የደቡብ ሱዳን በጋምቤላ ክልል በፈጸሙት የደፈጣ ተኩስ ጥቃት ስድስት ሰዎች ተገደሉ

የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በፈጸሙት “የደፈጣ ተኩስ ጥቃት” ስድስት ሰዎች ተገደሉ

ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች፤ በጋምቤላ ክልል፣ በአኙዋሃ ዞን፣ ዲማ ወረዳ በሚገኝ ቦታ ላይ በከፈቱት “የደፈጣ ተኩስ ጥቃት” ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የወረዳው የአስተዳደር እና የፖሊስ ኃላፊዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። በትላንትናው ዕለት ጠዋት በተፈጸመው በዚህ ጥቃት፤ በዘጠኝ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን መመልከታቸውን በአካባቢው የሚገኙ የህክምና ባለሙያ ገልጸዋል።

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ጥቃቱን የሰነዘሩት፤ ከዲማ ወረዳ 39 ሰዎች አሳፍሮ ወደ ጎግ ወረዳ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ እንደሆነ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ኡታክ ሜዶ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሱ የደፈጣ ጥቃት የተሰነዘረበት፤ ከዲማ ከተማ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዞ አቻኛ እና 45 በተባሉ ቀበሌዎች መካከል በደረሰበት ወቅት እንደሆነ የፖሊስ አዛዡ አስረድተዋል።

ታጣቂዎቹ በአውቶብሱ ላይ ተኩስ በከፈቱበት ወቅት “መሳሪያ የያዘ ተሳፋሪ” መልሶ በመተኮስ አጸፋውን መመለሱን ረዳት ኢንስፔክተር ኡታክ አመልክተዋል። በተኩስ ልውውጡ አንድ ታጣቂ መገደሉንም የፖሊስ አዛዡ ጠቁመዋል። በታጣቂዎቹ የደፈጣ ጥቃት የአውቶብሱን ሹፌር ጨምሮ የስድስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በስድስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱንም ጨምረው ገልጸዋል።

🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16005/