ፌደራል መንግሥቱ፣ በወልቃይት-ጠገዴ-ሰቲት ሁመራ ዞን የትግራይ የጦርነት ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ በአማራ ክልላዊ መንግሥት ሥር በአካባቢው የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር ለማፍረስ ማቀዱን የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አማካሪ ጌታቸው ረዳ እንደነገሩት ጠቅሶ ዘ ሪፖርተር ዘገበ።
ጌታቸው ይህን የተናገሩት፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ከትናንት ወዲያ በሁመራ ጉብኝት አድርገው ከተመለሱ በኋላ መኾኑን ዘገባው ጠቅሷል።
ኾኖም የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት ለመተግበር ትብብር እንደሚያስፈልግ ጌታቸው መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
ጌታቸው፣ ሦስተኛ ወገን ጣልቃ ሳይገባ ውስጣዊ ልዩነቶችን መፍታት እንደሚያስፈልግ አጽንዖት መስጠታቸውን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።