ባሕርዳር መኮድ ካምፕ!
የሰሜን ምዕራብ ዕዝን ጨምሮ የአገዛዙ ወታደራዊ ኃይል ዋና ማዘዣ ጣቢያ በሆነው መኮድ ካምፕ ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ተደረጉ!
የግጭቱ መነሻ ዛሬ የካቲት 04/2018 ዓ/ም ማርፈጃውን በተካሄደ ወታደራዊ የግምገማ መድረክ “በፋኖ ቁጥጥር ስር እየገቡ በሚገኙ አከባቢዎች ላይ ንፁኋንን ያነጣጠረ የድሮን ጥቃት እንዲፈፀምና በዚህም ሕዝቡ አስመታችሁን በሚል ፋኖን እንዲቃዎም ማስደረግ” የሚል መመሪያ የወረደ ሲሆን፡ “የገጠምነው ከፋኖ ጋር እንጂ ንፁኋኖች ምን አደረጉን?”
በሚል መመሪያውን የተቃዎሙ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የጦር መኮነኖች ከግምገማ መድረኩ በኋላ መረሸናቸውን የመረብ ሚዲያ ወታደራዊ ምንጮች ተናግረዋል።
ይሄንን ተከትሎ በካምፑ ውስጥ በሚገኘው ሰራዊት መካከል ከባድ የሆነ የእርስ በእርስ ውጊያ ተቀስቅሶ በርካታ ወታደሮች መገደላቸው ተሰምቷል።
በአሁን ሰዓት በካምፑ ውስጥ የአማራ ተወላጅ የሰራዊት አባላትና የጦር መኮነኖች እየተመረጡ ትጥቅ እንዲያወርዱ ተደርገው እየታሰሩ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ፋኖ ወደ ከተማዋ መጠጋቱን ተከትሎ ሊከዱ ይችላሉ በሚል የሚጠረጠሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን በስውር እያፈነ የሚገድል ስኳድ ቡድን በካምፑ ውስጥ ተዋቅሮ ወደ ስራ ገብቷል።
በካምፑ ውስጥ የተቀሰቀሰቀሰው የእርስ በእርስ ውጊያም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት 8:20 ሰዓት ድረስ ተባብሶ ቀጥሏል።
“አማራዋ እናቴ ላይ የድሮን እሳት ሲዘንብ ከጠላቴ ጋር ተባባሪ አልሆንም” ያሉ በርካታ ወታደሮችም ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ለሊቱን ከወታደራዊ ካምፑ ወጥተው ጠፍተዋል።