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ናቸው፡፡ ለእነዚህ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት አባቶች ኹለት መሠረታዊ ጥያቄዎችን አቅርበውላቸዋል፡፡ አንደኛ ቤተ ክርስቲያን ከዛሬ ነገ ይሻላል በማይባል ጥቃት ውስጥ ገብታለች፡፡ ይህ ያላባራ ጥቃት ይቆም ዘንድ መንግሥት የሚሰጠው ዋስትና አለን? ኹለተኛ፡- ጥቃት አድራሾችን ለይቶ ሕጋዊ ርምጃ ለመውሰድ ያለው ቁርጠኝነት እስከምን ድረስ ነው? የሚሉ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ጥያቄዎች በተጨማሪ
Posted in Ethiopian News

ወንጀለኞች ማባባል ነገ የከፋ ችግር ያመጣል – ዶ/ር አብይ እንደ ቻምበርሌን አይሁኑ #ግርማካሳ

እንደ አውሮፓዉያን አቆጣጠር ሙሱሊኒ በ1923፣ ሂትለር ደግሞ በ1933 ስልጣን ጨበጡ፡፡ በአውሮፓ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ እነዚህ ሁለት ሰዎች የፈጸሙት ጥፋት ተነግሮ አያልቅም፡፡ሂትለርና ሙሶሊኒ በቀሰቀሱት ጦርነት በጀርመን በጣሊያን ብቻ ወደ 10 ሚሊዮን ሕዝብ ሞቷል፡፡ ከጀርመንና ከጣሊያን ውጭ ፣ ያሉትን ስንደምሩ ቁጥር ሶስት፣ አራት እጥፍ ይደርሳል፡፡ በ 1935 ዓ.ም ሙሶሊኒ ኢትዮጵያን ወረረ፡፡ የመንግስታት ሕብረት፣ League of Nations የሚባለው ጣሊያን ወራሪ ናት ብሎ አወገዛት፡፡ ሆኖም ግን ዉሳኔው ጥርስ አልነበረውም፡፡ እንግሊዝና ፈረንሳይ (በወቅቱ ኃይል አገራት የነበሩ) ብዙ የጥቅር ህዝብ ጉዳይ አላሳሰባቸዋውም፡፡ሙሶሊኒ ዝም ተባለ፡፡ ከአንደኛ የዓለም ጦርነት በኋላ በጀርመን ራይንላንድ የሚባለው አካባቢ ከዉትድርና እንቅስቃሴ ነጻ እንዲሆን በ1919 የቨርሳይ ስምምነት ተወስኖ ነበር፡፡ ሆኖም ሂትለር በጀርመን ውስጥ ያሉት ተቃዋሚዎችን ሁሉ ከጨፈለቀ በኋላ፣ በ1936 ዓ፣ም ያንን ስምምነት አፍርሶ በራይንላንድ ወታደሮችን አሰማራ፡፡ ይሄን ሲያደርግ ዝም ተባለ፡፡ በማርች 12 ቀን 1938 ሂትለር ፣ ትኩረቱን አውስትሪያ ላይ በማድረግ፣ የአዋስትሪያዉን ቻንስለር ኩርት ሹስሽኒግን አስወግዶ፣ ቪዬናን ወረረ፡፡ አውስትሪያን ወደ ጀርመን ቀላቀለ፡፡ ይሄ ሁሉ ሲሆን ሌሎች የአውሮፓ አገር መሪዎች ምንም አይነት እርምጃ አልወሰዱም፡፡ሂትለር ዝም ተባለ፡፡ እዚያ ላይ አላበቃም፡፡በቼኮስሎቫኪያ ጀርመኖች በብዛት ይኖሩበታል የተባሉ አካባቢዎችን፣ በአንድ ላይ ሱድተንላንድ የሚባሉትን፣ ወደ ጀርመን መቀላቀል አለባቸው በሚል ሂትለር ትኩረቱን ወደዚያ አዞረ፡፡ ቼኮስሎቫኪያዎች አገራቸውን ለመከላከል ወታደሮች ወደ ድንበሩ ማዞር ጀመሩ፡፡ በዚያ ያለውን ቀውስ ለማብረድ የእንግሊዙ ጠ/ሚኒስተር ኔቪል ቻምበርለን ሂትለርን እንዲያናገሩ ልኡካን በርሊን ላከ፡፡ በሴፕቴምበር 15 ቀን 1938 ዓ.ምም አሱ ቻምበርለን ራሱ
Posted in Ethiopian News

ከመቶ በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠሩ ኢንጂነር በወህኒ ይገኛሉ #ግርማካሳ

ኢትዮጵያ አገራችን ለአገር የሚሰራ፣ ለአገር የሚያስብ ፣ ለአገር የቆመ የሚታሰርባት፣ አገር የሚያጠፉ ግን የህግ ከለላ የሚያገኙባት አገር ሆናለች። የኢትዮጵያ መንግስት ከዳይስፖራ የሄዱ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶችን የሆቴል እየከፈለ፣ጥበቃ እየመደበ ወደ አገር እንዲገቡ አድርጓል። ከጥቂት ቀናት በፊት መንግስት ከአንድ አመት በላይ ጥበቃ አቆሞለት የነበረ አንድ ግለሰብ፣ ጥበቃ ሊነሳብኝ ነው በሚል፣ አገር እንዲታመስ ማድረጉና ለብዙ ወገኖች መሞት ምክናት መሆኑ ይታወቃል። ከዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ ከሁሉም ማእዘናት ፍትህን እየጠየቁ ይገኛሉ። በሌላ በኩል አገር ለመጠቀም ከዳያስፖራ ወደ አገር ቤት የሀዱ፣ ለብዝይ ኢትዮጵያዉያን የስራ እድል የፈጠሩ ወገኖች ግን ፍትህ ተነፍገው በወህኒ እየማቀቁ ነው። ከመቶ አመታት በፊት አባቶቻችን በአድዋ ካደረጉት ድል፣ ቅኝ ካለመገዛታችን፣ በተለያየ ጊዜ ከምናስመዘግባቸው የሩጫ ዉድድር ድሎችና በቅርቡም ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ካገኙት የኖቢል ሰላም ሽልማት ውጭ ፣ ኢትዮጵያዉያን በአለም አቀፍ ደረጃ በአዎንታዊነት ብዙ የምንታወቅበት ነገር የለም። በስፋት የምንታወቀው በድህነት፣ በረሃብ፣ በስደትና በልመና ነው። ኢትዮጵያ የልጆች መካን አይደለችም። የተፈጥሮ ሃብት አላነሳትም። ልጆቿ ተሰያይተው፣ ተበታትነው፣ ተሰባስበውና በፍቅር መኖር ስላቃታቸው እንጂ፣ ለአገር አይደለም ለመላው አፍሪክ የሚበቁ ነበሩ። በርካታ ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው ያላያገኙትን እድል በመጠቀም በተለያዩ አገሮች፣ ተምረው፣ ትልቅ ደረጃ ደርሰውና ልቀው በመገኘት አኩሪ ስራ እየሰሩ ነው። አገርን እያስጠሩ ነው። ከነዚህ ወገኖች መካከል ዛሬ ስለ አንድ ኢትዮጵያዊ ላወራችሁ ፈለኩ። በኤሌትሪካል ኢንጂነሪንግ የማስተርስ ዲግሪ አላቸው። በአሜሪካ በሚገኙ ትላልቅ ኩባኒያዎች የሃያ አምስት አመት የስራ ልምድ አካብተዋል። እንደ ኢንጄነርና የኢንጂነሪን ሪሰርች ዳይሪክተር ሆነው ሰርእዋል።፡
Posted in Ethiopian News

ለዜጎች ደህንነት መከላከያ ኦሮሞ ክልልን በሙሉ መቆጣጠር አለበት #ግርማካሳ

“ከኢህአዴግ የውህደት ሃሳብ ይልቅ የህወሓት ህብረብሄራዊ ፌደራሊዝም አስተሳሰብ አሸናፊነት እያገኘ ነው” ይላል ጃዋር መሐመድ፡፡ሕብረ ብሄራዊ ፌዴራሊዝም የሚሉት በሕወሃትና በኦነግ በሕዝቡ ላይ የተጫነ የጎሳ የዘር አወቃቀርን ነው፡፡ ሜዳ ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ስንመለከት፣ ፍቃዱንና ፍላጎቱን በሌላው ላይ በኃይል ለመጫን የሚፈልገው፣ የጽንፈኞች ቡድን የበላይነቱን የያዘ ይመስላል፡፡ ብዙዎቻችን ተስፋ እንዳደረግነው ዉህደት የተባለው ነገር ሳይከሽፍ እንዳልቀረ ነው፡፡ “አልከሸፈም፣ እየተነጋገርንበት ነው፣ ከምርጫ በኋላ ይህናል ” የሚል ማዘናጊያ ንግግሮች እየሰማን ነው፡፡ የኦሮሞ ጽንፈኞች በአቶ ለማ መገርሳ በኩል የፈለጉትን እያገኙ ያለ፣ ዶ/ር አብይ አህመድም ወስኖ፣ ቆርጦ መምራት ያቃተው ይመስላል፡፡ ለሕዝብ የሚያቀርበው ነገር ስለሌለውም ኮስሜቲክ የሆኑ ፣ የተለመዱ የማዘናጊያ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ብቻ ነው የተጠመደው፡፡በአጭሩ አነጋገር የተሸነፈ፣ ለኦህዴድ ጽንፈኞች የተንበረከከ ነው የሚመስለው፡፡ በኦሮሞ ክልል በወለጋ፣ በአርሲ፣ በጉጂና በቦረና…ሕግና ስራዓት ያስጠብቃል ተብሎ የሚጠበቀው፣ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶ/ር አብይ አህመድ፣ ወንበዴዎችና አሸባሪዎች በመኪና ተጭነው በመምጣት፣ መሐል አዲስ አበባ እስኪያምሷት ድረስ ዝም ብሎ እያየ ነው፡፡ ምን እንደሚጠብቅም እግዜር ይወቀው፡፡ በጣም አዝናለሁ፡፡ ብዙዎቻችን እጅግ በጣም ከመጠን በላይ benefit of the doubt እየሰጠነው፣ እርሱ ላይ ላለመጨከን ወደ ኋላ ስንጎተት፣ በርሱ ላይ ተስፋችንን ሳናሟጥጥ ፣ የተለያዩ ሰበቦች እየሰጠን፣ ስራዉን ላለመስራቱ የተለያዩ ምክንያቶች በማቅረብ justify ስናደርግለት ቆይተናል፡፡ከሶስት፣ አራት ቀናት በፊት እንኳን ለዶ/ር አብይ ሁለተኛ እድል እንስጠው ብዬ ስከራከር ነበር፡፡ ግን ላለፉት ሁለት ቀናት የሆነው አይቼ፣ የዶ/ር አብይን ዝምታ በምንም መስፈርት justify ላደርገው፣ ልቀበለው አልችልም፡፡
Posted in Ethiopian News

የጽንፈኛ ቄሮ መሪ ጦርነት አውጇል – እንግዲህ ሕዝብ ሆይ ራስህን ተከላከል #ግርማካሳ

የጽንፈኛው ቄሮ መሪ ጃዋር መሐመድ ለኦሮሞ ክልል መንግስት ሌላ መመሪያ አስተላልፏል። በፌስ ቡክ ገጹ ላይ የሚከተለውን ነበር የለጠፈው፡ “Dhaabbileen Miti-Mootummaa ( NGO) Oromiyaa keessa jiran irra jireessi isaanii Afaan Oromoon hin hojjatan. Kaayyoon isaanii ummata naannichaa tajaajiluu erga tahee afaan naanichaan dubbachuu qabu. Afaan Oromoon hojjachaa dhalattoota naannoo sanii hiree hojii dhoowwachaa itti fufuu hin qaban. Oromiyaa kleessa turuu yoo barbaadan afaan Oromoon hojjachuu; san didnaan dhoortoo isaanii qabatanii haa bayan.” አንድ ላቲን የሚያነብ ፣ ግን በላቲን ኦሮምኛ በአገራችን ፊደል እንዲጻፍ እየሰራ ያለ የኦሮሞ ልጅ ወዳጄ፣ ብርሃኑ ገመቹ ትርጉሙን እንደሚከተለው አቀበለኝ። “በኦሮምያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ በብዛት በኦሮምኛ አይሰሩም። ዓላማቸው ህዝቡን ማገልገል ከሆነ የክልሉን ቋንቋ መናገር አለባቸው። በኦሮምኛ ባለመስራት የክልሉን ተወላጅ ስራ መንፈግ የለባቸውም። በኦሮምያ በስራ ለመቀጠል የሚፈልጉ ከሆን በኦሮምኛ መስራት አለባቸው። አለበለዚያ ግን በአስቸኳይ ተጠራርገው መውጣት አለባቸው” ከዚህ በፊትም ጃዋር “Ethiopians Out of Oromia” እያለ የጽንፈኛ አክራሪዎችን ሰልፍ ሲመራ እንደነበረ ሁላችንም የምናውቀው ነው። ያኔ ጃዋር ብዙ ደጋፊ አልነበረውም። አሁን ግን በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ፣ ገደል ግቡ ቢላቸው ገደል የሚገቡ ጭፍን ደጋፊዎች አሉት። በተለይም በምእራብ አርሲ ፣ በባሌና በሃረርጌ ዞኖች። በተጨማሪም በኦህዴድ/ኦዴፓ መዋቅር ውስጥም ከነ ዶ/ር አብይ በበለጠ በጣም ተጽኖ ፈጣሪ ነው። በአብዛኛው ነዋሪ በማይደገፍበት ቦታ ደግም፣ ያሰማራቸው የማፊያ ቄሮ ቡድኖች አሉ። በጣም ጥቂቶች። ለምሳሌ ለገጣፎ አብዛኛው ነዋሪ ኦሮሞዉን ሳይቀር
Posted in Ethiopian News

የትግራይ ልጆችና የኦሮሞ ልጆች ልዩነት (ግርማ ካሳ)

የትግራይ ልጆችና የኦሮሞ ልጆች ልዩነት (ግርማ ካሳ) አንድ ታሪክ ልንገራችሁ። አንድ የግል መስሪያ ቤት ነው። ቦታዉንና የመስሪያ ቤቱን ስም አልጠቅስም። የመስሪያ ቤቱ ባለቤት የአንድ ወዳጄ ዘመድ ነው። የሚንቀሳቀሰው በኦሮሞ ክልል ነው። የመስሪያ ቤቱ የስራ ቋንቋም አማርኛ ነው። ከኦሮሞ ክልል ጋር የሚደረጉ የደብዳቤ ልውውጦች በላቲን ነው። መስሪያ ከክልሉ ወይም ወረዳው ደብዳቤ ሲደርሰውም ሆነ ሲልክ እያስተረጎመ ነው። አንድ ከዩኒቨሲቲ የተመረቀ ሰው ተቀጠረ። አማርኛ ለመግባባት ያህል ይናገራል። ስራዉን ሰርቶ ሪፖርት መጻፍ ነበረበት፣ ግን ሪፖርት አያቀርብም። አለቃው ይጠራዉና ለምን ሪፖርት እንደማያደርግ ይጠይቀዋል። “ጋሼ ለምን አሁን እዚህ በቃል አልነግሮትም ? ” ይላል። “አይደለም ጊዜ ስለሌለኝ፣ ጽፈህ ዛሬዉን አቅርብልኝ” ሲል፣ ከወጣቱ ጋር መፋጠጥ ሆነ። “ጋሼ አማርኛ መጻፍ አልችልም” አለው። Image result for ethiopia alphabet አለቅዬው ደነገጠ። አላባረረዉም። አዘነለት። በስድስት ወር ውስጥ አማርኛ መጻፍ እንዲማር፣ እንደሚረዳው” ነገረው። መጽፍ ካልቻለ ግን፣ በስራው ላይ መቀጠል እንደማይችል፤ ቢዝነስ ስለሆነ አስቸጋሪ እንደሆነ ነገረው። እስከዚያውም” ሪፖርቱን በቃል እየነገርከኝ እኔ ለጊዜው እጽፍልሃለሁ” አለው። ከዚያ በኋላ ምን እንደሆነ አላውቅም። ይሄ ወጣት ያጋጠመውን አይነት ችግር እንዳያጋጥማቸው ነው አማርኛ በሁሉም የአገሪቷ ክፍል ከአንደኛ ክፍለ ጀምሮ እንዲሰጥ ለማድረግ አዲስ የትምርህት ፍኖተ ካርታ እነ ዶ/ር አብይ አሀምድ ያዘጋጁት። በዚህ አዲሱ ፍኖተ ካርታ ኦሮምኛ፣ ትግሪኛ፣ ሶማሌኛ አትማሩ አልተባለም። እንደውም እንደ አዲስ አበባና አማራ ክልል ያሉም ከ እንግሊዘኛና አማርኛ በተጨማሪ ሌላ ሶስተኛ ቋንቋም ይማሩም ይላል ፍኖተ ካርታው ያስቀምጣል። ሕወሃት አማርኛ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ ትምህርት እንዲሰጥ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጃዋርን ሀሳብ ስቀሉት! – የቦረናው ሙክታር አደም ለኦሮሞ ጽንፈኞች ይናገራል

(ሙክታሮቪች ኦስማኖቭ) የኦሮሞ ወጣቶች ሆይ ጃዋርን ስቀሉት። አዎ! እሱን ትታችሁ፣ ሀሳብና የገነባውን ተክለስብዕና ስቀሉት። ሀሳቡን ስቀሉት! ይህን ለምን እንደምል በጥሞና አድምጡኝ። ***** የጃዋር መንገድ የጤነኛ ፖለቲካ መንገድ አይደለም። የፖለቲካን መካረር ጉዳይ በቋንቋ ጭንብል ማቅረብ ስህተት ነው። የፖለቲካ ጉዳይ በፖለቲካ መንገድ፣ ሰጥቶ በመቀበል፣ በመደማመጥ እና የጥቅም ግጭትን ወግ ባለው፣ ስርአት በተበጀተለት፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ “እነሱ የኛን ካልተማሩ እኛም የነሱን አንማርም የሚለው ብሂል ጉዳዬ ከአማርኛ ጋር ሳይሆን ከህዝብ ጋር መሆኑን የሚያሳይና ለመግባባትም መፍትሄ የማያመጣ የእልህ ፖለቲካ ነው። የፖለቲካ ጉዳይን በትምህርት ጭንብል ማቅረብ ትክክል አይደለም። መደረግም ካለበት ወይይቱ ለልጅ ከአፍ መፍቻ በተጨማሪ ሌላ ቋንቋ ማስተማር ማንነቱን ያስለውጠዋል ወይ ብሎ ጥያቄውን በዚህ መንገድ ፍሬም በማድረግ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ለሀገርና ለትውልድ የሚጠቅም የሀሳብ ሙግት ማድረግ ነው። የጥላቻና የእልህ መንገድ፣ የመንግስትን እጅ መጠምዘዝ ለሁላችንመ የማይበጅ በመሆኑ ተክለስብእናውን በመቅበር በእራስ ማሰብን መለማመድ በማስፈለጉ: የጃዋርነ ሀሳብ ስቀሉት! ስለቋንቋና ባህልና የልጆች ትምህርት ጃዋር ከሚናገረው ባሻገር ማንበብ፣ ማሰናሰል እና ግራቀኝ ማየት ያስፈልጋል። + በዚህ በኩል እኔ ኢንተርኔት ውስጥ መልከት ባደረግኩት መሰረት:— • ልጆች እስከ አስራ ሰባት ቋንቋ በአንድ ላይ በአንድ ወቅት መማር የሚችሉ መሆኑን • ተጨማሪ ቋንቋ በልጅነታቸው የሚችሉ ልጆች ችግር የመፍታት፣ አካባቢን የመረዳት፣ ነገሮችን በተለያዩ አቅጣጫዎች የመመልከት፣ በቡድን የመስራት፣ የመተባበር፣ ከሰው የመግባባት እና ሌሎች ችሎታዎችን ለማዳበር እንደሚጠቅማቸው • የብዙ ቋንቋ ባለቤት መሆን ከነባርና አንድ ሰው ከበቀለበት ባህል የማያፈናቅል
Posted in Ethiopian News

ይድረስ ለአቶ ልደቱ አያሌው፣ ለምን አምርሬ እጠላህ እንደነበረም ዛሬም ድረስ በቅጡ አይገባኝም – እያሱ እንድሪስ ተሰማ

ይድረስ ለአቶ ልደቱ አያሌው ። እንደ ልጅነቴ ማንዴላ ብዬ እጄን ደም እስኪያግት ድረስ ባላጨበጭብልህም ተጨማሪ ዕድል ያሻሃል ። ከማንም የከፋህ ሴይጣንም አይደለህም ፣ ቢያንስ ቢያንስ እንደ ሌሎቹ ሁሉ ሌላ ፓስፖርትና በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የምትቆምረዉን ሴራ ከአሉባልታ ዉጪ አልሰማሁም ። እዉነት ለመናገር ለምን አምርሬ እጠላህ እንደነበረም ዛሬም ድረስ በቅጡ አይገባኝም ነበር። “የእርሻ ዉስጥ አረም” የሚለዉን መፅሃፍህን ራሱ ከሰዉ ተዉሼ አቃጥዬዉ እንደነበረ ሁሉ አስታዉሳለሁ። ምናልባትም ምክንያት አልባነት ሳይሆን የተጫንነዉ ሶፍትዌር በልካችን የተሰፋ ስለነበር ይመስለኛል። ወንበር ለመደርደር መጥቶ ፖለቲከኛ የሆኑ እስካርቭ ጠምጣሚ አያሌ መንደርተኞችና ጭራ ለምኔ ሰዎች ፖለቲካዊ አቅማቸዉ ድንኮች “ፒግሚ” የሆኑ ስምህን ሲያከፋፉት ሰምቼያለሁ ። ሀጥያትህን ለሚሰርይልህ አምላክ እንተወውና ። እስቲ ፃድቃኖቹ ነቢያት ነን ባዮቹ የመጀመሪያዉን ድንጋይ ሲወረዉሩ እንያቸዉ ??? መልሱን አሳምረዉ ያዉቁታል። በመስታዉት ቤት ያለ ሰዉ ድንጋይ ወርዉሮ “እንደርቢ” አይጠራም። ትርፉ -ዉሃ- መረጫጨት ነዉ ። በግሌ የዛኛዉን ዘመን የ”ቸ” እና የ” ሸ” ሴረኞች ቩቩዜላ አልሆንም ፣ በተለይም ያችን ካባና ለምድ ገፈዉ እስካልጣሉ ድረስ ፣ የማንም ቲፎዞ መሆን አልፈልግም ። በመጨረሻም የገባኝ ነገር የዛን ዘመን የፖለቲካ ጀብራሮች የሴራቸዉን ክህሎት እና የካበተ ልቀት ነዉ ። ለምን እንደዚህ እንደሚፈሩህም ጭምር የተከሰተልኝ ደግሞ ዘግይቶ ነዉ። ዛሬ ትላንትና አይደለም ። እንደ ሆሞ ሳፒያንስ ዘመን በጋርዮሽ ልጓም አንሰተርም። በደቦ ዉደዱ ጥሉ የሚባል ትናንሽ ነገስታቶች በጫንቃችን የሉም። ሲጀመር ፖለቲካን ለፅድቅ ብለህ አልጀመርክም።  “ኤጲስ ቆጶስም” አይደለህምና ከአንተ ቡራኬ መጠበቅም
Posted in Ethiopian News

እስቲ ላቲንን ከኢትዮጵያ ፊደል እናወዳድር – በመረጃና ሳይንስ እንነጋገር #ግርማካሳ

“አመሰግናለሁ” በላቲን “galatoomaa” ነው። በ ኢትዮጵያ ፊደል ደግሞ “ገለቶማ” ነው። በላቲን 10 ፊደላት ሲፈጅ በግ እዝ 4 ብቻ ነው የሚፈጀው። ከእጥፍ በላይ። “galatoma” , “galatooma”, “galatomaa” አይደለም። “galatoomaa” ነው። ስፔሊንግ ላይ ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ የግድ ነው። እንደ ኢትዮጵያ ፊደል እንደ ሰማነው ልንጽፍ አንችልም። “በጣም አመሰግንዎታለሁ” ወይም “በጣም አመሰግናቹሃለሁ” ማለት ደግሞ በኢትዮጵያ ፊደል ፣ “ባይ ኤን እስን ገለቴፈደ” ነው። 13 ፊደላት ያስፈልጋሉ። በላቲን “Baay’een sigalateeffadha” ነው። 23 ፊደላት ያስፈልጋለኡ። በግእዝ ለመጻፍ ከሚያስፈልገው ሁለት እጠፍ ማለት ነው። አሁን አንድ የላቲን ተማሪ፣ “Baay’een sigalateeffadha” እጽፋለሁ ብሎ፣ “Bay’een sigalateeffadha”፣ “Baay’en sigalateeffadha” ፣ ” Baay’een sigalateffadha”፣ “Baay’een sigalateefadha” ወይም “Baay’een sigalateeffadha” ሊጽፍ ይችላል። ኮንሶነቶች ከቫወሎች እንዴት እንደሚጻፉ ስፔሊንጉን በሚገባ ጠንቅቆ ካላወቀ። እንግዲህ ፍረዱ። ለሌላው ፊደልን ለሚያውቅ ፣ አማርኛ፣ ትግሬኛ፣ ጉራጌኛ በኢትዮጵያ ፊደል ማንበብና መጻፍ ለሚችል፣ ኦሮምኛ መማር ካስፈለገው፣ ኦሮሞኛ እንዲማር የቱ ነው የሚቀለው ?????? ሌላ ልጨምርላችሁ። “አዎ” በኦሮምኛ በኢትዮጵያ ፊደል ” ኤዬ” ነው። በላቲን ደግሞ ሶስት እጥፍ ፊደል እንጠቀማለን። ” Eeyyee” ነው። ኦሮምኛ በኢትዮጵያ ፊደል መጻፍ አይቻልም የሚሉ፣ እንዳንድ ለአማርኛ፣ ለግእዝ ፣ ኢትዮጵያዊ ለሆነ ነገር አለርጂክ የሆኑ ዘረኞች ሲያጭበረበሩና ሲዋሹ ብዙ ጊዜ ይሰማሉ። ያንን ማድረጋቸው አያስደንቅም። ለምን በሐሳብ መሞገት የማችል፣ መረጃና ሳይንስ ይዞ መከራከር የተሳነው ሰው፣ የሚኖረው ምርጫ ነገሮችን መሸፋፋእን፣ መዋሸትና ማምታት ነው። ከዚህ በታች ያለው ዝግጅት አቶ በቀለ ገርባ በመቀሌ በተናጋሩት አንድ ዝግጅት ላይ፣
Posted in Ethiopian News

ላቲን የኦሮሞ ልጆችን ክፉኛ ጎድቷል #ግርማካሳ

አባ አናሲሞስ ነሲብ፣ ከአንድ መቶ አመት በፊት መጽሀፍ ቅዱስን በኦሮምኛ በኢትዮጵያ/ግእዝ ፊደል የተረጎሙ የወለጋ አባት ነበሩ። የኦሮሞ አባት ያላልኩት አባ አናሲሞስ ኦሮምኛ ተናጋሪ የነበሩ ቢሆንም ኦሮሞ ስለመሆናቸው ግን ማረጋገጫ ስለሌለኝ ነው። ለምን በወለጋ ብዙ ማህበረሰቦች ኦሮሞ ሳይሆኑ ኦሮምኛን ግን በግዳጅ እንዲናገሩ የተደረጉ ስላሉ።በወረራ። ( በነገራችን ላይ አጤ ሚኒሊክ ወለጋን በወረራ አላስገበሩም። ነገር ግን የኦሮሞ አባ ገዳዎች በወረራ ነው በዚያ የሚኖሩ ብሄረሰቦችን በነርሱ ስር ያደረጉት) እንግዲህ ኦሮምኛ ቋንቋ በበቂ ሁኔታ በግእዝ ፊደል መጻፍ እንደሚቻል ከአንድ መቶ አመት በፊት አባ አናሲሞስ አሳይተዉናል፡፡ በግእዝ ብቃት ላይ በርካታና ዝርዝር ሳይንሳዊ መረጃዎች በብዛት አሉ። ያለ ምንም ጥርጥር የግእዝ ፊደል ለኦሮምኛ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሁሉ ብቁ ነው። ብቁ ብቻ ሳይሆን ከላቲን በእጅጉ የተሻለ ነው። ሆኖም የጥቁር ፈረንጆች የሆኑ፣ የኦሮሞን ማህበረሰብ ከተቀረው ኢትዮጵያዊ ለመነጠል የሚፈልጉ፣ ኢትዮጵያዊ የሆነን ነገር የሚጠየፉ ጠባቦች አሉ። ኦሮምኛ አባ አናሲሞስ እንዳደረጉት በግእዝ ፊደል ከተጻፈ፣ ኦሮሞ ከኢትዮጵያዊነት ጋር ትስስሩ ይቀጥላል የሚል ፍርሃት ስላለባቸው፣ ለግእዝ ፊደል ካላቸው ጥላቻ የተነሳ፣ ሕዝብ ሳይፈልግ ነው ኦሮምኛ በላቲን እንዲጻፍ ያደረጉት። በግድ፣ በጉልበት። ያንንም በማድረጋቸው በተወሰነ መልኩ ተሳክቶላቸዋል። ብዙ የኦሮሞ ልጆች ላቲን ብቻ ነው ማንበብና መጻፍ የሚችሉት። ግን የነዚህ ሰዎች መጠነኛ ስኬት ለኦሮሞ ማህበረሰብ ጉዳት ነው የሆነው። የግእዝ ፊደልን፣ አማርኛ እንዲጠሉ ተደርጎ ስላደጉ ፣ አማርኛ ማንበብን መጻፍ አይችሉም። ከዚህም የተነሳ ከተወሰኑ የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች ውጭ ስራ የማግኘት እድላቸው ዜሮ
Posted in Ethiopian News

ግልጽ መልእክት ለጠ/ሚ አብይ አህመድ – ከኦሮሞ ጽንፈኞች ተፋተው ከሕዝብ ጋር ይወግኑ #ግርማካሳ

ጠ/ሚ አብይ አህመድ፣ «መደመር ውጤት እንደሚያመጣ ያየንበት ተጨባጭ ማስረጃ ነው። ተደምረን ይሄን አሳክተናል። ተደምረን ብዙ ጉዳይ እናሳካለን። በተደጋጋሚ እንዳልነው የሚጮሁ ድምጾች አሉ። እነሱ አቧራዎች ናቸው። እኛ አሻራ ለማሳረፍ ፣ ታሪክ ለመስራት በጋራ ከቆመን ኢትዮጵያ ለሁላችን የምትበቃ ፣ ሁላችን የምታኮራ ሃገር ስለሆነች ይህንን በማድረግ ኢትዮጵያውያን ዳግም አዳዲስ ታሪክ ማስመዝገብ ይችላሉ ፤ ያደርጋሉም የሚል እምነት አለኝ» ሲሉ የችግኝ ተከላዉን ዘመቻ መሳካቱን ገልጸዋል። Deforestation በአገራችን ሳይሆን በአለም ደረጃ ትልቅ ችግር እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ቀደም ሲል የነበሩ የኢትዮጵያ መሪዎች ችግሩን ተረድተው የችግኝ ተከላ ዘመቻ ያደረጉበት ጊዜም ነበር። ጠ/ሚኒትር አብይ አህመድም በተመሳሳይ መልኩ ኢትዮጵያዉያንን በዚህ አንገብጋቢ አጀንዳ ዙሪያ ማንቀሳቀሳቸው ሊያስመሰግናቸው ይገባል። ሆኖም ግን የችግኝ ተከላ ካለው አገራዊ ፋይዳ ባሻገር፣ ችግኝን ለፖለቲካ ፍጆታና ለፕሮፖጋንዳ መጠቀሙ፣ ችግኝን ፖለቲሳይዝ ማድረጉ ግን አሳዛኝ ነው። በአገሪቷ ዜጎች በጅምላ ሲታሰሩ፣ የሰብአዊ መብቶች ሲረገጡ፣ ዜጎች በግፍና በጭካኔ ሲፈናቀሉ፣ በሕወሃት ጊዜ ወደ ነበረበው ስንመለስ … ዝምታን የመረጡና ለስብእና ደንታ የሌላቸው፣ አሁን የአገር ችግር ችግኝ ብቻ የሆነ ይመስል፣ ከሰው ልጅ ችግኝ በልጦባቸው፣ ችግኝ ሲተክሉ የሚያሳይ ፎቶ ለመለጠፍ ሲሽቀዳደሙ ማየታችን፣ ምን ያህል መርህ የመከተል ችግር እንዳለብን በግልጽ የሚያሳይ ነው። ይሄን ብዬ ጠ/ሚአብይ በተናገሩት ላይ ፣ የሚከተለውን ምላሽ እንድሰጥ ይፈቀድልኝ ———- ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ሆይ፣ – የርስዎ አገዛዝ ዜጎችን በጅምላ እያሰረ ፣ – የርስዎ ድርጅት ዘረኛና አፓርታይዳዊ የኬኛ ፖለቲካን እያራመደ፣ – የርስዎ ድርጅት አባላትና መሪዎች በየቦታው
Posted in Ethiopian News

ይድነቃቸው ከበደ የባላደራው አመራር አባላትን ለማግኘት በወህኒ ሞክሮ የሚከተለውን ዘገባ አስፍሯል።

ይድነቃቸው ከበደ፣ የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር በወህኒ የባላደራው አመራር አባላትን አለማግኘት ሞክሮ የሚከተለውን ዘገባ አስፍሯል። ————— ዛሬ ጠዋት ወንድሞቼን የእውነት አምላክ ያስፈታችሁ ለማለት ፤ በግፍ ወደ-ታጎሩበት እስር ቤት ለመጠየቅ ሄጄ ነበር ። የእስር ቤቱን የአሰራር ደንብ ተከትዬ ለ1 ሰዓት ያህል ወረፋዬን ጠብቄ ፤ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ፣ አቶ መርከቡ ሀይሌ እና አቶ ስንታየሁ ቸኮል አግኝቻቸዋለሁ ። ሦስቱም ለጤናቸው ደህና ናቸው ፤ በፊታቸው ላይ የሚታየው የወትሮው የእነሱ መገለጫ የሆነ ፈገግታቸው እና ቅን የሆነዉ ንግግራቸው አሁንም እንዳለ ነው። የጤናቸው ሁኔታ እና የወዳጅነት ሰላምታ ከተለዋዋጥን በኋላ ፤ ሦስቱም ስለ-ተጠረጠሩበትና ታስረው ስለሚገኙበት የሽብር ክስ ሃሳባቸውን አጋርተውኛል ፤ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ሊያውቁልን ይገባል የሚሉትን መልዕክት አስተላልፈዋል ። ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ፦ ” በስመአብ” በማለት የአግራሞት ሳቅ በመሳቅ ፤ ” ከእኔ ጋር ተከሳች የሆኑት 13ቱ ተከሳሾች አንዳቸውንም ከዚህ ቀደም አይቼቸው አላቅም ፣አያውቁኝም አላውቃቸውም ፤ ነገር ግን ከእነሱ ጋር በመሆን ፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት ግድያና መፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገሃል ተብዬ በሽብር ወንጀል ተጠርጥሬ መታሰሬ አስገርሞኛል። በዶ/ር ዐቢይ የሚመራው መንግስት እንዲህ አይነቱ የሐሰት ውንጀላ ውስጥ በዚህ ፍጥነት ይገባል ብዬ አልገመትኩም ነበር ፤ በእኔ ላይ የተፈጸመው መንግስታዊ በቀል ነው ፤ ሃሳቡን በነፃነት የመግለጽ መብቴን ተጠቅሚ ለአገር እና ለወገን ይጠቅማል ብዬ የማስበውን ሁሉ፣ የሌላውን መብት ሳልጋፋ በአገኘሁት አጋጣሚ ከመግለጽ ወደኋላ አላልኩም ። በተለይ በአዲስ አበባ ጉዳይ ሃሳብና ትችት ከመስጠት
Posted in Ethiopian News

መለያየት ቀላል ነው፣ አንድ ማድረግ ከባድ ነው #ግርማካሳ

ጃዋር የኦሮሞ ብሄረተኛ አክቲቪስት ነው። ኢትዮጵያዊ ነኝ ስለማለቱ የማውቀው ነገር የለም። ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ያለን ሰው በግድ ኢትዮጵያዊ ነህ ልለው አልችልም። ኢትዮጵያዊ አይደለሁም የማለት መብቱ ነውና። ኦሮሞ ነኝ ስለሚል ግን ኦሮሞ ነው። እኔ ግን የኦሮሞ አያቶች ቢኖሩኝም ራሴን ኦሮሞ ነኝ ብዬ አልጠራም። በጎጃሜና መንዜ አያቶቼ ምክንያት አማራ ነኝ እንደማልለው። እንኳን “ኦሮሞ፣ አማራ” ልል ቀርቶ ሌላውም ኦሮሞ፣ አማራ ሲል አይመቸኝም። ጃዋር መሐመድ በኢትዮጵያ ውስጥ በክፉም ሆነ በበጎ ብዙ የሚጠራ ሰው ነው። ታዋቂ ነው። በተለያዩ ጊዜያትም ይህ ሰው በሚያራምደው ፖለቲካ ዙሪያ ጠንካራ ትችቶችን አቅርቤ አውቃለሁ። በግሌ በአሁኑ ወቅት በአገራችን ትልቅ ችግር እየፈጠሩ ያሉትም እነ ጃዋር ያሉበት የኦሮሞ ጽንፈኛ ፖለቲከኞችና አክቲቮስቶች እንደመሆናቸው፣ የነርሱ እንቅስቃሴ ላይ ብእሮቼ የተሳሉ ናቸው። ታዲያ አንድ አብርሃም ለማ የሚባል የኦሮሞ ብሄረተኛ፣ በነጃዋር ዙሪያ የምጽፈውን ተመልከቶ፣ ‹አታስበዉ ጀዋር እነዳንተ ቃዥቶ አይደለም እዚህ የደረሰዉ። ቀን ሌሊት እየስራ ነዉ፡፡ ወደድክም ጠላህም ጀዋር የተግባርና የመርህ ሰዉ ነዉ፡፡ስለማታዉቀዉ ስለሱ አዉርቶ ታዋቂ መሆን አይቻልም፡፡ከቻልክ ከሱ የተሻለ ስራ» ፣ የሚል አስተያየት ሰጠኝ። እኔም የመለስኩለትን እንደሚከተለው ላጋራችሁ ወደድኩ። «ወዳጄ ማፍርስ ቀላል ነው፣ መገንባት ከባድ ነው። ማለያየት ቀላል ነው። አንድ ማድረግ ከባድ ነው። መረበሽ ቀላል ነው። ሰላም ማምጣት ከባድ ነው። ዘርን ሰብኮ ደጋፊ ማሰባሰብ ቀላል ነው። ፍቅርን ሰብኮ ሰውን ማዛመድ ከባድ ነው። መጥላት ቀላል ነው። መውደድ ከባድ ነው። የጎሳ ፖለቲካን ማራመድ ቀላል ነው። የአንድነት ፖለቲካን ማካሄድ ከባድ ነው። ብሶት
Posted in Ethiopian News

‎ዶ/ር አቢይ የአክራሪ ኦነጋዊያን አይዲኦሎጂ የትሮዣን ፈረስ ወይስ ኢትዮጵያዊነት የዶ/ር አቢይ የትሮዣን ፈረስ??-ወንድወሰን ተክሉ

**አንድ -መነሻየዶ/ር አቢይ መራሹ የኦዴፓ መንግስት በትረስልጣኑን የጨበጠው በሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግልና ብሎም መጨረሻ ላይ የማሸነፊያዋን ጎል (Penalty )ባስቆጠረው በአዴፓ ቢሆንም ይህ የአዴፓና ብሎም መላው የአማራ ህዝብ ለለውጥ ያደረገው ታላቅ ተጋድሎ፣መስዋእትነትና ወዳጃዊ ወገንተኝነት በዶ/ር አቢይ የሚመራውን ኦዴፓ መሰሪ የሆነ የክህደት እርምጃ እንዲወስድበት የልብ ልብ ከመስጠትና አማራ ተኮር ሴራ እንዲያራምድ ከማድረግ ውጭ ለነገደ አማራ ህዝብም ሆነ ለአዴፓ የፈየደው ነገር እንደሌለ ዛሬ ላይ በእርግጠኝነት ለመናገር ያስገደዱን ተግባራት ሲፈጸሙ እያየን ነው፡፡እንደ ሀገር ኢትዮጵያ እንደማህበረሰብ ደግሞ የነገደ አማራ ህዝብ የኦዴፓ መራሹ ሴራ ገፈት ቀማሽ በመሆን በህልውናቸው ላይ ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦ ይገኛል የሚሉ ድምጾችን ተአማኒነትን የሚገልጹ በርካታ አመላካች እርምጃዎች ሲወሰዱ በአንክሮ ለማየት ተችሏል፡፡ ከሶስት ሳምንት በፊት በባህር ዳር የተከሰተው አደጋ እንደ አቢይ መራሹ የኦዴፓ መንግስት አገላለጽ «መፈንቅለ መንግስት» ሁኔታን ተከትሎ በነገደ አማራ ላይ የተከፈተው ሁሉን አቀፍ ዘመቻ፣የአዲስ አበባ ጉዳይ፣የአክራሪ ኦነጋዊያን አጀንዳ ያላቸው የኦሮሞ ፖለቲከኞች አይገፌ መሆን፣የጠምሩ ለዴሞክራሲና ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ላይ ያላቸው አቋም ከጠቋሚ ኦዴፓዊ ድርጊቶች ውስጥ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ይፋዊ ተግባራት ሲሆኑ ከእነዚህ ይፋዊ ተግባራቶች ሌላ ከመጋረጃው ጀርባ የተወጠኑትንና የታቀዱትን ዓላማዎች ማየቱ ደግሞ እንደ ሀገር አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብና ሉአላዊቷ ኢትዮጵያን ህልውናን እና እንደ ነገድ ደግሞ የነገደ አማራን ህልውናን ምን ያህል ለአደጋ የተጋለጡ ስለመሆናቸው እንድናይ ያስገድደናል፡፡ ነገሮች በፍጥነት እየተለዋወጡ በሚሄዱበት በአሁኑ ሰዓት በዶ/ር አቢይ የሚመራው የኦዴፓ መንግስት የዜግነት ፖለቲካን እናራምዳለን ከሚሉ የአንድነት ጎራው ዘንድ የሚደግፉት
Posted in Ethiopian News

በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የባላደራውን ስብሰባ ሕጋዊ አይደለም ማለቱ ተሰማ

የባላደራው ምክር ቤት በአገር ውስጥ ሰላማዊ የሆነ እንቅስቅሴዉን እንዳያደረግ በኦህዴድ/ኦዴፓ በሚመራው አገዛዝ እመሰናክሎች እየገጠሙት እንደሆነ ይታወቃል። በቅርቡም ሰኔ 15 የተፈጠረው የባለስልጣናት ግድያን እንደ ሰበብ በመዉሰድ . በርካታ አመራር አባላቱ በሽብርተኝነት ክስ ታስረዋል። በጀርመን የኢትዮጵያ መንግስት ተጠሪ የሆነው በበርሊን የኢትዮጵያ እምባሲ ባለስልጣናት ባላደራው በአውሮፓ ለማድረግ ያሰበውን እንቅስቃሴ በመቃወም ሕግ ወጥ ብለዉታል። “የባለአደራ ምክር ቤት በጀርመን የሚያደርገው ስብሰባ ተቀባይነት የለውም” ሲል በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ ባላአደራው ም/ቤት በበኩሉ ቅስቀሳው “በሀገር ውስጥ ያለውን ጭቆና የሚያሳይ ነው” ብሎታል። የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በአምስት የአውሮፓ ከተሞች ስብሰባ ለማድረግ ያሰበው የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት እንቅስቃሴው ህጋዊ አይደለም በማለት በጀርመን ያኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡ የባለአደራው ም/ቤት በበኩሉ አስተያየቱ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ጭቆና የሚያሳይ ነው ብሏል፡፡ በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዳያስፖራ እና ኮንሱላር ክፍል አንደኛ ሚኒስተር አቶ ከበደ በየነ ባስተላለፉት መልእክት “የአዲስ አበባ ባለ አደራ ም/ቤት በአገር ቤትም ይሁን በውጭ አገር የሚያካሄደውን እንቅስቃሴ ኢ-ህገመንግስታዊ ፤ በኢትዮጵያ ሥርዓት አልበኝነትን የሚያስፋፋ እና የአገሪቱን ሰላም የሚያደፈርስ ስለሆነ ኢትዮጵያን የምንወድ በሙሉ ከህገወጥ ድርጊት መቆጠብ ይኖርብናል።” የሚለው የሃላፊውን አስተያየት ተከትሎ የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት ዋና ሰብሳቢ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለኢትዮ ታይምስ እንደገለፀው “አስተያየቱ ከእውነት የራቀ እና የሚያሳዝን ነው፡፡ ሀጋዊ መሆናችንን እና በሰላሚዊ መንገድ መነቀሳቀሳችን በምነሰጠው መግለጫና የራሳችን ቢሮ እንዳለን ይታወቃል፡፡ አስተያየቱ ሃገር ውስጥ ያለውን ጭቆና የሚያሳይ ሲሆን ሰዎች በሰላማዊ መንገድ የመንቀሳቀስ መብታቸውን የሚጋፋም
Posted in Ethiopian News

የጅምላ እስር ፣ በባላደራው ላይ የሚደረገው ወከባ …ይቁም – መኢአድና ስድስት ድርጅቶች

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ህብረት (ኢዴህ)፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ)፣ የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ ፓርቲ (ኦነንፓ)፣ የአፋር ሕዝብ ነፃነት ፓርቲ (አሕነፓ) እና የአፋር ሕዝብ ፍትሃዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አሕፍዴፓ) በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፣ በመግለጫቸው  በሕወሃት ጊዜ ይታይ የነበረው የሰብአዎ መብት ረገጣ እየቆጠቆጠ መምጣቱና በፊት ወደነበረው ሁኔተ የመመለስ ዝንባሌ እንዳለ በመገልጽ መንግስት በአስቸኳይ ማሻሻያዎችን በማድረግ ለዜጎች መብት እንዲቆም ጠይቀዋል። በመግለጫው ሰባት ነጥቦች የተቀመጡ ሲሆን፣ ድርጅቶቹ በተለየም በጋዜጠኛና ሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንደር ነጋ የሚመራውን የባላደራውን ምክር ቤትን በስም በመጥቀስ ፣ ንቅናቄው በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የሚያራምደውን እንቅስቃሴ ያለምንም ችግር ማድረግ እንዳለበት በማስቀመጥ፣ ለባላደራው አጋርነታቸው ገልጸዋል። የባላደራው ምክር ቤት፣ የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድን “ጦርነት ውስጥ ነው የምንገባው” ንግግር ተከትሎ በርካታ የኦህዴድ ባለስልጣናት ባላደራው ላይ ተመሳሳይ ዛቻ ማድረጋቸው፣ ባላደራው ስብሰባዎች እንዳያደረግ፣ ጋዜጣዊ መገጫዎችን እንዳይሰጥ መከልከሉና አባላቱም እየታሰሩበት መሆኑ ይታወቃል። ድርጅቶቹ በመገጫቸው ያስቀመጧቸው  አሁን እየተወሰደ ያለው ዘርን መሰረት ያደረገ እስራት፣ ጅምላ ፍርጃ በአስቸኳይ ቆሞ ህግን መሰረት ያደረገ አሰራር እንዲዘረጋ፣ በመላ አገሪቱ የሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎችን በአፋጣኝና ተገቢ በሆነ መልኩ ምላሽ መስጠት፣ በሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ህይወታቸው ባለፈው ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት ጉዳይ በገለልተኛ ወገን ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ፣የሰኔ 15ቱን ግድያ ተከትሎ ያለበቂ ማስረጃ በጅምላ በየቦታው የታሰሩ የመንግስት ባለሥልጣናት፣ የፓርቲ አመራሮች አባላት እና ንፁሀን ዜጎች በአስቸኳይ
Posted in Ethiopian News

የዘር አወቃቀሩና ፖለቲካው ከቀጠለ አገር ትፈርሳለች፣ ደም ይፈሳል #ግርማካሳ

የክልሉ ባለስልጣናት ከተናገሩትና እንደ ቢቢሲ፣ ሮዮተርስ ያሉ የአለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ፣ እንዲሁም እንደ ኢሳት ያሉ ሜዲያዎች ከዘገቡት ለመረዳት እንደሚቻለው፣ ኢጄቶ የተባለው ቡድን፣ ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም፣ በጀመረውና ባልተሳካለት የሲዳማ ክልልን በጉልበት የማወጅ እንቅስቃሴ፣ ከሃያ በላይ ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአዋሳ አንድ ወጣት ግንባሩ ላይ በጥይት ተመቶ ወዲያው እንደሞተ፣ ሶስት ቆስለው የሕክምና እርዳታ ቢደረግላቸው መትረፍ እንዳልቻሉ ኢሳት ዘግቧል። ቢቢሲ በወንዶ ገነት ሶስት ፣ ሮይተርስ ደግሞ በዋተራ ካሳ አስራ ሶስት ኢትዮጵያውይን መገደላቸውን ዘግበዋል። እነዚህ በግልጽ የታወቁና የተረጋገጡ ሲሆኑ የሟቾች ቁጥር ከመቶ ፣ የቆሰሉ ደግሞ ከአራት መቶ በላይ እንደሆኑ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በሃገረ ሰላም 26፣ በወንዶገነት 8፣ በዳሌ 5፣ በላኮ 6፣ በአገታ ጉኮ 5፣ በአፋራራ 2፣ በአለታ 2 ዜጎች መገደላቸውን ሲዳማ ፔጅ የተሰኘው ገጽ አስፍሯል። የተወሰኑት ሕይወታቸው ያለፈው ከታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ሲሆን፣ ኤጄቶዎች በግፍ የገደሉዋቸው የሌሎች ማህበረሰባት አባላትም ቁጥር ብዙ ነውና በንዴትና በበቀል፣ በጥላቻ፣ ሲዳማ ባልሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የደረሰውም ዘር ተኮር ጥቃት ጥቃት በጣም አስከፊ ነበር። ለምሳሌ በሃገረ ሰላም አቶ የንዬ የሚባሉ ግለሰብ በኤጀቶዎች በተፈፀመባቸው ድብደባ ተጎድተው ጤና ጣቢያ ገብተው የነበረ ቢሆንም፣ በነጋታው፣ ልጃቸው ሊጠይቃቸው ሄዶ ሳለ፣ አጄቶዎች በድንገት ጠያቂ መስለው፣ ጤና ጣቢያ ውስጥ ገብተው አባትና ልጅን በቀርቀሃ ዱላ ቀጥቅጠው መግደላቸውን ከስፍራው የደረሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በድንጋይ ተወግረው የሞቱም ብዙ ናቸው። በዜጎች ሕይወት ላይ ከደረሰው አሳዛኝ ጥፋት በተጨማሪ በርካታ ሱቆች፣
Posted in Ethiopian News

እነ ዶ/ር አብይ ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ለመቆም ድፍረቱ ይኖራቸው ይሆን? #ግርማካሳ

አንዳንዶች ኢትዮጵያ ትፈርሳለች የሚል ስጋት አላቸው። እኔ ደግሞ ምንም ስጋት የለኝም። የኛ ህዝብ ትግሬ፣ በሉት ኦሮሞ፣ አማራ በሉት ሲዳማ፣ ጉራጌ በሉት አፋር….አንድ ሕዝብ ነው። የተሳሰረ፣ ለዘመናት አብሮ የኖረ፣ ትልቅ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ስነ-ምግባርና ጨዋነት ያለው። ችግሩ ያለው ፡ አንደኛ – ሕወሃትና ኦነግ የዘረጉትና የረጩት የዘር ፖለቲካ ላይ ነው። የዘር አወቃቀሩና ኢትዮጵያዊነት፣ አንድነት፣ መተሳሰርና መደመር ላይ ሳይሆን ልዩነት ላይ ያተኮረው ሕግ መንግስት መሆኑ ነው። ሁለተኛ – የለማ ቲም የሚባለው የ”ለውጥ” ሃይል፣ አሁን አገሪቷን ከዘር ፖለቲካ ለማውጣት በበቂ ሁኔታ እንቅስቅሴ ማድረግ አለመቻሉ ነው። የድሮውም የተበላሸና የቀረቀሰ መኪና ይዘው፣ የሹፌሮቹን ቦታ እነርሱ ተክተው እናሻግራቹሃለን ማለታቸው ነው። የኢሕአዴግ እህት ድርጅቶች የዘር አሰራራቸውን ትተው ከተዋሃዱ፣ ሕገ መንግስቱንና የፌዴራል አወቃቀሩን ለማስተካከል ከሞከሩ፣ ሹፌሩን ብቻ ሳይሆን መኪናዉን ቀየሩ እንደማለት ስለሚሆን ፣ እመኑኝ፣ ነገሮች ይስተካከላሉ። የሚቀጥለውም ምርጫ ሰላማዊና ፍትሃዊ እንዲሆን ማድረግ ይችላሉ።ማሻገር ይችላሉ። ይሄን ሲያደርጉ በሕወሃቶችና እንደ ኦነግ፣ ጃዋር ባሉ ጽንፈኞች ከፍተኛ ተቃዉሞ ይገጥማቸዋል። ሕወሃቶችና እነ ጃዋርም በቅንጅት ፣ በትግራይና በአንዳንድ የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች (በዋናነት ወለጋ፣ ምእራብ አርሲና ባሌ..) ፣ እንዲሁም ኢጄቶዎችን በማስተባብር በሲዳማ ዞን ተቃዉሞዎችን ሊያስነሱ ይችላሉ። የጃዋር ቀኝ እጅ የሆነው ሕዝቄል ጋቢሳ በመቀሌ ተገኝቶ ሲናገር የነበረው ጸረ-ኢትዮጵያ ንግግሮችን፣ በሕወሃትና በኦሮሞ ጽንፈኞች ያለውም መቀራረብ እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። በነዚህ ጥቂት ጽንፈኞች ዘንድ ተቃውሞ ሊነሳ ቢችልም፣ በአማራ ክልል፣ በደቡብ ክልል፣ በኦሮሞ ክልል እንደ ሸዋ፣ አርሲ፣ ጂማ፣ ኢሊባቡር ..ባሉ አካባቢዎች፣
Posted in Ethiopian News

ኢጄቶን አደብ ማስገዛት ያስፈለጋል እያልኩ እንሆ መፍትሄው ለሲዳማ  #ግርማካሳ

በሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሰረት ከኦሮሞ፣ አማራ፣ ሶማሌና ትግሬ ቀጥሎ በሕዝብ ብዛት ትልቁ የሲዳማ ማህበረሰብ ነው። 3% የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲዳማ እንደሆነ ነው የሚነገረው። ወደ 3 ሚሊዮን ይጠጋሉ።ጋምቤላዎች፣ ቢኔሻንጉል ጉሞዞች፣ አፋሮች ከሲዳማዎች ያነሱ ናቸው በቅጡር። ከሲዳማዎች ብቻ ሳይሆን ከወልያታዎችና ከጉራጌጌዎችም …ያነሱ ናቸው። ግን ለነርሱ ክልል ተሸንሽኖላቸዋል፡ ሃረሬዎች አስር ሺህ አይሞሉም። የኢትዮጵያ ህዝብ 0.001% አካባቢ ናቸው። ግን ለሃረሬዎች ክልል ተሰጥቷቸዋል። ለሃረሬዎች ክልል ተፈቅዶ ፣ ለሲዳማዎች መከልከሉ በምንም መስፈርት ትክክል ነበር ማለት አይቻልም። በርግጥም ሲዳማዎች ‘እኛ ለምን ክልል አይሰጠንም ?” ብለው መጠየቃቸው ያለ ምንም ጥርጥር ትክክለኛ ናቸው። ይህ በሲዳማዎች ላይ የታየው ኢፍትሃዊነት በራሱ አሁን ያለው አከላለል በደንብ ሳይጠና የተተገበረ፣ ብዙ ግድፈቶች ያሉትና የተመሰቃቀለ መሆኑን አመላካች ነው። ሆኖም ግን የሲዳማ ክልል ጥያቄ ጉዳይ በተያያዥ የሚያስከትለው በርካታ ቀውሶችም እንደሚኖሩ መዘንጋት አያስፈለግም። ምን አልባትም ይህ ቀውስ ራሱ የሲዳማ ማህበረሰብን ችግር ውስጥ ሊከትም የሚችል ነው። የሲዳማ ወገኖች፣ በተለይም የአገር ሽማግሌዎች ነገሩን ሰፋ አድርገው በመመልከት ፣ ለማህበረሰቡ ከምንም በላይ የሚጠቅመው፣  ሰላምና ከሌሎች ጋር በፍቅር ተሳስሮ መኖሩ መሆኑን በማሳሰብ፣  በተለይም እንደ ጃዋር ባሉ የኦሮሞ ጽንፈኞች በስተጀርባ እየተገፉ ያሉ፣ ራሳቸውን ኢጂቶ ብለው የሚጠሩና  ችግር እየፈጠሩ ያሉ ወጣቶች ማስተማርና ማግባባት ቢጀምሩ ጥሩ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ። በሲዳማ ያለውን ጥያቄ እነዚህ የሕግ ማእቀፍ የሌላቸው ኢጄቶዎች በተወሰነ መልኩ፣  እንደ ጃዋር መሐመድ ካሉ የኦሮሞ ጽንፈኞች የሐሳብ፣ የገንዘብና የሕዝብ ግንኙነት ድጋፍ እያገኙ ጉዳዩን ከመጠን በላይ
Posted in Ethiopian News

አዴፓ ከኦዴፓ ጋር ያለውን ግንኙነት መመርመር አለበት #ግርማካሳ

አቶ ዮሐንስ ቧያለው የአማራ ክልል ርእስ መስተዳደር ሆነው ሊመረጡ እንደሚችሉ አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ።  ምን አልባት ከአዴፓዎች፣ ከአዴፓ ውስጥ አዋቂዎችና የቀድሞ ብአዴኖች ከነበሩት ውጭ፣ ስለ አቶ ዮሐንስ ብዙ ሰው በቂ መረጃ ይኖረዋል ብዬ አላስብም። አቶ ዮሐንስም ሆነ ሌላ አመራር፣ በሰኔ 15 የባህር ዳሩ ግድያ  ሕይወታቸው ያለፈውን  ዶ/ር አምባቸው መኮንን ተክተው በአማራ ክልል ርእስ መስተዳደር ሲሆኑ፣ ከፊታቸው ትልቅ ፈተናዎች ይጠብቃቸል። ከነዚህ ፈተናዎች  በቀዳሚነት የሚጠቀሰው አንዱ ፈተና፣  የሚያጠነጥነው አዴፓ ከኦዴፓ ጋር የሚኖረውን ግንኙነት በተመለከተ ነው። አዲሱ ርእስ መስተዳደር ከኦዴፓ ጋር የሕዝቡን ፍላጎት በማዳመጥ፣ በመርህና በእኩልነት ላይ ተመርኩዞ ይሰራሉ ወይ?  በተለይም በኦዴፓ ያሉ አፍራሽ ጽንፈኞችን የመጋፈጥ ድፍረት ይኖራቸዋል ወይ? የሚሉት ጥያቄዎች ብዙዎች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ናቸው። ኦዴፓ በፌዴራል መንግስት ስልጣን የያዘው በአዴፓ ድጋፍ እንደሆነ ራሳቸው ኦዴፓዎች ይክዱታል ብዬ አላስብም። አዴፓዎች ባይኖሩ ኖሮ፣ ኦዴፓዎችን  የሕወሃት ሃይል ሊጨፈልቃቸው እንደሚችል የሚታወቅ ነው ። አዴፓዎች ከኦዴፓዎች ጋር አብረው መስራት የፈለጉትም በቅንነትና አምነዋቸው ስለነበረ ነው ። አማራ፣ ኦሮሞ .. ሳይባል እንደ ኢትዮጵያዊያን በጋራ አብረን አገራችንን እናሳድጋለን በሚል ትልቅ ተስፋና መተማመን። ኦዴፓዎች ግን ስልጣን ሲይዙ ተስገበገቡ። ተረኞችን ነን በሚል ቁልፍ ቁልፍ የሚባሉ ቦታዎችን ያዙ ። (ምንም እንኳን ዶ/ር አብይ ያ እንዳልሆነ በአደባባይ ቢናገሩም፣ የሚወጡት መረጃዎች የሚያሳዩት ግን ኦዴፓዎች ዋና ዋና የሚባሉ ቦታዎችን መያዛቸውን ነው) ። የጽንፈኛ ኦሮሞዎችን ፍላጎት ለማሳካት ሲስተማቲክ በሆነ መንገድ መንቀሳቀስ ጀመሩ። “እኩል አብረን እንደግ” ሳይሆን “ኦሮሞ ይቅደም፣ የኦሮሞ
Posted in Ethiopian News

የአማራ ብሄረተኝነት ትልቅ ስጋት ነው፣ ግን መፍትሄው እነ ዶ/ር አብይ እጅ ውስጥ ነው ያለው #ግርማካሳ

  አንዳንድ ሰዎች የአማራ ብሄረተኝነት በጣም አደገኛ ደረጃ ደርሷል ይላሉ። ከነዚህ ሰዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ይገኙበታል። አንድ ወቅት በሰጡት አስተያየት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ “የአማራ ናሽናሊዝም ወደ ሚያስፈራ ደራጃ እያደገ ነው” ብለው ነበር የተናገሩት። የአማራ ብሄረተኝነት ስጋት ነው ተብሎ ከታሰበ፣ በቀዳሚነት ይሄ ከጥቂት አመታት በፊት ያልነበረ ብሄረተኝነት እንዴት በአጭር ጊዜ   ውስጥ አሁን የደረሰበት ደረጃ መድረስ ቻለ ብለን መመርመር ያለብን መሰለኝ።  መፍትሄ ወደምንለው ከመሄዳችን በፊት የችግሩን ምንጭ መረዳት አስፈላጊ ነው። የአማራ ብሄረተኝነትን የተወለደው አማራ-ጠል በሆኑ የትግራይና የኦሮሞ ብሄረተኝነት ነው። ስልጣን ላይ የነበሩና አሁንም ያሉ የኦሮሞ(ኦነግ/ኦህዴድ) እና የትግራይ (ሕወሃት) ብሄረተኛ ፖለቲከኞች፣  አሁን ሕግ መንግህስት የሚባለውን ሲያረቁ፣ በዘር ላይ እንዲያተኩር ነው ያደረጉት። ክልል የሚሏቸው የፌዴራል መስተዳድሮች የተዘረጉት በዘር ነው። ከአማራ ክልል ውጭና በአማራ ክልል ውስጥም የኦሮሞ ዞን(ከሚሴ) ውስጥ ፣ አማራዎች እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየተቆጠሩ  ከፍተኛ በደልና ግፍ ላለፉት ሃያ ሰምንስት አመታት ሲፈጸምባቸው ነበር። አማራው ኢትዮጵያዊነቴ ይበቃኛል ብሎ ሲቆም፣ ነፍጠኛ፣ ትምክህተኛ ተብሎ ተጠቃ። ተፈናቀለ፣ ተገደለ። አማራ ተብሎ፣ ተነጥሎ፣ በስርዓቱና በመንግስታዊ አሰራሩ፣ በደልና ግፍ እየደረሰበት ስለሆነም፣ ለሕልውናው ሲል፣ በአማራ ስም መደረጃት ተፈለገ። የአማራ ብሄረተኘነትም አቆጥቁጦ በእግሩ መሄድ ጀመረ። በዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኦዴፓ አገዛዝ፣ ከሰኔ 15ቱ የባህር ዳርና የአዲስ አበባ የባለስልጣናትን መሞትን ተከትሎ፣  “መፈንቀለ መንግስት” ብለው የጠሩትን፣ የራሳቸው የኢሕአዴጎች የርስ በርስ ሽኩቻንና መገዳደልን፣ እንደ ሰበብና መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ ከነርሱ የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው
Posted in Ethiopian News

ለጀነራል አሳምነው ቀብር የላሊበላ ህዝብ በነቂስ መውጣቱ ተዘገበ

ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት የሆኑት የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ሰኔ 19 ቀን 2011 ዓ.ም በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በቤተ ጊዮርጊስ የቀብር ቦታ ተፈፅሟል። ለስርዓተ ቀብሩም የከተማው ሕዝብ በነቂስ ወቷል። የከተማው ነዋሪና የቀብር ሥነስርዓት አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አባይ ወዳጀ አስክሬኑ የእርሳቸው መሆኑን ሳጥናቸውን ከፍተው አረጋግጠዋል። የጄኔራሉን አስክሬን አጅቦ የመጣ የመንግሥት አካል አልነበረም። አስክሬኑ ከአውሮፕላን ማረፊያ ወደ ተዘጋጀለት ማረፊያ አደባባይ ተብሎ በሚጠራ ሥፍራ ያረፈ ሲሆን ሌሊቱን ሙሉ ፀሎተ ፍትሃት ሲደረግላቸው፤ ነዋሪዎችም ሃዘናቸውን ሲገልፁ አድረዋል። ዛሬም ከተለያዩ አካባቢዎች በመኪና የመጡ ወጣቶችን ጨምሮ ፖሊስና ሚሊሻ፣ ከተማ አስተዳደሩ፣ ነዋሪዎች በጋራ በመሆን በደማቅ ሁኔታ ሥነ ስርዓቱን ለመፈፀም የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርጉ ቆይተዋል። ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በተኩስ ከተማዋ ተናውጣለች [በሃዘን ወቅት በሚተኮስ ተኩስ]። ‘አሳምነው ፅጌ እንዲህ ዓይነት ድርጊት አይፈፅምም፤ ይጣራልን። አማራ ክልል አንድነት እንዳይኖረው የተደረገ ሴራ ነው። የታሰሩት እነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ ይፈቱልን ” የሚሉ መፈክሮች ሲሰሙ ውለዋል። በአካባቢው እንዲህ ዓይነት ጥያቄዎች ይነሱ እንጂ በከተማው የተፈጠረ የፀጥታ ችግር አልነበረም። ከትናንት ከሰዓት ጀምሮ ዛሬም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዝግ ነበሩ። “ጄነራል አሳምነው ባለፈው ዓመት ለአሸንድዬ በዓል አከባበር ላሊበላ ተገኝተው ንግግር ሲያደርጉ ‘ከዚህ በኋላ የምኖረው ለአማራ ህዝብ ነው’ ብሎ ስለተናገረ ‘ አማራን ለማጥፋት የተደረገ ሴራ ነው’ የሚሉ ነዋሪዎች መንግሥትን እየኮነኑ፣ ጥይት እየተተኮሱ፤ በፉከራና ቀረርቶ ታጅቦ ሥነ ሥርዓቱ ተከናውኗል። የቢቢሲ አማርኛ ዘገባን መሰረት በማድረግ የተጠናቀረ
Posted in Ethiopian News

የአማራ ሳታለያት ቴሌቭዥንና (አስራት) ራዲዮ ጋዜጠኞች ታሰሩ

የአሥራት ሚዲያ አስተባባሪና መስራች አቶ በሪሁን አዳነ “የመፈንቅለ መንግስት” ተሳታፊ ነህ በሚል ዛሬ በአራዳ ፍርድ ቤት ችሎት ክስ እንደተመሰረተባቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ከአቶ በሪሁን ጋር ወጣት ጌታቸው አምባቸውም ለእስር እንደተዳረገ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ሁለቱም የአስራት ሜዲያ ባልደረቦች በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በጨለማ ቤት ውስጥ እንደታሰሩና ጠያቂም እንደተከለከሉ አስራት ሜዲያ ዘግቧል። ሰኔ አስራ አምስት ቀን ተፈጸመ ያሉትን “መንፈቀለ መንግስትን” ተከትሎ ፣ ከመንግስት ከሚሰጡ እርስ በርሳቸው የሚቃረኑና የተዘበራረቁ መግለጫዎች ውጭ፣ ምን አይነት ገለልተኛ ሆነ ከዚያ ወገኝ የሚሰጥ መግለጫ የሌለ ሲሆን፣ በኦህዴድ/ኦዴፓ የሚመራው ገዢው ፓርቲ ልክ ህወሃት ሲያደርግ እንደነበረው ህዝብ እነርሱ ከሚሰጡት መረጃ ውጭ ሌላ ምንም አይነት መረጃ እንዳያገኝ ኢንተርኔቱን ጠርቅሞ በተለይም በአማራ ክልል ዘግቷል።
Posted in Ethiopian News

“እያጣራን ነው የምናስረው ቀርቶ”፣ ዜጎች በጅምላ እየታሰሩ ነው

ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ፣ በጋዜጠኛና ሰብ አዊ መንብት ተሟጋች እስክንድር ነገአ የሚመራውን የባንደራስ ባላደራው ምክር ቤትን በተመለከተ ጠንካር ታለ፣ ዛቻ አዘል ንግግር መናገራቸው ይታወሳል። ባላደራው የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ፍጹም ሰላማዊና ሕጋዊ መሆናቸው እየታወቀ ጠቅላይ ሚኒስተሩ፣ “ጦርነት እንገጥማለን” ማለታቸው በወቅቱ ከፍተኛ ተቃዉሞ አስነስቶባቸው ነበር። በተመሳሳይ ሁኔታ የገዢው ፓርቲ የኦህዴድ/ኦዴፓ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊም  “በቄሮ ትግል ፌስታሉን ይዞ ከእስር ወጥቶ ሲያበቃ ዛሬ ‘ባለደራ መንግሥት’ ብሎ ራሱን መሾም አልያም ‘ባላተራ መንግስት’ ብሎ ለውጥን ማጣጣል በምንም ስሌት ተቀባይነት የለውም። መንግስታችንን ለመፈታተን ባለተራ ባላደራ እያለ የሚያላዝነውን ወደ ትክክለኛ መስመር ለመመለስ እንሰራለን” ሲሉ የባላደራዉን ሠላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ሃሳብ እንዳለ ገልጸው ነበር። የባላደራው ሰላማዊ እንቅስቃሴ፣ በገዢዎች ስላልተፈለገ፣ ምክር በቱ የአዳራሽ ስብሰባዎችን ፣ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን በአዲስ አበባ ከተማ እንዳያደረግ በተደጋጋሚ ክልከላ የተደረበት ሲሆን፣ ያለፈው ሳምንት በባህር ዳር ህዝብ ጥያቂር ሰኔ 16 ቀን ሕዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ አስቦ የነበረ ቢሆንም በባህር ከአንድ ቀን በፊት በተፈጠረው ቀዉስ ስብሰባው ሊራዘም ችሏል። ሰኔ 15 በአዲስ አበባ በባህር ዳር የተከሰተውው እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ተከትሎ፣ “የምናስርው አጣርተን ነው” የሚል አባባል ሲጠቀሙ የነበሩት የኦህዴዴ/ኦዴፓ አመራሮች የሚቃወሟቸውን ሁሉ ፣ እነርሱ የመፈንቀለ ሙከራ ብለው በጠሩት እንቅስቅሴ ተሳትፋቹሃል በሚል፣ ከተፈጠረው ቀውስ ጋር ያልተገናኙ ዜጎች እያሰሩ ነው። ከዚህ በታች ያሉት አቶ ስንታየሁ ቸኮል የባላደራው ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊና የኢሳት የኦሮምኛ ክፍል ጋዜጠኛ የሆነው አቶ አማኑለም መግስቱ ነው። በዚህ
Posted in Ethiopian News

የጠቅላይ ሚኒስትሩም እጅ ነፃ ነው ብሎ ለማመን የሚያስችል ሁኔታ የለም – ያሬድ ጥበቡ

ባላወቅኩት ምክንያት በተለይ የሁለቱ ጄኔራሎች የሰአረና የአሳምነው ሞት መረረኝ ። ልጅነታቸውን ለህዝብ ትግል የሰጡ ጀግኖች በአልባሌ መንገድ ሲገደሉ ያማል። ጦር ሜዳ ላይ ከጠላት ጋር ተናንቀው መስዋእት ሆነው በነበሩ የለመድነውን “ትግል አይሞትም” እየዘመርን በሸኘናቸው ነበር ። አሟሟታቸው ለቀባሪ እንኳ ለማርዳት አይመችም። ለምን ተገደሉ? ማን ገደላቸው? እንዴት ተገደሉ? ወዘተ የሚሉት ጥያቄዎች ቀላል መልስ አልተገኘላቸውም። የሰአረን ሞት ከክንፈ አሟሟት ጋር የሚያመሳስሉ ብዙዎች ናቸው። እጅግ የበዙ ጥያቄዎች በዜጎች አንደበት እየተመላለሱና እየተነገሩ ነው። ከብዙዎቹ በጥቂቱ የሚነሱት ጥያቄዎች ይህን ይመስላሉ። 1) የአዴፓ ከፍተኛ አመራር እንዴት ቅዳሜ ከሰአት በኋላ በ11 ሰአት ስብሰባ ሊጀምር ቻለ? ምን አጣዳፊ አጀንዳ ቢያጋጥመው ነው በሰንበት ምሽት ስብሰባ የጠራው? የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ደመቀ፣ ለህክምና ወደ ዲሲ በሄዱበት ቀን እንዴት የአመራሩ ስብሰባ ሊጠራ ቻለ? 2)ስብሰባው የጄኔራል አሳምነውን በስልጣን መቀጠል አለመቀጠል ለመወሰን የተጠራ ነበርን? ጄኔራል አሳምነው ስብሰባው የት እንደሚካሄድና በምን አጀንዳ ላይ እንደሚወያይ ያውቁ ነበርን? ስብሰባው ከአዲስ አበባው ባለአደራ ኮሚቴ አባላት መምጣትና በሚቀጥለው ቀን ከሚደረግ ስብሰባ ጋር የተያያዘ ነበርን? ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለዚህ ስለ እሁዱ ስብሰባ መደረግ ሃሳብ (ከንሰርን) ነበራቸውን? እንዲቆም ትእዛዝ ሰጥተው ነበርን? ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እስክንድር ባህርዳር የሄደው ከጄኔራል አሳምነው ጋር መንግስት ሊያውጅ ነው የሚል ፍርሃት ነበራቸውን? ይህን ፍርሃታቸውን ለአዴፓ ከፍተኛ አመራር ገልፀው፣ አስቸኳይ ስብሰባ በቅዳሜ ምሽት የተጠራው ለዚህ ይሆን? ከሆነ የዶክተር አምባቸው አመለካከት ምን ነበር? በዶክተር አምባቸውና በጠቅላይ ሚኒስትሩ መሃል አለመግባባቶች ነበሩን? ዶክተር አምባቸው፣
Posted in Ethiopian News

በገለልተኛ አካል ሳይጣራ ጀነራል አሳምነውን መክሰስ ኢፍትሃዊነት ነው #ግርማካሳ

June 23 2019 የትላንቱ ቀን በጣም የሚያሳዝን ቀን ነው። ለሞቱት ነፍስ ይማር ፣ ለወዳጅ ዘመድም መጽናናቱን ይስጥልን እላለሁ። ከነ ዶ/ር አምባቸውና ጀነራል ሰአረ መኮንን በተጨማሪም ስማቸው የተጠቀሰ ያልተጠቀሰም ብዙ ሞተዋል። ጀነራል አሳምነውንም ገድለዉታልም ይባላል። ያ ሁሉ መሆን አልነበረበት ፣ ግን ሆኗል። እግዚአብሄርን የተመሰገነ ይሁን፣ ዛሬ ነገሮች ተረጋግተው ነው የዋሉት። የፈሰሰ ደም ስለመኖሩ የሰማነው ነገር የለም። ሆኖም ትላንት ለተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት፣ በመመሪያ በተደረገ መልኩ፣ በዘመቻ ጀነራል አሳምነው ጽጌንና አንድ ወገንን፣ demonize የማድረግ፣ የመክሰስ፣ የመወንጀል እንቅስቃሴ እያየን ነው።  በጀነራል አበበ ጁላ የሚመራው የፌዴራል ጦር የአማራ ክልልን ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል ተቆጣጥሯል። አዴፓ ውስጥ በነበሩ አለመስማማቶችና ግብግቦች አፍቃሪ ኦዴፓ የሚባለው አንጃ፣ በመከላከያ ሰራዊት ታግዞ የበላይነቱን በባህር ዳር የያዘ ይመስላል። በክልሉ ያሉ ፣ የክልሉ የጸጥታ ሃላፊዎች እነ ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል የመሳሰሉት በሙሉ እንደታሰሩ እየሰማን ነው። ይሄው አንጃም ለተፈጠረው ቀውስ በመግለጫ ጀነራል አሳምነው ጽጌ እንደመሩት አድርጎ እየለፈፈ ነው። ልክ በደርግ ጊዜ መንግስቱ ሃይለማሪያም እነ ኮሎነል አጥናፉ አባተን ካስረሸነ በኋላ “ከሃዲው አጥናፉ አባተ” እያለ ነጋሪት ሲያስጎስም እንደነበረው፣ አሁንም በጀነራል አሳምነው ጽጌ ላይ ተመሳሳይ ነገር አያየን ነው። የራስን ጉድ ሸፍኖ ሌላው ላይ ብቻ ማላከክ። ጀነራል አሳምነው ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ የሚታወቅ ነገር የለም። ተይዘዋል፣ ተተኩሶባቸው ቆስለዋል፣ ተገድለዋል ..የሚሉ መረጃዎችን እየሰማን ነው። የኦዴፓው አዴፓ፣ “ጀነራል አሳምነው አምልጠዋል” የሚል መግለጫም ሰጥቷል። የሕዝብን ቁጣ ለማብረድ። በኔ እይታ የጀነራሉን
Posted in Amharic News

የኦሮሞ ወታደራዊ ጭፍራ ጥንካሬን አድንቀው የጻፉት አባ ብሕርይ – አቻሜለህ ታምሩ

የአባ ባሕሬይን መጽሐፍ አንብቦ ለጨረሰና የአጻጻፉን ጥራትና የስነ መዋቅሩን ልቀት ላስተዋለ ፊልም የማየት ያህል ቢሰማው አይፈረድበትም። መጽሐፉ በትዝታ አምስት መቶ ዓመትን ወደ ኋላ መልሶ ታሪኩ የተነገረበትን ዘመን የኖሩ ያህል ስሜት ይፈጥራል። ብዙዎቹ ኦነጋውያን ግን የአባ ባሕርይን መጽሐፍና መጽሐፉን ከግዕዝ ወደ አማርኛ በስተ እርጅና ዘመናቸው እረፍት ሳያምራቸው የተረጎሙልንን ፕሮፈሰር ጌታቸው ኃይሌን ሲያብጠለጥሏቸው ይውላሉ። ይህ የውለታ ቢሶቹ ኦነጋውያንና ተከታዮቻቸው አስጸያፊ ተግባር ግን የእውቀት ጾመኛነታቸውንና ድንቁርናቸውን እንዲሁም የበሉበትን ወጪት ሰባሪና የጎረሱበትን እጅ ነካሽ መሆናቸውን ከማሳየቱ በስተቀር ፋይዳ ያለውም። ኦነጋውያን ሕሊና አልባ ነውረኞች ስለሆኑ እንጂ የአስራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መነኩሴ አባ ባሕርይ ፍጹም ሞያዊነትንና ስነ ምግባርን በተላበ መልኩ ባይናቸው ያዩትን የኦሮሞ እውነተኛ ታሪክ በመመዝገባቸው መታሰቢያ ሊቆሙላቸው በተግባና የሚገባቸውን የታላቅ ሰውነት ክብር ሊያጎናጽፏቸው በተገባ ነበር። ዛሬ ታሪክ እንጽፋለች የሚሉን ኦነጋውያን የታሪክ ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች ሁሉ የአባ ባሕርይን ሩብ ያህል ሞያዊና ሚዛናዊ የታሪክ አመዘጋገብ የላቸውም። የአባ ባሕርይን ጠንቃቃ ጸሐፊነትና ሞያዊ ስብዕና ለመገንዘብ ሩቅ ሳንሔድ ራሳቸው አባ ባሕርይ ያስቀመጡልንን ታሪክ ብቻ በማንበብ መጽሐፋቸውን ሲቋጩ ያሰፈሩትን መደምደሚያ ማየቱ ይበቃል። አባ ባሕርይ በመጽሐፋቸው በሙሉ የኦሮሞ አባ ገዳዎች ከደቡብ ኢትዮጵያ ተነስተው ወደ ሰሜን በሚፈልሱበት ወቅት የተቀዳጇቸውን ድሎች እንደወረዱ ሲዘግቡ በተለምዶ በራስ ወገን ወይንም በሌላ አቅጣጫ የተፈጸመን ተግባር እንደ ጀብዱ ማንሳት ባልተለመደበት ዘመን ሆነው ያንን ታሪክ መጻፋቸው የርሳቸውን የተለየ የአጻጻፍ ዘዴና ሚዛናዊ አቀራረብ የሚያሳይ ነው። የአባ ባሕርይ በዘመናቸው ወደር የማይገኝላቸው ምሁርና
Posted in Ethiopian News

በአ/አ ለኦሮሚያ ልዩ ጥቅም እሰራለሁ አለ አዴፓ/ብአዴን፣ ክፍል 1 #ግርማካሳ

ዶ/ር አምባቸው መኮንን የአማራ ክልል ርእስ መስተዳደር፣ የአዲስ አበባ ከተማን አስመልክቶ ከተሳታፊ በተነሳላቸው ጥያቄ፣ በሰጡት ምላሽ ከፍተኛ ተቃዉሞና ዉግዘት አስተናግደዋል። ብዙዎች “ዶ/ር አማባቸው ፈንጂ ረገጡ” እስከማለትም የደረሱ አሉ። ከዚህም የተነሳ አዴፓ/ብአዴን በመግለጫ ማብራሪያ ለመስጠት የተገደደ ሲሆን፣ ዶ/ር አምባቸውም ራሳቸው ከምሁራን ጋር ባደረጉት ስብሰባ፣ ጉዳዩን አንስተው ምላሽ ሰጥተዋል። ዶ/ር አምባቸው አዲስ አበባን በተመለከተ በአምቦ ፣ “አዲስ አበባን በተመለከተ ሕግ መንግስቱ (ወያኔና ኦነግ በሕዝቡ ላይ የጫኑትን ማለታቸው ነው) ያስቀመጠውን የሚሸራርፍ አቋም ማንም የለውም .… የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሕግ መንግስታዊ መብት አለው። ልዩ ሕገ መንግስታዊ መብቱ እንዲከበርለት ደግሞ እኛም እንታገላለን” ነበር ያሉት። “ሕግ መንግስቱ ያስቀመጠውን” ሲሉም አንቀጽ 49ን ማለታቸው እንደሆነ ግልጽ ነው። ይህ በሕግ መንግስቱ ላይ ያለው፣ በአዲስ አበባ የኦሮሚያን ክልል “ልዩ ጥቅም” የተባለው መከበር አለበት ብሎ የሚደነግገው አንቀጽ ፣ ግልጽ ያልሆነና ሆን ተብሎ በአዲስ አበባ ጉዳይ  ላይ ንትርክ ለመፍጠር በሕወሃት ተሰንቅሮ ሕገ መንግስቱን ውስጥ የገባ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ። የዚህ አንቀጽ አሻሚነቱና አወዛጋቢነቱ በብዙ መልኩ ሊገለጽ ይችላል። አንደኛ – አንቀጹ አዲስ አበባ ራሷን በራሷ የማስተዳደር መብት አላት ይልና፣ በሌላ በኩል በአዲስ አበባ የኦሮሞ ክልል ልዩ ጥቅም ይጠበቃል ይላል። ይሄም እርስ በርሱ የሚቃረን፣ የኦሮሞ ክልል በአዲስ አበባ ጉዳይ የይገባኛል ጥያቄ እንዲያቀርብ  የገፋፈውን ምክንያት ሆኗል። ሁለተኛ  – የኦሮሞ ክልል ልዩ ጥቅም ይኖረዋል ብሎ አንቀጹ ሲያስቀምጥ፣ ጥቅሞቹ ምን እንደሆነ አልተገለጸም። “ጥቅም” ማለት ጽ/ቤት አዲስ አበባ ውስጥ
Posted in Ethiopian News

በደብረ ብርሃን/ሸዋ ሕዝቡ በነቂስ አብን በጠራው ስብስበ ወጣ – ናኦሚን በጋሻው

ከተመሰረተ አንድ አመት የሆነው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ዛሬ እሁድ ሰኔ 9 ቀን 2011 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ዞን ዋና ከተማ በታሪካዊቷ ደብረብርሃኑ በጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ ቁጥሩ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ የተገኘ ሲሆን በስብሰባውም ከፍተኛ የድርጅቱ አመራሮች ለሕዝቡ ንግግር አድርገዋል።  ሕዝባዊ ስብሰባው በሁለት ቦታ የተደረገ ሲሆን፣ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በአፄ ዘርአ ያዕቆብ ስታዲየም፤ ከሰዓት በኋላ ከ 8:00 ጀምሮ ደግሞ በሲኒማ ደብረብርሃን አዳራሽ የተሳካ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል። በደብረ ብርሃኑ በተደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ በጣም ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያለው ህዝብ መገኘቱ፣ በአንድ በኩል የአብንን ድርጅታዊ ጥንካሬ የሚያሳይ ሲሆን በሌላ በኩል ክልሉን በሚመራው አዴፓ/ብአዴን ላይ ህዝቡ ተስፋ እየቆረጠ መምጣጡን የሚያመላክት መሆኑን ተንታኞች ይናገራሉ። አብን ምንም እንኳን  በዘዉግ ስም የተደራጀ ቢሆንም፣ የፖለቲካው ፕሮግራሙና ማኒፌስቶ ግን ለዜግነት ፖለቲካ የቀረበ እንደሆነ የሚናገሩት ለአብን ቅርበት ያላቸው ተንታኞች፣ አብን በኢትዮጵያዊነት ላይ እንደማይደራደር፣ በአገሪቷ የዘር ፖለቲካ ለአገር ጉዳት ነው ብሎ እንደሚያምን፣ በኢትዮጵያ ሁሉም የዘዉግ ድርጅቶች ራሳቸውን ካከሰሙ፣ በአገር ደረጃ በዘር መደራጀት ከታገደ፣ አብን በደስታ ራሱን ለማከሰም ወደ አገር አቀፍ ድርጅትነት ለመቀየር ዝግጁ እንደሆነ የሚናገሩት ለአብን ቀርበት ያላቸው ተንታኞች፣ አብን የተደራጀው፣ የአማራን የበላይነት ለማስፈንና አማራን ልዩ ተጠቃሚ ለማድረግ ሳይሆን ፣ ሳይፈልግ ፣ ተገፍቶና፣ ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት በተዘረጋው አማራ-ጠል ፖለቲካ አማራው ላይ ብዙ ፍ ስለደረሰ ራስን ለመከላከል ታስቦ እንደሆነ ይናገራሉ።
Posted in Ethiopian News

የጉራጌ ሕዝብ ከ158 ዓመታት በፊት. . .- አቻሜለህ ታምሩ

የጉራጌ ሕዝብ ከ158 ዓመታት በፊት. . . ሰማዩም ምድሩም የኛ ነው የሚሉን ኦነጋውያን የሚይዙት ቅጣምባሩ ጠፍቷቸዋል። ከሰሞኑ ደግሞ ባሰራጩት በምስል የታገዘ ዜና በጉራጌ ምድር ከ158 ዓመታት በፊት ተቋርጦ ነበር ያሉን የገዳ ስርዓት ማስጀመራቸውን ነግረውናል። እንዲህ አይነት ዜና ሲሰማ ዝም ማለት ተገቢ ባለመሆኑ ከ158 ዓመታት በፊት የጉራጌ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት ጋር ስለነበረው ግንኙነት፣ የነበረውን የውስጥ አስተዳደር ታሪክና ገዳ የሚባለው የወረራና የዘመቻ ስርዓት ወደ በአካባቢው በደረሰበት ወቅት ስለተከተሉ ሁኔታ ሳነብ ከተማርሁት የሚከተለውን ጀባ ብያለሁ። የጉራጌ ምድር ከጥንት ጀመሮ የኢትዮጵያን መንግሥት ያቆሙ ዋናዋና የጦር መሪዎችን ያፈራ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አውራጃ ነበር። ተመዝግቦ ከምናገኘው ታሪክ ብንነሳ እስከ ሞቃድሾ ድረስ የነበረውን የኢትዮጵያ ግዛት ባስተዳድሩት ዐፄ ዐምደ ጽዮን [እ.ኤ.አ. ከ1314 ዓ.ም. – 1344 ዓ.ም. ድረስ የነገሡ] ዜና መዋዕል ውስጥ ጉራጌ ከኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት ጋር ቅርብ ቁርኝት የነበረው ሕዝብ እንደነበር ተጽፎ እናገኛለን። በዘመኑ የጉራጌ አውራጃ የውስጥ አስተዳደር ይመራ የነበረው በጉራጌ ተወላጅ አበጋዞች ነበር። ጉራጌ አውራጃውን ከራሱ በተወለዱ አበጋዞች ያስተዳድር የነበረው ኦሮሞ በገዳ መተዳደር ከመጀመሩ ቢያስ ከ208 ዓመታት በፊትና ኦሮሞ ደቡብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና መካከለኛው ኢትዮጵያን መውረር ከመጀመሩ ከ200 በላይ ዓመታት በፊት ነበር። የኦሮሞ ብሔርተኛው ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን “The Oromo and the Christian Kingdom of Ethiopia” በሚል ማሳተመው መጽሐፉ ገጽ 158 ላይ እንደጻፈው ኦሮሞ በገዳ መመራት የጀመረው እ.ኤ.አ. በ1522 ዓ.ም. እንደሆነና የመጀመሪያው ገዳ “ገዳ መልባ” እንደሚባል ነግሮናል። ጉራጌ ግን
Posted in Ethiopian News

ኦሮምኛ በግእዝ ፊደል የመጻፉን ጥቅም- ከቋንቋ ምሁሩ ዶ/ር ጌታቸው ሃይሌ

የኢትዮጵያ ፊደል፤ ስለ ኢትዮጵያ ፊደል ሌላ ጊዜ ጽፌ ሌላ ቦታ ያሳተምኩትን በመጠኑ ለዋውጬ ላካፍላችሁ። ኢትዮጵያ የትም ከሌላ አገር የማይገኝ የራሷ ፊደል አላት። የሩቅ ምሥራቁን (የቻይናን፥ የኮሪያን . . .) ለብቻ ትተን የቀረውን ስናየው የተለያዩ ቋንቋዎች ፊደሎቻቸው ዝምድና እንዳላቸው ምልክት እናያለን። በላቲንና በኢትዮጵያ ፊደል መካከል ያለው ዝምድና እንኳን ደብዛው ፈጽሞ አልጠፋም። ለምሳሌ፥ እነዚህን እናስተያያቸው፤ አ (A), ተ (t), መ (m), ወ (w), ቀ (q). እዚህ ላይ የኦሮሞ ልሂቃን ቢሰሙት የማይወዱት ነገር አለ። ቁቤ የሚሉት የላቲን ፊደል በብዙ ተዘዋዋሪ ከኛ ፊደል የተወሰደ ነው። ግን ከፊደሎች ሁሉ ከኢትዮጵያው ፊደል ጋር የበለጠ ዝምድና የሚታይበት “የደቡብ ዐረብ” ወይም “የሳባውያን” የሚባለው ፊደል ነው። ሆኖም፥ ብዙ ጥናት ሳይደረግ፥ የፊደሎችን ተመሳሳይነት በማየት ብቻ፥ “ዝምድናቸው አንዱ የሌላውን ከመውሰድ የመጣ ነው” ማለት አይቻልም። ከተቻለ፥ የኢትዮጵያው ከሳባው ወሰደ ከማለት ይልቅ የሳባው ከኢትዮጵያው ቢወስድ ነው የማይባልበት ምክንያት የለም። “አንድ ጥንታዊ ሕዝብ ለራሱ ቋንቋ የፈጠረውን ፊደል ሌሎች ሕዝቦች ወስደው ለራሳቸው ቋንቋ መጻፊያ እንዲሆን አስተካክለውታል። ከነዚህ ሕዝቦች ውስጥ ኢትዮጵያውያንና ሳባውያን ይገኙበታል” ማለትም ይቻላል። ስለ ዓለም ፊደሎች ስንነጋገር በኢትዮጵያ ፊደል ላይ አንድ የሚገርም ነገር እናያለን፤ የሌሎቹ ፊደሎች በ “አ” ጀምረው ሲዘልቁ፥ የኢትዮጵያው የሚጀምረው በ “ሀ” ነው። ይኸ አሰላለፍ ምን ምስጢር ይዞ ይሆን? መልሱ አልተገኘም። ሌላ ተዛማጅ ጥያቄ፥ በያንዳንዱ ቋንቋ ውስጥ ያሉ የቋንቋ ድምፆች እጅግ የተወሰኑ ከሆኑና ማንኛውም ሕዝብ ለቋንቋው ፊደል የሚቀርጸው ለአንድ ድምፅ አንድ ፊደል
Posted in Ethiopian News

ቤቶች ለማፍረስ የአ/አ መስተዳደር ያወጣዉን እቅድ ሃላፊነት የጎደለው ሲል መኢአድ አወገዘው

  በሕዝብ ያልተመረጡትና ከአዲስ አበባ መስተዳደር ሕግ ውጭ በኦደፓ በምክትል ከንቲባነት ማ እረግ እንደ ከንቲባ ሆነው እንዲሰሩ የተሾሙት ኢንጂነር ታከለ ኡማ በቅርቡ በአዲስ አበባ ሕግ ወጥ ናቸው በሚል ከሰላሳ ሺህ በላይ  ቤቶች በአዲስ አበባ ለማፍረስ እቅድ እንዳለ መግለጻቸው ይታወሳል። ይሄንን ተከትሎ በአዲስ አበባ በስፋት እየተንቀሳቀሰ ያለው የባልደራስ ባላደራው ምክር ቤት ጠንካራ የተቃዉሞ መግለጫ ያወጣ ሲሆን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ፣ የኦዴፓው አመራር ኢንጂነር ታከለ ፣ ቤቶች በርግጥም ህወ ወጥ ስለመሆናቸው ምንም አይነት ገለልተኛና ፍትሃዊ ማጣራቶች ሳይደረጉ ፣ ሊፈናቀሉ ያሉ ዜጎችም ቤታቸው ከመፍረሱ የተነሳ ሜዳ ላይ እንደማይወድቁ ምንም አይነት ማስተማመኛና ዝግጅት ሳይደረግ፣ ሌላ ስንት መሰራት ያለባቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች እያሉ ቤቶችን ለማድፈስ መጣደፉ ሰብአዊነት የጎደለው ነው በሚል ጠንካራ ተቃዉሞና ትችት እያቀረቡ ነው። የባላደራው ምክር ቤት ለሰጠውም ጠንካራ መግለጫ ጋአር በመሆን፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) ሰኔ ሰባት ቀን ባወጣው መግለጫ በኢንጄር ታከለ የተሰጠው ቤቶችን የማፍረስ እቅድን አጥብቆ መቃወሙን ገልጿል። ” የከተማ አስተዳደሩ ለልማት በሚል ሰበብ ቤት አፍርሳለሁ ብሎ ባወጣው መግለጫ ፍፁም ኃላፊነት የጎደለው መሆኑን እንገልፃለን፡” ሲል ነበር መኢአድ በኢንጂነር ታከለ ኡማ የሚመራውን የአ/አ ከተማ መስተዳደር ሕግ ወጥ ቤቶችን የማፍረስ እቅድ  ያወገዘው። እንደ ለገጣፎ ባሉ አካባቢዎች በኦዴፓ ባለስልጣናት በርካታ ዜጎች በግፍና በጭካኔ መፈናቀላቸውም ይታወቃል። ተፈናቃዮችም በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ችግር ውስጥ ያሉ ሲሆን ምንም አይነት መንግስታዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንዳልሆነ መረጃዎች ይጠቁሉ።
Posted in Ethiopian News

የዶ/ር አብይ ችግር ባረጃ ጎማ/መኪና ህዝብን ለማሻገር መሞከራቸው ነው #ግርማካሳ

ለዶ/ር አብይ፣ ለአቶ ለማ መገርሳና ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ትልቅ አክብሮት አለኝ። የለማ ቲም ለሚባለው ማለት ነው። አቶ ገዱና አቶ ለማ ከክልል ርእስ መስተዳደርነት ለቀዋል። ዶ/ር አብይ ግን አሁንም በሃላፊነታቸው ላይ ነው ያሉት።የፈለገውን የማድረግ አቅም ግን የላቸውም። ሕጋዊ ስልጣን  አላቸው። ጠቅላይ ሚኒስተር እንደመሆናቸው በሕግ መንግስቱ መሰረት ተጠሪነታቸው ለፓርላማው ነው። ግን በኢሕአዴግ ኢትዮጵያ ከሕግ መንግስቱ በተጻራሪ ፓርላማው ሳይሆን ፓርቲው ነው ትልቅ ስልጣን ያለው። ከአንድ የፓርላማ ተወካይ ይልቅ፣ አንድ የኢሕአዴግ አባል የበለጠ የፖለቲካ ሃይል አለው። በፓርቲው አሰራር ደግሞ ፣ የፓርቲው አመራሮች ነው በጋራ የሚወስኑት። አሁን ባለው የኢሕአዴግ አሰራር ፣ድርጅቱ የወሰነዉን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያስፈጽሙት። አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚለው ፣ ድርጅታዊ ማ’እከላዊነት የጠበቀ አሰራር ማለት ነው። ከድርጅቱ ውሳኔ ውጭ ምንም ማድረግ አይችሉም። በፓርላማ የሕወሃትና የኦህዶእድ/ኦዴፓ ተወካዮች ድምጻቸው ከ 210 አይበልጥም። የደሃዴንና የአዴፓ/ብአዴን ተወካዮች ከ280 በላይ ናቸው። 547 ወንበሮች ባለው ፓርላማ አብልጫ ድምጽ ነው ያላቸው።በኢሕአዴግ ድርጅቱ ውስጥ ከሄድን ግን ህወሃትና ኦህዴድ በጋራ ሆነው ግማሹን መቀመጫ ይዘዋል። ህወሃት ብቻ በፓርላማ 6.5% መቀመጫ ሲኖራት በኢሕአዴግ ውስጥ ግን 25% መቀመጫ ነው ያላት። በዚህ ምክንያት አብዛኛው ኦህዴድ/ኦዴፓዎች ህወሃቶች የተጀመረዉን ለውጥ ስለማይፈልጉ፣ ዶ/ር አብይ በድርጅቱ ውስጥ ያንን ያህል ስልጣን የለውም። ድርጅቱን አሳምኖ ድርጅቶ ካልወሰነ በቀር እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር እጁ የታሰረ ነው። ይሄንን ካለመረዳት ይመስለኛል ብዙ ወገኖች በዶ/ር አብይ ላይ ያላቸው ተስፋቸው መሟጠጥ አይደለም ወደ ተቃዋሚነት መሸጋገር የጀመሩት። ይሄን አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አስራር
Posted in Ethiopian News

የአዴፓ/አማራ ክልል ሃላፊዎች ሰልፈኞችን ወጥተው ለማናገር ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ

በአማራ ክልል በበርካታ ከተሞች ደማቅ ሰላማዊ ሰልፎች ተደርገዋል። ሰልፎቹ የተደረጉት በቤኒሻንጉል ክልል በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ ተከትሎ ቀድሞ ብአዴን ተብሎ የሚታወቀውና አሁን አዴፓ ብሎ ራሱን የሰየመው ክልሉን የሚያስተዳድረ ድርጅትን አካሄድ በመቃወም ነው። ሰልፈኞቹ በቅርቡ በአጣዬና አካባቢዎች በኦነግ ታጣቂዎች በደረሰው ግፍና ሰቆቃ የክልል መንግስቱ  ከንፈር ከመምጠትና ላይ ላዩን ሃዘኔታ ከመግለጽ ባለፈ ምንም ማድረግ እንዳልቻለ የገለጹ ሲሆን፣  አሁንም በቤኒንሻጉል በአማራ ተወላጆች ላይ ለደረሰው ጥቃት አዲስ ሳይሆን የተለመደ እንደሆነ እንደሆነ ይናገራሉ። ሰለፈኞቹ በባህር ዳር የአማራ ክልል ርእስ መስተዳደር  ጽ/ቤት ሲደርሱ ወጥቶ ጥያቄዎቻቸው ለማዳመጥ የወጣ ባለስልጣን  ስለመኖሩ  መረጃ ለሰልፈኞች ባቀረበው ጥያቄ ፣  “ቁጥሩ ቀላል የማይባል ህዝብ ድምጹን ለማሰማት በሚመጠበት ጊዜ፣ የሕዝብ ተወካይ ነን እያሉ፣ እንኳን ሊያናግሩን እዚህ ግንቡ ውስጥ ተደበቀው ነው  እያዩን ያሉት”  ሲሉ በሰለፉ የተገኙ አንድ እናት ሲናገሩ፣ ከሰልፉ አስተባባሪዎች መካከል ያለ አንድ ወጣት ” እነርሱማ ጭራሽ ሕዝቡ ሕገ መንግስታዊ መብቱን እንዳይጠቀም ሰው ሰልፍ እንዳይወጣ ሲያከላክሉ ነበር” የሚል ምላሽ ነው የሰጠው። እንዳጋጣሚ ባህር ዳርን ለመጎብኘት ከአሜሪካ የመጡ  በሰልፉ አካባቢ የነበሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ፣ በዋሺንግንት ዲሲ ኢትዮጵያዉያን የተቃወሞ ሰላማዊ ሰልፍ በዉጭ ጉዳይ መስሪያ ሲያደርጉ ሁልጊዜ የስቴት ዲፓርትምነት ሃላፊዎች ወጥተው ደብዳቤዎችን እንደሚቀበሉና ሰልፈኞችን ለማነጋገር እንደሚሞክሩ አስረድተው፣ “ይሄ ሁሉ ሕዝቡ መጥቶ ከክልሉ ርእስ መስተዳደር ጽ/ቤት ዋና ሃላፊዎችም ባይሆንም፣  ታች ያሉ ተራ አመራሮች ወጥተው የህዝቡን ጥያቄ እንደሰሙ መናገር አለመቻላቸው ለሕዝብ ያላቸውን ትልቅ ንቀት የሚያሳይ ነው”
Posted in Ethiopian News

ግእዝ ኦሮምኛ ጨምሮ ለሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ብቃት እንዳለው ዶ/ር አበራ ይናገራሉ

“አገርኛ ቋንቋን ከኮምፒዩተር ያዋሃዱ ሳይንቲስት! ” በሚል  ረ እስ  አዲስ ዘመን ጋዜጣ  ስለ ዶ/ር አበራ ሞላ የሕወሃት ታሪክና ትልቅ አስተዋጾች ሰፋ ያለ ዘገባ አስፍሯል። ዶ/ር አበራ  በእንስሳ ሕክምና ዙሪያ ከሰሯቸው በርካታ አኩሪ ተግባራት በተጨማሪ ፣ የአፍሪካ ብቸኛ ፊደል የሆነው ግ እዝ  በኮምፒተር እንዲጻፍ ያደረጉ ምሁር ናቸው። ሰንዳፋ የተወለዱ፣ ኦሮምኛና አማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው  የሆኑት ዶ/ር አበራ  ትግርኛ፣ አማርኛ፣ ቤንች፣ ጉሙዝ፣ ጉራጌ፣ ምኢን፣ ጋሙ ጎፋ፣ ዳውሮ፣ ባስኬቶ  ኦሮምኛ በትክክልና በብቃት በ ገዝ ፊደል መጻፍ እንደሚቻል ይናገራሉ። አዲስ ዘመን የሚከተለውስ አስፍሯል፡ ————————— ጽጌረዳ ጫንያለው  የአማርኛ ቀለማትን በኮምፒዩተር ዶክተር አበራ ሞላ የተስፋ ገብረሥላሴ የፊደል ሠራዊትን ወደ ኮምፒዩተር ያዘመቱ የፊደል ጀኔራል ናቸው። በዚህ የግዕዝ ፊደል ከተራ ጽሑፍ እስከ ተንቀሳቃሽ ፊደልና ሌሎች እንግዳ ጉዳዮችን ወደ ኮምፒዩተር ያለምንም መሸራረፍ እንድናሰፍር አድርገዋል። በብዙ ሀብት የሚገዙትን የኮምፒዩተር የእንግሊዝኛ ፕሮግራሞች የግዕዝ ፊደልም እንዲጠቀምባቸው ያደረጉም ናቸው። አማርኛን ያካተተውን እያንዳንዱን የግዕዝ ቀለም ለመጀመሪያ ጊዜ በኮምፒዩተር እንዲጻፍ አሜሪካ ውስጥ የፈጠሩት ዘዴ ኢትዮጵያ እንዲመዘገብ ሲሉም ከ30 ዓመታት በላይ የታገሉ ስለመሆናቸው ይመሰክርላቸዋል። የተመዘገበ የአሜሪካ ኮፒ መብትም አላቸው። ዶክተር አበራ በሕክምናው ዓለም ፈውስ ሲሰጡ፤ በፊደል የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂያቸው ደግሞ ለታላቅ እውቅና ከመሰጠታቸው ጋር ተያይዞ “የግዕዝ አባት” የሚል የቅጽል ስም ተሰጥቷቸዋል። ዶክተሩ ኮምፒዩተርና ፊደላቱን ለማዋሃድ ብዙ ለፍተዋል። ብዙ ገንዘብ፣ ጊዜና ጉልበትም አፍሰዋል። ኢትዮጵያ የፓተንት ሕግ የላትም ቢባሉም አላማቸውን ሳይለቁ ከልጃቸው ጋር የመጀመሪያውን የግዕዝ የእስክሪንና የማተሚያ ቀለሞች ሠርተው
Posted in Ethiopian News

ሶስት አራተኛ የከሚሴ/ባቲ ነዋሪ አማርኛ ተናጋሪ፣ ግን የስራ ቋንቋው ላቲን#ግርማካሳ

በአማራ ክልል “በርከት ያሉ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ያሉበት ነው” በሚል ሶስት ወረዳዎች የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን በሚል ልዩ መስተዳደር ውስጥ ተካተዋል። እነዚህ ወረዳዎች የአርጡማ ፉርሲ፣ የባቲና የጨፌ ጎላና ወረዳዎች ናቸው። የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ተብሎ ዞኑ ለኦሮሞዎች በሚል ቢሸነሸንም ፣ አንደኛ ዞኑ በአማራ ክልል መስተዳደር ስር ያለ ዞን ነው። ሁለተኛ በዞኑ ኦሮምኛ ተናጋሪ ያልሆኑ ማህበረሰብት በብዛት አሉበት። በኢሕአዴግ ዘመን ሁለት የሕዝብ ቆጠራዎች ተደርገዋል። አንደኛው እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ1994 ዓ.ም የተደረገ ሲሆን ሁለተኛው በ2007 ዓ.ም የተደረገ ነው። የ2007 የሕዝብ ቆጠራ ውጤት በወረዳና በከተማ ደረጃ የዜጎች የአፍ መፍቻ ቋንቋ ምን እንደሆነ በሪፖርቱ ይፋ አላደረገም። ይሄን የሆነበት ምን አልባት ከፖለቲካ ዉሳኔ የተነሳ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ። ከዚህም የተነሳ በ1994ቱ የሕዝ ቆጠራ ውጤት የተቀመጡ ቀመሮችን እንደ ግባት በመውሰድ አንዳንድ ሐሳቦችን ለማስቀመጥ እሞክራልሁ። በባቲ ወረዳ፣ በ1994 የሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሰረት ወደ 144904 ሺህ ነዋሪዎች ነበሩ። ከነዚህ ነዋሪዎች 51.1% የሚሆኑት የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው አማርኛ ነው። 48.3% ደግሞ ኦሮምኛ። ስለዚህ ወረዳው ሕብረ ብሄራዊ ወረዳ ነው ማለት ነው። በወረዳው ያሉ ሶስት ከተሞችን ብንወስድ ኦሮምኛ ተናጋሪው እጅግ በጣም ጥቂት ነው። በባቲ ከተማ 17.7%፣ በገብራ ከተማ 2.4%፣ በደገን ከተማ ደግሞ 0.2%። ያ ማለት በባቲ ከተማ ከ75% በላይ፣ በገብራና በደገን ደግሞ ከ96% በላይ ነዋሪዎች አማርኛ ተናጋሪዎች ናቸው ማለት ነው። የአርጡማ ፋርሲን ወረዳ ብንወስድ 80% ነዋሪው፣ አብዛኛው በገጠር የሚኖር፣ ኦሮምኛ ተናጋሪ ነው።
Posted in Ethiopian News

ለሸዋ የብሄር/ዘር አወቃቀር አይሰራም #ግርማካሳ

የሚከተለው ሰነድ የተዘጋጀው እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ 1994 ነው። ይሄን የሕዝብ ቆጠራ ውጤት ዋቢ በማድረግ አንዳንድ ሐሳቦች ለማመላከት እሞክራልሁ። ከ 1994 ቀጥሎ በ 2007 የተደረገ የሕዝብ ቆጠራ አለ። ሆኖ የቆጠራው ሪፖርት የተሟላ አይደለም። በወረዳ ደረጃ ነዋሪዎች የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ምን እንደሆነ የ2007 ሪፖርት አላስቀመጠም። በዚህ ጽሁፍ የአፍ መፍቻ ቋንቋን እንጂ ማንነት/ብሄር ወይም ethnicity የሚባለው ከግምት አላስገባሁም። አሻሚ ስለሚሆን። ሸዋ ውስጥ ደግሞ የሚኖረው አብዛኛው ቅይጥ ነው። እናቱ አማራ፣ አባቱ ኦሮሞ የሆነ በወቅቱ ኦሮሞም አማራም ብሎ መጻፍ አይቻልም ነበር። ሌላው በኦሮሞ ክልል ስራ ለማግኝት ለመቀጠር ኦሮሞ መሆን ግዴታ ስለነበረ9አሁንም ስለሆነ) አማራ ሆነው ኦሮሞ ነን ያሉም ብዙ ናቸው። ስለዚህ ሳይንሳዊ ያለሆነን ቀመር ላይ ተመርኩዤ አስተያየት መስጠት አልፈለኩም። የአፍ መፋች ቋንቋ ግን አሻሚ ሆኖ አላገኘሁትም። እንግዲህ በቀዳሚነት ከዚህ የምንማረው የኦሮሞ ማህበረሰብ ምን ያህል ከሌላው ማህበረሰብ ጋር ተደበላልቆ እንደኖረ ነው። ከሌላው ጋር የተሳሰረ ነው። አሁን በአገራች ችግር እየተፈጠረ ያለው ይሄን የተሳሰረ ማህበረሰብ ለማለያየት እየተሞከረ መሆኑ ነው። በሸዋ ከአማራው፣ ከጉራጌ..የተለየ የኦሮሞ ማህበረሰብ ለመፍጠር የኦሮሞ ብሄረተኞች ደፍ ቀና ይላሉ። መጋብባት እንኳን እንዳይችል ኦሮምኛን የሚያስተምሩት ብቃት ያለው የግእዝ ፊደል እያለ በላቲን ነው። በሶስት ወረዳዎች፣ ደራ፣ ፈንታሌና የአዳማ ወረዳ ኦሮምኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ያልሆኑ ዜጎች ማጆሪቲ ናቸው። በገራር ጃርሶ ከኦሮምኛ ተናጋሪው እኩል ሲሆኑ፣ በቆቂርና በሎሜ ወረዳዎች ከ40% በላይ ናቸው። በአዲስ አበባ ዙሪያ በ 1994 የነበረው አብዛኛው የአቃቂ ወረዳ ወደ
Posted in Ethiopian News

ኦሮሞውን ከሶማሌው፣ ከጌዴኦው፣ ከጉሙዙ፣ ከሃረሬው …አሁን ደግሞ ከአማራው እያጣሉት ነው #ግርማካሳ

የኦሮሞ ጽንፈኞች፣ ኦነጎች፣ የጃዋር ቄሮዎችና በኦዴፓ/ኦህዴድ ውስጥ ያሉ ያልተደመሩ፣ ለነ ዶ/ር አብይና አቶ ለማ ራስ ምታት የሆኑ ዘረኛ አመራሮችና አባላት፣  በኦሮሚያ ክልልና በአማራ ክልል ከሚሴ ዞን ውስጥ በሚኖሩ፣ ኦሮሞ ባልሆኑ ማህበረሰባት ላይ፣ እንደዚሁም እነዚህን አካባቢዎች በሚያዋስኑ የሌሎች ክልሎችና ዞኖች ወረዳዎች በሚኖሩ ዜጎች ላይ የሽብር ተግባራት እየፈጸሙ እንደሆነ በገሃድ እያየን ነው። በተለይም ዶ/ር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስተር ከሆኑና ኦህዴድ/ኦዴፓ በፌዴራል መንግስቱ የበላይነቱን ከያዘ በኋላ ፣ ጽንፈኞቹ በሕወሃት ጊዜ የማይታሰብ ድርጊቶችን ነው እየፈጸሙ ነው ያሉት። አንዳድን ዜጎች ህወሃት ይሻል ነበር እስከማለትም እየደረሱ ነው። በጌዴኦ ዶ/ር አብይ ተፈናቃዮችን ለማነጋገር ሄደው በነበረ ጊዜ ፣ አንድ የጌዴኦ እናት እንደተናገሩት፣ ምን አልባትም እነዚህ ሰዎች  “የኛ ሰው ስልጣን ይዟል፣ ማንም አይነካንም”  ከሚል አስተሳሰብ ይሆናል እኩል ዘር ተኮር ተግባራት ላይ የተጠመዱት። ለምሳሌ የሚከተሉትን በግልጽ የሚታወቁትን መጥቀስ እንችላለን። ከእነዚህ ጽንፈኞች የተነሳ በኦሮሞ ክልል የቦረናና ጉጂ ዞኖችን በሚያዋስኑ አካባቢዎች የሚኖሩ በአስር ሺሆች የሚቆጠሩ ሶማሌዎች በግፍ ተፈናቅለዋል፤፡ ብዙዎች ተገድለዋል። በጉጂ ዞን ውስጥ የሚኖሩ በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ የጌዴዎና የቡርጂና ወገኖች በግፍ ተፈናቅለዋል።የሞቱም አሉ። ምእራብ ወለጋን በሚያዋስኑ የቤኔሻንጉል ክልል ወረዳዎች በሚኖሩ ጉሞዞች ላይ ኦነጎች በከፈቱት ጥቃት ምክንያት በተነሳው ግጭት፣ ከመቶ ሺህ በላይ ዜጎች ፣ አብዛኞቹ ኦሮሞዎች፣ ተፈናቅለዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ተገድለዋል። በሃረር ዙሪያ ያሉ ጽንፈኛ ቄሮዎች የሃረርን ከተማ የዉህ መስመሮች ለወራት ዘግተው በከተማዋ ላይ ትልቅ ሽብር ፈጽመዋል። በአዲስ አበባ ዙሪያ በቡራዩ በአስር ሺሆች የሚቆጠሩ
Posted in Ethiopian News

ብሄረተኝነት ለኦሮሞ አይጠቅምም፣ ለማንም አይጠቅም ይላሉ አቶ ታከለ ኡማ #ግርማካሳ

አቶ ታከለ ኡማ በጋዜጠኛና አክቲቪስት እስክንድር ነጋ ከሚመራው የባለአደራ ምክር ቤት ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ መያዙን ሰምቻለሁ። ይሄ መልካም ዜና ነው። መሰረታዊ የአዲስ አበባ ሕዝብ ጥያቄ ይዘው ከተነሱ ጋር የአዲሳ አበባ ከተማ አመራር ነን የሚሉ ማዳመጥና መስማት ከስራ ዘርፋቸው አንዱ ነው። እግርጠኛ ነኝ አቶ ታከለ ኡማ እነ እስክንድር ባቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ይስማማሉ የሚል እምነት አለኝ። ይሄን ብዬ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ስለሰጡት አንድ ንግግር ልውሰዳችሁ። ንግግሩን በጣም ሃሪፍ ንግግር ሆኖ አግኝቼዋለሁ። “ብሄረተኝነት ለኦሮሞ አይጠቅምም፣ ለማንም አይጠቅም” ይላሉ ኢንጂነር ታከለ። ኢንጂነር ታከለ ሲሾም የተሾሙበት አካሄድ በጣም መስመር የለቀቀና ከአዲስ አበበ አስተዳደር አሰራር ውጭ በኦዴፓ/ኦህዴድ የተሰጠ ሹመት በመሆኑ ከፍተኛ ተቃዉሞ ማቅረቤ ይታወቃል። “ለምን ታከለ ኡማ መነሳት እንዳለበት” በሚል ርእስ ከሰባት ወራት በፊት ሶስት ምክንቶችን በማቅረብ ነበር ኢንጂነሩ እንዲነሱ ጥያቂር አቅርቤ የነበረው። አንደኛው አሿሿማቸው ትክክል ስላልነበ፣ ሁለተኛው ከመሾማቸው በፊት የነበራቸው አቋም ለአ.አ ጥቅም እንዲቆሙ አያደርጋቸው ብዬ በማሰቤና ሶስተኛ የጣይቱ ሃዉልት እንዲሰራ ከፈቀዱ በኋላ እንዳይሰራ በማድረጋቸው ነበር። ከሶስት ሳምንታት በፊት “ሶስት ነጥቦች ስለታከለ ኡማ” በሚል ርእስ ስለ ም/ከንቲባው አዎንታዊ አስተያየት ሰጥቻለሁ። አንደኛው አቶ ታከለ ምንም እንኳን የእቴጌ ጣይቱ ሃዉልት እንዲሰራ ከፈቀዱ በኋላ እንዳይሰራ ማድረጋቸው በወቅቱ ተቃዉሞ እንዳቀርብ ካደረግኝ አንዱ ምክንያት የነበረ ቢሆንም፣ ከመከልከላቸው በፊት መፍቀዳቸው ግን ፣ አይምሯቸው እንደተበላሸ የኦሮሞ ብሄረተኞ አንዱ አለመሆናቸውን የሚያሳይ ነው። እንደዚያ ቢሆኑ ኖሮ በመጀመሪያዉኑ አይፈቅዱም ነበር። ሆኖም ከሌሎች፣ የኦሮሞ ብሄረተኞችና በዉሸት
Posted in Ethiopian News

ለምን ባለአደራውን እንደምደግፍ #ግርማካሳ

የባለ አደራ ድጋፍ ማህበር በአሜሪካ ተቋቁሟል። ያለፈው ሳምንት በአዉሮፓ ኢትዮጵያዊያን በለደን በነቂስ በሰላማዊ ሰልፍ ለባለአደራ ድጋፍ እንደሰጡ ይታወቃል። የባለአደራው ንቅናኤ አንደኛ – የተመሰረተው በአዲስ አበባ አስር ሺሆች በሚቆጠሩ ነዋሪዎች ነው። አገር በቀል እንቅስቃሴ ነው። ዳያስፖራ ያቋቋመው ወይንም በፌስቡክ የተቋቋመ አይደለም። ሁለተኛ – አላማው እኩልነት ነው። አዲስ አበባ ሕብረብሄራዊነት መልኳን ለማጥፋት፣ በአዲስ አበባ የአንድ ጎሳ የበላይነትን ለመጫን፣ አንዽ ክልል ወይም ጎሳ ልዩ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ዘረኛ ቡድኖችን ለመመከት፣ በአዲስ አበባ ሁሉም እኩል ተጠቃሚ፣ ሁሉም፣ ዘራቸውና ሃይማኖታቸው ሳይታይ እኩል እንዲታዩ ለማድረግ የተመሰረተ ነው። የልዩ ጥቅም ሳይሆን የእኩል ጥቅም ተጠቃሚ መርህ ይዞ የሚንቀሳቀስ ነው። ሶስተኛ፡፡ ዱላና ቆንጨራ ይዞ፣ ሌላውን በማስፈራራትና በሌላው ላይ በመዛት ያል የተመሰረተ አይደለም። በብእርና በሐሳብ ላይ የተመሰረተ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ነው። ሰላማዊ በሆነ መንገድ በምርጫ የአዲስ አበባን ህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚሰራ ነው።በአንዳንድ ወገኖች መንፈቀለ መንግስት እየተባለ የሚወራው ወሬ፣ ትኩረት ለማስቀየር የሚወራ መሰረተ ቢስ ተራ ወሬ ነው። ምርጫን የሚፈራ፣ ህዝብ አይደግፈኝም ብሎ የሚፈራ አካል ካልሆነ በቀር ባለ አደራውን ከሰላማዊነት ውጭ በሌላ መፈረጅ ተሸናፊነት ነው። አራተኛ – የፖለቲካ ፓርቲ አይደለም። ግን ለሕዝብ ቅርብ የሆኑ ፖለቲከኞች እነ ማን እንደሆኑ ለይቶ፣ ለነርሱ ድጋፍ ያደርጋል። አምስተኛ – ሁሉን አቃፊ፣ ሁሉንም አሳታፊ ነው።፡የዘር ወይንም የሃይማኖት ልዩነት የለም። ጋሞ ሆንክ፣ ጉራጌ፣ ኦሮሞ ሆንክ አማራ፣ ሶማሌ ሆንክ ሲዳማ ዘርህ ምንድን ነው ? የት ነው የተወለድከው ተብለህ አትጠየቅም። ሰው
Posted in Ethiopian News

ታላቅ ወገንን የመርዳት ዘመቻ በአዲስ አበባ ወጣቶች (ግርማ ካሳ)

ከመጋቢት 16 እስከ መጋቢት 21 – 2011ዓ.ም በሐገር ፍቅር  በአዺጽ አበአብ ወጣቶች ለሁሉም በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ህይወት ማቆያ አስቸኳይ እርዳታ ለማሰባሰብ የተጀመረው ዘመቻ በተጠናከረ መልኩ እየተካሄደ ነው። ወጣቶቹ በአገራቸው የመፈናቀል አደጋ የደረሰባቸው ወገኖቻችን ለመፈናቀላቸው ምክንያት የሆነው በዋናነት አገሪቱኢአ ያለው የዘር ፖለቲካን የዝሸር ፖለቲካውም የፈጠረው የዘርና ይጎሳ ግጭቶች መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም ፖለቲካውን ማስተካከል፣ ዜጎች በሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች ዘራቸውና ሃይማኖታቸው ሳይጠየቅ፣ ሳይፈሩ እንዲኖሩ በማድረጉ አንጻር ትልቅ ስራ መስራት እንዳለበት  ቢታወቅም.፣ ፖለቲካው በአንድ በኩል እንዲስተካከል ጥረት እየተደረገም፣ በአጓዳኝ ለተጎዱ ወገኖች መቆም አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያዊያን ግደታም ነው። ከዚህም የተነሳ ነው ከሁሉም በፊት ሰባአዊነት ይቅደም በሚል የአዲስ አበባ ወጣቶች በአገሪቷ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ለማሰባሰብ ዘመንቻ የከፈቱት። የማሪዮት ሆቴል፣ የአፍሪካ ዩኒየን፣ የኢትፖል ሴኪዩሪቲ አባላት ብዙ ድጋፎች አሰባብሰው ይሄን ዘመቻ እያንቀሳቀሱ ላሉ፣ እንደ አክቲቪስት ያሉ፣ እነ አክቲቪስት ያሬድ ሹመቴ ላሉበት ግብረ ሃይል እርዳታዎች አቅርበዋል። የሐምሌ 19 ቁጥር 2 ተማሪዎች ብዛታቸው 400 የሚሆኑ እያንዳንዳቸው ከቤተሰቦቻቸው 1 ፓስታ እና 1 ሳሙና በድምሩ 400 ፓስታና 400 ሳሙና በመሰብሰብ  ለወገናቸው አስረክበዋል። አስተባባሪቹ አሁን ለኢትዮጵያዉያን ጥሪ እያቀረቡ ነው። ከዚህ በታች የተጠቀሱትን አስቸኳይ እርዳታዎች የሀገር ፍቅር ቴአትር የጀርባውን በር በመጠቀም በቅጥር ግቢ ውስጥ፣  “የአቅማችሁን ያህል አስቸኳይ እርዳታዎች ታመጡልን ዘንድ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን” ይላሉ። አስተባባሪውፖቹ  ገንዘብ እንደማይቀበሉ አሳውቀዋል። ለበለጠ መረጃ መሐመድ ካሳን እና ያሬድ ሹመቴን በተከታዩ ቁጥር ያነጋግሩ። 094 014
Posted in Ethiopian News

የአዲስ አበባ ጉዳይ አዴፓን ከኦዴፓ ወይም እነ ዶ/ር አብይን ከኦዴፓ መለየቱ አይቀርም #ግርማካሳ

የአዲስ አበባ ጉዳይ ትኩረት አግኝቶ መነጋገሪያ የሆነው፣ በዳዎድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ፣ በሌንጮ ለታ የሚመራው ኦዴፍ፣ በዶ/ር መራራ ጉዲና የሚመራው ኦፌኮ እና ሌሎች ሁለት ደርጅቶች በጋራ ሆነው ያወጡትን መግለጫ ተከትሎ ነው። “ኦሮሞ ካልሆነ አትጋቡ” ያሉት አቶ በቀለ ገርባ ነበሩ መግለጫዉን ያነበቡት። በመግለጫው የአዲስ አበባ ባለቤት ኦሮሞው እንደሆነና ሌሎች ኦሮሞ ያልሆኑ ፣ ኦሮሞው “አቃፊ” ስለሆነ መኖር እንደሚችሉ ነበር የተገለጸው። ልክ ኬኒያ ኢትዮጵያዊያን እንደሚኖሩት ማለት ነው። የአዋሳው የኢሕአዴግ ጉባዬ ከመደረጉ በፊት ፣ ብአዴን ስሙን ወደ አዴፓ በቀየረበት የባህር ዳሩ ጉባዬ፣ አዲስ አበባ የነዋሪዎቿ ናት የሚል አቋም ነበር ይዞ የተያዘው። በአዋሳው ጉባዬ የአዴፓ ተወካዮች ፣ የባህር ዳሩን ዉሳኔ በመያዝ፣ ኢሕአዴግ እንደ ድርጅት በአዲስ አበባ ላይ አቋም እንዲወስድ ይጠይቃሉ። በዚህ ጊዜ አብዛኛው የኦህዴድ/ኦዴፓ ተወካዮች “ፊንፊኔ የኦሮሞ ናት” የሚል አቋም በመያዛቸው፣ ስብሰባው ሊረበሽ ሆነ። ዶ/ር አብይ አህመድ ጣልቃ ገብተው ለማረጋጋት ሞከሩ፤ “ጉዳዩን ሌላ ጊዜ እንመለስበት” በሚል። የአዴፓ ተወካዮች ግን “በዚህ ጉባዬ መወሰን ካልተቻለ መቼ ሊወሰን ነው ?” በሚል ጠንከር ያለ አቋም ያዙ። በወቅቱ በነበረኝ መረጃ፣  የአዴፓ፣ ህወሃትና ደሃዴን ተወካዮች በሙሉ ወይም አብዛኞቹ፣ እንዲሁም ወደ አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት የተወሰኑ ኦዴፓዎች “ አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ናት፣ በተለይም ደግሞ የነዋሪዎቿ ናት” የሚል አቋም ያዙ። ይህ አቋም ግን በይፋ አልተገልጸም። አብዛኛው ኦዴፓዎችን ላለማስከፋት በሚልና በኦሮሞ ብሄረተኞች ዘንድ ጩኸት እንዳይሰማ ስለተፈለገ፣ ነገሩ ተሸፋፈነ። የኦሮሞ ብሄረተኞች “ፊንፊኔ ኬኛ” ፖለቲካቸውን ቀጠሉበት። በኮንዶሚኒየም
Posted in Ethiopian News

የኦሮሞ ብሄረተኞች ከማንም በላይ ኦሮሞዉን እየጎዱት ነው #ግርማካሳ

ዶ/ር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት ለጨፌው(የኦሮሞ ክልል መንግስት ምክር ቤት) የተናገሩት ነገር ነበር። “ኦሮሞ አቃፊ ነው፣ ዘር አይለይም፤ ለምንድን ነው ታዲያ ሌሎች የሚፈሩንና የሚጠሉን? ያንን በሌሎች ዘንድ ያለው የተሳሳተ አመለካከት ማስተካከል አለብን” ነበር ያሉት። በተወሰነ ደረጃ እነ ዶ/ር አብይ በኦሮሞዉና በሌሎች ማህበረሰባት መካከል፣ የሕወሃትና የኦነግ ፖለቲካ የፈጠረውን የሃያ ሰባት አመታት አለመተማመን ለማስቀረት ችለው ነበር።  በጣም አመርቂ፣ ተስፋ ሰጪ ስራዎችን ሰርተዋል። ሆኖም ግን ለኦሮሞ ጥቅም እንቆማለን የሚሉት ጽንፈኛ ሃይሎች፣ እነ ዶር አብይ የገነቡትን በአሁኑ ወቅት እያፈረሱት ነው። ጽንፈኞች እያደረጉት ባለው በጣም አሳፋሪን አሳዛኝ ግፎችና ሰቆቃዎች፣ አብዛኛው ማህበረሰብ በኦሮሞ ላይ ያለው አመለካከት እንዲቆሽሽ እያደረገ ነው። እነዚህ ጽንፈኞች በጽንፈኛ ፖለቲካቸው ከማንም በላይ እየጎዱ ያሉት፣ ራሱ የኦሮሞ ማህበረሰብን ነው። በዚህ በጽንፈኛ ፖለቲካ ምክንያት አሁን የኦሮሞ ክልል የሚባለው አካባቢ በእጅጉ እየታመሰ ነው ያለው። እዚህ ጋር እነ ዶ/ር አብይ ስል፣  በኦህዴድ ያሉ ጥቂት የለዉጥ ሃይሎችን ማለቴ ነው። ጽንፈኞች ስል ደግሞ የጃዋር ቄሮዎችን፣ ኦነጎችንና በዋናነት አብዛኞቹ ኦህዴዶች/ኦዴፓዎች ማለቴ ነው። እነ ዶ/ር አብይም ሕግን ማስከበር ባለመቻላቸው፣ ጽንፈኝነትና አክራሪነት የተላበሱ ሃይላት በነጻነት አገር ውስጥ ገበተው የመንግስት ድጋፍ ተደረጎላቸው እንዲቀንሳቀሱ በመፍቀዳቸውም ነው ችግሩ የተባባሰው። ይሄ ስንጽፍ ብዙዎች ጸረ-ኦሮሞ ይሉናል። ግን ከኦሮሞ ብሄረተኞች ይልቅ ለኦሮሞ ማህበረሰብ የሚጠቅመን ሀሳቦች ያስቀመጥን እኛ ነን።  ከዚህ በታች ያለውን ፣ በተለይም የኦሮሞ ልጆች በርጋታ እንዲያነቡ እጠይቃለሁ። እኛን መረጃ ሳይኖራችሁ ጸረ-ኦሮሞ ማለት አቁመው፣ እኛ ለኦሮሞ
Posted in Ethiopian News

ነጋዴ በኦሮምኛ ካልሸጠ አትግዙ – አቶ በቀለ ገርባ

አቶ በቀለ ገርባ የኦፌኮ ም/ሊቀመንበርና በኦሮሞ ፖለቲካ ውስጥ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ናቸው። ትውልዳቸው በወለጋ ሲሆናሁ አሁን ነዋሪነታቸው በአዳማ/ናዝሬት ነው። አቶ በቀለ ፣ ከኦሮሞ ሜዲያ ኔትዎርክ ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሐመድ ጋር በቅርበት የሚሰሩ የለማ ቲም ስልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ በለማ ቲም ደስተኛ አለመሆናቸውን ብዙ ጊዜ ሲናገሩ የሚደመጡ ናቸው። ልክ እንደ አቶ በቀለ የወለጋ ተወላጅ የሆኑና ኦሮምኛን አቀላጥፈው የሚናገሩ ዶ.ር አብርሃም አለሙ ፣ የአቶ በቀለ የኦሮምኛ ንግግር እንደሚከተለው ተርጉመው አቅርበዉልናል። ——————————- ስለ ኦሮሞ ቋንቋና ባህል እድገት – በኦሮሞ ባህል ማእከል የተካሄደ የፓነል ውይይት አዲስ አበባ፣ 08/07/2011 የኦሮሞን ቋንቋና ባህል አዲስ አበባ ውስጥ ማሳደግን ዐቢይ ዓላማው አድርጎ የተቋቋመው የኦሮሞ ቋንቋና ባህል ቦርድ፣ ምሁራንና የማህበረሰቡን ልዩ ልዩ አካላት ያሳተፈ የፓነል ውይይት በአዲስ አበባ የኦሮሞ ባህል ማእከል በ 08/07/2011 አካሂዷል፡፡ ….. በውይይቱ ላይ ንግግር ያቀረቡት የፖለቲካ መሪና የቋንቋ ባለሙያ የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ፣ “የኦሮሞ ቋንቋ ጉዳይ፣ የኦሮሞ ማንነት ጉዳይ ነው፤” አሉ፡፡ ቋንቋ የሌለው ህዝብ (ማህበረሰብ) የለም፡፡ አንድ ማህበረሰብ እንደ ማህበረሰብ አለ፣ እከሌ የሚባል ማህበረሰብ ነው ተብሎ ከሚታወቅበትም ነገር አንዱ ትልቁ ቋንቋው ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ያን ማህበረሰብ እንዳይኖር ሲፈልጉ፣ አስቀድመው ቋንቋውን ይገሉታል፤ ቋንቋውን ይገሉታል፡፡ እንዲህ ነው የሚሉት፤ መፈክራቸውም እንዲህ ነው፤ “ቋንቋውን ግደል፤ ከዚያም ቀጥለህ ሰውዬውን ግደል፤” ይላሉ፡፡ በዚህ ምክኛት የራስን ቋንቋ መጠበቅ፣ መንከባከብ፣ የራስን ማንነት መጠበቅ ማለት እንደሆነ ይታወቃል ማለት ነው፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ
Posted in Ethiopian News

ሕዝብን የማደራጀትስራ፣ ህዝባዊ ስብሰባዎች በሁሉም ክ/ከተሞች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይደረጋሉ

ሕዝብን የማደራጀትስራ፣ ህዝባዊ ስብሰባዎች በሁሉም ክ/ከተሞች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይደረጋሉ መጋቢት አንድ ቀን በአስር ሺሆች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች “ አዲስ አበበ ለሁሉም ኢትይጵያ፣ ሁሉም ኢትዮጵያ ለአዲስ አበባ” በሚል መርህ ድምጻቸውን ማሰማታቸው ይታወቃል። በወቅቱም አዲስ አበባ ተወካይ ስለሌላት፣ አሁን በአመራር ላይ የተቀመጡት የአዲስ አበባን ሕዝብ የሚወክሉ ስላለሆነና መርጭ እስኪደረግ ድረስ ለአዲስ አበባ ህዝብ የሚሰራ የተደራጀ ሃይል መኖር ስለላበት፣ በአቶ እስክንደር ነጋ ለሚመራው ኮሚቴ በሺሆች የሚቆጠሩ የከተማ ነዋሪዎች ዉክልና መስጠታቸው ይታወሳል። በዚህ መሰረት፣ “የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት” ተቋቁሞ ስራዉን ጀመሯል። አንዱና ትልቁ ስራም ሕዝብ የበክፍለ ከተማ፣ ወረዳ፣ ቀበሌ ማደራጀት ስለሆነ፣ ምክር ቤቱ በአንድ ወት ጊዜ ውስጥ በሁሉም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማ ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ለማድረግ ተዘጋጅቷል። በቦሌና ቦሌ እና አቃቂ ቃሊቲ  ክፍለ ከተሞች ስብሰባዎች በማድረግ ይጀምራል። ምክር ቤቱ፣  “ በአንድ ወር በሁልም ክፍለ ከተማ አዲስ አበባ ! ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ በ10 ክፍለ ከተማ ሙሉ በሙሉ ሕጋዊ መዋቅር ለመዘርጋት እና የየክፍለ ከተማ ተወካዮች ለመምረጥ እንዲሁም ስለ-አዲስ አበባ ምክክርና ወይይት ይደረጋል፡፡ ይህ በአዲስ አበባ በሁልም ክፍለ ከተማ የተጠራወ ታላቅ ህዝባዊ ሰብሰባ ከመጋቢት 14 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት “ባልደራስ” በየክፍለ ከተማ የሚካሄደውን ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ መራኀ-ግብር በቅደም ተከተል የሚገልፅ ይሆናል። በዚህም መሰረት የቦሌ ክፍለ ከተማ እና አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ነዋሪዎች እሁድ መጋቢት 15/ቀን 2011ዓ.ም ከ
Posted in Ethiopian News

የኦህዴድ/ኦዴፓ ሜዲያዉን የመቆጣጠር እርምጃ #ናኦሚን በጋሻው

አቶ ፍቃዱ ተሰማ የኦህደድ/ኦዴ የስራ አስፈጻሞ ኮሚቴ አባል ናቸው። የዶ/ር አብይን ሹመት በማጽደቅ ፓርላማው ፣ የኢቢሲ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ እንደመረጣቸው ከአዲስ አበባ የወጡ መረጃዎች ይጠቁማል።  አቶ ፍቃዱ በሃላፊነት፣  በኦሮሞ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ውስጥም ሰርተው የነበረ ሲሆን፣ በኦህዴድ አመራር አሉ ከሚባሉ ቁልፍ ሰዎች መካከል አንዱ መሆናቸው ይነገራል። በአገሪቷ ውስጥ አሉ ከሚባሉ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ የመንግስት ሜዲያ አንዱ የሆነው ኢቢሲ፣ ለአመታት ህዝብን ገለልተኛ በሆነ መልኩ ከማገለገል፣ የገዢው ፓርቲ የፕሮፖጋዳ አውታር ሆኖ የቆየ እንደሆነ ይታወቃል። ዶ/ር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ ኢቢሲ በፊት ከነበረው በተሻለ ሁኔታ መረጃዎችን ለሕዝብ ማቅረብ መጀመሩም ብዙዎችን አስደስቷል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት ሕዝብ በኦህዴድ/ኦዴፓ ላይ ከፍተኛ ተቃዉሞና ትችት እያቀረበ ባለበት ወቅት፣ ኢቢሲ በኦሮሞ ክልል የሚፈጸሙ ግፎችንና ሰቆቃቸውን በስፋ በመዘገቡ፣  በኦሮሞ ክልል መንግስትና በኦህዴድ/ኦዴፓ  አመራሮች የተወደደለት አይመስልም። ኢቢሲ ብቃት ባላቸው፣ ገለልተኛ በሆኑ ኢትዮጵያዉያ እንዲመራ በሚፈለግበት ጊዜ፣ የኦህዴድ/ኦዴፓ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ፍቃዱ የኢቢሲ የቦርድ ሰብሳቢ መሆናቸው፣ ኦህዴድ/ኦዴፓ የሜዲያዉን ነጻነትና ገለልተኛነት በመገደብ፣ ሜዲያው በፊት ህወሃትን ያገለግል እንደነበረውም፣ አሁን ኦህዴድ/ኦዴፓን እንዲያገለግል፣ የነበረውን አንጻራዊ ነጻነት እንደገና ለመገደብ ታስቦ ሊሆን እንደሚችል መገመት አያስቸግርም።
Posted in Ethiopian News

እኩልነትን ስንጠይቃቸው መጨፍለቁንና የበላይ መሆኑን መረጡ #ግርማካሳ

አንዳንዶች የኦሮሞ ፖለቲከኞች ላይ ታከራለህ ይሉኛል። ማክረር የሚለው ቃል ትንሽ ጠንከር ያለ ቃል ቢሆንም ፖለቲካቸውንና አመለካከታቸውን ግን ጠንከር ባለ መልኩ ቻሌንጅ ማድረግ ብቻ ሳይሆን አደገኛ እንደሆነ ጽፊያለሁ። ለዚያም ምክንያት አለኝ። ከሶስት አመታት በፊት የኦሮሞ ተቃዉሞ (#Oromo Protest)  በሚል ብዙ ተቃወሞ በተወስኑ የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች በስፋት ይደረግ ነበር። በወለጋ፣ በሃረርጌ፣ በምእራብ ሸዋና በምእራብ አርሲ ዞን በዋናነት። ብዙ ወገኖች በአጋዚ ጦር ተገድለዋል። ብዙ ደም ፈሷል። በዚያን ወቅት፣ ኦሮሞው ለብቻው የኦሮሞ ጥያቄ ብቻ ይዞ፣ ሌላውን ማህበረሰባት ባገለለ መልኩ የሚያደርገው ትግል ዉጤት ሊያመጣለት ስላልቻለ፣  እንደውም የማህበርሰቡን ስቃይና ሰቆቃ ስላበዛው፣ የኦሮሞ ተቃወሞ(#Oromo Protest) ወደ ኢትዮጵያ ተቃዉሞ (#Ethiopia Protest) ለማዞር አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን ጀመርኩ። በጸረ-ሕወሃት አቋም ብቻ አብሮ መታገል በቂ ስላልሆነ፣ ከሕወሃት  በኋላ ቢያንስ በጊዜያዊነት ስለሚሆነው  የጋራ አጀንዳዎች ማስቀመጡ አስፈላጊ ነው በሚል፣  ስድስት ነጥቦችን ያካተተ፣  የኦሮሞ ታጋዮች ከሌላው ጋር ሊያቀራረብ የሚችል አጭር ሰነድ አዘጋጅቼ የኦሮሞ አክቲቪስት ለሚባሉት እንዲደርሳቸው አደረኩ። ያቀረብኳቸው ስድስት ነጥቦች አራቱ ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል፣ የኦሮሞ አክቲቪስቶች የሚፈለጉትና የሚጠይቁት ነው። እነርሱ ከሌላው ጋር አብረው እንዲሰሩ በጣም ከነበረኝ ፍላጎት የተነሳ ርቄ በመሄድ ነበር ወደነርሱ የቀረብኩ። የነርሱን ድጋፍ ካገኘው ወደ ሌሎች ማህበረሰባትና አክቲቪስቶች ለመሂድ ነበር ያሰብኩት። ምን አልባትም ይሄን በመጻፊ እንዴት እንዲህ ትላለህ ብለው ብዙ ወገኖች ሊናደዱብኝ እንደሚችሉ አስብያለሁ። ግን “ግድ የለም፣ የኦሮሞ አክቲቪስቶች ከተስማሙ ፣ ሌሎች ቢናደዱብኝም፣  ደፍሬ፣ ተጋፍጬ እከራከራለሁ፣ አሳምናለሁ” ብዩ በመወሰን ነበር የተነሳሁት። ሆኖም
Posted in Ethiopian News

የአቶ ንጉሱ የተለሳለሰ አስተያየት ግፈኞችና ዘረኞችን የሚያበረታታ ነው #ግርማካሳ

የቀድሞ የአማራ ክልል መንግስት ቃል አቀባይ፣ አሁን በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የፕሬስ ሴክረተሪ የሆኑት አቶ ንጉሱ ጥላሁን ፣ “በለገጣፎ ከተማ የተወሰደውን የህገ ወጥ ቤቶች ማፍረስ እርምጃ ተክትሎ በቦታው ተገኝተን ከአመራሩ እና ከነዋሪዎች ጋር ተወያይተን ነበር። በዚህም መሰረት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጉዳዩን የሚያጣራ አንድ ግብረ ሀይል ተደራጅቶ ወደ አካባቢዉ እንዲሰማራ አድርጏል። የዜጎችን ቅሬታ የማዳመጥ እና ህግን የማስከበር ተግባራት ሳይነጣጠሉ ይፈፀማሉ” ሲሉ በፌስ ቡክ ድህረ ገጻቸው ጽፈዋል። በለገጣፎ በከተማዋ ባለስልጣናት የተፈጸመው ሰቆቃና ግፍ የተለያዩ ሜዲያዎች በስፋት የዘገቡት ሲሆን ከተለያዩ ማእዘናት ኢትዮጵያዊያን ድርጊቱን እያወገዙ ይገኛሉ። ሆኖም አቶ ንጉሱ ጥላሁን፣  በሕዝብ ላይ የደረሰውን ግፍና በደል በአይናቸው አይተውም፣  ድርጊቱን የማዉገዝ ድፍረት አለማግኘታቸው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። በከተማዋ አስተዳደሮች  የተፈጸመው ሕግ ወጥ ብቻ ሳይሆን አረመኔያዊ ድርጊትን ወደ ጎን በማድረግ፣  አቶ ንጉሱ ህገ ወጥ አድርገው ያቃረቡት ቤታቸው የፈረሰባቸው ዜጎችን ብቻ መሆኑ ብዙዎችን አስከፍቷል።አሳዝኗልም። በለገጣፎ የፈረሱ ቤቶችን ተከትሎ፣ እኩይ ተግባራቶቻቸውን ለመሸፋፈን ፣  የኦህዴድ አመራሮች የፈረሱ ቤቶች “ሕገ ወጥ” እንደሆኑና ቤቶቹን ሲያፈርሱ ሕግን የማስከበር ስራ እንደሆነ በስፋት ለመናገር ሞክረዋል። አቶ ንጉሱም የኦህዴድ ሃላፊዎችን ንግግሮች እንደ ወረደ በመቀበል ሳይሆን አይቀርም፣ ነዋሪዎቹን ሕግ ወጥ ቤት የሰሩ አድርገው ያቀረቡት። የአቶ ንጉሱ የቀዘቀዘና ደካማ አስተያየት ብዙዎችን ያስቆጣ ሲሆን፣ አቶ ንጉሱ ሕወሃት የበላይ የነበረ ጊዜ፣ “ አንዱ ልጅ፣ ሌላው የእንጀራ ልጅ የሚሆንበት አሰራር መኖር የለበትም” በሚል እኩልነት እንዲሰፍን ያሳዩትን ድፍረት ፣ አሁን እርሳቸው በአራት ኪሎ
Posted in Ethiopian News

ለኦሮምኛ የሚያዋጣው የግእዝ ፊደል ነው- አበበ ቶሎሳ ፈይሳ

የበደል ነጋዴዎች አባዝተው በደሉን ሸጠውልን እንጂ… እንዲህም ነበርን! በጣም የሚቆጨኝ Dha የሚለውን የኦሮምኛ ቃል የምትወክል ፊደል በግዕዝ ፊደላት ተካታ ለረጅም ግዜ ቆይታ ወደ ታይፕ ቴክኖሎጂ ሳትገባ ቁቤ መጥቶ መጥፋቷ! እውነት እውነት እላችኋለሁ ኦሮምኛን ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋዎች አንዱ ለማድረግ የግዕዝ ፊደላትን ቢጠቀም በጣም የተሻለ ይመስለኛል። አሁንም ቢሆን ቀና አሳቢ ኦሮሞ ፀሃፊዎች ፅሁፎቻችሁን በግዕዝ ፊደላት ጭምር ብትፅፉልን… ወደፊትም ከላቲን ፊደላት ጎን ለጎን የግዕዝ ፊደላትም ለኦሮምኛ ቋንቋ ግልጋሎት ቢሰጡ እና ቀስ በቀስ ዳግም ወደ ሃገር በቀል ፊደላችን ብንመለስ ምኞቴ ነው። ችግሩ ፖለቲካው እና ሳይንሱ ተምታተው እና ተደበላልቀው ነው እንጂ ትክክለኛ ሳይንሳዊ ጥናት ቢደረግ ለኦሮምኛም ሆነ ለሌሎቹ ሃገር በቀል ቋንቋዎች የሚያዋጣቸው የግዕዝ ፊደላትን መጠቀም ይመስለኛል። ብንተባበር…አፍሪካችን ያፈራቻቸውን ፊደላት ለመላው አፍሪካ ሁላ ኩራት ማድረግ እንችል ነበር!
Posted in Ethiopian News

ግንቦት 7 ለኢትዮጵያዊነት ቆሚያለሁ የሚለን የምሩን ወይስ ድራማ እየሰራብን? #ግርማክሳ

እሁድ የካቲት 10 ቀን 2011፣ ግንቦት ሰባት በደብረ ማርቆስ ከተማ ሕዝባዊ ስብሰባ አድርጓል። ስብሰባው የተሳካ ስብሰባ እንደነበረ ነው ደብረ ማርቆስ ነዋሪ ከነበሩ የደረሰኝ መረጃ የሚገልጸው። የተለቀቁ ፎቶዎችም ይሄንን በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው። አንዳንድ ጽንፈኛ ቤተ አማራዎች የደብረ ማርቆስ ህዝብ ላይ፣ “ለምን ግንቦት ሰባትን ደገፋችሁ ?” በሚል ነው መሰለኝ ጣት ለመቀሰር የሞከሩም አሉ። ይህ ማሳዘን ብቻ ሳይሆን አሳፋሪም ነው። የደብረ ማርቆስ ሕዝብ ፣ ማን እንደሆነ፣ አገር ሁሉ የሚያውቀው ነው። “የኛን የአማራነት ፖለቲካ ለምን አልተቀበለም ?” ብሎ አፍላፊ መካፈት ትርፉ መላላጥ ነው። ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ ጽፊያለሁ። የአማራ ወይንም አማርኛ ተናጋሪ ማህበረሰብ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄረተኛው ፣ በትግራይና ኦሮሞ ብሄረተኛ ፖለቲከኞች ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት፣ እንደ ጠላት እየታየ፣ ተለይቶ ሲጠቃና ሲገለል ነበር። አሁንም እንደተገለለ ነው። ከዚህም የተነሳ፣ “ራሳችንን መከላከል ስላለብን ፣ የሕልዉና ጉዳይ ነው” በሚል እንደ አብን ያሉ በአማራነት ስም ተደራጅተዋል። መደራጀታቸውን ባልደግፈውም፣ እንደማልቃወም፣ ለምን እንደተደራጁም እንደምረዳ በመግለጽ፣ በሂደት ግን ከአማራነት አልፈው አድማሳቸውን ካላሰፉ በቀር ለጊዜው ድጋፍ ቢያገኙም፣ ብዙ ዘልቀው መሄድ እንደማይችሉ መክሪያለሁ። ሆኖም የአማራ ድርጅቶች “አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፣ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ” የሚል አግላይ መፈክር እያነገቡ፣ ውስጣችን አለ የሚሉትን ኢትዮጵያዊነትን ከማጉላት ይልቅ፣ አማራነትን ብቻ ማጉላታቸው ለብዙ ወገኖች፣ እኔንም ጨምሮ ምቾት አልሰጠም። የደብረ ማርቆሱ ሰልፍ እንደ አብን ላሉ ድርጅቶች ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ሰልፍ ነው። አንደኛ ከአማራ ድርጅቶች ሕዝቡ፣ “አማራ ተበደለ” ከማለትና ብሶት ከማሰማት
Posted in Ethiopian News

በፌዴሬሽን ምክር ቤት ዙሪያ ያሉ ሕገ መንግስታዊ ግድፈቶች #ግርማ_ካሳ (በረራ ጋዜጣ ላይ የወጣ)

በቅርቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወሰን፣ አከላለልና የማንነት ጉዳዮችን የሚመለከት ኮሚሽን በአዋጅ አቋቁሟል። የዚህን ኮሚሽን መቋቋምን አንዳንድ ወገኖች “ሕገ መንግስቱን የጣሰ ነው፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ሃላፊነት የሚጋፋ ነው” እያሉ ይከሳሉ። በሌላ በኩል የኮሚሽኑ መቋቋም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ሆኖ ጥናትና ሪፖርት የሚያቀርብ እንደሆነ የሚናገሩት የኮሚሽኑን መቋቋም የሚደገፉ አካላት፣ “የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የኮሚሽኑን ሪፖርት እንደ ግባት ሊጠቀምበት ይችላል” በማለት የኮሚሽኑ መቋቋም በፌዴሬሽን ምክር ቤት ስራ ጣልቃ መግባት እንዳለሆነ በመግለጽ ይከራከራሉ። ያ ማለት አሁን የዶ/ር አብይ አስተዳደር የወሰንና የማንነት ኮሚሽን እንዲቋቋም ቢያደርግም፣ ኮሚሽኑ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ውጭ ምንም ነገር የማድረግ ስልጣን እንደሌለው ነው። የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዬ ወ/ሮ ኪሪያ ኢብራሂም በወልቃይት ጠገዴና ራያ አካባቢ ስላለው ቀውስ ፣ የፌዴሪሽን ምክር ቤቱ ሰላማዊና ህዝብን ማእከል ባደረገ መልኩ ችግሮቹን ለመፍታት ገለልተኛ ኮሚቴ እንደሚያዋቅሩ እንደገለጹ ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሰምተናል። በወልቃይት፣ ራያና ተመሳሳይ በሆኑ ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሊሰራ ያሰበውን ለጊዘው እናቆየዉና ይሄ የፌዴሪሽን ምክር ቤት የሚባለው አካል ምን እንደሆነ የሚገልጽ አንዳንድ ሐሳቦችን ለማስቀመጥ እምክራለሁ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት በዋናነት ሁለት ቁልፍ ተግባራትን እንደሚፈጽም በሕግ መንግስቱ ተደንግጓል። እነርሱም በአንቀጽ 48 እና አንቀጽ 83/84 ላይ ይገኛሉ። አንቀጽ 48 ፣ “የክልሎችም ወሰን በሚመለከት ጥያቄ የተነሳ እንደሆነ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ክልሎች ስምምነት ይፈጸማል። የሚመለከታቸው ክልሎች መስማማት ካልቻሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕዝብን አሰፋፈርና ፍላጎት መሰረት በማድረግ ይወስናል”
Posted in Ethiopian News

የኦሮሞ ብሄረተኞች ከአገር አልፈው ለአህጉር የበቁትን ወደ ጎጥ እያወረዷቸው ነው #ግርማካሳ

ለኦህዴድ/ኦዴፓ ቅርበት አለው የሚባለው ጦማሪ፣ ደረጄ ገረፋ ቱሉ(፣ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ጸጋዬ ላይ ብእሩን አንስቷል። “ቴዎድሮስ ፀጋዬ በርዮት የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ጠቅላይ ሚንስትሩን በተመለከተ አዲስ መረጃ ይዘናል በሚል የተክደናል እና ተታለናል ረጅም ሙሾ አውርዷል” ሲል ጦማሩን የጀመረው ደረጄ ፣ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ባልተጣራ መረጃ ላይ አስተያየት እየሰጠ እንደሆነ ነቅፏል። ስለ ዶ/ር አብይም ደረጃ ሲጽፍ አንደኛ ዶክተር አብይ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ያላቸው ፅኑ አቋም እና ለሀገራቸው ያላቸው ፍቅር፣ ሁለተኛ ለገዳ ስርዓት ያላቸው አድናቆትና የገዳ ስርዓት እሴቶች ለሀገር ግንባታ እና ለህዝቦች ወንደማማችነት በጣም ጠቃሚ እንደሆነ ደጋግመው ስለመናገራቸው፣ ሶስተኛ ስለ አፋን ኦሮሞ እና ሌሎች ቋንቋዎች በሀገራችን በተጨማሪነት በሁሉም አከባቢ በስራ ላይ መዋል ለሀገር አንድነት ትልቅ እንዳለው እንደሚያምኑ ይነገርናል። ስለ ዶ/ር አብይ ያስቀመጣቸው ሶስቱ ነጥቦች ላይ ብዙም የሚከራከር ይኖራል ብዬ አላስብም። ጋዜጠኛ ቴዎድርስ ጸጋዬም ሆነ ሌሎች እያነሷቸው ያሉ መሰረታዊ ሌሎች ጥያቄዎች ግን አሉ፣ እስከ አሁን ዶክተር አብይ ለመመለስ ፍቃደኛ ያልሆነባቸው። ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ጸጋዬ ላይ ትችት ስናቀርብ ፣ አንድ መረሳት የሌለበት ትልቅ ጉዳይ ቢኖር፣ ቴዎድሮሶ ጸጋዬ በግልጽና በአደባባይ ዶክተር አብይ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያላቸውን አቋም ምን እንደሆነ ጠይቆ፣ ዶክተር አብይ በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን በሚል ምላሽ ለመሰጠት ፍቃደኛ እንዳልነበሩ ነው። ጦማሪ ደረጄም ሆነ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ላይ ትችት የሚያቀርቡ ወገኖች “ለምን ተጠየቀ? ለምን ተጻፈ? …” በሚል ዜጎች ጥያቄ በማንሳታቸው መከፋት ሳይሆን እንደውም ለሚነሱ ጥያቄዎች ግልጽ ምላሽ እንዲሰጥ እነርሱም ግፊት
Posted in Ethiopian News

የጽንፈኛ የኦሮሞ ብሄረተኝነት የጀርባ አጥንት የሚሰበረው በሸዋ ኦሮሞዎች ነው #ግርማካሳ

አንዳንድ ወገኖች ስለኦሮሚያ ክልል ለምን ብዙ ትጽፋለህ ይላሉ። ምክንያቱ ቀላል ነው፤ በአገራችን ካሉት ችግሮች ዋናዎቹ ያሉት በኦሮሞ ክልል በመሆኑና በኦሮሞ ክልል ያለው መረን የለቀቀ ጽንፈኛ የኦሮሞ ብሄረተኝኘት ትልቁ የአገራችን ፈታና ስለሆነ ነው። አንዳንድ ወገኖች ደግሞ ስለ ሸዋ ስጽፍ ሸዋዬ አድርገው ይወስዱኛል። ለነገሩ ሸዋዬ ነኝ።የሸዋ ሰው።ሸገር፣ አዲስ አበባ የሸዋ እንብርት ናት። ስለዚህ እንደ ሸገር ልጅ የሸዋ ልጅም ነኝ። ሸዋ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ እንደመሆኑም ኢጆሌ ሸገር፣ ኢጆሌ ሸዋ ፣ ኢጆሌ ኢትዮጵያ ነኝ። የተወለድኩትና ያደኩት አዲስ አበባ ሸዋ ነው። አያት ቅድም አያቶቼ ከሸዋ ነበሩ። ሁለት ከአዳ(ቢሾፍቱ አካባቢ)፣ አንድ ከሸንኮራ፣ አንድ ከመንዝ። ሁለት ወደ ነገሌ ቦረና ሁለት ደግሞ ወደ ጎጃም ናቸው። ስለዚህ ሸዋ በመወለዴና ግማሽ የሚሆኑ ቅድም አያቶቼ ከሸዋ ስለነበሩ፣ ከሸዋ ጋር አዎን የበለጠ ቁርኝነት አለኝ። ግን ስለ ሸዋ የምጽፈው እኔ ከሸዋ ጋር የበለጠ ቁርኝነት ስላለኝ አይደለም። የኢትዮጵያ አንድነት ማረጋገጥ፣ ኢትዮጵያዊነት ማስቀጠል የሚቻለው ሕብረብሄራዊ የሆነችዋን ሸዋን እንደገና በማጠናከር ነው። ሸዋን እንደገና ማጠናከር በጣም እጅግ ሲበዛ በጣም ቀላል ነው። የሸዋ ሕዝብ፣ በያንዳንዱ ወረዳ አስተያየቱን እንዲጠይቅ ማድረግ ነው። “በኦሮሞ ክልል መቀጠል ትፈልጋላችሁ ወይስ አማርኛና ኦሮምኛ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ተደርጎ ሸዋ የራሱ ፈዴራል መስተዳደር ሆኖ እንዲቀጥል ትፈልጋላችሁ ?” በሚል ህዝብ ቢጠየቅ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የሸዋን መስተዳደር መመለስ የሚፈልጉ አብላጫ ድምጽ ሊኖራቸው ይችላል ብዬ አስባለሁ። አንደኛ – በሸዋ በተለያዩ ቦታዎች በሃላፊነት የተቀመጡት ከወለጋ፣ አርሲ …የመጡ ናቸው። የሸዋ ኦሮሞዎች
Posted in Ethiopian News

አፓርታይድና ዘረኘነት በድሬዳዋ፣ ሃረር፣ አዳማ/ናዝሬትማ ጂማና በርካታ ቦታዎች #ግርማካሳ

  በድሬዳዋ 40:40:20 በሚል የድሬዳዋን ከተማ የኦሮሞና የሶማሌ ፖለቲከኞች ናቸው እየተፈራረቁ የሚያስተዳድሩት። አርባ ለኦሮሞ፣ አርባ ለሶማሌ ተመድቦ ሌላው ማህበረሰብ 20% ድርሻ ብቻ ነው ያለው። ከዚህም ዘረኛ አሰራር የተነሳ ህዝቡ፣ በተለይም ኦሮሞና ሶማሌ ያልሆነው ማሀብረሰብ ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት ከፍተኛ በደልና መድልዎ ሲደርስበት ነበር። የዚህ ሕዝብ ብሶት ገንፍሎ ላለፉት በርካታ ቀናት ድሬዳዋ ከተማ ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃዉሞን እያስተናገደች ነው።   ከድሬዳዋ በባሰ ሁኔታ በሌሎች ማህበረሰባት ላይ በደል፣ ግፍና ልዩነት የሚፈጸምባቸው ሌሎች ከተሞችና አካባቢዎች ጥቁት አይደሉም።   ከድሬዳዋ አቅራቢያ ያለችዋን ታሪካዊቷን የሃረር ከተማ መውሰድ እንችላለን።በዚያ 8% ነዋሪው አደሬ ነው። 30% አማራ፣ 56% ኦሮሞ። ኦሮሞና አደሬ ያልሆኑት 36% ናቸው። ግን የከተማዋና የሃረሬ ክልል መስተዳደር የተያዘው 50% በኦሮሞ ፣ 50% በአድሬ ነው። ሌሎች አማራዎችን ጨምሮ 36% ነዋሪዎች ምንም መብት የላቸው። ዜሮ። ስለዚህ በሃረር፣ ከድሬዳዋ በባሰ 50፡50 ዘረኛ አሰራር ነው ያለው ማለት ይችላል። አምሳ ለኦሮሞ፣ አምሳ ለአደሬ።፣ ዜሮ ለሌሎች።   ወደ አዳማ/ናዝሬት ስንሄድ ደግሞ ሌላ የባሰ ሁኔታ ነው የምናየው። ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ወደ ሃያ በመቶዎች ቢሆንም የከተማዋ ባለቤት ኦሮሞው ብቻ ስለሆነ፣ ሌሎች በከተማዋ አስተዳደር ውስጥ እጣ ፋንታ የላቸውም። እርሱ፣ ወላጆቹ፣ ቅድመ አያቶቹ ናዝሬት ከተወለደ የናዝሬት ልጅ ይልቅ፣ በቅርቡ በአዳማ ነዋሪ የሆነ፣ ከያቤሎና ደምቢዶሎ፣ ፣ ከኮፈሌና ከሞያሌ፣ ከጊምቢና ከደምቢ የመጡ፣ የበለጠ መብት አላቸው። ኦሮሞ ስለሆኑ ብቻ።   የአዳማ ህዝብ አብዛኛው አማርኛ ተናጋሪ ቢሆንም መሰረታዊ የዜግነት መብቱ ተረግጦ በሚናገረው ቁንቋ የመንግስት አገልግሎት እንኳን ተነፍጓል።
Posted in Ethiopian News

ኢትዮጵያዊነት ላይ ሳይሆን ዘር ላይ ዜጎች እንዲያተኩሩ ያደረገው ሕገ መንግስቱና አወቃቀሩ ነው #ግርማካሳ

“የአማራ፣ የትግሬ፣ የኦሮሞ መሬት ነው የሚለው ነገር ድንቁርና ነው ” አንዳንዴ በምስልና በፎቶ ነገሮች በቀላሉ ግልጽ የመሆን እድላቸው በጣም ሰፊ ነው። አንድ ብዙ ጊዜ የምንጽፍበትና የምንከራከርበት ጉዳይ አለ። እርሱም ዜጎች በአገራቸው እንደ መጤና አገር አልባ የመቆጠራቸው ችግር ነው። “አገራችሁ አይደለም፣ መጤ ናችሁ፣ ውጡልን ..” መባሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለኢትዮጵያ ትልቅ ፈተና እየሆነ ነው። “መጤ ናችሁ፣ አገራችሁ አይደለም..” ተብለው ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት በተለይም በደቡብ፣ በኦሮሞና በቤኔሻንጉል ክልል አማራዎች፣ አማራ ያልሆኑ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ ከተለያዩ ብሄረሰብ የተወለዱ፣ ጉራጌዎች፣ ከንባታዎች …ከቅያቸው ተፈናቅለዋል። አሁን በቅርቡ እንኳን በምስራቅ ሸዋ ዞን በፈንታሌ ወረዳ በአክራሪ ኦሮሞዎች ከአገራችን ውጡልን ተብለው በጭካኔ ብዙ አማራዎች ተፈናቅለው። በአሁኑ ወቅት በአዋሳ በአክራሪ ሲዳሞዎች የጉራጌ ማህበረሰብ አባላት ሱቃቸው እየተዘጋ ከአገራችን ዉጡልን እየተባሉ ነው። ብዙ ከንባታዎች ከአርሲ ተፈናቅለዋል።በሌሎች አካባቢዎች ያሉትን ስንመለከት ደግሞ ወደ ስድስት መቶ ሺህ ኦሮሞዎች ከሶማሌ ክልል፣ አራት መቶ ሺህ ሶማሌዎች ከኦሮሞ ክልል፣ ሁለት መቶ ሺህ ኦሮሞዎችና አማራዎች ከቤኔሻንጉል ክልል፣ በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ጌዴዎኦች ከኦሮሞ ክልል፣ በአስር ሺሆች የሚቆጠሩ ጋሞዎች አሁንም ከኦሮሞ ክልል….መጤ፣ አገራችሁ አይደለም ተብለው ተፈናቅለዋል። ብዙዎች በዘር ተኮር ጥቃት ተገድለዋል። ይሄን ዜጎች መጤ የማለትና የማፈናቀል መንፈስ ያመጣው ፣ ያመጣው ብቻ ሳይሆን ያጠናከረው፣ በሕወሃትና በኦነግ የተረቀቀው ዘረኛ ሕገ መንግስትና ዘረኛ የፌዴራል አወቃቀር ነው። በፌዴራሉ አወቃቀር መሰረት አገሪቷ በዘርና በጎሳ ነው የተሸነሸነችው። ስለዚህ አማራው ከአማራ ክልል ውጭ፣ ጉራጌው ከጉራጌ ዞን ውጭ፣
Posted in Ethiopian News

የዜግነት ፖለቲካ ይሰራል፣ አሸናፊም ነው- ምላሽ ለአብኖች – ግርማ_ካሳ

ዋልታ ከአብን ም/ሊቀመንበር አቶ በለጠ ሞላና ከሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ ክርስቲያን ታደለ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ፣ ሁለቱንም ክፍሎች አደመጥኩ። ወደ ቃለ መጠይቆቹ ይዘት ከመግባቴ በፊት ስለ ዋልታ ጋዜጠኛው ትንሽ ማለት ፈለኩ። የቤት ስራውን በደንብ ሳይሰራ የመጣ ነው የሚመስለው። ያ ብቻ አይደለም እንደ ገለልተኛ ጋዜጠኛ ሳይሆን የሌላ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካይ ነበር የሚመስለው። በግለሰቦች የሚታተመውን የበረራ ጋዜጣ የአብን እንደሆነ እድርጎ መግለጹን እንደ አንድ ምሳሌ ማቅረብ ይቻላል። ካልጠፋ አጀንዳ፣ በአብን አርማ ላይ ስላለው የንስር ምልክት በማንሳት “የንስር ምልክት ያላችሁት ከሌላው የበላይ ነን ለማለት ብላችሁ ነው” የሚል መላምታዊ አስተያየት መስጠቱንም እንደሌለ ሁለተኛ ምሳሌ ልንጠቅሰው እንችላለን። በአጠቃላይ በኤልቲቪ የቤቲ ታፈሰ ዝግጅት ላይ እንደበረው፣ አብኖች ከዋልታ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ “hostile” ቃለ ምልልስ ነበር ማለት ይችላል። አንዳንድ “ታዋቂና በሳል” የሚባሉ የፖለቲካ አመራሮች ለነርሱ አመለካከት ቅርብ የሆኑ ሜዲያዎች ላይ ብቻ እየመረጡ እንደሚቀርቡ ይታወቃል። አብኖች ” hostile” በሆኑ ሜዲያዎች ላይ ቀርበው ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት መቻላቸው ምን አልባት ከነርሱ ጋር የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ስላለን ላይታየን ይችል ይሆናል እንጂ ጥንካሪያቸውን በአንድ ጎኑ የሚያሳይ ነው። ወደ ቃለ ምልልሱ ይዘት ስንመለስ ብዙ ጥያቄዎች ያጠነጠኑት ከአማራነትና በአማራ ማንነት ዙሪያ በእደራጀት አስፈላጊነት ዙሪያ ላይ ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ ያለኝ የግል አቋም በፊትም የነበረኝ፣ አሁንም ያለኝ ወደፊት ይኖረኛል ብዬ የማስበው አቋም ያው ነው። ትግሬ፣ አማራ፣ ኦሮሞ..እየተባባሉ በዘር መደራጀት አይጠቅምም፣ ጎጂ ነው የሚል እምነት
Posted in Ethiopian News

የዘዉግ ፊዴራሊዝሙ እያለ ዜጎች እኩል ይሆናሉ ማላት አሳ በመሬት ላይ ይሄዳል ማለት ነው #ግርማካሳ

ዩጎዝላቪያ አንድ ወቅት አውሮፓ ውስጥ ታላቅ ከሚባሉት አገሮች አንዷ ነበረች። የፊልድ ማርሻል ጆሴፍ ቲቶ፣ የማዜር ቴሬዛ አገር። ስድስት ክፍለ ሃገራት የነበሩበት የፊዴራል ስርዓት ነበራት። ክፍለ ሃገራቱ ሰርቢያ፣ ሞንቴኔግሮ፣ ቦዝኒያ ሄርዞጊቪና፣ ማሳዶኒያ፣ ክሮዊሺያና ስሎቬኒያ ነበሩ። በሰርቢያ ክፍለሃገር ውስጥ ደግሞ ኮሶቮና ቮጅቮይዳና የሚባሉ የራስ ገዝ አስተዳደሮችም ነበሩ። ከሁለተኛ አለም ጦርነት በኋላ ዩጎዝላቪያን ሲገዙ የነበሩ ጆሴፍ ቲቶ ከሞቱ በኋላ በአገሪቷ ብሄረተኝነት ማቆጥቆጥ ጀመረ። ከዚያም የተነሳ ወደ አስር አመታት ገዳማ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ አገሪቷ ተዘፈቀች። ፌዴረሺኑ ፈረሰ። ከአንዲቷ ዩጎዝላቪያ ሰባት ትናንሽና ደካማ አገሮች ተፈጠሩ። በቀዳሚነት ከፊዴረሽኑ የወጣችሁ ጀርመን ድንበር ላይ ያለችው ስሎቪኒያ ነበረች። ስሎቬኒያ በብዛት ስሎቬኒያዉያን የሚኖሩባት ስለነበረች፣ መጀመሪያ አካባቢ ከፌዴራል መንግስቱ ጋር ከነበሩ የአሥር ቀናት ጦርነት ውጭ ብዙ የከፋ ቀውስ አላጋጠማትም። የሕዝብ መፈናቀል፣ የዘር ማጽዳት ተግባራትም ብዙ አልታዩም። በሞንቴነግሮም ብዙ ጦርነት አልተከሰተም። በሰርቢያ፣ በክሮዌሺያ፣ በቦስኒያ ሄርዞጎቪናና በማሳዶኒያ ግን አንድ ዘዉግ ብቻ የሚኖሩባቸው አካባቢዎች ስላልነበሩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ችለዋል። በክሮዊሺያ እጅግ በጣም ብዙ ሰርቦች ይኖሩ የነበረ። በቦዚያን ሄርዞጎቪና ደግሞ ከቦስኒያኖች ጎን ሰርቦችና ክሮዊሺያኖችም፣ በሰርቢያ ከሰርቦች በተጨማሪ ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ የኮሶቮ አልቤኒያኖች የነበሩ ሲሆን፣ በማሳዶኒያ ደግሞ አንድ አራተኛ የሚሆነው ነዋሪ አልቢኒያኖች ነበሩ። ክፍለ ሃገራቱ የተለያዩ ማህበረሰባትን ያቀፉ እንደመሆናቸው፣ በክፍለ ሃገራቱ የተከሰተው ብሄረተኝነት አንዱን ከሌላው በማላተም ፣ ምን አልባትም ከሁለተኛ አለም ጦርነት በኋላ ፣ በአዉሮፓ አህጉር፣ የከፋ የሚባል፣ የደም መፈሰስ፣ የሕዝብ ጅምላ እልቂትና
Posted in Ethiopian News

ከ0.50$ ወደ 1.20$ በሁለት ወር አድገናል፣ ግን ብዙ ይቀረናል #ግርማካሳ

ከአንድ ሳምንት በፊት በዳያስፖራ ፈንዱ የተሰበሰበው ግማሽ ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነበር። ወደ ሶስት ሚሊዮን ዳያስፖራ ይኖራል ተብሎ ነው የሚጠበቀው። ግን ቁጥሩን አሳንሰን አንድ ሚሊዮን ነው ያለው ብንል እንኳን በቀን አንድ ዶላር ሳይሆን በሁለት ወር አምሳ ሳንቲም የማዋጣት ያህል ነበር ። አሁንም በጣም፣ እጅግ በጣም ትንሽ ነበር። ባለፉት አስር ቀናት ግን የተሰበሰበው ገንዘብ ቁጥሩ ወደ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ደርሷል።፡ በሶስት እጥፍ ነው ያደገው። ይሄ ትልቅና አስደሳች ለዉጥና ስኬት ነው። ሆኖም ቁጥሩ አሁንም መሰብሰብ ካለበት በጣም ያነሰ መሆኑን ላሰምርበት እወዳለሁ። በሁለት ወር አምሳ ሳንቲም ከመሰብሰብ ፣በሁለት ወር አንድ ብር ከሃያ ሳንቲም ወደ መሰብሰብ ነው የተሸጋገርነው። በአጠቅላይ አሁን መሰብሰብ ከነበረበት ሰባ ሁለት ሚሊዮን ዶላር፣ አንድ ነጥብ አምስት አካባቢ ብቻ መሰብሰቡ፣ መሰብሰብ ካለበት ሁለት ከመቶ ብቻ መሰብሰቡን የሚያሳይ ነው። አዎን ከግማሽ ሚሊዮን ወደ አንድ ነጥብ ግማሽ ሚሊዮን መድረስ ትልቅ መሻሻል ነው። ግን አሁንም እዚያው ገና እየተንፏቀቅን በመሆናችን እንደ ኢሊ ሳይሆን እንደ ጥንቸል ወደ ፊት ትልቅ እርምጃ የምንራመድበትን አሰራር ማስቀመጥና ተግባራዊ ለማድረግ መነሳት አለብን። – ከዚህ በፊት ደጋግሜ ጽፌዋለሁ፣ የትረስት ፈንዱ የቦርድ አባላት በጥቅሉ ገንዘብ አዋጡ ሳይሆን ፕሮጀክቶችን ነድፈው፣ በዚህ አመት እነዚህን ነው የምናደርገው ብለው ያቅርቡልን። ከፈረሱ በፊት ጋሪውን ማስቀደማቸው ለገንዘብ ማሰባሰቡ ትልቅ እንቅፋት ሆኗል። – ኮሚቴው በየከተማው ያሉ የእምነት ተቋሟት፣ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበራት ጋር በጉዳዩ ላይ ይምከሩ። ከነርሱ ጋር አብሮ የሚሰሩበትን
Posted in Ethiopian News

ወንድሜን፣ መሪዬን ዶ/ር አብይን የ2018 የአመቱ ሰው ብዬዋለሁ #ግርማ_ካሳ

እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር ወደ 2019 አዲስ አመት እየተሻገርን ነው። ባለፈው አመት በአገራችን ኢትዮጵያ ሕወሃት የተወገደበት አመት ነው። የድል አመት። ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ብሩህ ተስፋ የፈነጠቀበት አመት። ይህ ባለፈው አመት ያየነው ለውጥ ተጀመረ እንጂ አላለቀም። በሂደት ላይ ያለ ነው እንጂ ገና ሙሉ አይደለም። ብዙ ፈተናዎች አሉት። ምንም እንኳን ህወሃት ይሄን ለውጥ ሊቀለብሰው የሚችልበት ሁኔታ ጠባብ ቢሆንም፣ በፖለቲካ አስተሳሰብና ርዪት አለም ከሕወሃት ጋር ተመሳሳይነት ባላቸው አክራሪ የኦሮሞ ብሄርተኛ ፖለቲከኞች ግን ለውጡ የመጨናገፍ እድሉ የጠበበ አይደለም። እነዚህ ጽንፈኛ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ኦነግ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ያሉት፣ ገዢው ፓርቲ ኦህዴድ/ኦዴፓ ውስጥ በብዛት ተሰግስገው እንዳሉ ለማወቅ በኦሮሞ በክልል መስተዳደር ታችኛዉና መካከለኛ መዋቅር ያሉ አመራሮች እየፈጸሙት ያለውን መመልክት ብቻ በቂ ነው። ይህን ለውጥ እየመራ ያለው ሚሊዮኖች “አብያችን” የሚሉት ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ነው። ጀነራል አሳምነው ጽጌ የኢትዮጵያ ሙሴ ያለው ዶ/ር አብይ፣ በስልጣን ላይ በቆየ በሰባት ወራት ውስጥ ከትግል አጋሮቹ አቶ ገዱ፣ አቶ ደመቀ፣ አቶ ለማ መገርሳ፣ ወ/ሮ ዳግማዊት ከመሳሰሉት ጋር በመሆን በፌዴራል ደረጃ ከፍተኛና መሰረታዊ ለውጦች በአገሪቷ አምጥቷል፤ እያመጣም ነው። እንደ ጦማሪና አክቲቪስት በክልል ደረጃ በዜጎች ላይ እየደረሱ ያሉትን ጸረ-ዲሞክራሲያዊ፣ ኢሰብአዊ፣ ዘር ተኮር ግጭቶችን፣ መፈናቅሎችን፣ ግድያዎችና ሽብሮችን መቆጣጠርና ሕግን ማስከበር ባለመቻሉ፣ የዶ/ር አብይ አስተዳደር ላይ ከፍተኛ ተቃዉሞና ትችትን አቅርቢያለሁ። በተለይም በኦሮሞ ክልል ውስጥ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመሩት ኦህዴድ/ኦዴፓ ፓርቲ ውስጥ ያሉ የታችኛውና መካከለኛ፣ው አመራር አባላት፣ በወረዳዎች፣ በቀበሌዎችና በከተሞች
Posted in Ethiopian News

ሻሽመኔ በአክራሪ ኦህዴዶች እስከተዳደረች ድረስ የሚለወጥ ነገር አይኖርም #ግርማ_ካሳ

እንደገና በሻሸመኔ የሆነውን አንገት የሚያስደፋ አሳፋሪ ድርጊትን የሚያሳይን ፎቶ ብቻ እንጂ ቪዲዮ ማሳየቱን አልፈለኩም። በጣም ማየቱ ስለሚከብድ። ሻሸመኔ የፍቅር ከተማ ናት። አማራው ጉራጌው፣ ሲዳማው፣ ከንባታው፣ ኦሮሞው ….ሁሉም በሰላምና በፍቅር የኖሩባት ከተማ። የከተማዋ ሕዝብ ሕብረ ብሄራዊ ነው። አብዛኛውም ነዋሪ አማርኛ ተናጋሪ ነው። ሆኖም ከተማዋ የኦሮሞ ናት በሚል በኦሮሞ ክልል ስር እንድትሆን ተደርጋለች። ከተማዋን ከላይ እስከ ታች የሚያስተዳድሯት፣ በከተማዋ ማይኖሪቲ የሆኑት ኦሮሞዎች ብቻ ናቸው። ልክ እንደ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ጂማ፣ አሰላ..እንዳሉ ከተሞች ማለት ነው። አብዛኛው የሻሸመኔ ነዋሪን የሚወክል አስተዳደር ባለመኖሩ፣ በሌሎች ማህበረሰባት ላይ አድልዎ፣ በደል፣ ግፍ ሲፈጸም ፣ የዘር ልዩነት ሲደረግ፣ ለሌሎች ማህበረሰባት የሚቆም አካል የለም። ልክ በደቡብ አፍሪካ በአፓርታይድ ዘመን ለጥቁሮች መብት የሚቆም በአፓርታይድ የመንግስታዊ መዋቅር ውስጥ እንዳልነበረው ሁሉ። ያኔ ነጮች በጥቁሮች ላይ ግፍ ሲፈጸሙ የሚከለክላቸው፣ የሚቀጣቸው የበላይ አካል አልነበረምና። በሌሎች የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች እንደሚታየው በሻሸመኔም ጥቂት የኦሮሞ አክራሪ ቄሮዎች የፈለጉትን ሲያደርጉ፣ የፈለጉትን ሲገድሉ፣ ሲያስሩ ለምን የሚላቸው አካል የለም። የከተማዋ የኦህዴድ/አዴፓ አመራሮች ሕዝቡን የማይወክሉ ከነዚህ ከጃዋር አክራሪዎች ጋር  የሚያብሩ ናችው። በመሆኑም በሻሸመኔ እነዚህ ጽንፈኞች ከሕግ በላይ ሆነዋል። የከተማዉን ህዝብ የሚወክል የከተማ ፖሊስ ሃይል፣ የከተማዋን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ የከተማዋ አስተዳደር ቢኖር ኖሮ፣ ሻሸመኔ እንደዚህ አትሆንም ነበር። አሁን ግን የሻሸመኔን ሕዝብ የማይወክሉ ጥቂት የኦሮሞ ዘረኛ ግሩፖሽ ከተማዋን ስለያዙና በሃላፊነት ላይ ስልተቀመጡ  ከተማዋ የወንበዴ ከተማ ሆናለች። ከዚህም የተነሳ የአክራሪ ቄሮ መሪን ጃዋርን ለመቀበል በሻሸመኔ ተሰባስበው በነበረበት
Posted in Ethiopian News

በቀን አንድ ዶላር ሳይሆን በሁለት ወር አምሳ ሳንቲም ብቻ ? መሆን የለበትም። #ግርማካሳ

ዶ/ር አብይ የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በሁለት ወር ጊዜ ግማሽ ሚሊዮን ብር ብቻ በመሰብሰቡ ማዘኑን ገልጿል። ማዘኑም ተገቢ ነው። ከአንድ ወር በፊት ” በ 3 ሳምንታት $250000 ብቻ? ከዚህ በላይ ማድረግ እንችላለን” ብዬ ችግሮች እንዳሉ በመግለጽ የማሻሻያ ሃሳቦችን አቅርቤ ነበር። የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ላለፉት ሁለት ወራት ፣ ከኦክቶበር 22 2018 ጀምሮ ለልማት ባሰባሰበው ገንዘብ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆን ገንዘብ እንደተሰበሰበ በድህረ ገጹ አሳውቋል። ገንዘብ ላዋጡ 2819 ዜጎችንም እናመሰግናለን ብሏል። ይህ ገንዘብ እጅግ፣ እጅግ በጣም ትንሽ ገንዘብ ነው። ለምን እንደሆነ ላስረዳ። የተባለው አንድ ዶላር በቀን ነው። ወደ ሶስት ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዉያን ይኖራሉ ተብሎ ነው የሚገመተው። ሆኖም በዚህ ጽሁፍ ላይ አንድ ሚሊዮን ነው ያለው ብለን እንውሰድ። በቀን አንድ ዶላር ከወሰድን በሁለት ወር ፣ በስድሳ ፣ ስድሳ ሚሊዮን ዶላር መሰብሰብ ነበረበት። ግን የተሰበሰበው መሰብሰብ ከነበረበት ከአንድ በመቶ በታች ነው። በሌላ መልኩ ላስቀምጠው፣ አንድ ሚሊዮን የዳያስፖራ አባል በሁለት ወር አምሳ ሳንቲም እንዳዋጣ ማለት ነው። ያለ ምንም ጥርጥር ዳያስፖራ በአመት ቢያንስ አንድ ቢሊዮን ዶላር ማዋጣት ይችላል። አቅሙ አለው። እንግዲህ ጥያቂዎች መጠየቅና መሰረታዊ ግምገማዎች ማድረግ ያስፈለጋል። ይሄንን ሃይል ለምን በብቃት ማንቀሳቀስ አልተቻለም? ምንድን ነው ችግሩ? አሰራራችን እንዴት ብንቀየር ነው የበለጠ ዉጤት የምናመጣው? ብለን መጠየቅ አለብን። ከወር በፊት የጻፍኩትን እንደገና ከልሼ የሚከተሉትስ አራት ነጥቦች እንደሚከተለው አቅርባለሁ፡ ፩. የትረስት ፈንዱ ግሩማ ፕሮፌሽናል ድህረ ገጽ አዘጋጅቷል። ሆኖም ድህረ
Posted in Ethiopian News

የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ሁሉ በግእዝ ፊደል እንዲጠቀሙ ማግባባት ያስፈልጋል – ያሬድ ጥበቡ

የኦሮሞ ብሄርተኞች ኢትዮጵያን ማስተዳደር ከፈለጉ አፋን ኦሮሞን የየትኛውም ብሄረሰብ ብቸኛ ሃብት ባልሆነው በግእዝ ፊደል ወይም ኢትዮጲስ እንዲፃፍ ቢፈቅዱ የተገንጣይ ስሌት እርግፍ አድርገው መተዋቸውንና፣ ኢትዮጵያን ከነሙሉ ታሪኳ ለማቀፍ መወሰናቸውን ስለሚያሳይ ሃገር የሚያረጋጋ ይመስለኛል። በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ መሪነት ብቸኛ የአፍሪካ ፊደል የሆነውን ግእዝ የአፍሪካ ቋንቋዎች ፊደል እንዲሆን ኢትዮጵያ ሃሳብ ታቀርባለች ብዬ አስባለሁ። ያ ከመሆኑ በፊት ግን የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ሁሉ በግእዝ ፊደል እንዲጠቀሙ ማግባባት ያስፈልጋል፣ ይህም ሃላፊነት በጠቅላይ ሚኒስትሩና በኦቦ ለማ መገርሳ ትከሻ ላይ ወድቋል። እነርሱ ኦሮሞን ማሸነፍ ከቻሉ፣ የተቀረው ገብስ ነው። የተለየ የኦሮሚያ ሪፐብሊክ ለመመሥረት የወረረን የላቲን ቁቤ እንዲያከትም መከራከር፣ መምከር መጀመር አለብን። በጉዳዩ ላይ ብዙ ጥናት ያደረጉትም የኮምፒዩተር ሳይንስ ምሁር ዶክተር አበራ ሞላ ከሰሞኑ ወደ አዲስ አበባ ስለሚያቀኑ፣ መንግስት፣ ምሁራንና፣ ሚዲያው ተገቢውን ትኩረትና መድረክ ይሰጣቸዋል ብዬ አስባለሁ። ከ42 ዓመታት በፊት በግእዝ ፊደል የተፃፈውን በሪሳ ጋዜጣ እስኪ ተመልከቱት።
Posted in Ethiopian News

የኦሮሞ ብሄረተኝነትና ተስፋፊነት ለሚሊዮኖች መፈናቀል ምክንያት ነው #ግርማ ካሳ

በለማ ቲም የሚመራው የለውጥ እንቅሳሴ ከመጣ በኋላ በአገራችን ያለው ትልቁና ዋናው ችግር የኦሮሞ ተስፋፊ ብሄረተኝነት እንደሆነ ደጋግሜ ጽፊያለሁ። ይሄን ብሄረተኝነት ከማንም በላይ የጎዳውም የኦሮሞ ማህበረሰብን ነው። የኦሮሞ ብሄረተኞች ፣ የኦሮሞ ነው የሚሏቸው ቦታዎች ትንሽ አይደሉም። ኦሮሞዎቹ የኦሮሞ ነው እንደሚሉትም ሌሎችም አሁን ኦሮሞ ክልልው ውስጥ ያሉ አንዳንድ ቦታዎችን የኦሮሞ አይደለም የኛ ነው የሚሉም አሉ።በምሳሌ ለማስረዳት እሞክራለሁ። የኦሮሞዎ ብሄረተኞች፡ ፩. አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት፣ በኦሮሞ ክልል ስር ሙሉ ለሙሉ መሆን አለባት” ይላሉ። ፪. ሙሉ ለሙሉ የሃረርና የድሬዳዋ ከተሞች ፣ ከሶማሌ ክልል በርካታ መሬቶች ከደቡብ ሽንሌ/ሲቲ ዞን፣ ከምእራብ ፋፋንና ኖጎግ ዞኖች ወደ ኦሮሞ ክልል ምስራቅ ሃረርጌ ዞን እንዲጠቃለል ይፈልጋሉ። ፫. የተወሰኑ መሬቶች ከሶማሌ ክልል ምእራብ አፍዴር ዞን፣ የሊበንና የዳዋ ዞን ሙሉ ለሙሉ (የሞያሌን ከተማ ጨምሮ) ወደ ኦሮሞ ክልል እንዲዞር ይፈልጋሉ። ፬. በምስራቅ ወለጋና በምእራብ ወለጋ መካከል ያለው አብዛኛው ጉሞዞች በብዛት የሚኖሩበት የቤነሻንጉል ክልል ከማሽ ዞን ወደ ኦሮሞ ክልል እንዲጠቃለል ይፈልጋሉ። አዲስ አበባ የኛ ነው የሚለው ድፍረታቸው በአዲስ አበባ ህዝብ ከፍተኛ ወገዛ ያስከተለባቸው ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ራሷን በራሷ ከማስተዳደር አልፋ የራሷን እድል በራሷ እንድትወሰን ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው። አዲስ አበባን የኦሮሞ ለማድረግ የአዲስ አበባን ዲሞግራፊን ለመቀየር፣ የኦሮሞ ብሄረተኞች እነ ዶ/ር አብይን ውስጥ ውስጡን አስገድደው ያስቀመጡት ታከለ ኡማ፣ ከፍተኛ ተቃዉሞ እየደረሰበት በመሆኑ እንዲያፈገፍግ የተደረገበት ሁኔታ ነው ያለው። በሸገር ረገድ የኦሮሞ ብሄረተኞች መቶ በመቶ
Posted in Ethiopian News

ግንቦት ሰባትና አብን ሊነጋገሩ መሆኑ መልካም ዜና ነው #ግርማካሳ

ታስሮም፣ ከመታሰሩም በፊት፣ ከታሰረም በኋላ ብዙ ጊዜ ጽፊያለሁ። አንዳርጋቸው የማከብረውና የማምው ሰው ነው።አደርባይና አጨበራባሪ አይዸለም። አዎን ከቅንጅት ወደ ግንቦት ሰባት ሲሄድ፣ የአላማ ሳይሆን የስትራቴጂ ልዩነቶች ስለነበሩኝ፣ እንደ አንዳራጋቸው ሳይሆን እንደ ግንቦት ሰባት አመራር እቃወመው ነበር። ያም ቢሆን ፣ ያመነበትን፣ ሰው ባይቀበልም ሳይፈራ የሚናገር ፣ ኢንቴግሪቲ ያለው ሰው እንደሆነ አውቃለሁ። እኔ ብቻ ሳልሆን ከርሱ ጋር በፖለቲካ አመለካከት የማይስማሙ የማውቃቸው ወገኖችም ተመሳሳይ አመለካከት ነው ያላቸው። አንዳርጋቸው ከወ/ሮ እማዋይሽ ጋር በድብረ ታቦር ግንቦት ስባትን ወክሎ ህዝባዊ ስብሰባ አድርጓል። ስበሰባዉን ለመረበሽ፣ አንዳንድ ቄሮ መሳይ አክርሪዎች በሶሻል ሜዲያ “ረብሹ፣ በጥብጡ፣ ባነር ንቀሉ ..ወዘተረፈ” እያሉ ርካሽና የወረደ ቅስቀሳ ቢያደርጉም፣ ስብሰባው ግን በሰላም ብዙ ሕዝብ ባለበት ተጠናቋል። በአንድ ደርጅት ላይ ተቃዉሞ ሊኖር ይችላል። ያ ደርጅት ፣ “እኔ ስለምቃወመው አባላቱንና ደጋፊዎችን መሰብስ የለበት” ከማለት በስብሰው ተገኝቶ ተቃዉሞም ካለ ተቃዉሞን ማቅረብ፣ ጥያቄዎችም መጠየቅ የሰለጠ ፖለቲካ ነው። በደብረ ታቦሩ ስብሰባ በግንቦት ሰባት ደስተኛ ያልሆኑ ብዙ ወገኖች ተገኝተው አንዳርጋቸው ጽጌን ጠይቀዉታል። ይሄን ጊዜ ሌሎች ቢሆኑ ይሳደቡ፣ arrogantly ምላሽ ይሰጡ ነበር። አንዳርጋቸው ግን ግልጽነት ባለው መልኩ ነው በትህትና ምላሽ የሰጠው። ሁለት ከተናገራቸው ያስደሰቱኝ መልሶች አሉ። አንደኛው የአብን አመራር ስልክ እንዳለውና ከአብኖች ጋር እንደሚነጋገር መግለጹ ነው። ይሄ ትልቅ ነገር ነው። አብኖች በአማራ ስም ተደራጁ እንጂ የመጨረሻ ግባቸው የአንድነት ሃይሉ የሚፈልገው ለሁሉም እኩል የሆነች ፣ አንዲት ዴሞክራሲያውት ኢትዮጵያን ማየት ነው። አሁን አብን ውስጥ ያሉ
Posted in Ethiopian News

ስብሃት ነጋ ዶ/ር አብይን ደካማ ነው እያለው ነው #ግርማካሳ

  “አሁን አገሪቷ እያስተዳደረ ያለው ሀይል ደካማ፣ አገሪቱን ማስተዳደር የማይችል እና ፀረ ዲሞክራሲ ሀይል ነው”   ይሄን ያለው የዘረኞች አባት የሆነው ስብሃት ነጋ ነው። ዶ/ር አብይን ጸረ-ዲሞክራሲያዊ ነው ያለውን እዚያው ለርሱ ሰዎች ይንገራቸው። ዶ/ር አብይ የፖለቲካ ምህዳሩን የከፈተ፣ ጋዜጦች እንዲያብቡ ያደረገ፣ የፍርድ ቤትን የምርጫ ቦርድ ላይ ገለልተኛ ሰዎች የመደበ በአገራችን ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጾ ያደረገ ነው። አብያችን በዚህ አይታመም። ሌሎች የአፍሪካ አገሮች የኛ መሪ በሆነ እያሉት ነው።   ግን ስብሃት ነጋ “ደካማ ነው፣ አገሪቷን ማስተዳደር አልቻለም” ያለው ላይ ግን በተወሰነ ደረጃ ትክክለኛነት አይበታለሁ። እንዴት ነው ዶ/ር አብይ ደካማ አይደለም፣ አገር ማስተዳደር ችሏል ብለን መናገር እንችላለንን ?????   የኦሮሞ፣ የትግራይና የቤኒሻንጉል ክልሎች ከቁጥጥር ውጭ ሆነዋል። ሕዝብ ትልቅ በደል እየደረሰበት ነው። ህዝብ እየተፈናቀለ፣ ዜጎች በግፍና በጭካኔ እየተገደሉ ነው ።   – በምስራቅ ኦሮሚያ በሃረርጌ፣ በደቡብ ኦሮሚያ በቦረና ፣ በምእራብ ኦሮሚያ በወለጋ፣ በመሀል ኦሮሚያ ቡራዩና ፈንታሌ ..የኦነግ ርዝራዦች፣ የጃዋር አክራሪ ቄሮዎች ከሕግ በላይ ሆነው ፣ በአካባቢው ካሉ የዶ/ር አብይ ፓርቲ የኦህዴድ/ኦዴፓ የቀበሌ፣ የወረዳ አመራሮች ጋር በመተባበር እጅና ኋንት በመሆn ህዝቡን እያሸበሩት ነው። ዶ/ር አብይ እንኳን አገርን በሰላም ሊያስተዳደር፣ የራሱን አባላትን እንኳን መቆጣጠር አልቻለም፡፡ እነዚህ፣ እንደ አሰላዋ አክራሪ ከንቲባ ዘይነባ ያሉ፣ የኦህዴድ ታችኛውና መካከለኛው አመራሮች የድርጅቱን መሪ ዶ/ር አብይን ሳይሆን የሚሰሙት ጃዋር መሐመድን ነው። በአጭሩ እነ ዶ/ር አብይ ሕግን ማስከበር ካለመቻላቸው የተነሳ ክልሉን አሳልፈው ለአክራሪዎች ሰጥተዋል፡   – በትግራይ በሕግ
Posted in Ethiopian News

እነ ዶ/ር መራራ ማሳመን ሲያቅጣችው ማስፈራራቱን እንደ ስትራቲጂ እየተጠቀሙበት ነው #ግርማ_ካሳ

ዶ/ር መራራ ጉዲና አሁን ያለውን የጎሳ ፌዴራል አወቃቀር መቀጠል አለበት እያሉ ነው። ችግሩ ያለው ፌዴራሊዝሙ ላይ ሳይሆን አተገባበሩ ላይ ነው ያሉት ዶ/ር መራር ፣ ወደ ቀድሞ አስተዳደር መመለስ ዋጋ እንደሚያስከፍል ይናገራሉ። አሁን ያለው አወቃቀር ዋጋ እንዳላስከፈለ። ‹‹የትግራይ፣ የኦሮሞ፣ የሶማሌ፣ የጋምቤላ …ነፃ አውጭ ድርጅቶች ባሉበት፤ የአማራ ነፃ አውጭ የሚመስሉ ድርጅቶች እየተፈጠሩ ባሉበት ሁኔታ ወደቀድሞው አስተዳደር ሥርዓት (ጠቅላይ ግዛት) ለመመለስ መሞከር ዋጋ ያስከፍለናል” ያሉት ዶ/ር መራራ፣ መፍትሔው አሁን ያለውን የፌዴራላዊ ሥርዓት በሕዝቦች ፈቃድ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ማድረግ ነው ይላሉ። ዶ/ር መራራ አሁን ያለው የፌዴራል አወቃቀር የሚቃወሙ ወገኖች ለምን እንደሚቃወሙ ጠንቅቀው ያውቃሉ ብዬ አስባለሁ። ቅንጅት፣ አንድነት፣ ሰማያዊ፣ ኢዴፓ፣ መኢአድ ..በአገር ውስጥ ሲንቀስቀሱ የነበሩና የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄረተኛ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያንና አክቲቪስቶች፣ አሁን ያለውን የጎሳ አወቃቀር ሲቃወሙ ፣ ወደ ድሮ አሃዳዊ፣ ፌዴራል ያልሆነ ስራዓት እንመለስ በማለት አይደለም። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ፌዴራሊዝምን አይቃወምም። ፌዴራሊዝም ላይ ምንም ችግር የለም። ማንም የድሮውን አሃዳዊ ስርዓት ይምጣ አለለም። ይሄን እውነታ ዶ/ር መራራ ጠንቅቀው እያወቁ፣ የድሮውን ፣ አሃዳዊ የሆነውን አስተዳደር ስለመመለስ ለምን እንደሚያወሩ ግልጽ ሊሆንልኝ አልቻለም። አሁን ያለውን የጎሳ አወቃቀር ይቀየር በሚባልበት ጊዜ የጎሳ አወቃቀሩን የሚደገፉ ወገኖች፣ አሁን ያለውን የጎሳ አወቃቀር ለምን የተሻለ እንደሆነ አሳማኝ መከራከሪያ ከማቅረብ ይልቅ ፣ በሐሳብ ማሸነፍ ሲያቅታቸው፣ “ወደ ድሮው ስርዓት ሊመለሱን፣ ነው፣ አሃዳዊ ስርዓት ሊያመጡበን ነው፣ ደም መፋሰስ ነው የሚሆነው… .ወዘተረፈ” እያሉ ደጋፊዎቻቸውን በዉሸት በማታለልና
Posted in Ethiopian News

ሕገ ወጥ አክራሪ የሲዳማ ኢጄቶዎች ባዘዙት መሰረት በሐዋሳ ለአምስት ቀናት ት/ቤት ተዘግቶ ነበር

የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ስጋት ገብቶናል አሉ – ኢሳት (ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 3/2011)የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የከተማዋ ጸጥታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ስጋት ገብቶናል ሲሉ ገለጹ። ኤጄቶ በሚል የሚንቀሳቀሱ የሲዳማ ወጣቶች ስም የተደራጁ ሃይሎች የአካባቢውን ነዋሪ እያዋከቡ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገልጸዋል። ኢሳት ያነጋገረውና ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ የኤጄቶ አባል አንዳንድ የሲዳማን ወጣቶች መልካም ስም ለማጉደፍ ተገቢ ያልሆነ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት እንዳሉ ተናግሯል። ሰሞኑን በመኪና አደጋ ህይወታቸውን ያጡ 5 የሲዳማ ወጣቶችን ሃዘን ከመግለጽ ጋር ተያይዞ የከተማዋ ትምህርት ቤቶችና የመንግስት መስሪያ ቤቶች ስራ እንዲያቆሙ በኤጄቶ ስም የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች በማስገደዳቸው ከተማዋ ውጥረት ውስጥ መግባቷን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የከተማዋ አስተዳደር በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ እንዲሰጠን ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሃዋሳ ነዋሪዎች ተሳቀን እንድንኖር ተገደናል። በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ለሃዋሳ ነዋሪ ስጋትና ፍርሃትን ይዞብን መጥቷል፣ ከተማዋ የእኛ ናት በሚሉ አንዳንድ ወገኖች የተነሳ ወጥቶ በሰላም መግባት አስቸጋሪ እየሆነ ሲሉ ቅሬታቸውን በማቅረብ ላይ ናቸው። የኤጄቶ የማህበራዊ ድረገጽ ላይ በኢጄቶ ስም እየተፈጸመ ያለውን ረብሻና አድማ የሚያወግዝ መልዕክት ተላልፏል። ከኤጄቶ እውቅና ውጪ ረብሻዎች፣አድማዎችና ትንኮሳዎች እንዲፈጸም የሚያደርጉ ሃይሎች የኤጄቶን ጥያቄ አቅጣጫ ለማሳት ነው ሲል በገጹ ላይ አስፍሯል። በዚህ ዙሪያ የከተማው አስተዳደር ምላሽ የሚሰጠን ከሆነ ኢሳት ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑንም እንገልጻለን።
Posted in Ethiopian News

በኦህዴዶች ድጋፍ በፈንታሌ፣ ከረዩና ከኢቱ የኦሮሞ ጎሳዎች የመጡ ሽብርተኞች ሕዝብ እያፈናቀሉ ነው – ናኦሜን በጋሻው

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ለዉጥ እንዲመጣ ጉልህና ታሪካዊ ሚና የተጫወቱ የሚባሉት አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሞ ክልል ርእስ መስተዳደር ከሆኑ ወደ ሁለት አመት ሊሆናቸው ነው። የለማ ቲም ተብሎ የሚታወቀው፣  አቶ ለማና የትግል አጋሮቻቸው የሆኑ ዶ/ር አብይ አህመድ፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ዶር አምባቸው መኮንንና ሌሎችን ያካታተው ቡድን፣ፌዴራል ደረጃ ተጨባጭና የሚታዩ ለውጦች እያመጣ መሆኑም ይታወቃል። የሕሊና እስረኞች ተፈተዋል፤ የፖለኢትካ ምህዳሩ ተከፍቷል፤ የሜዲያ ነጻነት ያለ ገደብ ሆኗል። የአገሩቷን ሃብት የዘረፉና በዜጎች ላይ የሰባአዊ መብት ረገጠ ሲፈጽሙ የነበሩ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው። ሆኖም በክልል ደረጃ በተለይም በኦሮሞ ክልል፣  በተለይም በክልሉ ለሚኖሩ  በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኦሮሞ ላልሆኑ ኢትይጵያዉያን፣ እንኳን ለውጥ የመጣ እንደውም የባሰበት ሁኔታ እንዳለ ነው ነውሪዎች የሚናገሩት። አቶ ለማ መገርሳ ከክልሉ ስፋት የተነሳም በሚመሩት ደርጅት ኦህዴድ/ኦዴፓ ውስጥ ከተሰገሰጉ ያልተደመሩና አክራሪ አስተሳሰ ካላቸው የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች የተነሳ በክልሉ ሕግን ስርዓትን ማስጠበቅ አስቸጋሪ እየሆነባቸው ነው። ዜጎች መጤ እየተባሉ በተደራጁ አክራሪዎች ዝቻ፣ ማስፈራራት እየደረሰባቸው ሲሆን፣ በአንዳንድ ቦታዎች ሕይወትና እስከማጥፋትና መፈናቀል እስከምፈጠር ድረስ ጥቃቶች የተፈጸሙበት ሁኔታም አለ። በቅርቡ በምስራ ሸዋ ዞን ፈንታሉእ ወረዳ ፣ አልዴ ቀበሌ የሚኖሩ ነዋሪዎች “ለቃችሁ ውጡ” እንደተባሉና ግድያም እንደተፈጸመ፣ እንደተፈናቀሉም ኢሳይ ዘግቧል። “ቤታችንን ላይ ስማቸውን እየጻፉ ይሄ የኔ ቤት..” ብለው የታጠቁ አክራሪዎች ቤቶቻቸውን እንደወሰዱ ገልጿል። አንድ ኢትዮጵያዊት አባቷ ለወረዳው አስተዳደር ” ባካችሁ ድረስሉን፣ መሳሪያ ይዘው እየዞሩ ነው” በሚሉበት ጊዜ አስተዳዳሪው “ችግር ያለብህ እንደውም አንተ ነህ፣
Posted in Ethiopian News

ህልሜ አማርኛ ይፋዊ የአፍሪካ የስራ ቋንቋ እስኪሆን ድረስ መስራት ነው-ኒጀራዊቷ የፊልም ሰው ራማቱ ኪየታ

ህልሜ አማርኛ ይፋዊ የአፍሪካ የስራ ቋንቋ እስኪሆን ድረስ መስራት ነው-ኒጀራዊቷ የፊልም ሰው ራማቱ ኪየታ ባህር ዳር፡ ጥቅምት 17/2010 ዓ/ም (አብመድ)በፊልሙ ዓለም የአፍሪካን ወዳጅነት ለማጠናከር እየሠራች ያለችው የአፍሪካ ፊልም ስራ ባለሙያዎች ማህበር አባል ራማቱ ኪየታ አማርኛ የአፍሪቃ ህብረት የስራ ቋንቋ እስከሚሆን ድረስ ጥረቷን እንደማታቋርጥ እንደገለጸች ዶቼ ዌሌ ዘገበ፡፡ ‹‹አማርኛ ብቸኛው የአፍሪካ የስነ ጽሁፍ ቋንቋ ነው፡፡ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌት ናት፡፡ኢትዮጵያ በአማርኛ ትናገራለች፡፡ አፍሪካ ደግሞ አፍሪካን መምሰል አለባት፡፡የአፍሪካን ባህል በማዳበር ወዳጅነት መመስረት አለብን ››ትላለች ራማቱ ኪየታ ፡፡ እስካሁን በአማርኛ ላይ ምን ሰራሽ ለሚሉኝ ራሴን የአማርኛ ቋንቋ አምባሳደር አድርጌ በመሾም ዓለም አቀፍ ፊልሞች ላይ አማርኛን እስከ ሆሄያቱ እየጨመርኩ ነው የምትለው ነገ ደግሞ ፊልሞቼን በሙሉ ወደ አማርኛ እመልሳለሁ ለዚህ ስኬትም ከፕሮፊሰር ሀይሌ ገሪማ ጋር እየሰራሁ ነው ብላለች ፡፡ 1ነጥብ 2 ቢሊየን ህዝብ ባላት አፍሪካ ጥንታዊውን ባለፊደል ቋንቋ የሚናገሩት 100 ሚሊየን አይደርሱም፡፡የአፍሪካ ህብረት መሪዎችን አነጋግሪያለሁ፡፡ አሁንም አማርኛ ይፋዊ የአፍሪካ የስራ ቋንቋ እስኪሆን ድረስ ጥረቴን እቀጥላለሁ ያለችው ራማቱ ፊልሞቼም በአማርኛ ቋንቋ ይሰራሉ ብላለች፡፡ ፊልሞቿን በጀርመኖቹ ኮሎኝ እና ሀምቡርግ ስታሳይ ዶቼዌሌ አግኝቶ ያነጋገራት የአፍሪካ ፊልም ባለሙያዎች ማህበር አባል ራማቱ ኪየታ ለዶቼዌሊ አማርኛው ክፍለጊዜ እንደገለጸችው ፊልሟን በኒጀር፣በቡርኪናፋሶ፣በፈረንሳይ፣በጀርመን እና በሆላንድ ማሳየቷን ትናገራለች፡፡ አማርኛ እ.ኤ.አ. በ1955 ለአፍሪካ የስራ ቋንቋነት ታጭቶ እንደነበር መዛግብት ያሳያሉ፤ለምን እንደቀረ ግን ምክንያቱ እስካሁን በውል ባይታወቅም፡፡ ከዚህም በቀር አማርኛ በአንዳንድ የአሜሪካ ግዛቶች የስራ ቋንቋ ሲሆን፣እስራኤልም የስራ ቋንቋ ለማድረግ
Posted in Ethiopian News

የአማራ ክልል የሚባለው መፍረሱ ጥቅም አለው- ቅማንትን በተመለከተ – ግርማ ካሳ

አንድ የሆነውን ሕዝብ በጎጥ ለመክፋፈል፣ የአማራ ክልል መንግስት በሕወሃት አዛዥነት የቅማንት ብሄረሰብ አስተዳደርን እንፍጠር በሚል ከስድሳ በላይ የሰሜን ጎንደር ቀበሌዎችን ወደ ቅማንት አስተዳደር አካቷል። ወደ አርባ ሁለት ቀበሌዎች ከጅምሩ ነው ያለ ህዝብ ዉሳኔ መሬቱ የቅማንት ነው በሚል ከነባሩ የጎንደር ዞን የተለዩት ። በአስራ ሁለት ቀበሌዎች ሕዝብ ዉሳኔ ይደረግ ተብሎ ተወሰነ። በስምንቱ ህዝብ ዉሳኔ ተደረገ። በአራቱ ምርጫው ተላለፈ። ምርጫ ከተደረጋባቸው ስምንት ቀበሌዎች ሰባቱ “እኛ አንድ ነን” ብለው በነበረው የጎንደር ዞን ስር ለመቀጠል ድምጽ ሰጡ። ኳቤር ሎምየ በተባለው ቀበሌ ግን፣ የቀበሌው ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎች ድምፅ በመስጠታቸው፣ ወደ ቅማንት አስተዳደር የሚለው አዘነበለና ቀበሌው ወደ ቅማንት አስተዳደር ዞረ። ሆኖም ከሌላ ቦታ የመጡ ሰዎች ናቸው የመረጡት በሚል ተቃወሞ በመነሳቱ ጉዳዩ እስከአሁን እልባት አላገኝም። ወደፊት ምርጫ ይደረግባቸዋል የተባሉ ላዛ ሹምየ፣ አንከራ አዳዛ፣ ገለድባና ናራ አውዳርዳ በተባሉ አራት ቀበሌዎች እንደተባለው ምርጫ ሳይደረግ፣ ህዝብ ሳይጠየቅ ዉሳኔ ተላለፈባቸው። ላዛ ሹምዬና አንከራ አዳዛ የተባሉት ቀበሌዎችን ለሁለት ከፍለው ግማሹ ወደ ነባሩ የጎንደር ዞን ግማሹን ወደ ቅማንት ሸነሸኑ። ሶስተኛውን የናራ አውዳርዳ ቀበሌ ወደ ቅማንት ፣ አራተኛው የገለድባና ቀበሌ ደግሞ በነባሩ አስተዳደር እንዲቀጥል አደረጉ። እንግዲህ እነዚህ አራት ቀበሌዎች ምርጫ ይደረግባቸዋል ተብሎ ነው ፣ ያ ታጥፎ፣ ህዝብ ሳይጠየቅ ዉሳኔ የተላለፈባቸው። መጀመሪያ ወደ ቅማንት እንዲገቡ ከተወሰኑት አርባ ሁለት ቀበሌዎች በተጨማሪ ከሃያ በላይ ወደ ቅማንት እንዲገቡ የተደረጉ ቀበሌዎች እንዳሉ ይነገራል። ሆኖም የትኞቹ እንደሆኑም በግልጽ የሚታወቅ ነገር
Posted in Ethiopian News

የኦሮሚያ የጸጥታው ጀነራል ከማል በደራ መገነኘታቸው ጥያቄ እያስነሳ ነው -ናኦሚን በጋሻው

በስሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ፣ አማርኛ ተናጋሪዎች እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ በማንሳት የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል። በወለጋ፣ በሃረርጌ በርካታ የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች መጠነ ሰፊ የጸጥታ ችግሮች አያሉ፣ ካልጠፋ ቦታ ሰላማዊ በሆነው በደራ የክልሉ የጸጥታ ሃላፊ ጀነራል ከማል ገልቹ ተገኝተው የነበረ ሲሆን፣ የጀነራሉ በደራ መገኘት በአንዳንድ ወገኖች ዘንድ ጥያቄዎችን እያስነሳ ነው። የጸጥታው ሃላፊው ምን አልባት በደራ የተነሳውን የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ፣ የፖለቲካና ዴሞክራሲያዊ መፍትሄ ከመስጠት፣ በሃይል እርምጃ ለማፈን ከመታሰቡ የተነሳ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ ያላቸው አንዳንድ ወገኖች ቢኖሩም የተደረገው ሰልፍ ፍጹም ሰላማዊና ምንም አይነት ችግር ያልታየበት ሰልፍ ነበር። በደራ ወረዳ ከ 85% ነዋሪዎች አማርኛ ተናጋሪ ሲሆኑ፣ ኦሮምኛ ካልተናገራችሁ በሚል፣ ኦሮምኛ ባለማዋቃቸው ምንም አይነት የወረዳው፣ የዞኑና የክልል መንግስት አገልግሎት የማያገኙ ሲሆን፣ የመምረጥ፣ የመመረጥ መብታቸውን ተነፍገው በአገራቸው በቃያቸው እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረው ነው እየሰሩ ያሉት። በደራ ወረዳ በቀዳሚነት ጥያቄው ገንፍሎ ወጣ እንጂ ከሰባ አምስት በላይ የኦሮሞ ክልል ወረዳዎች ኦሮምኛ የማይናገሩ፣ ወይም ኦሮሞ ያልሆኑ ማህበረሰባት በብዛት የሚኖሩባቸው ናቸው። እዚያው ሰሜን ሸዋ ሳንወጣ፣ በቅምብቢት ወረዳ 60%፣ በአብቹ ወረዳ 55% ነዋሪዎች አማርኛ ተናጋሪዎች ይኖራሉ። ወደ ምስራቅ ሸዋ ስንሄድ በአዳማ ልዩ፣ ከአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ወረዳዎች ቢያንስ ከሰባ በመቶ በላይ ነዋሪው አማርኛ ተናጋሪ ነው። በጂማ በአሰላና አካባቢው፣ በተለያዩ የምስራቅ አርሲ ቦታዎች ቁጥራቸው ኦሮሞ ያልሆኑ ወይንም ሕብረሄራዊ የሆኑ ማህበረሰባት ብዙ ናቸው። የደራ ህዝብ ያነሳው ጥያቄ በመላው የኦሮሞ ክልል የሚኖሩ ማሀበረሰባት
Posted in Ethiopian News

የአማራ ብሄራዊ ንቃንቄ- አብን፣  ሕወሃትን የሽብር ቡድን ብሎ፣ በሕግ እንዲታገድ ጠየቀ 

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን) በምእራብና መካከለኛ ጎንደር ዞኖች በቅማንት ስም የተደራጁና በሕወሃት የሚትገዙ ቡድኖች እየፈጠሩ ባሉት ቀውሱ ዙሪያ ማወጣው መግለጫ፣ ሕዝብን እያሸበረ ነው ያለው የኢሕአዴግ አባል ደርጅት የሆነው ሕወሃትን ከሷል። “በአማራ ሕዝብ በአጠቃላይ፤ በሰሜን ምዕራብ አማራ በተለይ እየደረሰ ላለው የሽብር ድርጊቶች ጠንሳሽ እንዲሁም የሥልጠና፣ የትጥቅና ፋይናንስ ድጋፍ እያደረገ የሚገኘው የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር–ሕወኃት ነው” ያለው አብን ” ቡድኑ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በተለይም በአማራ ሕዝብ ላይ በፈፀማቸውና እየፈፀማቸዉ ባሉ የዘር ማጥፋት፣ ዘር ማፅዳት፣ መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ከፍተኛ ዘረፋና ውንብድና እንዲሁም በአገርና በሕዝቦች አንድነት ላይ እየፈፀመ ባለው የሽብርና የጥፋት ድርጊቶች መነሻነት በአሸባሪነት ተፈርጆ ከማናቸውም የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች መታገድ እንዳለበት አብን በጽኑ ያምናል። ስለሆነም ሕወኃት ከአገሪቱ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝርዝር ውስጥ እንዲፋቅ አብን እየጠየቀ ከዚህ አሸባሪ ቡድን ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልኩ የሚሰሩ የንግድ ድርጅቶች፣ ግለሰቦች/የጥፋት ቡድኖች ግንኙነታቸውን እንዲያቋርጡ አብን በአንክሮ ያሳስባል። ከሕወኃት ጋር ግንባር የፈጠሩ ፓርቲዎችም ውሳኔያቸውን እንዲያጤኑ አብን ይጠይቃል” ሲል በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ጠንካራ መግለጫ ነው ያወጣው። አብን ሕወሃት እንድታገድ ጥሪ ክማቀረቡ በተጨማሪ፣ የአማራ ክልል መንግስትና እሪ ደርጅቱ አዴፓ ፣ በጎንደር ለተፈጠረው ችግር ሃላፊነት መዉሰድ እንዳለበትም አሳስቧል። “የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና ገዥ ፓርቲ አዴፓ የሕዝባችንን ሰላምና ደኅንነት ከማስጠበቅ አኳያ ኃላፊነቱን በአግባቡ ባለመወጣቱ የተነሳ በሕዝባችን ላይ ለደረሰው ከፍተኛ ጥፋት ኃላፊነቱን መዉሰድ እንዳለንበት ይገለጸው የአብን መግለጫ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባልተወጡ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥትና ፓርቲ
Posted in Ethiopian News

አቶ ለማ ትኩረታቸው ከኦሮሞ ድርጅቶች አንስተው ሕዝቡ ላይ ቢያደርጉ ጥሩ ነው #ግርማካሳ

  ከአስር በላይ የሆኑ የኦሮሞ የፖላቲካ ድርጅቶች፣ ምሁራን፣ አክቲቭስቶች እና ታዋቂ ሰዎችን ያካተተ የጋራ ምክክር መድረክ በአንድ እና ሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለማቋቋም መወሰናቸውን ሰምተናል።   ስብስቡ እዉን እንዲሆን ትልቅ ሚና የተጫወቱት አቶ ለማ መገርሳ ናቸው። አቶ ለማ ያለ ማጋነን ላለፉት አመት የኦሮሞ ድርጅቶች ከጽንፈኛ አስተሳሰቦቻቸው ተመልሰው ወደ መሐል እንዲመጡ ለማግባባት ፣ በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ለማድረግ በጣም ሲሰሩ የነበሩ ሰው ናቸው። እጅግ በጣም ደክመዋል። ሆኖም ግን ኦሮሞ ከመሆናቸውና ከዘራቸው በቀር በነ አቶ ለማ መገርሳና በሌሎች የኦሮሞ ድርጅት መሪዎችና አክቲቪስቶች መካከል፣ ትላልቅ የአጀንዳ፣ የአስተሳሰብ፣ የፖለቲካ አመላካከት ልዩነቶች አሉ። ከዚህም የተነሳ የሄ ስብስብ ሆነ መድረክ ስብስብና መድረክ ከመሆን ዉጭ ለኦሮሞ ማህበረሰብ ሆነ ለሌላው ኦሮሞ ላልሆነ ኢትዮጵያዊ የሚፈይደው ይኖራል ብዬ አላስብም።   በኦሮሞ ክልል ያለው ትልቁ ችግር የኦሮሞ ብሄረተኞች የመስፋፋት ፖሊሲ፣ የኦሮሞ ብቻና የኦሮሞ አንደኛ ፖለቲካ የፈጠረው ችግር ነው። ላለፉት ሃያ ስምንት አመት የነበረው ፖሊቲካና የጎሳ አወቃቀር ፣ ኦሮሞው፣ ከሶማሌው፣ ከጉሙዙ፣ ከሃረሬው፣ ከአማራው ከጌዴዎ፣ ከጉራጌ፥ ከአዲስ አበቤዉና ኢትዮጵያ ብሄረትኛው…..ከሁሉም ጋር እንዲጋጭና ፣ እንዳይተማመን አድርጓል። በተለይም ከአማራውና ከአማርኛ ተናጋሪዎች ጋር ትልቅ መቃቃርና ክፍተት ተፈጥሯል።   እነ አቶ ለማ ያንን ክፍተት ለመሙላት፣ በኦሮሞውና በሌላው መካከል መቀራረብ መያያዝ እንዲኖር፣ አብሮነት ፣ አንድነት፣ መደመር፣ ፍቅር፣ የጋራ እሴት የሆኑትን ኢትዮጵያዊነት እንዲጠናከር ለመስራት ቢሞክሩም፣ ሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶችና አክቲቪስቶች ግን በተግባር ትልቅ መሰናክል ሲሆኑባቸው ነው ያየነው። (በነገራችን ላይ እነ አቶ ለማ
Posted in Ethiopian News

የደራ ጥያቄን ተከትሎ ቅምብቢት፣ አቢቹ፣ አዳማ ….መቀጠላቸው አይቀርም #ግርማካሳ

ከአንድ አመት በፊት በደራ ጉዳይ ሰፋ ያሉ ጦማሮች ለቅቄ ነበር። በተለይም በኦሮሞ ክልል የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ማህበረሰባት ላይ የሚደርሰው በደል፣ አፓርታይዳዊ ተጽኖና አድልዎ እንደማያዋጣና አንዱ የበላይ ሌላው የበታች ሳይሆኑ ሁሉም ዜጎች እኩል የሚታዩበት ስርዓት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አጠንክሬ ለረጅም ጊዜ ተከራክሪያለሁ። በተለይም ኦሮሞና አማራ የተደባለቀ፣ ለዘመናት አብሮ የኖረ በመሆኑ፣ ኦሮሞንና አማራን በክልል መለየት መዘዙ በጣም የከፋ እንደመሆነ በማሳሰብ ፣ በተለይም ኦሮሞዉም አማራዉም እኩል የሚታዩበት፣ ኦሮምኛና አማርኛ የስራ ቋንቋ የተደረጉበት ሸዋ የሚባለ የፌዴራል መስተዳደር እንዲኖር ክፊት አድርጊያለሁ። የአማራዉና የኦሮሞዉን መተሳሰር ዶ/ር አብይ “አማራና ኦሮሞው ሰርገኛ ጤፍ ናቸው” በማለት፣ አቶ ገዱ ደግሞ “አማራና ኦሮሞ ሰምና ፈትል ናቸው” በማለት ነበር ለማሳየት የሞከሩት። አሁንም አቶ ገዱን በመጥቀስ “ኢትዮጵያ ውስጥ በደንብ ቢጠና የአማራና የኦሮሞን ያህል የተቀላቀለ ህዝብ የለም” ። ከአመት በፊት በጦመርኩት፡ “በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ደራ ውስጥ የተወለደ አማራ ገበሬ ክልሉ ኦሮሞ ስለሆነ ብቻ ፍርድ ቤት ለመሔድ የአማርኛ ማመልከቻውን፣ ደረሰኝ ወዘተ በኦሮምኛ አስተርጉሞ መቅረብ አለበት፡፡ በዚህ መልኩ ገበሬው ለብጣሽ ሪሲት ሳይቀር መቶ ብር ወይም ከዚያ በላይ አውጥቶ ያስተረጉማል፡፡ ብዙ ኢንተርፕራይዞችም የአማርኛ ደብዳቤን በማስርጎም ሥራ የደሃ ገበሬዎችን ሀብት ይዘርፋሉ፡፡ በዚህም ምክንያት 20 ወይም 30 ገጽ ያለው አቤቱታ ለማስተርጎም ብዙ ሺህ ብሮች ስለሚያስፈልግ ከፍትኅ ሥርዓቱ እንዲገለሉ ያደርጋል ማለት ነው፡፡ በመሠረቱ እንኳንስ ትንሽ የማይባሉ ዜጎች ያሉበት አካባቢ ሆኖ አንድ ሰውም ቢሆን በራሱ ቋንቋ ፍትኅ ማግኘት የሚያስችል ሥርዓት መኖር
Posted in Ethiopian News

አቶ ለማና አቶ ገዱ ሲወዳደሩ #ግርማ_ካሳ

ሕወሃት ሳትከረበት በፊት ትልቅ ትግል የነበረባቸው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ነበሩ። ከአቶ ለማ መገርሳ ጋር ሲነጻጸሩ። አቶ ለማ በኦህዴድ ውስጥ ያሉ የሕወሃት አገልጋዮችን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጥርተው( ብዙም ስላልነበሩ) ኦህዴድ ከሕወሃት ገለልተኛ እንዲሆን በቀላሉ ነበር ማድረግ የቻሉት። አቶ ገዱ ግን ብአዴን ውስጥ ከአንድ ሶስተኛ በላይ ህወሃትና አፍቃሪ ህወሃት ስለነበሩ እንቅስቃሴያቸው በገመድ ላይ እንደመራመድ ነበር። እንደውም አንድ ወቅት የስራ አስፈጻሚ ውስጥ የሞሉት አፍቃሪ ህወሃት የብአዴን አመራሮች፣ አቶ ገዱን እስከማንሳትና ራሺያ አምባሳደር አድርጎ እስከመሸኘት የወሰኑበትም ጊዜ ነበር። ያኔ ለአቶ ገዱ በጣም ከባድ ነበር። አሁን ደግሞ የተገላቢጦሽ ሆኗል። በአማራ ክልል ትልቅ መረጋጋት አለ። ለተወሰኑ ቀናት በመተማ አካባቢ ሕወሃት አስርጎ ባስገባቸው አንዳንድ ቡድኖች ⶭግር ተፈጥሮ ነበር። ከዚያ ውጭ ግን በአሁኑ ወቅት መረጋጋት የት ነው ያለው ቢባል በአማራ ክልል ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ አብን፣ ግንቦት ስባት፣ ሰማያዊ…በነጻነት ይንቀሳቀሳሉ። የአማራ ቴሌቪዥን በአሰደናቂ ሁኔታ ገለልተኛ ነው። አቶ ለማ መገርሳ ግን በጣም እየተንገዳገዱ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው። በኦሮሞ ክልል በፍጹም መረጋጋት ብሎ ነገር የለም። ሕግና ስርዓትን ማስጠበቅ አልቻሉም። የቀበሌ፣ ወረዳ፣ ዞን የኦህዴድ አመራሮች እነ አቶ ለማን  አይሰሙም፤ የሚሰሙት እነ ጃዋርን ነው። አቶ ለማ ወለጋንና ሃረርጌ ማስተዳደር ትልቅ ፈተና ሆኖባቸዋል። እነ ጃዋርና ኦነጎች ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ነው የከተቷቸው። አቶ ለማ የሚሰሩትን እያፈረሱባቸው። የኦሮሞ ማህበረሰብ ከሌላው ማህበረሰብ ጋር በማቀራረብ በንግድ፣ በቱሪዝም፣ በኢንቨስትመንት በስራ እድል የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ አቶ ለማ ሲደክሙ
Posted in Ethiopian News