በኦነግ አባልነት የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት አሊማ አብዲ መሃመድ እንዳትማር ተከለከለች
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በኦነግ አባልነት የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት አሊማ አብዲ መሃመድ እንዳትማር ተከለከለች #Ethiopia #Oromo
በ2004 ዓ.ም በኦሮሞ ነፃአውጭ ግንባር (ኦነግ) አባልነት ተጠርጥራ ከታሰረች በኋላ የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት አሊማ አብዲ መሃመድ እንዳትማር መከልከሏን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘው አሊማ (ቢፍቱ) አብዲ ባለፉት አራት አመታት በማረሚያ ቤት እየተማረች እንደነበርና አምስተኛ ክፍልም መድረሷ ተገልፆአል፡፡
ይሁንና በዚህ አመት እንዳትማር የተከለከለች ሲሆን የተከለከለችበትን ምክንያት ስትጠይቅም ‹‹አንቺ መማር አይገባሽም!›› እንደተባለች የነገረ ኢትዮጵያ ታማኝ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ አሊማ አብዲ መሃመድ የ23 አመት ወጣት ስትሆን በመደበኛ ጊዜ እንዳትጠየቅ በመከልከሏ ክፍለ ሀገር በሚኖሩት የተወሰኑ የቤተሰብ አባላት ብቻ ከ6፡00 እስከ 6፡30 ለሰላሳ ደቂቃ ብቻ እንደምትጠየቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ( በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር)