በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ዞን በሰሃላ ሰየምት ወረዳ፣ ሐሙስ’ለት በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 36 ሰዎች መገደላቸውን ምንጮችን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘገበ።
የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው ስብሰባ ላይ በነበሩ የወረዳው ሚሊሺያ አባላት ላይ መኾኑን የገለጠው ዘገባው፣ በጥቃቱ 16 ሰዎች ጉዳት እንደደረሠባቸው መረዳቱን ጠቅሷል።
የሚሊሻ አባላቱ፣ የፋኖ ታጣቂዎች ወደ ወረዳው እንዳይገቡ ጥበቃ የሚያደርጉ መኾናቸውን የወረዳው አስተዳደር ሃላፊዎች ማረጋገጣቸውንም ዘገባው አመልክቷል።
በአካባቢው የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች በበኩላቸው፣ የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው “በስህተት” መኾኑን ተናግረዋል ተብሏል።
መከላከያ ሠራዊት፣ ስለ ድሮን ጥቃቱ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በይፋ ያለው ነገር የለም።