በዚሁ ሰፊ አዳራሽ ባለው ጠባብ በር ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ጋር ተጋፍቶ የወጣው ለምሳ ነበር፡፡ ርቦታልም፡፡ ደጃፍ ላይ ቆሞ ግን አጠገቡ ከሚታየው የምግብ ገበታ ይልቅ ዩኒቨርሲቲው በር ላይ የሆነ ነገር ቀልቡን የሳበው ይመስላል፡፡ እጃቸው ላይ ደብተርና ስክርቢቶ የያዙ በርከት ያሉ ተማሪዎችና ሌሎችም