የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የድርጅቱን መመስረት በተመለከተ እና ስለ አማራ የህልውና ትግል ወቅታዊ ሁኔታወች ለዓለም አቀፍ ሚዲያወች ማብራሪያ ሰጠ።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የድርጅቱን መመስረት በተመለከተ እና ስለ አማራ የህልውና ትግል ወቅታዊ ሁኔታወች ለዓለም አቀፍ ሚዲያወች ማብራሪያ ሰጠ።

የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ባዘጋጀው የሚዲያ ብሪፊንግ መድረክ የአማራ የህልውና ትግል ጠቅላላ ሁኔታ፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስረታ፣ የጦርነቱ አጀማመር፣ ትግሉ ያለበት ነባራዊ ሁኔታ፣ ስለ ሰብአዊ መብት አያያዝ፣ ስለ ምርኮኞች እና የጦርነት ህግ አተገባበር፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የአማራን የህልዉና ትግሉን በመረዳት ረገድ ስላለው ክፍተት እና ሌሎችም ጉዳዮች ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ቀርቧል።

በተጨማሪም ከጋዜጠኞቹ ለቀረቡት ጥያቄወች በመምሪያ ኃላፊው በኩል ማብራሪያ እና ምላሽ ቀርቧል።
በሚዲያ ብሪፊንግ መድረኩ ላይ ሮይተርስ፣ ኒውዮርክ-ታይምስ፣ ፍራንስ-24፣ አሶሼትድ-ፕሬስ፣ አልጃዚራን ጨምሮ የተለያዩ ሚዲያወችን የወከሉ እና ሌሎች የውጭ ሚድያ የግል ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል።

በርካታ አለም አቀፍ ጋዜጠኞች በተገኙበት የተደረገው ይህ የሚዲያ ብሪፊንግ ስራ በአንፃራዊነት ሲታይ ዓለም አቀፍ ትኩረት የተነፈገውን የፋኖ ትግል እና የአማራ የህልዉና ተጋድሎ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል። ድርጅታን መሰል ተግባራትን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።