የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ወደ ኤርትራ ሲያቀኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው አምባሳደር አሊ ዩሴፍ አህመድ አል-ሻሪፍ ደግሞ በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ነው። ሁለት ዓመት ሊሞላው በተቃረበ ከአገሪቱ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጋር በሚካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የሚገኘው የሱዳን ጦር ኃይልን የሚመሩት ጄኔራል አል-ቡርሃን ዛሬ ማክሰኞ ረፋድ ላይ ነው ለጉብ…