ብፁዕ አቡነ ያሬድ ከምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ተነሱ

ብፁዕ አቡነ ያሬድ ከምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ተነሱ። ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ  ሀገረ ስብከቱን እንዲመሩ ተመድበዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የምሥራቅ አርሲ ሀገረስብከትን እስከ ግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ጉባኤ ድረስ ደርበው እንዲመሩ በቋሚ ሲኖዶስ ተመደቡ።

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ከሚመሩት ሀገረ ስብከት በተጨማሪ የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከትን እስከ ግንቦት 2018 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ጉባኤ ድረስ ደርበው እየመሩ እንዲቆዩ በቋሚ ሲኖዶስ ተወስኖ በቅዱስ ፓትርያርኩ በተጻፈ ደብዳቤ ተመድበዋል።

ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ከሚገኙ ካህናት፣ አባ ገዳዎች፣ሀደ ሲንቄዎች፣ ወጣቶችና ምዕመናን የቀረበለትን ተደጋጋሚ አቤቱታ ሲቀርብለት ነበር።

ይህን መነሻ በማድረግ አጣሪ ልዑክ መድቦ ችግሩ በዝርዝር ተጠንቶ እንዲቀርብለት ካደረገ በኋላ ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ብፁዕ አቡነ ያሬድ ከምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ተነስተው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርሰቲያን የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስነት ሥራቸውን እያከናወኑ እስከ ግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ጉባኤ እንዲቆዩ ውሳኔ አስተላልፏል።

የቅዱስ ሲኖስ ምልዐተ ጉባኤ ጥቅምት 2018 ዓ.ም ባደረገደው ጉባኤ  ቋሚ ሲኖዶስ የተከሰተውን ችግር በመመርመር መፍትሔ እንዲሰጥ ውሳኔ ማሰተላለፉ ይታወሳል።

መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው