በአዲስ አበባ ባለቤት ያልተገኘላቸው ህንጻዎች 100 መድረሳቸው ተሰምቷል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ የሚገኙ ህንጻዎች፣ ታጥረው የሚገኙ መሬቶች እና የቀበሌ ቤቶችን በተመለከተ እየተደረገ ባለው ዳሰሳ እስካሁን 100 ህንጻዎች ባለቤት እንዳልተገኘላቸው ገልጸዋል።

ይህን የገለጹት ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተማ ከተውጣጡ የከተማዋ ወጣቶች ጋር በተካሄደው ውይይት ላይ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ ታጥሮ የተቀመጠ ከ1 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ባለቤት ሳይገኝለት ቀርቷል ብለዋል።

ም/ከንቲባዋ በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶች ላይም ማጣራት እየተደረገ መሆኑን አክለው ተናግረዋል። (EBC)