ዓረብ ሊግ ኢትዮጵያ በግድብ ውዝግቡ ዙሪያ መለሳለስ እንድታሳይ ጥሪ አደረገ

Egypt appeals to Arab nations for help in Nile dam dispute with Ethiopia

Country facing ‘grave’ threat from Gerd, Foreign Minister Sameh Shoukry tells Arab counterparts

ግብጽ የዓረብ አገራት ኢትዮጵያ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ውዝግብ “አሳሪ የሦስትዮሽ ስምምነትን” እንድትቀበል እንዲያሳምኗት መጠየቋን የመካከለኛው ምሥራቅ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ካይሮ ውስጥ ሰሞኑን በተካሄደ የዓረብ ሊግ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ስብሰባ ላይ ጥያቄውን ያቀረቡት፣ የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳሜህ ሽኩሪ እንደሆኑ ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ዓረብ ሊግ በበኩሉ፣ ኢትዮጵያ በውዝግቡ ዙሪያ “መለሳለስ እንድታሳይ” በስብሰባው ማብቂያ ባወጣው የአቋም መግለጫ ጥሪ አድርጓል።

Egypt is looking to fellow Arab nations to persuade Ethiopia to accept a legally binding deal on the filling and operation of the Grand Ethiopian Renaissance Dam, the country’s Foreign Minister said on Wednesday. Ethiopia is building the dam, also known as Gerd, on the Nile, which Egypt fears will reduce its vital share of the river’s waters.Addressing an Arab League meeting in Cairo, Egyptian Foreign Minister Sameh Shoukry said he wanted fellow Arab nations to pressure Ethiopia to halt its “unilateral and unco-operative practices and embrace the necessary political will to accept one of the compromise solutions offered on the negotiations table”.

ሽኩሪ ከስብሰባው በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ደሞ፣ ኢትዮጵያ በውዝግቡ ላይ “የዓረቦች የጋራ አቋም” መኖሩንና “ከዓረብ አገራት ጋር ልትጠብቃቸው የሚገቧት የሁለትዮሽ ጥቅሞች” እንዳሏት እንድትረዳ ማድረግ ያስፈልጋል በማለት ተናግረዋል ተብሏል።

ግብጽ የዓረብ አገራት ኢትዮጵያ ላይ ግፊት እንዲያደርጉ በይፋ ስትጠይቅ የአሁኑ የመጀመሪያዋ መሆኑን ዘገባዎቹ አመልክተዋል። በውዝግቡ ላይ የመጨረሻው የሦስትንሽ ድርድር የተደረገው ከዓመት ከመንፈቅ በፊት ነበር።

https://www.thenationalnews.com/mena/2023/03/08/egypt-boycotts-cairo-arab-league-meeting-over-libya-chairmanship/

 

Egyptian Foreign Minister Sameh Shoukry. Reuters