ግብፅ እና ሱዳን ትራምፕ የናይል ወንዝ ውሃ ክፍፍል ውዝግብን ለማሸማጋል ያሳዩትን ፍላጎት በደስታ ተቀብለዋል።

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ እና የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ አብዱልፈታህ አል ቡርሃን፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የናይል ወንዝ ውሃ ክፍፍል ውዝግብን ለማሸማጋል ያሳዩትን ፍላጎት በደስታ ተቀብለዋል።

ፕሬዝዳንት ሲሲ፣ ግብጽ በናይል ወንዝ “የውሃ ደኅንነት” ላይ ያሏትን አቋሞችና ስጋቶች ውዲያውኑ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ በላኩት ደብዳቤ ማሳወቃቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በፕሬዝዳንት ትራምፕ የአሸማጋይነት ፍላጎት ዙሪያ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በይፋ ያለው ነገር የለም።