ሰባት የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ሰባት ጥቁር ክላሽና ከ1400 በላይ ተተኳሽ በመያዝ ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ!
ከአንድነቱ ብስራት ማግስት እየተናደ የሚገኘው የብልፅግና ወንበር ጠባቂ መከላከያ ሰራዊት ስድስት የ61ኛ ክፍለ ጦር እና አንድ የ65ኛ ክፍለ ጦር ባጠቃላይ ሰባት አባላቶቹ ምኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነው ኮር ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: የክፍለ ጦሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::
👉ሰባት ክላሽ፣ከ1400 በላይ የክላሽ ተተኳሽ፣14 የእጅ ቦምብ፣ሰባት የወገብና የደረት ትጥቅ በመያዝ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር አካል የሆነውን ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
ፋኖን የተቀላቀሉት የመከላከያ አባላት አክለውም የሀገሪቱ መከላከያ ተቋም የሀገር ዳር ደንበርና ሉዓላዊነትን ከማስከበር በተቃራኒ የአማራን ህዝብ ለሚጨፈጭፈው፣ለሚያርደውና አማራ ሀገር እንደሌለው ለሚያሳድደው የብልፅግና መንግስት ተባባሪ አንሆንም፣ህዝባችንን አናሳዝንም በማለት ፋኖን የተቀላቀሉ ሲሆን በተደረገላቸው አቀባበል ደስተኛ እንደሆኑና ከዚህ በኋላ የአማራን ህዝብ ለመካስ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ