አለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በሱዳን የጦር ወንጀሎች ተፈፅመዋል አለ።
አለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት(ICC) በሱዳን ዳርፉር ሰብዓዊነት ላየ የተቃጣ ጥቃትና የጦር ወንጀሎች ስለመፈፀማቸው ማስረጃ ማግኘቱን ገልጿል።
ፍርድ ቤቱ የተለያዩ የቪዲዮ፣ የድምጽና የሳተላይት መረጃዎችን በመጠቀም አደረኩት ባለው ምርመራ በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል በዳርፉር የጦር ወንጀሎች ተፈፅመዋል ብሏል።
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በዳርፉር አረብ ያልሆኑ ሰዎችን መግደልን ጨምሮ ያለ አግባብ ይዟል ያለው ፍርድ ቤቱ ወሲባዊ ጥቃቶችና አስገድዶ መድፈርም በዳርፉር እንደ ጦር መሳሪያነት ጥቅም ላይ ውሏል ብሏል።
በተያያዘ ዜና በሱዳን ከ8 ሚሊየን በላይ ህፃናት ከ500 ቀናት በላይ ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ሴቭ ዘ ችልድረን ገልጿል።
በሱዳን ለትምህርት ከደረሱ 17 ሚሊየን ህፃናት መካከል በጦርነቱ የተነሳ 8 ሚሊየን ያህሉ ከ500 ቀናት በላይ ከትምህርት መራቃቸው ነው የተገለጸው።
በሰሜናዊ ዳርፉር ካሉ 1100 ትምህርት ቤቶች መካከል እየሰሩ ያሉት 3% ብቻ መሆናቸው ሲገለጽ፣ መምህራን ደመወዝ ስላልተከፈላቸው ስራቸውን ማቆማቸውና ህፃናትም ጭምር ለጦር እየተመለመሉ መሆኑ ተነግሯል።
ዘገባው የአናዶሉና AFP ነው።