የአሜሪካ ኢምባሲ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ መልዕክታቸው ላይ ማሻሻያ አድርጓል

የአሜሪካ ኢምባሲ፣ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ መንግሥት የድሮን ጥቃቶችን “በራሱ ሕዝብ ላይ” መፈጸምን “በአፋጣኝ እንዲያቆም” በጠየቁበት የዛሬው መልዕክታቸው ላይ ማሻሻያ አድርጓል። በተሻሻለው መልዕክት፣ ይህ መልዕክት ተነስቶ በምትኩ መንግሥት ለግጭቶች “ከኃይል ውጪ ያሉ ሰላማዊ አማራጮችን” መፈለግ እንዲቀጥልና “የዜጎቹን ደኅንነት እንዲያስቀድም” አምባሳደሩ መጠየቃቸው ብቻ ተጠቅሷል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የኦሮሚያው ግጭት እንዲያበቃ የሰላም ድርድሩን እንዲቀጥል፣ የፋኖ ቡድንም “ተጨባጭ” እና “ሰላማዊ የኾኑ” ግቦችን እንዲይዝና “በትጥቅ ትግል ስም የሚካሄድ ሕገወጥነት እንዲያበቃ” አምባሳደሩ በቀደመውም ኾነ በተሻሻለው መልዕክታቸው ጠይቀዋል። ኢምባሲው፣ የአምባሳደሩ መልዕክት በምን ምክንያት እንደተሻሻለ አላብራራም። https://www.facebook.com/profile.php?id=100007836377373