የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉተረዥ ኢትዮጵያና ኤርትራ በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት አንዱ የሌላኛው የግዛት አንድነት ለማክበር ቁርጠኝነታቸውን ዳግም እንዲያረጋግጡ አሳሰቡ። የዋና ጸሐፊው ቃል አቀባይ ስቲፋን ዱጃሪክ የስምምነቱን 25ኛ ዓመት አስመልክተው ባስተላለፉት የዋና ጸሐፊው መልዕክት ሁለቱም ሐገራት ዘላቂ ሰላምን በማምጣት ላይ ተግተው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች ከ7 አመታት በፊት ያደሱት ሰላማዊ ግንኙት ያወደሰው የጉተረዥ መልዕክት ይህም የውይይትና የትብብር ዋጋ የሚያሳይ ነው ብሏል። አያይዘውም በአልጀርስ ስምምነት ላይ የተካተተውን የዘላቂ ሰላም፣ ሉአላዊነት እና የግዛት አንድነትን ለማክበር ቁርጠኝነታቸውን ዳግም እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርበዋል።