የምስራቅ ጎጃሙ የህወሓት ሴል እየተንቀሳቀሰ ይመስላል። ከወራት በፊት ህግማስከበር በሚል የነቁ የአማራ ወጣቶችን ለማጥፋት ሲደረግ በነበረው ዘመቻ መቶ ዐለቃ አበበን መያዝ ባለመቻላቸው የ3 ዓመት ሕፃን ልጁን እና ሚስቱን አስረዋቸው እንደነበር ይታወሳል።
የህግ ማስከበር ዘመቻው አብቅቶ የታሰሩት እየተፈቱ እና የህወሓት ዳግም ወረራን ለመመከት እየተፋለምኩ ነው የሚለው ብልፅግና ዛሬ ሌሊት መቶ ዐለቃ ፋኖ አበበን አፍነው ወስደውታል።
ፎቶው መቶ ዐለቃ ፋኖ አበበ እና ጓደኞቹ ከጎጃም ወደ ወለጋ ለሸኔ ጥይት ሊሸጡ የነበሩ የወረዳ ካድሬዎችን ይዘው ለመንግስት ሲያስረክቡ የሚያሳይ ነው። እንዲሁም ሰሞኑን ደግሞ ወቅቱን የዋጀ ነጠላ ዜማ የለቀቀበትን ፎቶ ነው
© ጥላሁን አበጀ