አዲስ አበባ የሚገቡ የውጭ ጋዜጠኞች በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ትግራይ ሲካሄዱ ለቆዩና አሁንም በመካሄድ ላይ ለሚገኙ ግጭቶችና የድሮን ጥቃቶች ሽፋን እንዲሠጡ ጠየቀ።

ኢሕአፓ፣ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤን ለመዘገብ አዲስ አበባ የሚገቡ የውጭ ጋዜጠኞች በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ትግራይ ሲካሄዱ ለቆዩና አሁንም በመካሄድ ላይ ለሚገኙ ግጭቶችና የድሮን ጥቃቶች ሽፋን እንዲሠጡ ጠየቀ።

የውጭ ጋዜጠኞች ከአዲስ አበባ ውጭ በሚካሄዱ ግጭቶች ዙሪያ የተጣራ መረጃ እንዲሰበስቡ፣ በግጭቶች ጉዳት የደረሠባቸውን ወገኖች፣ የረድኤት ድርጅቶች ሠራተኞችንና ገለልተኛ ታዛቢዎችን እንዲያናግሩ የጠየቀው ፓርቲው፣ የውጭ ጋዜጠኞች እስር ቤት የሚገኙ የአገር ውስጥ ጋዜጠኞችን፣ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችንና ሲቪሎችን እንዲጎበኙም ጥሪ አድርጓል።

ፓርቲው፣ የበርካታ ሲቪሎች ሠቆቃ በአፍሪካ ኅብረት መሪዎች ጉባዔ ተዳፍኖ እንዳይቀር የውጭ ጋዜጠኞች ሃላፊነት እንዳለባቸውም አሳስቧል።