የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ የብልጽግና ፓርቲ ደጋፊዎችን ወቀሱ

የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ የማነ ገብረ መስቀል፣ የኢትዮጵያው ብልጽግና ፓርቲ ደጋፊዎች “በኤርትራ የመንግሥት አስተዳደር” እና “የኢኮኖሚ ፖሊሲ” ላይ “ሐሰተኛ መረጃዎችን” ማሠራጨት ቀጥለውበታል በማለት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሠፈሩት መልዕክት ወቀሱ።

የማነ ኾኖም የብልጽግና ደጋፊዎች በኤርትራ ላይ “የስም ማጥፋት” ዘመቻ የሚያካሂዱት፣ ኢትዮጵያ ከገባችበት “ውስጣዊ የጸጥታ ቀውስ አቅጣጫ ለማስቀየር” እና የፓርቲው የባሕር በር ጥያቄ “በቀጠናዊ መረጋጋት” ላይ የፈጠረውን ስጋት “ለመሸፋፈን” ነው በማለት ተችተዋል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ ይገኛል በማለት የማነ አስተያየታቸውን የሠጡ ሲኾን፣ የብልጽግና ፓርቲ “ውስጣዊ” እና “ቀጠናዊ” ግጭቶችን ከመፍጠር ይልቅ የአገሪቱን የኢኮኖሚና መንግሥታዊ አስተዳደር ችግሮች በመቅረፍ ላይ ቢያተኩር ይሻለዋል ብለዋል።