የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ፖሊት ቢሮ የመጀመሪያ ስብሰባውን አደረገ።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ፖሊት ቢሮ የመጀመሪያ ስብሰባውን አደረገ።

ጥር 09 ቀን 2018 ዓ. ም በይፋ መመስረቱ የተገለፀው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የፖሊት ቢሮ ጥር 12 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ አጀንዳወች ላይ ውይይት አድርጎ ውሳኔወችን አሳልፏል።

የድርጅቱ ስራ አመራር አባላት በተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላለፉት 30 ወራት በነበረው የትግል ሂደት በነበሩ የእርስ በእርስ ሽኩቻወች እና አለመግባባቶች እንዲሁም የአደረጃጀት ልዩነቶች ምክንያት ለተፈፀሙ ጥፋቶች የእርስ በእርስ የይቅርታ መርሀ ግብር በማከናወን ውይይቱ ተጀምሯል።

በፍፁም መተማመን እና ጓዳዊነት የተጀመረው ውይይትም የድርጅቱ ቀሪ የአመራር መዋቅር ስለሚዋቀሩበት ሁኔታ፣ የወለጋ ክፍለ ሀገር ፋኖ እዝ (ቢዛሞ) ያቀረበውን የአደረጃጀት ጥያቄ፣ የቀጠና እና የዕዝ ስያሜወችን በተመለከተ፤ የሰራዊት እና የነባር ዕዞችን ውህደት እንዲሁም የወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ፍኖተ ካርታ ዝግጅትን በተመለከተ ሰፊ ውይይት አድርጎ የስራ መመሪያወችን ሰጥቷል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!